giovedì

ከመሰለፍህ በፊት መሰለፊያዉን እወቅ


ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
በጣሊያን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት (permesso di soggiorno / carta di soggiorno) ለማሳደስም ሆነ አዲሱን ለመዉሰድ የሚያስችለዉን ማለትም ባለፈዉ ጊዜ የወጣውን አዲስ መመሪያ በተመለከተ ሰሞኑን ብዙ ሰዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ስልክ ደዉለዉ ይጠይቁኛል::
ጥያቄዎቹን ሙሉ በሙሉ በዚህ መድረክ ለመመለስ ጊዜ ቢያጥረኝም ለጥቂቶቹ መልስ ይሆናሉ በማለት የመመሪያዉን ይዘት ከዚህ ቀጥሎ አጠር ባለ መልኩ ለአንባቢያን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ:: በመጀመሪያ ደረጃ ከመሰለፍ በፊት ዬት መስሪያ ቤት ሄዶ መሰለፍ እንደሚገባ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል::
በጣሊያን ለመኖር የሚያስችል የዉጭ አገር ዜጎች ጉዳይ ሁሉም በፖስታ ቤት አይጠናቀቅም:: ይበልጡ አጅ በፖስታ ቤት ሲከናወን ጥቂቱ በፊት እንደነበረዉ በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ እንደነበረዉ ይቀጥላል:: አጉልና ከንቱ የማያልቅ ሰልፍ ተሰልፎ ጊዜና ጉልበት እንዲሁም ገንዘብን ከማጥፋት ሌላ የአእምሮ ህመም በሽታ ከመሸመት መጠንቀቁ ተገቢ ነዉና በተቻለ መጠን ጠይቆ ትክክለኛ መረጃ (እንፎርሜሽን) ማግኘት ያስፈልጋል::
.
በፖስታ ቤት ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ማሳደስ (permesso di soggiorno);
- ልጅ አስመጥቶ ማሳደግ;
- ጣሊያን ተወልዶ ወላጆቹ ሊያሳድጉት ያልቻሉ ልጅ;
- የማደጎ ልጅ አስመጥቶ ለማሳደግ;
- የፓስፖርት ለዉጥ;
- ስራ አጥ ስራ ፈላጊ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት እድሳት;
- የመኖሪያ ወረቀት ለአዉሮፓ ህብረት ዜጎች (carta di soggiorno cittadini U.E.);
- የመኖሪያ ወረቀት ለዉጭ አገር ዜጎች (carta di soggiorno cittadini stranieri);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት መቀየር (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (carta di soggiorno);
- ቤተሰብ;
- ቤተሰብ እድሜያቸዉ ከ 14 እስከ 18 አመት;
- የግል ስራ (lavoro autonomo);
- የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato);
- በተለያዩ ምክንያቶች የስራ ፈቃድ;
- ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato - stagionale);
- ጉዞ ወደ ዉጭ አገር;
- ሃይማኖት;
- የፖለቲካ ምርጫ;
- ትምህርት;
- ጉብኝት;
- የሙያ ማሻሻይ ስልጠና ወዘተ ...

በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- ንግድ ወይም ብዝነስ ነክ ስራዎች;
- ህክምና;
- እስፖርት ዉድድር;
- እርዳታና ማስተባበርያ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ;
- ህግና ፍትህ;
- ከ 14 አመት በታች እድሜ ያላቸዉ ልጆች;
- ከጣሊያን አገር ዉጪ ሰዉ በዋስትና ማስመጣት::

በዝርዝሩ ላይ ማብራርያ ካስፈለገዎት በሚከተለዉ የመገናኛ ዘዴ መጠየቅ ይቻላል::
zeleke_eresso@yahoo.it
Tel. 3395764139


