sabato

ያለማወቅ ከምንም አያድንም


ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ (ከቦሎኛ)
...... ሰላም ለአንባቢያን እንዴት ሰነበታችሁ?
..... በቅድሚያ ሰለቸኝና ደከመኝ ሳይል ቀንና ሌሊት በመድከም ይህንን መድረክ በማዘጋጀት የተጠቃሚነት እድል ለሰጠኝ ለአቶ አብርሃም ዘውዴ ልባዊ የሆነ ምስጋናዬን እቀርባለሁ::
...... ቀጥሎም እትዮጵያን በውጭዉ ዓለም ሁሌ በጥሩ ስም ለማስጠራት ለሚደክሙትና ይህቺ ዌብ ሳይት አምራ ደምቃና ከግብ ደርሳ ማየት እንድንችል ለተባበሩትና ወደፊትም ለሚተባበሩት ሁሉ መልካም ስራ፣ አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ግፉበት የድካማችሁ ውጤት ስራችሁ ነዉ እላለሁ::
...... በመሆኑም ነዉ አባቶች ሲተርቱ እንዲህ ያሉት "ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም":: ይህ በቅርቡ የተከፈተዉ እትዮጵያ በጣሊያን በመባል የታወቀዉ የኢንተርነት አድራሻ ማንኛችንም በጣሊያን ሃገር ነዋሪ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ትምህርት የምንቀስምበት መድረክ ከመሆን አልፎ አንዱ ከሌላዉ ጋር ሀሳብ ለሀሳብ የሚለዋወጥበት ጥሩ ዘመናዊ የመገናኛና የመወያያ ዘዴ ነዉ::
...... ለዚህም ነዉ "ያለማወቅ ከምንም አያድንም" በማለት ሀሳብ መስጠት የጀመርኩት:: በእርግጥ ብዙዎቻችን የጊዜ እጥረትና የስራ ሁኔታዎች ያለመመቻቸት ችግር ሊኖረን እንደሚችል ማወቅ ተስኖኝ ሳይሆን ከዚችው ካለችን ጊዜ የተወሰነችዋን ጠቃሚ በሆነዉ በትምህርት ላይ ብናዉላት የአዕምሮ እረፍት እናገኛለን የሚል የጠና እምነት ስላለኝ ነዉ::
.
ይህ የእትዮጵያ በጣሊያን ኢንተርኔት ዌብ ሳይት ለምን ለምን ይጠቅማል? ማንንስ ይመለከታል?
...... ከመልሶቹ በጥቂቱ:-
1. የጣሊያንኛ ችግር ላለባቸዉ ግለሰቦች ሁሉ በአማርኛ የመጻፍና የማንበብ እድል ይሰጣል;
2. በጣሊያን ሀገር የእኛን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዜና ያቀርባል;
3. ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ተቀይሮ የነበረዉን የስልክ ቁጥር ችግር በማቃለል በአሮጌዉ ምትክ አዲሱን ፈላልጎ ማግኘት ይቻላል;
4. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋን የሚመለከት የመኖሪያ ፈቃድ ህግን በተመለከተ ማብራሪያ ያቀርባል;
5. በጣሊያን የእትዮጵያ ኤምባሲን አድራሻና የስልክ ቁጥር ከመጠቆም አልፎ ለኤምባሲዉ ባለጉዳዮች ምን ሰነዶች እንደሚያስፈልጉ ያስረዳል;
6. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእናት ሀገሩን የተለያየ ወቅታዊ ዜና በሚፈልገዉ ማግኘት ይችላል;
7. በጣሊያን ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ ማህበራት ዝርዝርና አድራሻ ያቀርባል;

8. የአዉሮፓ የቀን አቆጣጠርን ወደ ኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር በቀላሉ መቀየር ይቻላል;
9. የተለያዩ የሀገር ባህላዊ ዘፈኖችን መስማትና ድራማዎችን መከታተል ይቻላል;
10. የተለያዩ አስተያየቶችን መላክና መቀበልም ጭምር ይቻላል::
11. ...ይቀጥላል ...


