sabato

ያለማወቅ ከምንም አያድንም


ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ (ከቦሎኛ)
...... ሰላም ለአንባቢያን እንዴት ሰነበታችሁ?
..... በቅድሚያ ሰለቸኝና ደከመኝ ሳይል ቀንና ሌሊት በመድከም ይህንን መድረክ በማዘጋጀት የተጠቃሚነት እድል ለሰጠኝ ለአቶ አብርሃም ዘውዴ ልባዊ የሆነ ምስጋናዬን እቀርባለሁ::
...... ቀጥሎም እትዮጵያን በውጭዉ ዓለም ሁሌ በጥሩ ስም ለማስጠራት ለሚደክሙትና ይህቺ ዌብ ሳይት አምራ ደምቃና ከግብ ደርሳ ማየት እንድንችል ለተባበሩትና ወደፊትም ለሚተባበሩት ሁሉ መልካም ስራ፣ አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ግፉበት የድካማችሁ ውጤት ስራችሁ ነዉ እላለሁ::
...... በመሆኑም ነዉ አባቶች ሲተርቱ እንዲህ ያሉት "ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም":: ይህ በቅርቡ የተከፈተዉ እትዮጵያ በጣሊያን በመባል የታወቀዉ የኢንተርነት አድራሻ ማንኛችንም በጣሊያን ሃገር ነዋሪ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ትምህርት የምንቀስምበት መድረክ ከመሆን አልፎ አንዱ ከሌላዉ ጋር ሀሳብ ለሀሳብ የሚለዋወጥበት ጥሩ ዘመናዊ የመገናኛና የመወያያ ዘዴ ነዉ::
...... ለዚህም ነዉ "ያለማወቅ ከምንም አያድንም" በማለት ሀሳብ መስጠት የጀመርኩት:: በእርግጥ ብዙዎቻችን የጊዜ እጥረትና የስራ ሁኔታዎች ያለመመቻቸት ችግር ሊኖረን እንደሚችል ማወቅ ተስኖኝ ሳይሆን ከዚችው ካለችን ጊዜ የተወሰነችዋን ጠቃሚ በሆነዉ በትምህርት ላይ ብናዉላት የአዕምሮ እረፍት እናገኛለን የሚል የጠና እምነት ስላለኝ ነዉ::
.
ይህ የእትዮጵያ በጣሊያን ኢንተርኔት ዌብ ሳይት ለምን ለምን ይጠቅማል? ማንንስ ይመለከታል?
...... ከመልሶቹ በጥቂቱ:-
1. የጣሊያንኛ ችግር ላለባቸዉ ግለሰቦች ሁሉ በአማርኛ የመጻፍና የማንበብ እድል ይሰጣል;
2. በጣሊያን ሀገር የእኛን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዜና ያቀርባል;
3. ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ተቀይሮ የነበረዉን የስልክ ቁጥር ችግር በማቃለል በአሮጌዉ ምትክ አዲሱን ፈላልጎ ማግኘት ይቻላል;
4. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋን የሚመለከት የመኖሪያ ፈቃድ ህግን በተመለከተ ማብራሪያ ያቀርባል;
5. በጣሊያን የእትዮጵያ ኤምባሲን አድራሻና የስልክ ቁጥር ከመጠቆም አልፎ ለኤምባሲዉ ባለጉዳዮች ምን ሰነዶች እንደሚያስፈልጉ ያስረዳል;
6. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእናት ሀገሩን የተለያየ ወቅታዊ ዜና በሚፈልገዉ ማግኘት ይችላል;
7. በጣሊያን ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ ማህበራት ዝርዝርና አድራሻ ያቀርባል;

8. የአዉሮፓ የቀን አቆጣጠርን ወደ ኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር በቀላሉ መቀየር ይቻላል;
9. የተለያዩ የሀገር ባህላዊ ዘፈኖችን መስማትና ድራማዎችን መከታተል ይቻላል;
10. የተለያዩ አስተያየቶችን መላክና መቀበልም ጭምር ይቻላል::
11. ...ይቀጥላል ...