martedì

ከኩዌስቱራ ወደ ፖስታ ቤት


ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
Bologna (Italy) 28/11/2006

በእጣሊያን አገር ለመኖር የሚያስችለዉን የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት (permesso di soggiorno e carta soggiorno) አዲሱን ለማዉጣትም ሆነ አሮጌዉን ለማሳደስን በተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መመሪያ ተላለፈ::
ካሁን ቀደም በፖሊስ - በኩዌስቱራ - ሲሰጥም ሆነ ሲታደስ የነበረዉ የመኖሪያ የፈቃድ ወረቀት ከሚቀጥለዉ ሰኞ 04/12/2006 ጀምሮ በፖስታ ቤት እንዲከናወን የእጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስትሩ በአለፈው ጊዜ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ:: በመሆኑም ፖስታ ቤቶች ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ተጨማሪ ማስተናገጃዎችን ለማዘጋጀት በመሮጥ ላይ ይገኛሉ:: ለዚህም ዉሳኔ ሊደረስ የተቻለዉ ከ 06/11/2006 ጀምሮ በፕራቶ፣ በአንኮና፣ በፍሮስኖኔ፣ በብርንድሲ እና በመሳሰሉት ጥቂት የእጣሊያን ትናንሽ ከተሞች የተካሄደዉ ጊዜያዊ ሙከራ ባስገኘዉ ጥሩ ዉጤት መሰረት ነዉ ይባላል::
.
ለማሳደስም ሆነ አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት:-
1) በአቅራቢያ በሚገኘዉ ማንኛዉም ፖስታ ቤት በመሄድ ፎርም መቀበል;
2) ፎርሙ አዲስ መጠየቂያ፣ ማሳደሻ፣ መቀየሪያ፣ ማስተካከያ፣ ወዘተ ለመሳሰሉት ይጠቀማል;
3) የመኖሪያዉ ፈቃድ ለስራ (ቅጥረኛ ወይም የግል)፣ ለቤተሰብ፣ ለትምህርት፣ ለቱሪዝም፣ ለሃይማኖት እና ለመሳሰሉት ሁሉ ይጠቅማል;
4) የሰራተኛ ማህበር ተወካዮችም (patronati) አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል;
5) ፎርሙ ተሞልቶ ፖስታ ቤት መረከብ አለበት;
6) ፖስታ ቤቱ ለአስረካቢዉ ደረሰኝ ይሰጣል;
7) ፖስታ ቤቱ የተረከበዉን ጥያቄ ወደ ኩዌስቱራ ይልከዋል;
8) ኩዌስቱራም መዝገቡን አጣርቶ የመጀመሪያ ጥያቄ ከሆነ ግለሰቡን ለአሻራ ይጠራዋል ነገር ግን ለማሳደስ ከሆነ ቀርቦ እንዲወስድ ይጠራዋል::

.

ይህ ቀላል ለዉጥ አይደለም ቀደም ተብሎ በየዜና ማሰራጫዎች በሰፊዉ መነገር የነበረበት ጉዳይ ነዉ:: እንደሚታወቀዉ የእጣሊያን መንግስት የዉጭ አገር ዜጋ ጉዳይ ሲሆን ሁሌ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይደል? ይህን ለዉጥ ስንቶቹ የዉጭ አገር ዜጎች ሰምተዉታል? ምን ያህልስ ተግባራዊ ይሆናል? ዉጤቱን ለማየት ያብቃን::

.

የክፍያ ጉዳይ ማንኛዉም ጠያቂ እያንዳንዱ € 30,00 ለፖስታ ቤት የአገልግሎት ዋጋ ይከፍላል:: ለቴምብር € 14,62; € 27,50 ደግሞ ለፎርም የመክፈል ግዴታ አለበት:: መመሪያዉ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከሰኞ 11/12/2006 መሆኑን በዚህ አጋጣሚ በጣሊያን ለሚኖሩ አንባቢያን መግለጥ እወዳለሁ::