giovedì

የጣሊያን የምንስትሮች ምክር ቤት አዲስ የኢምግሬሽን የሕግ ረቂቅ አወጣ


(ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ)
.....በጣሊያን አገር የሰሞኑን የኢምግሬሽን የሕግ ለዉጥ በተመለከተ የተለያዩ ህሳቦች በተለይም ከእዉነት የራቁ ወሬዎች ከየአቅጣጫዉ ይሰነዘራሉ:: በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የሕግ ረቂቂ እንጂ ተግባራዊ የሆነ ሕግ አለመሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ:: በአንድ አገር አንድን ሕግ ተግባራዊ ሕግ ነዉ ሊያሰኘዉ የሚችለዉ የአገሪቱ ፓርላማ አፅድቆት በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣ በኋላ ነዉ:: ከዚህ ሁሉ የዉጣዉረድ ጉዞዉ በኋላ ሕጉ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሕግ ነዉ ብሎ ማለት ይቻላል:: ይህ ሕግ ገና ብዙ መሰናክሎችን ያላለፈ እንደመሆኑ መጠን ተጠቃሚዉን ክፍል ችግር ላይ ጥሎት ሰሞኑን አንዳንድ ግለሰቦች... "አዲስ ሕግ ወጥቷል ብለዉ የሆኑ ጣሊያኖች ሲያወሩ ሰማሁ እዉነት ነዉ?" "የዜግነት ጥያቄስ አሁኑኑ ማቅረብ እችላለሁ?" ... እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ:: በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከተዉና በጣሊያን አገር ነዋሪ የሆነዉ የዉጭ አገር ዜጋ በተለይም የአማርኛን ቋንቋ አንብቦ መረዳት የሚችል ሁሉ ትክክለኛዉን መልእክት ማግኘት ይችላል ብዬ በማመን የሕጉን ለዉጥና መንፈስ አጠር ባለ መልኩ ከዚህ በታች ላስቀምጥ እሞክራለሁ::

FLUSSI DI INGRESSO
ካሁን በፊት በየአመቱ የዉጭ አገር ዜጎች ወደ ጣሊያን አገር በመምጣት መስራት እንዲችሉ የተወሰነ ቁጥር ገደብ ተደርጎ ፕሮግራም ይወጣል በአዲሱ ህግ ግን ይህ ቁጥር በሶስት አመት አንድ ጊዜ ይወሰናል ቁጥሩም እንዳስፈላጊነቱ ሊጨምር ይችላል::
.
LAVORATORI ALTAMENTE QUALIFICATI
ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸዉ የዉጭ አገር ዜጎች ጣሊያን አገር መጥተዉ ለመስራት ጥያቄ ካቀረቡ የመምጣት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ይላል ካሁን ቀደም የነበረዉ ህግ ግን የጉልበት ስራን ብቻ ይመለከት ነበር::

LISTE DI COLLOCAMENTO
ማንኛዉም የዉጭ አገር ዜጋ ጣሊያን አገር ገብቶ ስራ ለመስራት ባለበት አገር የጣሊያን አምባሲ በሚገኘዉ የስራ ፈላጊዎች ዝርዝር ሰነድ ላይ መመዝገብ ይኖርበታል::

AUTOSPONSORIZZAZIONE
አንድ የዉጭ አገር ዜጋ በራሱ ሃላፊነት የራሱን ወጪ ችሎ ዋስትናዉን እራሱ ከሸፈነ ጣሊያን አገር ገብቶ ስራ የመስራት መብት አለዉ:: ለምሳሌ በዚህ አንቀጽ መሰረት አንድ ግለሰብ በቂ ገንዘብ አለኝ ለጣሊያን ቪዛ ይሰጠኝ ብሎ ቢጠይቅ ቪዛዉን የማግኘት እድል አለዉ ማለት ነዉ::

VISTI D’INGRESSO
አንድ የዉጭ አገር ዜጋ ጣሊያን አገር ለመምጣት ቪዛ በሚጠይቅበት ወቅት ያለአንዳች ቢሮክራሲና ዉጣዉረድ ለጥያቄዉ መልስ ባስቸኳይ ሊሰጠዉ ይገባል:: ጣሊያንም ከመጣ በኋላ ካሁን በፊት እንደነበረዉ የመኖሪያ ኮንትራት (contratto di soggiorno) የመፈረም ግዴታ አይኖርበትም::

DURATA DEI PERMESSI
የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የጊዜ ገደብ ካሁን በፊት ከነበረዉ የረዘመ ይሆናል:: ለምሳሌ የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ አነስተኛ ከሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ ለስድስት ወር ይሰጠዋል:: የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ ከስድስት ወር በላይ ከሆነ ግን የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ የሁለት አመት ይሆናል:: የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ የሌለዉ ከሆነ የሶስት አመት የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ይሰጠዋል:: የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ በሚታደስበት ወቅት የጊዜ ገደቡ እጥፍ ይሆንና የስድስት ወር የነበረዉ ለአንድ አመት፣ የሁለት አመቱ ለአራት አመት ይታደስለታል ማለት ነዉ::
.
PERMESSI PER MOTIVI UMANITARI
የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት በስራ ብቻ ሳይሆን በሰባዊ መብት ምክንያትም ለአንድ አመት ሊሰጥ ይችላል:: የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱንም ለማሳደስ ግለሰቡን ሊያኖር የሚችል የገቢ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል::
.
PASSAGGIO DELLE COMPETENZE AI COMUNI
ይህ ሕግ በተግባር ሲተረጎም የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማሳደሱ ተግባር ሃላፊነቱ የፖሊስ ጽ/ቤት ሳይሆን የማዘጋጃ ቤት ይሆናል:: ይህም በየፖሊስ ጽ/ቤቶች በራፍ ሲደረግ የነበረዉን የሰዉ ልጅ የማያልቅ ሰልፍ ሊያስወግድ ይችላል::

INSERIMENTO DEI MINORI STRANIERI
በጣሊያን አገር ነዋሪዉ የዉጭ አገር ዜጋ ህጻናትም ጭምር ከህብረተሰቡ ተዋህዶ አምራች ዜጋ መሆን እንዲችል የስራ፣ የትምህርት፣ የህክምና፣ የመኖሪያ ቤት፣ የጡረታ እኩልነት መብቱ ሁሉ ይከበርለታል::

ELETTORATO ATTIVO E PASSIVO ALLE AMMINISTRATIVE
በወንጀል ያልተነካካ በጣሊያን አገር በህጋዊነት ለአምስት አመት ያህል ነዋሪ የሆነ ማንኛዉም የዉጭ አገር ዜጋ በሚኖርበት ክፍለ ሀገር በሚደረገዉ የአስተዳደር ምርጫ በመራጭነትም ሆነ በተመራጭነት የመካፈል መብት ይኖረዋል::

PROGRAMMI DI RIMPATRIO E ASSISTITO
በተለያዩ ምክንያቶች በጣሊያን አገር መኖር የማይችሉት የዉጭ አገር ዜጎች ፕሮግራም ይዘጋጅና በወጣዉ ፕሮግራም መሰረት እርዳታ ተደርጎላቸዉ ወደየመጡበት አገራቸዉ እንዲመለሱ ይደረጋል:: አገራቸዉም ከገቡ በኋላ እንደገና ተመልሰዉ ጣሊያን አገር በስራ የመምጣት እድል ቅድሚያ ይሰጣቸዋል::

MODALITA’ DI ALLONTANAMENTO
አንድ በጣሊያን አገር የሚኖር የዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል ከተገኘበት እንደየወንጀሉ ክብደት፣ ቀላልነትና አደገኛነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ይታሰራል ወይንም አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ይደረጋል::

CENTRI DI PERMANENZA TEMPORANEA
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጣሊያን አገር የገቡ የዉጭ አገር ዜጎች ተይዘዉ ማንነታቸዉ ተረጋግጦ ወደያገራቸዉ እስከሚመለሱ ድረስ እስከ ስልሳ ቀናት ያህል ይቆያሉ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ይደረጋል:: የማረፊያ ቤቶቹም ቁጥር ካሁን ቀደም ከነበረዉ አነስተኛ ይሆናል::
ለማጠቃለል ያህል ይህ የሕግ ረቂቅ ከሞላ ጎደል ሲታይ የሰዉን ልጅ መብት የሚያስከብር ሌሎች በዴሞክራሲ የበለጸጉ አገሮች ካላቸዉ የኢሚግሬሽን ሕግ ጋር የሚቀራረብ ይመስለኛል ሆኖም አንዳንድ የጣሊያን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉ እንዳይጸድቅና ግቡን እንዳይመታ ከመፈለጋቸዉ የተነሳ ጣሊያን በዉጭ አገር ዜጋ ልትወረር ነዉ፣ አገሪቱ የወንጀለኛ ማጠራቀሚያ ልትሆን ነዉ፣ እና ወዘተ በማለት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር በመንዛት ፍርሃት በመፍጠር ላይ ይገኛሉ:: ጉዳዩ "አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ" እንደሚለዉ የአባቶች ተረት እንዳይሆን የጣሊያን መንግስት ጥንቃቄ ሊያደርግበት ይገባል ብዬ እላለሁ::
Bologna, 30/04/2007