lunedì

ሰሞኑን በጣሊያን ሚ/ምክርቤት የውጪ ዜጎችን በሚመለከት


03 12 06
በጣሊያን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰሞኑን የፀደቁትን የውጪ ዜጎችን የሚመለከቱ ሁለት አዲስ ሕጎችና የውስጣቸውን ደንብ ፍሬ ነገሮቹን ብቻ መርጠን ከዚህ በታች አስፍረናል። ሁለቱ ዋና ዋና አዲስ ሕጎችም በአለፈው የበጋ ወቅት በጠረቤዛ ላይ ለውይይት ቀርበው ከነበሩት መካከል ይገኛሉ። እነዚህም
1)የካርታ ዲ ሶጆርኖ
2)የቤተስብን ማስመጣት የሚመለከቱ ናቸው።
ከሚያፀድቋቸው ሌሎች ህግጋትና አንቀፅ ጋር በአንድላይ በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት ከላይ የተጠቀሱትንና ያፀደቁትን የሁለቱን አስቀድመን አጭር ይዘታቸውን እናቀርባለን።
.
Carta di Soggiorno - (ካርታ ዲ ሶጆርኖ)
1 - በጣሊያን ከ5 ዓመት በላይ የመኖሪያ ፈቃድ የነበረው ማመልከቻ ከአስገባ ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንደሚሰጠው እና ይህም በሁሉም የአውሮፓ ሕብረት ኣባላት ሀገሮች ውስጥ ሥራ የመሥራት ዕድል የሚክፍትለትና በኣባላት ሀገር እንደፈለገው የመዘዋወር ፍቃድ እንዲኖረው ያደርገዋል።
2 - ቤተሰቦቹን ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንዲኖራቸው ለማድረግ ማመልከቻ የሚሲያስገባ ከሆነ ቤተሰቦቹን በአስተዳዳሪነት የሚያስተናግድበት የመኖሪያ ቤት ሁኔታ በክፍለሀግሩ የተደነገገውን መመዘኛ ማሟላት አለበት። ይኸውም የሕብረተሰቡን የጤናአጠባበቅ ሥራዓት ይዞ የሚከታተልና ደንቡን የሚጠብቅ መሆን ሲገባው ይኸውም ግዴታውም ጭምር ሆኖ ይገኛል።
3 - ሌላው ደግሞ ይኸው መኖሪያ ቤት ለሕይወት አስጊነት የሌለው፣ በውስጡ መኖር የሚቻልበትን ሁኔታዎችን የሚያሟላ መሆኑን መረጋገጥ አለበት። ማሳሰቢያ
4 - ይህን ካርታ ዲ ሶጆርኖ ለማግኘት ተመኑ የተወሰነ የዓመት ገቢ እንዲኖረውና ለዚህም አስፈላጊውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርበታል።
5 - በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የነበሩ፣ በወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸውን እንዲሁም የሕብረተሰቡን ፀጥታን ያጎደሉና ከዚህ በፊት precedenza ያለባቸው ይህንን የcarta di soggiorno ፈቃድ ማግኘት አይችሉም።
.
Recongiungimento familiare (ቤተሰብን ለማስመጣት)
1 - ልጅ ያለው እድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ለማስመጣት ብዙ ማስረጃዎችን እንዲያሳይ አይጠየቅም። እንደገናም ወላጆቹን ለማስመጣት በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆን ይገባቸዋል። (65 ዓመት ...) ይህ ደግሞ ብዙ ጥያቄና ክርክር ይሚያስነሳ ይመስለናል። ለማንኛውም እዚህ ካስመጣ በኋላ (a carico suo) ወይም የአስተዳዳሪነቱን ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ መሆን አለበት።
2 - ከዚህ በፊት በመኖሪያ ቤት ስፋትና ጥራት ይወስን እንደነበረና ንገርግን አሁን ይህ ሁሉ እንዲቃለል ተደርጎ ASL የሚጠይቀውን requisiti ማሟላት አለበት
3 - በየክፍለሀገሩ የተተመነውን የዓመት ገቢ ለማሳየት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል።
4 - ልጅ ያለው ማንኛውም የውጪ ዜጋ እዚህ በአለው የጤና አጠባበቅ ስርዓትና ክትትል በማድረግ ግዴታውን እንዲወጣ መሆን አለበት።
5 - ጥገኝነት ጠያቂ ( refugiato ) ከሆነ የዓመት ገቢና የመኖሪያ ቤት የግድ እንዲኖረው አይጠየቅም። ነገርግን ፈልሶ የመጣበት ሀገር እና የጣሊያን የድንበር ስምምነት ወሳኝነት ሊኖረው ይችላል።