domenica

በጣሊያን በጥገኝነት ለሚኖሩ - Richiedenti asilo


በጣሊያን ጥገኝነት (የተገን መብት) ለማግኘት ማመልከቻ ላስገቡት ለየት ያለ የመኖሪያ ፍቃድ ...
27 04 06
እንደ አማራጭ እድል ሊወሰድ ይችላል ግን.....
ከዚህ በፊት በጣሊያን የተገን መብትን ለማግኘት ወይም በጥገኝነት ለመኖር ማመልከቻ ያቀረቡ ከኮሚሲዮኑ መልስ ሳያገኙ ለዓመታት በቁማቸው የቀሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የውጪ ዜጋዎች እንዳሉ ይታወቃል። የዛሬ ሁለት ዓመት (21 Aprile 2005) የተለየ መመሪያ ወጥቶ ብዙ ሺህ የሚሆኑ ተገን ጠያቂዎች ይህንኑ ማመልከቻ አቅርበው እስካሁን መልስ ያላገኙ ናቸው። "አጠራጣሪ ተስፋ ይዘው ከሚቀመጡ ሌላ አማራጭ እድል ይኑራችው" በማለት ከእዚህ በታች ያለውን ለየት ያለ መንገድ ፈጥረዋል።
ይኸውም፡- ማመልከቻቸውን ለሚያነሱ ወይም rinunciare ለሚያደርጉ ለየት ያለ ሰበዓዊ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጥ በማድረግ ነው። (ይህ ፍቃድ Permesso di soggiorno per Motivo Umanitari ተብሎ የሚጠራና ለየት ያለ ይዘት እንዳለው ደግሞ ማወቅ ይገባል። ምክንያቱም ማመልከቻ ጥያቄዎን ከማንሳትዎ በፊት አንዳንድ ሁኔታዎቹን መመርመር አይከፋም ለማለት ነው) ከዚህ በኋላ ግን ሁኔታውን መርምረው rinunciare ለማድረግ ውሳኔ ላይ ለደረሱት ወይም ይህ አማራጭ እድል ለሚስማማቸው ፎርሙን በቀጥታ ከዚህ አገናኝ አውርደው (scaricare አድርገው) ፎርሙን ከሞሉ በኋላ ለማዕከላዊ ኮሚሲዮኔ FAX መላክ አለብዎት። ይህም ኮሚሲዮኔ permesso umanitari ሊያገኙ እንደሚገባዎት ለኩዌስቱራ ያሳውቃል። እርስዎም እንደ አመልካችነትዎ ይህንን ማግኘትዎንና መብትዎት የሚከበርልዎት ዜጋ መሆኑዎን ለJudice Istruttore ያሳውቃሉ።
የተገን ጠያቂዎችን የሚመለክተው ማከላዊው የምክር ፅህፈት ቤትም ይህ እርምጃቸው በጣም የሚያረካቸው ሆነው አግኝተውታል። የጽህፈትቤቱ ዳይሬክተር የሆኑት Christopher Hein ሲናገሩም ከ 2002 ዓም ጀምሮ መልስ እስኪሰጣቸው ድረስ ይሚጣባበቁ አሁንም እንዳሉ በማስረዳት "ብዙዎቹ ይህንን እድል በመጠቀም በጣሊያን የመኖርና የመሥራት ፈቃድ የሚያገኙበት በመሆኑ በጣም ደስ ብሎናል" ብለዋል። እራሱን ይህን አማራጭ እድል በተግባር ላይ ለማዋል በስብሰባቸው ውሳኔ ላይ መድረሳችን ብቻ የሚያኮራን ነው ይላሉ።
.
ማስገንዘቢያ
በመሀል ተንጠልጥለው የሚቀሩ ጥያቄዎች አይጠፉም
ለምሳሌ
* ይህ permesso umanitario በየጊዜው ለማሳደስ ከበድ ሊል ይችላል
* ከ permesso di soggiorno የሚያንስ ጊዜ ያለው ነው
* Ricongiungimento familiari የማግኘት መብት አይሰጥም
* ...ወዘተ...
በእነዚህ ምክንያቶች ውሳኔ አድርገው ፎርም ሞልተው ፈርመውና ፋክስ ከማድረግዎ በፊት ሁኔታውን በደንብ ይመርምሩ።
etiopiainitalia@yahoo.it


giovedì

የጣሊያን መንግስት ለሰማኒያ ሺህ የዉጭ አገር ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ፍቃድ ሊሰጥ ነዉ