mercoledì

አሳዩን አትንገሩን


ዶክተር ዘለቀ እሬሶ
...... አንድ ጸሐፊ በቅርቡ የአገራችን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት “አሳዩን አትንገሩን” በሚል አርስት የሚከተለውን አስፍሮ ነበር:: በአለምም ሆነ በአንድ አገር ታሪክ ዉስጥ የአገር መሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች አዛዉንቶች፣ ህዝብና ሌሎች ሌሎች የሚፈተኑበት ልዩ ወቅት ይከሰታል:: ያም ወቅት አብዛኛዉን ጊዜ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ይሆናል:: ያን ችግር ለመፍታት በሚያደርጉት አዎንታዊ እንቅስቃሴ፣ ያን ችግር ለማባባስ በሚጫወቱት ሚና ወይም በሚይዙት የአያገባኝም ወይንም ደንታቢስነት ሚና ማንነታቸዉ ይለካል:: መልክቱ ባጭሩ ተግባራዊ እንሁን ማለቱ ይመስለኛል::
...... በኢጣሊያን አገር የሚኖሩትን የዉጭ አገር ዜጎች የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ ሰሞኑን ከምን ጊዜዉም በበለጠ የተለያዩ ወሬዎች ይነፍሳሉ አልፎም ይተረካሉ:: ይህ ዜና አዎንታዊ እንቅስቃሴ? ወይንስ ችግር የማባባስ ዘመቻ? መልሱ እንደፊደል ምርጫ ጥያቄ ሁሉም ሊሆን ይችላል::
...... የመጀመሪያዉ የዉጭ አገር ዜጋዉ ከገጠሙት የቢሮክራሲ ዉጣ ዉረድ እንዲላቀቅ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳይኖረዉ፣ የስራና የህክምና ችግሮች እንዳይገጥሙት ማለትም ግዴታዉን ተረድቶ መብቱ ተከብሮለት አምራች ዜጋ እንዲሆን አስፈላጊዉን ሁሉ ለማድረግ ቢያንስ የሚሞክሩትን አነስተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያጠቃልላል::
...... ሁለተኛዉ ደግሞ በሰዉ ቁስል እንጨት ስደድበት አይነት ነገር ነዉ:: የዉጭ አገር ዜጋዉን ከወንጀል ጋር በማጣመር ሁሉንም ወንጀለኛ በማድረግ የዉጭ አገር ዜጎች ገደሉ፣ ሰረቁ፣ አጭበረበሩ፣ ቀጠፉ፣ ደፈሩ፣ አቆሸሹ፣ ወዘተ በማለት የዉጭ አገር ዜጋዉ ከህግ ዉጭ እንደሆነና የተመቻቸ ኑሮ እንዳለዉ አስመስለዉ በማቅረብ እንዲያዉም ይባስ ብሎ የመንግስት እርዳታ ሁሉ የሚሰጠዉ ለዉጭ አገር ዜጋ ብቻ ነዉ በማለት የአገሬዉን ህዝብና የዉጭ አገር ዜጋዉን ለማጣላትና ለማጋጨት ከፍተኛ ቅስቀሳ በስዉር እየተካሓደ ነዉ::
...... ይህንንም ስል ሁሉም የዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል አይሰራም ለማለት ፈልጌም አይደለም:: እንዲያዉም ሰርቶ ከመኖር ይልቅ ሀገ ወጥ በሆነ መንገድ ሐብታም መሆን እንደሚቻል መጥፎ ትምህርት በማስተማር ላይ የሚገኙም እንዳሉ ተስኖኝ አይደለም:: ታዲያ እንክርዳዱን ከስንዴ መለየት አስፈላጊ በሆነበት ባሁኑ ሰአት አብዛኞች የኢጣሊያን አገር የዜና ማሰራጫዎች የሚጽፉአቸዉ ጽሁፎችና አርስታቸዉ ከመለያየቱ የተነሳ ሕግ አክባሪዉንና ወንጀለኛዉን የዉጭ አገር ዜጋ እንኳን በአግባቡ ለይቶ ማወቅ አልተቻለም::
በጠቅላላዉ ለመዝጋት ያህል ሰሞኑን በአንዳንድ የኢጣሊያን አገር ጋዜጦች ላይ የዉጭ አገር ዜጋን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ አርስቶች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፣ ለዉጭ አገር ዜጋዉ ግን ምንም የተቀየረለት አንዳችም ነገር አይታይምና ወሬዉ በተግባር መተርጎም እንዳለበት የሚመለከተዉን ክፍል ከመጠየቅ ወደ ኋላ ማለት አይገባም::
...... ስለ ጽሁፉ አስተያየት ካለዎት zeleke_eresso@yahoo.it

lunedì

ITALIA: Il governo cambia che cosa si aspetta lo straniero?