80 MILA STAGIONALI NON COMUNITARI
8 03 2007
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
Il prossimo 12 marzo 2007 sarà pubblicato, in gazzetta ufficiale, il decreto che ha stabilito le quote massime di ingresso di lavoratori non comunitari per l’anno 2007. Sono ammessi in Italia per motivi di lavoro subordinato, i cittadini stranieri non comunitari residenti all’estero, entro una quota massima di 80000 unità, da ripartire tra le regioni e le province autonome”. A partire dalla stessa data quindi sarà possibile presentare le domande per far entrare in Italia e assumere lavoratori stagionali extracomunitari.
Ci si può rivolgere alle associazioni di categoria o spedire la richiesta d'assunzione per raccomandata al Ministero dell’Interno.
Gli 80mila nuovi ingressi autorizzati dal nuovo decreto flussi sono riservati a stagionali provenienti dai seguenti paesi:
Serbia, Montenegro, Bosnia-Herzegovina, ex Repubblica Jugoslavia di Macedonia, Croazia, India, Pakistan, Bangladesh, Sri Lanka, Ucraina, Tunisia, Albania, Marocco, Moldavia, Egitto e altri.
Indipendentemente dalla nazionalità, potrà inoltre entrare chi è stato titolare di un permesso per lavoro stagionale negli ultimi tre anni. I datori di lavoro potranno presentare le domande attraverso le associazioni di categoria o spedendole per raccomandata semplice al ministero dell'Interno. La prima strada dovrebbe garantire tempi più brevi per il rilascio del nulla osta, dal momento che la procedura è completamente informatizzata. Gli sportelli delle associazioni di categoria possono infatti compilare le domande ondine e inviarle subito allo Sportello Unico per l'Immigrazione, che le inoltra alla Direzione provinciale del Lavoro.
Per presentare invece la domanda per posta si deve scaricare il modulo 07-STAG (non si possono utilizzare fotocopie) dal sito internet del Ministero dell'Interno, compilarlo e inserirlo in una busta insieme alla fotocopia dei documenti del datore di lavoro e del lavoratore straniero. Sulla busta va incollato o ricopiato il modello di frontespizio pubblicato dal Ministero dell'Interno, presso il quale è stata creata una task force che digitalizzerà la domanda e la inoltrerà allo Sportello Unico per l'Immigrazione.

Dai seguenti link potete scaricare moduli e istruzioni
(Cliccate col tasto destro e scegliete "salva oggetto con nome..."):
8 marzo 2007 Elvio Pasca


sabato

በጣሊያን አገር ሰራተኛ ከስራዉ ሲሰናበት ተጠራቅሞ ቆይቶ በመጨረሻ ላይ የሚከፈለዉን ገንዘብ የሚመለከት የህግ ለዉጥ


TFR
Che cos’è?
01 02 2007 ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ

ይህን በተመለከተ በቅርቡ የጣሊያን መንግስት አዲስ መመሪያ አዉጥቷል:: የመመሪያዉን ይዘት ከዚህ ቀጥዬ ባጭሩ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ::

እያንዳንዱ ማለትም ጉዳዩ የሚመለከተዉ ግለሰብ ሁሉ የጊዜዉ ገደብ ከማለፉ በፊት በመከታተልና ጠይቆ በመረዳት አስፈላጊዉን ፎርም መሙላት ይኖርበታል::

በመጀመሪያ ደረጃ TFR ማለት ምን ማለት ነዉ?

በጣሊያንኛ Trattamento di Fine Rapporto (TFR) ወይንም በዘልማድ አነጋገር Liquidazione በመባል የሚታወቀዉ የስራ መሰናበቻ በጀት አንድ አሰሪ ግለሰብ ወይንም ድርጅት ሰራተኛዉን በሚያሰናብትበት ወቅት ተጠራቅሞ የቆየዉን ለሚያሰናብተዉ ሰራተኛ የሚከፍለዉ የገንዘብ መጠን ነዉ:: ሰራተኛዉ ለብዙ አመታት በስራዉ ላይ ተሰማርቶ ከሆነ የገንዘቡም መጠን በዚያዉ ልክ ከፍ ይላል:: የስራዉ ጊዜ አነስተኛ ከሆነ ግን ገንዘቡም አነስተኛ ይሆናል:: ካሁን ቀደም የነበረዉን ህግ ከተመለከትን እንዲህ ይላል - አንድ ሰራተኛ ከስራዉ በሚሰናበትበት ወቅት ከደመወዙ ተቀናንሶና ተጠራቅሞ የቆየዉ ገንዘቡ ባንድ ጊዜ ለሰራተኛዉ ይከፈለዋል::

ባዲሱ ህግ ግን አንድ ሰራተኛ እስከ 30/06/2007 ባለዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ፎርም በመሙላት ገንዘቡ በአሰሪዉ እጅ እንዲቆይለትና መጨረሻ ላይ እንዲከፈለዉ ወይንም በሌላ የእንቨስትመንት መልክ ወደ ጡረታ በጀት እንዲዛወርለት የመምረጥ ግዴታ አለበት:: ከሁለቱ አንዱን ካልመረጠ ግን እንደችላ ባይ ተቀባይ ተቆጥሮ አሰሪዉ ይህንኑ ገንዘብ ወደ ጡረታ በጀት እንዲዘዋወር ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ያስተላልፋል:: ይህ አዲስ ህግ ለጊዜዉ የመንግስት ሰራተኛንና በቤት ሰራተኛነት ተቀጥረዉ የሚሰሩትን የቤት ሰራተኞችን (colf e badanti) አይመለከትም::

Che cos’è il TFR?
Il trattamento di fine rapporto (anche conosciuto come “liquidazione”) è la somma che viene corrisposta dal datore di lavoro al lavoratore al termine del rapporto di lavoro dipendente.

Come si determina?
Il TFR si determina accantonando per ciascun anno di lavoro una quota pari al 6,91 % della retribuzione lorda. La retribuzione utile per il calcolo del TFR comprende tutte le voci retributive corrisposte in dipendenza del rapporto di lavoro, salvo diversa previsione dei contratti collettivi. Gli importi accantonati sono rivalutati, al 31 dicembre di ogni anno, con l'applicazione di un tasso costituito dall'1,5% in misura fissa e dal 75% dell'aumento dell'indice dei prezzi al consumo Istat. Al momento della liquidazione, il TFR è tassato, in linea generale, con l’applicazione dell’aliquota IRPEF media del lavoratore nell’anno in cui è percepito. Per la parte di TFR che si riferisce agli anni di lavoro decorrenti dal 1° gennaio 2001, l’amministrazione finanziaria provvede poi a riliquidare l’imposta, applicando l’aliquota media di tassazione del lavoratore degli ultimi 5 anni.

La scelta sulla destinazione del Tfr
In base a quanto previsto dal disegno di legge finanziaria, dal 1° gennaio 2007 ciascun lavoratore dipendente può scegliere di destinare il proprio Trattamento di Fine Rapporto (TFR) maturando (futuro) alle forme pensionistiche complementari o mantenere il TFR presso il datore di lavoro. In relazione all’anzianità contributiva maturata presso gli enti di previdenza obbligatoria si aprono diverse possibilità di scelta per i lavoratori.

Lavoratori dipendenti iscritti ad un ente di previdenza obbligatoria dal 29 aprile 1993.

La scelta del lavoratore sulla destinazione del TFR riguarda l’intero TFR maturando e può essere manifestata in modo esplicito (dichiarazione espressa) o tacito (silenzio-assenso all’adesione).

Modalità Esplicite
Entro il 30 giugno 2007 per i lavoratori in servizio al 1° gennaio 2007, o entro 6 mesi dalla data di assunzione, se avvenuta successivamente al 1° gennaio 2007, il lavoratore dipendente può scegliere di: •
destinare il TFR futuro ad una forma pensionistica complementare; • mantenere il TFR futuro presso il datore di lavoro. In tal caso, per i lavoratori di aziende con più di 50 dipendenti, l’intero TFR è trasferito dal datore di lavoro al Fondo per l’erogazione del TFR ai dipendenti del settore privato, gestito, per conto dello Stato, dall’INPS.

Modalità Tacite (Silenzio - Assenso)
Se entro il 30 giugno 2007 per chi è in servizio al 1° gennaio 2007, o entro 6 mesi dall’assunzione, se avvenuta successivamente al 1° gennaio 2007, il lavoratore non esprime alcuna indicazione relativa alla destinazione del TFR, il datore di lavoro trasferisce il TFR futuro alla forma pensionistica collettiva prevista dagli accordi o contratti collettivi, anche territoriali, o ad altra forma collettiva individuata con un diverso accordo aziendale, se previsto. Tale diverso accordo deve essere notificato dal datore di lavoro al lavoratore in modo diretto e personale.



mercoledì

ጣሊያንና የዉጭ ዜጎችዋ


ከጠብ ወደ ፍቅር ወይንስ ከፍቅር ወደ ጠብ
ቃለ መጠይቅ

የተያያዝነዉ አዲስ ዓመት የሰላም፣ የደስታና የብልጽግና ይሁንልን በማለት እራሴን ላስተዋዉቅ።
አብረሃም ዘዉዴ እባላለሁ:: ከሁሉም በፊት በየዕለቱ ይህንን ድረገፅ የሚጎበኙት (በውጪ ሀገራት የሚኖሩት) ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እና ይህች ድረገፅ የራስዋ ግብ ላይ ለመድረስ ስለተቃረበች አዘጋጅና ተባባሪዎች የሆንን በሙሉ ደስታ ተሰምቶናል። ለዚህም እኔም ከልብ አመሰግናለሁ::
ከዚህም በመቀጠል ለዚህ መድረክ ዝግጅት መሳካት ተባባሪ ከሆኑት አንዱ ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ ጋር በጣሊያን የዉጭ አገር ዜጎችን በተመለከተ አጠቃላይ ሁኔታ ያደረግሁትን ቃለ መጠይቅ (ጥያቄና መልስ) ባጭሩ ከዚህ በታች አቀርብላችኋለሁ::