(dr.Zeleke Eresso)
... Secondo la stima della Caritas-Migrantes nell' anticipazione del rapporto annuale sull'immigrazione, relativo al 2005, gli immigrati regolari presenti in Italia all'inizio di quest'anno hanno superato, seppure di poco, la quota dei 3 milioni.
... L'immigrazione in Italia è ormai un fenomeno strutturale e politico. Secondo molti studiosi del campo, più di tre milioni di cittadini stranieri risiedono regolarmente in Italia e la loro presenza, sia come lavoratori che come imprenditori, contribuisce in modo determinante allo sviluppo economico. Quasi mezzo milione di bambini stranieri stanno crescendo in Italia al fianco dei loro coetanei italiani e hanno tutte le carte in regola per diventare insieme a loro i cittadini di domani.
... Il cittadino straniero, regolarmente residente in Italia, partecipa alla vita civile, politica, economica e culturale del paese è una risorsa positiva, la base su cui costruire l'integrazione. Un impegno che investe tutti gli aspetti della società e richiede quindi un approccio unitario e significativo ma non soluzioni superficiali, teoriche e complicate come spesso purtroppo accade.
... Quale è realmente l’intenzione del nuovo governo di centrosinistra in materia di immigrazione? per il momento non si sa nulla e l’unica cosa certa è qualche dichiarazione di principio, generico, da parte di qualche componente dell’attuale maggioranza. Nelle ultime settimane si è parlato molto di modifiche sostanziali, tanto attese dagli stranieri residenti in Italia, della legge Bossi-Fini.
... Il problema ormai cronaca dell’immigrazione non si risolve solo cambiando o modificando l'attuale politica sull'immigrazione che è rigida e "discriminatoria", ma dando priorità ai bisogni principali delle persone che lavorano e producono nella società.
Che cosa occorre fare fondamentalmente? andiamo per ordine:
* Il diritto di voto agli immigrati: un tema molto delicato, politico, “non esiste inclusione sociale senza partecipazione alla vita amministrativa nella città in cui si vive” visto che non si paga solo le tasse, come giusto che sia, ma si partecipa alla crescita collettiva;
* Questione di cittadinanza: le nuove regole di cittadinanza sono l’adeguamento di un paese alle regole di civiltà quindi occorre una riforma della quale fanno parte vecchi e nuovi cittadini;
* Regolarizzazione: in primo luogo occorre una verifica sulle richieste di regolarizzazione con l’obiettivo di regolarizzare coloro che svolgono attività lavorativa sotto forma di usa e getta.
... In conclusione, se si comincia a dare delle risposte adeguate, al meno a queste priorità, vorrà dire che lo straniero non è un oggetto da usare quando serve e gettare in un altro momento, ma è una persona che lavora e vive in un paese normale e civile.