ጥያቄ:- ... በቅርቡ አለም አቀፍ የስደተኞች ቀን (Immigration Day) በጣሊያንም አገርም ተከብሮ ነበር:: ይህን በተመለከተ በጣሊያን ለሚኖሩት ኢትዮጵያዉያንም ሆነ ከጣሊያን ዉጪ ለሚከታተሉን ሁሉ ምን መልዕክት ያስተላልፋሉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... ይህን ጥያቄ በብዙ መልኩ መመለስ ይቻላል:: ለምሳሌ የጣሊያን ፕሬዝደንት የተከበሩት ጆርጆ ናፖሊታኖ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰሞኑን እንዲህ ብለዉ ነበር: በጣሊያን ነዋሪዉ የዉጭ አገር ዜጋ ለኢኮኖሚያችንና ለባህላችን እድገት መሰረት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፣ ልዩነታችን የብልጽግናችን መሰረት ነዉ:: በታሪክ እንደሚታወቀዉ ሁሉ እኛ ጣሊያኖች በመሰደድ የመጀመሪያዎች ነበርን ዛሬ ግን የዉጭ አገር ዜጎች ስራ ለመፈለግ በራችንን በሚያንኳዋኩበት ባሁኑ ወቅት የማስተናገድ ችሎታችንም ያን ያህል ከፍተኛ መሆን አለበት:: ሁሉም የዉጭ አገር ዜጋ እንደወንጀለኛ መቆጠርና መታየት የለበትም:: በህጋዊ መንገድ ሰርቶ የሚኖር፣ ህጋችንን የሚያከብር የዉጭ አገር ዜጋ ሁሉ መብቱ ሊከበርለት ይገባል ያሉት ተስፋ የሚሰጥ ይመስለኛል::

ጥያቄ:- ... ባለፈዉ 21/12/2006 የጣሊያን ፓርላማ የ 2007 የአመት በጀቱን አጽድቋል:: በዚህ ህግ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጋን የሚመለከቱ ጉዳዮች ወይም አንቀጾች ካሉ በተለይ በጣሊያን ለሚኖሩ አንባቢያን ሊጠቅም ስለሚችል ባጭሩ ቢገልጹልን?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... አንዳንድ ጥቃቅን ጉዳዮች አሉበት ለምሳሌ የዉጭ አገር ዜጋን የስራና የመኖሪያ ችግር ለማቃለል ተብሎ የተወሰነ ያህል በጀት ተመድቧል፣ በቤት አገልጋይነት የዉጭ አገር ዜጋን ቀጥሮ የሚያሰራ ማንኛዉም አሰሪ ግለሰብ የግብር ቅነሳ ይደረግለታል፣ አዲስ ኮምፕዩተር ለሚገዛ ወይንም ያለዉን ለሚቀይር የዋጋ ቅናሽ ይደረግለታል፣ የያዘዉን አሮገ የቤት መኪና በአዲስ ለሚቀይር ድጎማ ይሰጠዋል፣ የግል ድርጅት ለማቋቋም ለሚፈልጉ አማካሪ ድርጅቶችን ይመድባል የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል:: በወረቀት ላይ ያሰፈሩት ተግባራዊ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ አንዳንዴ ህጎች ይጸድቁና ተግባራዊ ሳይሆኑ ይቀራሉና ተከታትሎ ዉጤቱንም ማረጋገጥ ያስፈለጋል::

ጥያቄ:- ... ለመሆኑ በጣሊያን ፓርላማ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጎች አሉ? ካሉ ቁጥራቸዉስ ምን ያህል ነዉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በጣሊያን ፓርላማ ዉስጥ በመጨረሻዉ ምርጫ የተመረጡት በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጋ በዜግነት ጣሊያናዊ የሆኑት ተመራጮች ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ:: ባልሳሳት አራት ወይም አምስት ቢሆኑ ነዉ:: ይህ የሚያሳየን በጣሊያን የዉጭ አገር ዜጋዉ በፖለቲካ የተጠናከረና የተደራጀ አለመሆኑን ነዉ:: ምንም በፓርላማ ባይመረጡም በየክፍለሃገሮችና በየማዘጋጃ ቤቶች ያስተዳደር ምርጫ በመካፈል የሚመረጡት በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጎች ቁጥር ግን እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፣ ይህም ያበረታታል ብዬ አምናለሁ::