venerdì

በጣሊያን የውጪ ዜጎችን ይሚመለከት ወቅታዊ ሁኔታ


di Abraham Zewdie
ኢጣሊያ - የውጭ ዜጎች የፍልሰት መመሪያ በአዲሱ የፕሮዲ አስተዳደር እየተለወጠ እንደሚገኝ የሰሞኑ የዜና መረጃዎች ያወሳሉ። አዲሱ መንግስት የBossi-Fini የፍልሰት መመሪያ ጽንሰ ሀሳቦች እንደሚቀየሩና እስካሁንም የተቀየሩትን ሰሞኑን በምክር ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባሉ።
ከዚህ በታች ትኩረት ከተሰጠባቸው፣ በውሳኔ ከአሳለፏቸው መካከልና ከተነጋገሩባቸው የመመሪያው ፅንሰ ሃሳቦች በንዑስ አርዕስት ሰፍረዋል።...
.
ስለ ካርታ ዲ ሶጆርኖ (Carta di Soggiorno)
በጣሊያን ኑሮአቸውን 5 ዓመት ያደረጉ የውጪ ዜጎች ካርታ ዲ ሶጆርኖ ሊያግኙ እንደሚችሉ ተገለጸ። እንደ Bossi-Fini የውጭ ዜጎች ፍልሰት መመሪያ "ካርታ ዲ ሶጆርኖ ለማግኘት የ6 ዓመት የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው" ይላል። አሁን ያለው የአዲሱ መንግሥት አስተዳደር ደግሞ መመሪያውን በማሻሻል እና አንድ ዓመት በመቀነስ ኑሮውን 5 ዓመት ያደረገ ከሆነ ሊሰጠው እንደሚችል" ነው። ይኼም በብሔራዊው የህዝብ ምክር ቤት (parlamento) ድምጽ ተሰጥቶበት ከአሸነፈ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የህጉን ረቂቅ አንቀጾች ቀምረው በአዋጅ እንዲድነገግ ይደረጋል። ከአዋጁም በኋላ ቁጥራቸው ወደ በመቶ ሺዎች የሚደርሱ የውጪ ዜጎች ሊገለገሉበት እንደሚችሉ ተገምቷል። ከሚፀናበት ጊዜ ጀምሮ ምዝገባዎችንና ማመልከቻዎችን በማስገባት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆኑ ይበጃል የሚሉ የውጪ ዘጎች ብዙኃን ናቸው።
የአውሮፓ ሕብረት የጋራ የሆነውን የፍልሰት መመሪያ (2003/109/CE) እንዳወጣ ብዙ ሳይቆዩ አንዳንድ አባላት ሀገሮች በአዋጅ እንዲፀና በማድረግ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በጣሊያን ዘግይቶ ቢደረግም በዚሁ የአዲሱ የመንግስት አስተዳደሯ ውስጥ በተግባር ላይ እንዲውል አሁን ጥረት እየተደረገ ነው ማለት ይቻላል።
ይህንን ካርታ ዲ ሶጆርኖ መያዙ ለምን ይጠቅማል? ለሚለው ጥያቄ የጣሊያን ሀገር አስትዳደር ሚኒስትር የሆኑት ጁሊያኖ አማቶ ሲመልሱ "ጣሊያን ሀገር ያሉትን የውጭ ተወላጆች የስደተኝነት ኑሮ በመጠኑም ቢሆን ሊያሻሽል ይችላል" ነው የሚሉት። ቀጥለውም "አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ 5 ዓመት ተቀምጦ እዚሁ ጣሊያን ሀገር ከሚኖሩ የአውሮፓ ሕብረት አባላት ዜጋዎች የማያንስ መብት እንዲኖራቸው ይገባል። ምንም ልዩነት ሳይደረግ በሰላም ሰርቶ ለመኖር እንዲችሉ፣ ትምህርት ተምረው የወደፊት የኑሮ እቅዳቸውን ለማውጣት እንዲችሉ መንገዱን ማስተካከል ይገባናል። ወደፊትም ከዚህ ጋር ተያይዞ መመሪያው ውስጥ ያሉትን ነጥቦች በማሻሻል የረጅም ጊዜ ኑሮ ለሚያደርጉት መብታቸው ከሀገሯ ዜጎች እኩል እንዲሆንላቸው መደረግ አለበት" በማለት አሳስበዋል።
.
ቤተስብን ለማስመጣት ... (Ricongiungimento)
አንድ የውጪ ዜጋ መኖሪያውን ለረጅም ጊዜ ጣሊያን ሀገር አድርጎ የቅርብ ቤተሰቡን አስመጥቶ ተቀማጭነቱ እዚሁ እንዲሆን ለማድረግና ለማስፈጸም የሚወስደው ረጅም ጊዜ ነው። ውጣ ውረድ የሚበዛበት ስለሆነ ይህን ውስብስብ ስርዓት አስተካክሎ በአጭር ጊዜ እንዲፈፀም የሚቻልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት።
የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ጁሊያኖ አማቶ በምክር ቤት ውስጥ እንደገለጹት "ይህንን ሁኔታ የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለማቃለል የአውሮፓ ሕብረት ያወጣውን መርሆችን መከተል እንደሚቻል" ተናግረዋል። ሚኒስትሩም በመቀጠል "ከረሃብ የተረፉትን ልጁ ወይም ወላጁን ለማስተናገድ በመኖሪያ ቤቱ ሜትር ስፋት መወሰኑ ብዙ ትኩረት የሚሰጠው መሆን የለበትም። ለደህንነታቸውና የጤና ችግር የማያመጣ ወይም የሚፈቀደውን ክራይቴሪያ ከአሟላ ይበቃል" ነው ያሉት። እንደገናም በማከል "የቤተሰብ ፍቅርን ማግኘትና መቀራረብ ለሁሉም ዜጋዎች ስበዓዊ መብታቸው መሆኑን መዘንጋት የለበትም" ብለው ደምድመዋል።

እየፈለሰ ለሚገባው የስደተኛውን ቁጥር ለመወሰን ...
ሀገር አስተዳዳሪው ሲያብራሩ "በአሁኑ ጊዜ ዋናውና ወቅታዊው ጥያቄ እየፈለሰ ለሚገባው ስደተኛ ቁጥሩን በየዓመቱ ምን ያህል እንደሆነ መወስን ሳይሆን ለጣሊያን የኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እስከአለው ድረስ እና የሕብረተሰብ ስርዓት እስካልተጓደለ ድረስ "እንኳን ደህና መጡ" ብሎ መቀበል እንጂ! ምን ችግር አለ? እስከሚቻለን ድረስ በመቀበልና ስርዓትን በማሲያዝ መወጣት እንችላለን" ነው ያሉት። ለጋዜጠኞች ቃለ ጥያቄ ሲመልሱም "የዓለም አቀፍን የሰበዓዊነት መብቶቹን እንዲከበር ለማድረግ በሚቻለን መንገድ ከመጣር ወደኋላ ማለት አይገባንም" ብለዋል። ...

በ nulla osta ሥራ መቅጠር ...
ሌላው ደግሞ በ Bossi-Fini የፍልሰት መመሪያ መሰረት የአውሮፓ ሕብረት አባላት የሆኑት የውጪ ዜጋዎችን አሠሪው በnulla osta አማካይነት ሥራ የማግኘቱ ዕድላቸው በጣም የሰፋ እንደነበረና አሁን ግን ይኼንን nulla osta እንዲቀር ተደርጎ ነፃና እኩል የሆነ የሥራ አቀጣጠር ላማንኛውም ዜጋ እንዲኖር ይደረጋል። ...