ጥያቄ:- ... በጣሊያን አገር በግምት ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ የዉጭ አገር ዜጎች እንደሚኖሩ እንሰማለን በፖለቲካና በማህበራዊ ኑሮዉ ሙሉ በሙሉ የተካፈሉት ጥቂቶች ናቸዉ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በመጀመሪያ ባንድ አገር የፖለቲካና ማህበራዊ ኑሮ ሙሉ በሙሉ ለመካፈል የዚያን አገር ቋንቋ፣ ባህል፣ የኑሮ ዘዴ፣ እና የመሳሰሉትን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል:: አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከጣሊያን ዉጪ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ በመፈለግ ጣሊያንን እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ አድርገዉ ስለሚወስዱ ቋንቋውን ለማጥናትም ሆነ አልፎ ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ብዙም የዉስጥ ፍላጎት አይኖራቸዉም፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ኑሮዉ ተካፋይነታቸዉም እየቀነሰ ይመጣል:: አንዳንድ ጊዜ የቁጥር መብዛት ብቻዉን በቂ ሊሆን አይችልም:: በሌላ በኩል ደግሞ ከጣሊያን የመንግስታዊ አካል በኩል ለብዙ ጊዜ የዉጭ አገር ዜጎች ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቆይቷል፣ ችግሮች ከመከሰታቸዉ በፊት ፕሮግራም አይወጣም ይህ ደግሞ ለቁጥጥር አመቺ አይሆንም እንክርዳዱን ከስንዴዉ ለመለየትም ያዳግታል::

ጥያቄ:- ... የጣሊያን ጋዜጠኞች ብዙ ጊዜ ስለዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል ብቻ ሲጽፉ እናያለን የዉጭ አገር ዜጋዉ ሁሉ ወንጀለኛ ነዉ ማለት ነዉ ወይንስ ይህ ጉዳይ እንዴት ነዉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... አዎን ጋዜጦች ለምዶባቸዉ ነዉ መሰለኝ የዉጭ አገር ዜጋዉን ሁሉ ከወንጀል ጋር ያዛምዱታል፣ ይህ በኔ ግምት የፕሮፌሽኒስት ወይም የባለ ሙያ ጋዜጠኛ ስራ አይደለም ምክንያቱም እየቆየ ሲሄድ ከፍቅር ይልቅ ወደ ጠብ ያመራል:: እዚህ ላይ አንድ የማስታዉሰዉ ነገር አለ ባለፈዉ ጊዜ አንድ የሴኔጋል ተወላጅ ለረፍት ባህር ሄዶ ከሌሎች ጋር ዋና በመዋኘት ላይ እንዳሉ አንድ ጣሊያናዊ ህጻን ይሰምጥና የሰመጠዉን ልጅ አድናለሁ ብሎ ገብቶ ሰምጦ ሞተ:: ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት ይህን ያህል አልተወራም ነበር:: እንደዚህ አይነት ተግባር ቢታይም ለህብረተሰቡ በተገቢዉ መንገድ አይቀርብለትም:: ይህ ብቻ አይደለም በጣሊያን ሰሜናዊ ክፍል ለፍተዉ የግል ድርጅቶች በመክፈት የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጎሳ፣ የቀለም ልዩነት ሳይሉ ጣሊያኖችንም ጭምር ቀጥረዉ የሚያሰሩ በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጎች በብዛት እንዳሉ መዘንጋት የለብንም:: ይህ ደግሞ ከጠብ ወደ ፍቅር ሊያመራ የሚችል ትክክለኛ መንገድ ነዉ::

ጥያቄ:- ... በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በሺህ በሚቆጠሩ በተለያዩ ምክንያቶች ከትዉልድ አገራችን ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ “አንድነት ሃይል” መሆኑን ሳንዘነጋ በጋራ ችግሮች ላይ እኛን ከመሰሉት ሌሎች የዉጭ አገር ዜጎች ጋር መቀራረብና መነጋገር ይኖርብናል:: እያንዳንዱ ግለሰብ የሚያዉቀዉን ለሌላዉ ለማያውቀዉ ወገኑ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት አዉቆ ተገቢዉን ቢያንስ የሞራል እርዳታን መለገስ ይኖርበታል:: የማናዉቀዉን ጉዳይ ከሚያዉቁት ጠይቆ ከመረዳት ወደ ኋላ አለማለት፣ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጥ:: ...