የጥቁር ሥራን ለማስወገድ ... (Lavoro nero)
በየፋብሪካውና በቤተሰብ አገልግሎት ውስጥ ብቻ የጥቁር ሥራ እየሠሩ ያሉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስለሆኑ ሁሉም regolarizzare መደረግ አለባቸው። ኢጣሊያዊው የአውሮፓው ሕብረት ምክትል ሊቀመንበር ማርኮ ፍራቲኒ አያይዘው "በ2004 ዓም በአንድ የእስታቲስቲክ ጥናት ላይ በሌሎች የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች ውስጥ በጥቁር ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ከ4% - 5% ያህል ነው። ነገርግን በኢጣሊያ ቁጥራቸው በጣም ከፍ ብሎ እንደሚገኝና እስከ16% - 17% የሚደርስ ነው" ብለዋል። እሳቸውም በመቀጠል "ይህንን በጊዘው ስራዓት ማሲያዝ ያስፈልጋል። ለዚህም በየክፍለሀገሩ የሚገኙት የጣሊያን ማዕከላዊ አስተዳደር ክፍሎች በጥቁር ሥራ ላይ የተሰማሩትን የውጪ ዜጋዎች ሙሉ በሙሉ በ regolare ሥራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ሁሉም ተሳትፎ ማድረግና ይሚቻለቸውን ግዴታ እንዲወጡት ብዙ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል።
.
የጣሊያን ዜግነት በ5 ዓመት ...
...........................................................
...........................................................
...........................................................
...........................................................
በጣሊያን ከ5 ዓመት በላይ የተቀመጡ ምን ያህል የውጪ ዜጎች አሉ?
የ Caritas /Migrantes የስታቲስቲክ መዝገብ እንድሚያስረዳው "በጣሊያን ኑሮአቸውን 5 ዓመት ያደረጉ የውጪ ዜጎች ቁጥር ወደ 900 ሺ ይደርሳሉ። ከ2 ዓመት በኋላ ደግሞ በ2002 ዓም regolarizzati የሆኑት 650 ሺ ዜጎች ተጨምረው በጠቅላላው 1 ሚሊዮን ተኩል የሚሆኑት ዜግነቱን የመውሰድ መብት ይኖራቸዋል። ታዲያ አልበዛም? እንዴት ሊሆን ነው? ለሚለው ጥያቄ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ጁሊያኖ አማቶ ሲመልሱ "እዚህ ላይ ቁጥርን በሚመለከቱ ነገሮች መጠንቀቅ ያለብን ይመስለኛል። ዜግነት ለመያዝ በየዓመቱ ቁጥራቸው እስከ 18 ሺህ ያህል የሚሆኑት የውጪ ዜጎች ሊቀርቡ ይችላሉ የሚል ግምት ነው ያለን። እንደውም በዚህ የቁጥር ገደብ ውስጥ ዜግነት ለማግኘት ማመልከቻ ያቀረቡት ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሏቸውን ልጆቻቸውንም ይጨምራል። ምክንያቱም በጣሊያን በየዓመቱ ከውጪ ዜጎች የሚወለዱት ህፃናት ብቻ ወደ 50 ሺ ይጠጋሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዜግነቱን የሚያገኙት ሁሉም አይደሉም። ወላጆቻቸው ኑሮአቸውን በጣሊያን ከ5 ዓመት በላይ ላደረጉት ብቻ ነው። ከእነዚህም ውስጥ በየዓመቱ ዜግነቱ ሊሰጣቸው ከሚችለው የቁጥር ገደብ ውስጥ በማስገባት ነው" ብለዋል። ....
ጠቅላይ ሚኒስትር ሮማኖ ፕሮዲ በማከል "10 ዓመት መሆኑ ቀርቶ 5 ዓመት መደረጉም ብዙዎቹ የአውሮፓ ሀገሮች የሚከተሉት በመሆኑ አንድ አይነት መስመር ለማሲያዝ ነው። በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ጣሊያን ከሌሎቹ የአውሮፓ የጋራ መርሕ ወደኋላ ስለምትገኝ ነው" ብለዋል፡ ጨምረው ሲያስረዱ "መጠን በማድረግ፣ ሌሎች መመዘኛዎች በማስገባትና እንዲሁም አመልካቾቹን በማወዳደር ገደብ እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል።
ለምሳሌ
1- ከዚህ በፊት ዜግነቱን ለማግኘት ብቻ ሲባል የውሸት ጋብቻ የሚፈፅሙት ላይ ጥንቃቄ ይደረጋል።
2- የቋንቋ ችሎታቸውን በመመዘን...
3- ..............." ብለው የቃለ መጠየቁን መደምደሚያ ሰጡ።
.
ሌሎች በስብሰባው ላይ ከተሰጡት አስተያየቶች ውስጥ (አስፈላጊ ከሆነ በዝርዝር ትንታኔዎችን ወደፊት እናቀርባለን)
ይህ በጣሊያን የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ በጊዜው ከተቃለለ ወደፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን እንዲስተካከል በማድረግና ስርዓት በማስያዝ የተወሰኑ የውጪ ዜጎች ችግር ለማቃላል ይረዳል።
ከእነዚህም ውስጥ አንዳንዱን ንጥብ
ለምሳሌ ...
* ዜግነትን በሚመለከት ከተሻሻሉት አንዳንድ የህጉ ረቂቆች ውስጥ ከዚህ በፊት በጋብቻ ምክንያት ዜግነቱን የሚያገኘው ማመልከቻውን ከአቀረበበት ጊዜ አንስቶ 2 ዓመት ያስፈልገው ነበር። አሁን በግማሽ ዓመት (6 ወር) ሊያገኝ ይችላል።
* በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙትም የተሻለ አማራጭ ዕድልና እኩል መብት እንዲኖራቸው፣
* በሌሎች የአውሮፓ ማህበር አባላት ሀገሮች ውስጥ ያለምንም እንቅፋት መዘዋወርና ሥራ የመሥራት ፍቃድ ለማግኘት የሚችሉበትን መብት ማስያዝ፣
* ለተገን ጥያቂዎች ዓለምአቀፋዊ የፖለቲካ ጥገኝነት መብት እንዳይነፈጋቸው ጥረት ማድረግ፣
* በጣሊያን ከረጅም ጊዜ የኑሮ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ምርጫ ላይ ተስትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
* ወደፊት የ5 ዓመት መኖሪያ ፈቃድ ያለው (ካርታ ዲ ሶጆርኖ ብቻ ሳይሆን) የተወሰኑ ... አሟልቶ የተገኘውን ዜግነቱንም መያዝ እንደሚችል ...
* ሥራ ፈላጊ ለሆነው የውጪ ሀገር ዜጋ በሩ እኩል ክፍት እንዲሆንለት፣
* መብታቸውና ስበዓዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ፣
* ደህንነታቸው አስተማማኝ እንዲሆን፣
... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ...