martedì

በጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ሰሞኑን አዲስ ሰርኩላር አስተላለፈ


ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
01 09 07
ካሁን ቀደም ማለትም በቅርቡ የስራ ቪዛ በማግኘት ብዙ የዉጭ ሀገር ዜጎች ጣሊያን ሀገር ለስራ እንደመጡ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ተነግሮ እንደነበር ይታወሳል::
ይህም ሊሆን የቻለዉ የ 2006 አመት መደበኛ ፕሮግራምን አስመልክቶ ሲሆን ችግሩ የተከሰተዉ ጣሊያን ሳይገቡ በፊት ሳይሆን በዚሁ በጣሊያን ምድር ላይ ነዉ::
አሰሪዉ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ሰራተኛ ለመቅጠር ማመልከቻ አስገብቶ በነበረበት ወቅትና ተቀጣሪዉ ጣሊያን በደረሰበት የጊዘ ገደብ መካከል ብዙ ቀናት በማለፉ በዚህ መካከል ቀጣሪዉ ወይም አሰሪዉ ሰዉ ሃሳቡን ቀይሮ ሰራተኛዉን ለመቅጠር ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘ የዉጭ ሃገር ዜጋው ችግር ላይ ይወድቃል መፍትሄዉስ ምን ሊሆን ይችላል?
የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ካሁን በፊት በ 07/07/2006 አዉጥቶ በነበረዉ ቁ. 2570 የዉስጥ ሰርኩላር መሰረት ከላይ ያነሳሁትን ጥያቄ ሊመልሰዉ ችሎአል::
የሰርኩላሩ ፍሬ ነገር ባጭሩ ይህን ይመስላል “አንድ የስራ ቪዛ በመያዝ ጣሊያን አገር የገባ የዉጭ አገር ዜጋ የስራ ኮንትራት ከመፈራረሙ በፊት አሰሪዉ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ሃሳቡን ቀይሮ አልቀጥርህም ካለና ሃሳቡን ከቀየረ የዉጭ ሐገር ዜጋዉ ግለሰብ የስራ ፈቃድ ወረቀት የማግኘት መብት አለዉ“ ይላል::
ተመሳሳይ ችግር የገጠማችሁ ካላችሁ በዚህ እድል በመጠቀም ችግራችሁን እንደምታቃልሉ ተስፋ አደርጋለሁ::


lunedì

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆን ከአጭበርባሪዎች ተጠንቀቅ


“EPISODIO DI SCIACALLAGGIO”

ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
ጉዳዩ በቂ የመኖሪይ ፈቃድ ወረቀት ሳይኖራቸዉ በጣሊያን ምድር ላይ ከዛሬ ነገ ኑሮ ያልፍልኛል ብለዉ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን የዉጭ ሀገር ዜጎች በተለይም የአማርኛ ቛንቛን አንብበዉ መረዳት የሚችሉትን ሁሉ የሚመለክት ነዉ::
በጣሊያን ሀገር እንደማንኛቸዉም ሌሎች ሀገሮች ሁሉ አንዳንድ አታላዮችና አጭበርባሪ ግለሰቦች ህገወጥ በሆነ መንገድ ገንዘብ ማግኘትን ብቻ ሙያዬ ብለው ተያይዘዉታል:: “ዬትም ፍጪዉ ዱቄቱን አምጪዉ” እንደሚሉት የአያቶቻችን ተረት ይሆንና ልባቸዉ ድንጋይ ከመሆኑ የተነሳ የሌላዉን ሰዉ ችግር ከምንም አይቆጥሩትም፣ ርህራሄ የሚባል በዉስጣቸዉ አልተፈጠረም፣ ማንንም ለይተዉ አያዩም::
ይህችንም ማስጠንቀቂያ ለመጫር ያስገደደኝ ነገር ቢኖር ሰሞኑን እዚሁ በጣሊያን ሀገር በፖርደኖኔ ከተማ (Pordenone) የመኖሪይ ፈቃድ ወረቀት በሌላቸዉ የዉጭ ሀገር ዜጎች ላይ የተከሰተዉ ይህ ነዉ የማይባል የበደል በደል ነዉ:: ፖርደኖኔ (Pordenone) ከተማ ላይ ሰሞኑን የመኖሪይ ፈቃድ ወረቀት ያለገደብ በፖርደኖኔ ፖስታ ቤት በኩል እየተሰጠ ነዉ ብሎ በማስወራት ያለአግባብ ገንዘብ በመቀበልና በማታለል አንዳንድ በጣሊያን ሀገር የሚገኙትን የመኖሪይ ፈቃድ ወረቀት የሌላቸዉን የዉጭ ሀገር ዜጎች ከፍተኛ ችግር ላይ ጥለዋቸዋል፣ የጣሊያን ፖሊስም አገሪቱን ለቀዉ እንዲወጡ አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ ተገዷል:: መጠንቀቅ የሚገባዉ ነገር ቢኖር ባሁኑ ወቅት የጣሊያን መንግስት ምንም አይነት የመኖሪይ ፈቃድ ወረቀት ሊያስገኝ የሚችል ህግ አልደነገገምና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል::
ይህንን መልእክት ሰምቶ ላልሰማ ማሰማት መልካም ስነምግባር መሆኑን መዘንጋት የለብንምና ተግባራዊ ለማድረግ እንሞክር እላለሁ::
መልካም ወቅት ለአንባቢያን
zeleke_eresso@yahoo.it


የተጓዥ የውጪ ዜጋዎች መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ


12 08 07
.
ለእረፍት ወደ ትውልድ ሀገር ደርሶ ለመመለስ የሚያስችለው መመሪያ ነጥቦች ላይ እርማትና ማሻሻያ ተደረገበት።
.
ይህ ከሚመለከታቸው የውጪ ዜጋዎች መሐከል ለመጀመሪያ ጊዜ ሶጆርኖ ለማውጣት ፎርም ሞልተው ማመልከቻ ያስገቡትንም ይጨምራል። አዎ እነሱም ሳይቀሩ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለእረፍት ሄደው መመለስ ይችላሉ። ይህ የታረመው የመመሪያ ነጥብ የሚጠቅሰው አንቀጽ እንዲህ ይላል…..
« አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ሶጆርኖ ለማውጣት ለመጀመሪያ ጊዜ ማመልከቻ ያስገባ ከሆነና ለዚህም ደግሞ የፖስታቤት ደረሰኝ (cedolino delle Poste) የተሰጠው ከሆነ ለእረፍት ወደ ትውልድ ሀገሩ ሄዶ መመለስ ይችላል።»

ማስገንዘቢያ
ይህ ለመጀመሪያ ተጓዦች ለሚሆኑት የውጪ ዜጋዎችን የሚመለከት የመመሪያ ማሻሻያ ድንጋጌ ከሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ውስጥ በ 6 08 2007 የታረመ ነው። ጽህፈትቤቱም ይህንን መመሪያ ለውጪ ሀገር ዜጋዎች ጉዳይ አስፈጻሚ (immigrazione) ቢሮዎች በደብዳቤ እንዲተላለፍላቸው እንዲሁም በመገናኛዎች እንዲወጡ ያደርጋሉ። ይህም እስከሚደረግ ጊዜ መጠባበቅ ይኖርበታል። በአስቸኳይ እንድሚያስተላልፉትና በቅርቡም በስራ ላይ እንዲያውሉት የሁላንም ምኞት ነው።
እስከዛሬ ድረስም በጣሊያን ለመኖርና ለመስራት ፍቃድ (ሶጆርኖ) ያልነበራቸው ፍቃዱን ለማግኘት ያገቡት ማመልከቻ የመጀመሪያቸው ስልሆነ በተሰጣቸው ደረሰኝ ወረቀት የትውልድ ሀገራቸው ደርሰው መመለስ የማይቻል ነበረ። ይኸውም በመጀመሪያው የደረሰኝ ወረቀት ብቻ ሄዶ ለመመለስ ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት በመኖሩ ማንም የሚሞክር እንኳን እንዳልነበረ ይታወቃል። አሁን ግን የመጀመሪያውን የመኖሪያው ፍቃድ ለማግኝት በመጠባበቅ ላይ ያሉትም በcedolino ብቻ ሄደው መመለስ ይችላሉ። ሶጆርኖ በእጃቸው እስከሚሰጣቸው ድረስ ለሚጠብቁት ሀገራቸው ለመሄድ ጥሩ አጋጣሚ ይሆንላቸዋል ማለት ነው።
.
እነዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶጆርኖ አውጪዎች ያላቸው መብት በኪሳቸው ሶጆርኖውን ከያዙት ወይም እስከሚታደስላቸው ድረስ በመጠባበቅ ላይ ካሉት ጋር እኩል ነው ማለት አይቻልም። በመጀመሪያው ሶጆርኖ አውጪ ላይ አንዳንድ መብቶች ላይ ወሰን በማድረግ የተለያዩ ፈቃዶችን ይነፍጋቸዋል። ነገርግን መብቱ እኩል ባይሆላቸውም የዚህ መመሪያ ማሻሻያ የሚያስከፋ አይደለም። መብታቸውን እኩል እንዳይሆን የሚያደርጉት ልዩነቶች ከዚህ በታች ሰፍረዋል።

የመጀመሪያ ሶጆርኖ አውጪ ከሆነ
1ኛ* ከጣሊያን በወጣበት በር ተመልሶ መግባት ይኖርበታል።
2ኛ* ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገር መጓዝ አይቻልም። በፊትም በነበረው ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌ መሠረት የarea schengen አካባቢ መዟዟር አይቻልም።
እነዚህ ሰነዶች በመውጪያም ሆነ በመግቢያ ጊዜ የድንበር ፖሊሶች ማህተም የሚያደረጉባቸው በመሆናቸው በጉዞ ላይ ምንግዜም በእጅ የሚያዙ ናቸው። ከጣሊያን በሚወጡበትም ሆነ በሚገቡበት ጊዜ ዶኩሜንታቸው ላይ (የፖስታቤት ደረሰኙ፣ ፓስፖርቱ፣ ቪዛው እንዲሁም ሶጆርኖ አሳዳሽ ከሆነ ጊዜው የወደቀበትን የሶጆርኖ ኮፒውን (ግልባጭ) ወዘተ… ወዘተ… ማሳየት ይገባቸዋል። በሁሉም መዝገቦች ላይ የድንበር ፖሊሶች ማህተም ወይም ቁጥጥር ስለሚያደርጉበት ነው። በአጠቃላይ ይህ የፖስታ ቤት ደረሰኝ ወረቀት እንደመጓጓዣ ሰነድ ቢያገለግልም ጉዞው (መነሻውና መድረሻው) የተወሰነ ነው።
3ኛ* (ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ...)
የእኛ አስተያየት
የመመሪያ ማሻሻያዎች በሚደረጉበት ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሥራ ላይ እንዲውል በየቦታው ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ስራውን የሚያስፈጽሙት የኢሚግሬሽን ጽህፈት ቤቶችና ቢሮዎች ሳያዘገዩ ጊዜው በስራ ላይ እንዲያውሉት ማድረግና በተለይም ለሰሞኑ የእረፍት ተጓዦች እንዳይተጓጎሉ ጥረት ቢደረግ አይከፋም። በተለይም ሀገራችንን የሚመለከተው የሚሊኒየም በዓል አከባበር ላይ ብዙ ተጓዦች የሆኑ ወገኖቻችን ስለአሉበትና የኦች የመመለሻ ቀን ገደብ አስከ 30 10 07 በመሆኑ.......

.
በፖስታ ቤት ደረሰኝ ወረቀት ወደ ውጪ የሚሄዱና የሄዱ በሙሉ እስከ … 30 10 2007 ድረስ መመለስ ይኖርባቸዋል
.
ሶጆርኖ ለማሳደስ የፖስታ ቤት ደረሰኝ ያላቸው ለእረፍት ከጣሊያን ለሚወጡና ለወጡ በሙሉ የመመለሻቸው ቀን ላይ የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ቀን ተደረገበት። ይኸውም የገደብ ቀን የሚመጣው October 30 2007 እንደሆነ በሀገር ውስጥ የአስተዳደር ሚኒስትር በወጣው የመመሪያ ማሻሻያዎች ላይ ባለፈው ሳምንት ተደነገገ።

የእኛ አስተያየት
ይህ እየተጓተተ ያለው የሶጆርኖ እድሳት ለሚያስከትለው የውጪ ዜጋዎች ችግር ለማቀለል በሂደቱ ላይ በየጊዜው የመመሪያ ለውጦች በማድረግ ማሻሻያ እያደረጉ ቢሆንም የሚወጡትን መመሪያዎች በጊዜው ለማስፈጸም ቢሮክራሲው በሚያስከትለው ችግር ምክንያት ሌሎች ችግሮች እየተፈጠሩ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ለማሳደስ ማመልከቻ በፖስታቤት አቅርበው እስከሚሰጣቸው ድረስ የሚጠባበቁ የውጪ ሀገር ዜጎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በመሆናቸውና ችግሮችን ለማቃለል እየተጓተተ ያለው የሶጆርኖ እድሳት ቢሮክራሲ ወደ የሀገራቸው ለእረፍት ለሚሄዱት ተጓዦች ችግር ከብዙ በጥቂቱ እንዲቃለልላቸው ቢያደርግም በዚሁ ቢሮክራሲ የተነሳ ብዙዎች የዉጭ ሀገር ዜጎች ሰራተኞች ከነበራቸዉ የስራ መስክ ሊባረሩ ተዳርገዋል። ሌላ ስራ የሚቀጥር ድርጅት ፈልገዉም ቢያገኙም እንኳን የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀታቸው በመዉደቁ ከመቀጠር እየተጓጎሉ ይገኛሉ። እናም መዘዙና ውጣ ውረዱ እየበዛ መጥቶ በብዙዎቹ ዉጭ ዜጋዎች ላይ ስቃይ ጨምሯል። ለዚህ ደግሞ መፍትሄ ይሆናል በማለት በአለፈው ሳምንት ላይ በዚሁ አምዳችን ላይ በዶክተር ዘለቀ ጥቆማዎች ተደርገው እንደነበር ይታወሳል። ይኸንንም በድጋሜ ለማስታወስ "ይህ ችግር የገጠማቸው የውጪ ዜጋዎች በሙሉ የፖስታ ቤት ደረሰኝ ወረቀታቸውን ይዘው በመሄድ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የስራ አጦች ሊስት ላይ መመዝገብ መቻል ይሆናል። በቁጥር 19/2007 የጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ድንጋጌ ላይ የወጣ በመሆኑ በሚኖሩበት ሀገር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ቢሮ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ" የሚል ነበር። ...


በፖስታ ቤት የደረሰኝ ወረቀት ነፍስህን አድን



የጣሊያን ቢሮክራሲና ማለቅያ የሌለዉ የዉጭ ሀገር ዜጋዉ ስቃይ
20 07 07
ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
ሰሞኑን ከተለያዩ ሰዎች “የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቴን ለማሳደስ ፖስታ ቤት ካስገባሁ ሁለት፣ ስድስት፣ ዘጠኝ፣ አስራ ሁለት ወራት ወዘተ ሞላኝ ዳሩ ግን እንዃንስ ወረቀቱ ታድሶ ሊላክልኝ ቀርቶ ፎቶግራፍ እንዳቀርብ እንኳን የጠየቀኝ ሰዉ የለም” በማለት ብሶታቸዉን ሲገልጹ እሰማለሁ:: ከዚሁ የቢሮክራሲ ዉጣ ዉረድ የተነሳ በብዙ የሚቆጠሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች ሰራተኞች ቀደም ሲል ከነበራቸዉ የስራ መስክ ሊባረሩ ተዳርገዋል፣ ፈልግዉም ሌላ ስራ ቢያገኙ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ በመዉደቁ የሚቀጥራቸዉ ድርጅት አይኖርም:: ይህ ብቻ ሳይሆን መዘዙ እየበዛ ይመጣና የዉጭ ሀገር ዜጋዉ ስቃይ ይጨምራል፣ መፍትሄዉ የፖስታ ቤት ደረሰኝን በማሳየት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የስራ አጦች ሊስት ላይ መመዝገብ መቻል ይሆናል:: የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱን ለማሳደስ ፖስታ ቤት አስገብቶ የፖስታ ቤት ደረሰኝ ተሰጥቶት በመጠባበቅ ላይ ያለ ግለሰብ ሁሉ በየክፍለ ሀገሩ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ቢሮ በመቅረብ መመዝገብ እንደሚችል በቁጥር 19/2007 የጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ሰሞኑን ደንግጓል::

ሶጆርኖ እስከሚሰጡኝ ጊዜ ቢፈጅም የራሱ ጉዳይ


መምሪያ

28 07 2007

ምንም እንኳን ይህ መምሪያ ለዚህ የውጪ ዜጎች ለእረፍት ጉዞዋቸው እንዲጠቀሙበት ዘግየት ብሎ የወጣ ቢሆንም ሰሞኑን በሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ጁሊያኖ አማቶ የተፈረመበት መምሪያ በመሆኑና ለሁላችንም መልካም ዜና ስለሆነ መልዕክቱን እንዲያነቡት ስናደርግ ከደስታ ጋር ነው።
"ማንኛውም የውጪ ዜጋ የመኖሪያ ፈቃዱን ለማሳደስ ማመልከቻ ያስገባ ከሆነና ለዚህም ደግሞ የፖስታቤት ደረሰኝ የተሰጠው ከሆነ መብቱ በሙሉ ሙሉ ሶጆርኖ በኪሱ ከያዘው እኩልና የማያንስ ነው" የሚል ነው። ስለዚህም ሥራ መቀየር፣ አዲስ የቤት ኪራይም ሆነ የሥራ ኮንትራት መውሰድ፣ የመኪና መንጂያ ፈቃድ ማውጣት፣ የትውልድ ሀገሩ ደርሶ መመለስ፣ ወዘተ...ወዘተ...ወዘተ...ወዘተ...
በአጠቃላይ የፖሊስ ጽህፈትቤቱ (ኩዌስቱራ) ሶጆርኖ እስከሚታደስላቸው ድረስ በመጠበቅ ላይ ያሉትን የሚነፍጋቸውን መብቶች አሁን ነጻ ያደርጋቸዋል። ሶጆርኖ በኪሱ ካለው ጋር እኩል መብት እንዲኖረው ያደርጋል ማለት ነው።
መምሪያውን ከዚህ ያውርዱ

ማስገንዘቢያዎች
* የትውልድ ሀገሩ ደርሶ መመለስ ለሚፈልግ ለፋሲካ፣ ለገና፣ እንዲሁም ለበጋው እርፍት ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ትውልድ ሀገር ደርሶ ለመመለስ ይችላል። ነገር ግን ወደ ከጣሊያን በወጣበት በር ተመልሶ መግባት ይኖርበታል። ምክንያቱም ሲወጣ ፓስፖርቱ ላይ ማሕተም የሚያደረግበት የድንበር ፖሊስ ሲገባም ማሕተም ስለሚያደርግበትና መመለሱ የሚመዘገብበ ስለሆነ ነው። ከዚህም በላይ የፖስታቤቱ ደረሰኝ ወይም ጊዜው የወደቀብት ሶጆርኖ ላይም ቁጥጥር ሊኖር ይችላል።
* ሌላው ደግሞ ይህ የፖስታ ቤት ደረሰኘ ወረቀት እንደመጓጓዣ ሰነድ ቢያገለግልም ጉዞው (መነሻውና መድረሻው) የተወሰነ በመሆኑ ከደርሶ መመለሱ ሌላ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገር መጓዝ አይቻልም። በፊትም በነበረው ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌ መሠረት የ (area schengen) አካባቢ መዟዟር አይቻልም።

ምንም እንኳን ይህ የተፈረመበት ዋና መመሪያ በሥራ ላይ እንዲውል በየቦታው የተላለፈ ቢሆንም ከፖሊስ ጽህፈት ቤቱ ሌላ በየቢሮዎች ሙሉ በሙሉ መሪያውን እንዲጠቀሙበትና በአስቸኳይ ለዚህ የእረፍት ጊዜ ተጓዦች እንዳይተጓጎሉና በቶሎ እንዲፈጸምላቸው የሁላችንም ምኞት ነው። ከዚህም በላይ ይህ መምሪያ በዚህ ዓመት ያለውን ጊዜያዊ የውጪ ዜጋዎችን ችግርና ይህንን እየተጓተተ ያለውን የሶጆርኖ እድሳት ቢሮክራሲ ለማቀለል ተብሎ የተደረገ ሊሆን ስለሚችል በሂደቱ ላይ ለውጦች ሊኖሩት ይችላሉ:: ስለዚህም ወደፊት ለተሻለ ሁኔታ ተስፋ እናደርጋለን።

አብራሃም ዘ. 28 07 2007



domenica

የውጪ ዜጎች ለእረፍት ወደ የሀገራቸው ሊሄዱ ይችላሉ


A casa col cedolino delle Poste
በአሁኑ ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ለማሳደስ ማመልከቻ በፖስታቤት አቅርበው እስከሚሰጣቸው ድረስ የሚጠባበቁ የውጪ ሀገር ዜጎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው። ይህንን የሶጆርኖ እድሳት ለሚጠብቁት በሙሉ ምንም እንኳን በእጃቸው የመኖሪያው ፈቃድ ገና ታድሶ ባይሰጣቸውም በዚሁ ወቅት ላይ ወደ የሀገራቸው ለአጭር ጊዜ እረፍት ለመሄድ እንደሚችሉ ሰሞኑን ከሀገር አስተዳደርና የህዝብ ጥበቃ ክፍል ለድንበር ጠባቂ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በተላለፈው የቴሌግራም መግለጫ መሠረት ሊታወቅ ተችሏል። (መግለጫውን ከዚህ ያውርዱ) ይኸውም የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ፖስታ ቤት በሄዱበት ጊዜ የተሰጣቸውን የደረሰኝ ወረቀት በመጠቀም (cedolino delle Poste) ለእረፍት ወደ ሀገራቸው ሄደው መመለስ ይችላሉ።
.
ከፖስታቤት በተሰጣቸው የእድሳት መጠባበቂያ የሆነው የደረሰኝ ወረቀት ይዘው ለብዙ ወራት በመጠባበቅ የነበሩና በዚህም ምክንያት በአለፈው የፋሲካ እና የገና በዓላት ላይ ሀገራቸው መሄድ ላልቻሉት አሁን ጥሩ አጋጣሚ ይሆንላቸዋል። ከዚህም በላይ የሶጆርኖ እድሳት የሚጠብቁት የውጪ ሀገር ዜጎች መብታቸው ሶጆርኖ ካላቸው ጋር ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት ነው ማለት ይቻላል። ነገርግን ከመጡበት ሀገር ሌላ ወደ ሌሎች ሀገሮች እንደፈለጉት መውጣትና መግባት የመቻልና ያለመቻላቸው ጉዳይ የሚያነጋግር ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም መግላጫ ላይ የአጭር ጊዜ እስከሆነ ድረስ፣ እንደየሚሄዱበት ሀገር የሚወሰንና እንዳላቸው የፈቃድ አይነት ሊለያይ እንደሚችል ይገልጻል። ለምሳሌ (il viaggio non dovrà prevedere il transito in altri Paesi dell'area Schengen)
.
ከጣሊያን በሚወጡበትም ሆነ በሚገቡበት ጊዜ
1 - ከፖስታቤት የተሰጣቸውን የደረሰኝ ወረቀት
2 - ፓስፖርታቸውን
3 - ጊዜው የወደቀበትን የሶጆርኖ ኮፒውን (ግልባጭ) ማሳየት ይገባቸዋል።
4 - (ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ...)
ከላይ የተጠቀሱት ሰነዶች በመውጪያዎም ሆነ በመግቢያዎ ጊዜ በድንበር ፖሊሶች ማህተም የሚደረጉባቸው በመሆናቸው በጉዞ ላይ ምንግዜም በእጅ የሚያዙ ናቸው።
.
ከልጆቻቸው ጋር ለሚጓዙ ወላጆች ጊዜያዊ ሶጆርኖ ይሰጣል
ሌላው ደግሞ በሀገር አስተዳደር የተፈረመበት ሆኖ ለፖሊስ ጽህፈት ቤት (ኩዌስቱራ) በተላለፈ ደብዳቤ ላይ (ደብዳቤውን ከዚህ ያውርዱ) እድሜአቸው 14 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች የራሳቸው ሶጆርኖ ሊኖራቸው የማይችሉ በመሆናቸው በወላጆቻቸው ሶጆርኖ ላይ የተመዘገቡ እስከሆነ ድረስ የሶጆርኖውን እድሳት ተጠባባቂ ለሆኑ ወላጆች ለየት ያለና ጊዜያዊ የሆነው የሶጆርኖ ወረቀት ከፖሊስ ጽህፈት ቤት ሊሰጣቸው እንደሚችልና በዚሁ ከልጆቻቸው ጋር አንድ ላይ ለእረፍት ወደሀገራቸው መሄድ እንድሚችሉ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት ወላጆች ጊዜው የወደቀበት ሶጆርኖዋቸው ላይ ልጆቻቸውን ያላስመዘገቡ ከሆነና ነገርግን አሁን በሚያሳድሱበት ጊዜ ያስመዘገቡ ከሆነ ከፖስታ ቤቱ ለመጠባበቂያ በተሰጠው የደረሰኝ ወረቀት ላይ የልጆቻቸው ስም ሊኖር ስለማይችል የተሰጣቸውን የፖስታ ቤት ደረሰኝ ማስረጃና ከፓስፖርት ጋር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ይዘው በመቅረብ ፎርም ሞልተው የልጆቻቸው ስም ያለበት ጊዜያዊ ሶጆርኖ ሊያገኙበት ይችላሉ። ይህም ጊዜያዊ ሶጆርኖ የሚያገለግለው ለዚሁ የቤተሰብ (የደርሶ-መልስ) ጉዞ ብቻ ይሆናል።
28 06 2007 Abraham Z.


ህገ ወጥ ስደተኞችን መቆጣጠሪያ መሣሪያ


የዕንቅስቃሴ መቆጣጣሪያ መሣሪያ ለስደተኞች መከላከያ መፍትሄ ይሆን ?

30 08 2007
.....ስፔይንና ሞሮኮ መሀከል የሚገኘው የጅብላልተር ወሽመጥ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ ከአፍሪቃ ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ አፍሪቃውያን መሸጋገሪያ ነበር። በዚህ በኩል አውሮፓና አፍሪቃ አስራ አራት ኪሎ ሜትር ብቻ ነው የሚራራቁት። በዚህ የተነሳም በርካታ አፍሪቃውያን በጅብላልተር አድርገው ወደ አውሮፓ ሲጎርፉ ኖረዋል። በአሁኑ ሰዓት ግን በዚህ ወሽመጥ በኩል ለዘመናት ሲካሄድ የቆየውን የአፍሪቃውያን ፍልሰት ለማስቀረት በስፍራው አንድ እጅግ የተራቀቀ የኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ መሳሪያ ተተክሏል። የመሳሪያውን ወጪ የሸፈነው የአውሮፓ ህብረት ነው። ይኽው መሳሪያ በብዙ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘውን የካናሪ ደሴቶችንም በመጠኑም ቢሆን ይቆጣጠራል። በአሁኑ ሰዓት አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ ካናሪ ደሴቶች መሻገርን ነው የሚመርጡት። ታዲያ ይህ የዕንቅስቃሴ መከታተያ መሳሪያ ህገ ወጥ ስደተኞችን መከላከያ ተዐምራዊ መፍትሄ ይሆን?
ወደ ስፋራው የተጓዘው የዶይቼ ቬለው ስቴፈን ላይድል ያቀረበው ዘገባ ሁኔታ በመጠኑ ያስቃኘናል...
.....ናይጀሪያዊትዋ አውጉስቲና ከባለቤትዋ ጋር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ስትነሳ ድርስ ርጉዝ ነበረች። እስከ ሞሮኮ ድረስ በመኪና ነበር የተጓዙት ከዚያም ወደ ስፔይኖቹ የካናሪ ደሴቶች የሄዱት በጀልባ ነበር ። በመንገድ ላይም ጀልባቸው ሲገለበጥ በአንድ ሞሮኮአዊ አሳ አጥማጅ ዕርዳታ ነው ህይወታቸው የተረፈው። ከዚያም እነ አውጉስቲና በስፔይን ፖሊስ እጅ ወደቁ። ባልዋ ወደ ሀገሩ ሲባረር እርስዋ ወደ ደቡብ ስፔይን ተወሰደች። እንደ አውጉስቲና ያሉ እርጉዝ ስደተኞችን ወደ ደቡባዊ ስፓኝ እንዲገቡ ይረዳሉ። ኢዚዶሮ እንደሚሉት ፖሊስ እርጉዝ ሴቶችን ምን መድረግ እንዳለባቸው ስለማያውቁ ወደኔ ያመጡዋቸዋል እስከሁን ቁጥራቸው ሀያ ደርሷል ይላሉ። አፍሪቃውያንን ወደ ስፔይን የሚያጓጓዙት ጀልባዎች በስፓኝ ቋንቋ ፓቴራ ነው የሚባሉት። አውጉስቲና እንደምትለው እነዚህ ጀልባዎች ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ናቸው። «ፓቴራ የተባሉት ጀልባዎች ጥሩ አይደሉም። በጀልባዋ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይሞታሉ። ባለቤቴ በዚህ ጀልባ እንዲመጣ አልፈልግም። » አውጉስቲና ባልዋ እንዲመጣላት ትፈልጋለች። ነገር ግን እርስዋ በተሳካላት መንገድ ባልዋ ከአሁን በኃላ ስፔይን መግባት መቻሉ አጠራጣሪ ነው። ...

.....በጅብላልተር ወሽመጥ በኩል ወደ ስፔይን የሚገቡ ህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር አሁን ቀንሷል። ምክንያቱን ኢዚዶሮ እንዲህ ያስረዳሉ። «ከቀን ወደ ቀን ሁኔታው በድንገት እየተቀየረ ነው። በወሽመጡ አድርጎ የሚመጣ የለም። የዚህ ምክንያቱም የፀጥታ ኃይሎች የተከሉት አዲሱ ቴክኖሎጂ ውጤት ነው። በዚህ ብቻ አይደለም በካናሪ ደሴቶች በኩል የሚመጡትም ጥቂት ናቸው ።»
ካለፈው ዓመት ታህሳስ ወር አንስቶ እስከ ሰኔ ባለው የስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አስራ ስምንት ሺህ የሚጠጉ ህገ ወጥ ስደተኞች በጀልባዎች ስፓኝ ገብተዋል። ሁሉም ማለት ይቻላል በካናሪ ደሴቶች በኩል አድርገው ነው ወደ ዚህች አገር የተሻገሩት። ከዘንድሮ ታህሳስ አንስቶ እስካሁን ግን ወደ ስፔይን የሚመጣው ስደተኛ ቁጥር ቀንሷል። ከስምንት ሺህ የሚያንስ ስደተኛ ነው በዚህ ጊዜ ውስጥ ስፔይን የገባው። ቀደም ባሉት ዓመታት ግን ከልክ በላይ የሆነ የአፍሪቃ ስደተኛው ነበር በወሽመጡ አድርጎ ወደ አውሮፓ የሚጎርፈው። በሁለት ሺህ ብቻ አስራ ሶስት ሺህ ስደተኛ ነው በዚህ በኩል ያቋረጠው ። አሁን ማንም በጅብላልተር ወሽመጥ በኩል አይመጣም ማለት ይቻላል። የተተከለው የኤሌክትሮኒክስ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ለህገ ወጥ ስደተኞች መከላከያ ጥሩ መድኃኒት ተደርጎ ነው የተወሰደው። የስፓኝ መንግስት በአውሮፓ ህበረት ዕርዳታ እ.አ..አ ከሁለት ሺህ ሁለት አንስቶ ነው መሳሪያውን ለመስራት ጥረት ማድረግ የጀመረው። ከሶስት መቶ ሚሊዮን ዩሮ በላይ በፈጀው በዚህ የኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ መሳሪያ አማካይነት በአንድ ሺህ አምስት መቶ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የሚካሄድ ዕንቅስቃሴን መከታተል ይችላል። በዚህ መሳሪያ ላይ ካሜራ የተገጠመ ሲሆን ባለ ቀለም ምስልም ያሳያል።

.....ሳልቫዶር ጎሜዝ የመቆጣጠሪያው መሳሪያ የሚገኝበት መስሪያ ቤት ባልደረባ ናቸው። « የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያው ማናቸውንም በውሀ ላይ የሚዋኙ ነገሮችን አቅርቦ ያሳያል። ከአንድ ሜትር ያነሰ ርዝመት ያላቸውንም ጭምር። ዛሬ ጠዋት ከወሽመጡ መሀከል ሁለት ወጣቶችን አግኝተን አውጥተናል። ወጣቶቹ የተሳፈሩት ከየትኛውም ቦታ ሊገዛ በሚችል በትንሽ ጀልባ ነበር። »
በኤሌክቶኒኩ መሳሪያ ከሚካሄደው ክትትል በተጨማሪ በፈጣን ጀልባዎችና በመርከቦች የፀጥታ ኃይሎችም በንቃት ጥበቃ ያካሂዳሉ። የቁጥጥር ዘዴው ህገ ወጥ ስደተኞችን ብቻ ሳይሆን የአደንዛዥ ዕጽ ንግድንም ለመቆጣጠር እየረዳ ነው። በምህፃሩ ሲቨ የሚባለው አዲሱ መሳሪያ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ስደተኞችን በውሀ ከመበላት በማዳን ረገድም ትልቅ ሚና ይጫወታል። ሆኖም አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አሁን ስራ ላይ የዋለው የመቆጣጠሪያ ስርዓት ህይወት ለማዳን አንዳችም የሚፈይደው ነገር የለም ነው የሚሉት። ወይዘሮ ባርባራ «ሲቨ እጅግ ብዙ ገንዘብነው የፈጀው ። ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ። አሁን ስደተኞቹ ሌላ መንገድ እየተጠቀሙ ነው። ሌላ ረዥም መንገድ ። የአሁኑ ጉዞአቸው ደግሞ አደገኛ ነው የሚሆነው። ሲቨ የጥፋት መንገድ ነው። ይህ ብቃት ያለው ፖሊሲ አይደለም። ይህ ገዳይ ፖለቲካ ነው ። » ሲቨ አሁንም ማወዛገቡን እንደቀጠለ ነው። ለአንዳንድ የዕርዳታ ሰራተኖች ደግሞ የመቆጣጠሪያው መሳሪያ መተከል በበጎ ተግባር ነው የተወሰደው። ማኑዌል ፌሊክስ የቀይ መስቀል ድርጅት ባልደረባ ናቸው ። ሲቨ ህይወት እያዳነ ነው ይላሉ ።
«ሲቨ ህይወት ያድናል ማለት ይቻላል። ምክንያቱም መሳሪያው ጀልባዎችን ከርቀት በማየት ችግር ላይ ከሆኑም ሊደረስላቸው ይችላል። ከዚህ ቀደም ግን ከመሞት በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። እንደ አለመታደል ሆኖ ወሽመጧ የሰዎች መቃብር ናት። »

30 08 2007 dw-world.de


venerdì

ነፃ አስተያየት
በጣሊያን millennium festa የማድረግ ጉዳይ ላይ


ከ-email ወይም ከ-comments ላይ የተወሰዱ
.
በጣሊያን የምንገኝ አበሾች ሚሊኔየማችንን አንድ ላይ ሆነን ብናክብርስ?
በጀርመን የሚገኙት ኢትዮጲያዊያውያን ተሰባስበው ሚሊኔዬሙን በተለየ መልክ ለማክበር ዝግጅት የመጀምራቸውን ዜና ከጀርመን ራዲዮ ከሰማሁ በኋላ አንድ ነገር ትውስ አለኝና ለናንተ ማካፈል ፈለኩኝ:: ይኼውም በጣሊያን የምንኖር ኢትዮጲያዊያውያን ተሰባስበን እጅግ በደመቀና በኢትዮጲያዊነት የሚያስተሳስሩንን ሁኔታዎች በመፍጠር ለምን አናከብርም የሚል ሀሳብ ነው:: አንዳንድ አርቲስቶችን እንዲገኙልን በማድረግና ተባብረን በማቀናባበር በዓላችን የደመቀ ሊሆንም ይችላል።
ባቀረብኩት ሀሳብ ላይ ሁላችሁም ያላችሁን አስተያየት እየሰነዘራችሁ ሀሳቤን እንደምታዳብሩት ተስፋ አደርጋለሁ። ለዚህ ገፅ አዘጋጆች አድናቆቴን አልደብቃችሁም። በርቱበት ። እናንተስ ምን አስተያየት አላችሁ?
እንኳን ለአዲሱ ምዕተአመት አደረሰን
ደ.አ. (ጣሊያን)

****************************************************************
ይድረስ ለአቶ ወይም ወ/ሮ - ወ/ት ... ደ.አ.

ወደ አዲሱ ሚሊኒየም ልንገባ በዋዜማው ላይ እንገኛለን:: ይህ መጪው የሺህ አመት መቀበያ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በዓል ነው። ታዲያ ከልጆቹዋ ጋራ ሆኖ እዚያው በሀገራችን በኢትዮጵያ ምድር ላይ "የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ" ብሎ መቀበል የምንችለው ደስም የሚለን እዛው ከአየሩ ከኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ነው:: ቢሆንም ደግሞ ወደ ሀገርቤት ለመሄድ የማይመቸንና እዚሁ ለምንቀረው በበጎ ፈቃደኝነት በመተባበር አመቺና ማዕከላዊ የሆነ ቦታ ላይ ተገናኝተን መጠነኛ ዝግጅት አድርጎ ማክበር እንችላለን ባይ ነን።
ሀይሌ ገ/እግዚአብሔር (ሮማ)

****************************************************************

Please help me

I want to write in amarigna on comments, I tried to copy from the guestbook and pasting to the comments, but with out any results. Please have you some advice how can I make it.

GF thank you

****************************************************************

selam

i have the same problem as g.f. i think the loading process is a bit complicated.

yammi

ውድ የኢትዮጵያ በኢጣሊያ ኣዘጋጆች የኣምዳችሁ ተከታታይ ነኝ። የሚያስመሰግን ስራ ነው እየሰራችሁ ያላችሁት። ሰሞኑን ከኣንባቢነት ወደ ተሳታፊነት ለመሽጋገር ፈልጌ የግእዝ ፎንቱ በትክክል ሊሰራልኝ ኣልቻለም።በጸሃፊነት ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ኣድሮብኛል። ምን ማድረግ አንዳለብኝ ብትጠቁሙኝ ብዬ ነው ብቅ ማለቴ። መልሳችሁን እጠብቃለሁ

ያሚ

****************************************************************

ጤና ይስጥልኝ
ይህንን የእርስዎን ኢሜል መልስ የማደርገው ከገጹ ጥቂት አዘጋጆች መሀከል አንዱ ነኝ። አዘጋጆችም የዚህ ገጽ ሌላ አዲስ ተከታታይ በማግኘታቸው ተደስተዋል። ከዚያም አልፎ ወደ ተሳታፊነት የሚሽጋገግሩ በመሆንዎ ደግሞ ደስታ ብቻ ሳይሆን ሞራላቸውን እንዲያነሳሳው አድርጎታልና ለዚሁ እኔንም ጨምሬ በቅድሚያ ምስጋናቸንን እናቀርባለን።

የብዙዎች ችግር ወደሆነው ማለትም በcomments ላይ በግዕዝ ፊደል የመጠቀሙን ጉዳይ ላይ እንመለስና - ለመረዳት ያህል በገጹ መጀመሪያ ክፍል ላይ download and install እንዲያደርጉ ያስቀመጥነውን Geèz Software ፕሮግራም አንዲያወርዱትና በኮምፒተርዎ ውስጥ እንዲያስገቡት ይሁን። ወይም ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን link ይጫኑና download and install ያድርጉ።
ftp://ftp.geez.org/pub/fonts/TrueType/amh-uni.exe

በcomments ላይ በግዕዝ ፊደል ለመጠቀም ከፈልጉ
የገጹን comments ከከፍቱ በኋላ ፕሮግራሙን attivare ማድረግ አለብዎት። ይኸውም ከታች በቀኝ ማዕዘን በኩል የሚገኘውን "K" ምልክት ይጫኑና "Amharic EZ+" ይምረጡ። ከዚህ በኋላ በፊደላችን comments ላይ መፃፍ ይችላሉ ማለት ነው።

አሁን እኔ ራሴ ይህንን ኢሜል የጻፍኩልዎ ይህንኑ ፕሮግራም በyahoo ኢሜል በመጠቀም ነው። ይህ የግዕዝ ሶፍትዌር ፕሮግራም ከሌልዎት እንዲሁም እንደ yahoo አይነት ኢሜል ካልተጠቀሙ ደግሞ ምናልባት በግዕዝ ላያዩት ይችላሉ። ለማንኛውም በcomments ላይ ሙከራዎት ካልተሳካልዎት ሌላ ኢሜል ልከውልን በሌላ መንገድ እናየዋለን። በስልክ፣ messenger እና በመሳሰሉት በቀጥታ በመገናኘት ማቃለል እንችላለን።
እስከዚያው ድረስ በሰላም ይቆዩ

****************************************************************

ሰላም

ለፈጣን መልሳችሁ በጣም ኣመሰግናለሁ። አኔን ያጋጠመኝ ችግር install ማድረጉ ላይ ኣይደለም። በምጽፍበት ጊዜ ኣንዳንድ ቃላቶችን ለማምጣት caps lock ከተጫንኩና ከተጠቀምኩ በህዋላ ውደ small leters ለመመለስ ኣልቻልኩም። የ caps lock light ብችጫነውም ኣይጠፋም ።ሌላ ድህረ ገጽ ላይ ስጽፍ ይህ ችግር ኣያጋጥመኝም ችግሩ ከኔ ወይም ከ keyboard ይሁን ማወቅ ኣልቻልኩም።ይህ ችግር ለመጀመሪያ ጊዜም keyman install ካደረኩ በሃላ ነው ያጋጠመኝ። የምታውቁት ነገር ካለ ብትተባበሩኝ ምስጋናዬ ወደር የለውም።ከኣቶ ኣብርሃም የደረሰኝን ኢሜል ማንበብ ኣልቻልኩም ።ፎንቱን ኣልተቀበለውም

ስላስቸገርኳችሁ ይቅርታ

ያሚ

****************************************************************

በእርግጥ ባአሉን ለማክበር ወደ ኢትዮጲያ የሚጓዙት ብዙዎች ይሆናሉ የሚባል ወሬ አለ። እዚህ የምንቀረው በቁጥር አንሰን የምንገኝ እንሆናለን። ታዲያም ቁጥራችንን ለማብዛት ከተለያዩ የኢጣሊያ ሀገሮች ለሚመጡት ማዕከላዊና አመቺ የሆነ ቦታው የት ሊሆን ይችላል?

ደ.አ. (ጣሊያን)

****************************************************************

ሰላም ለሁላችሁም

ለትብብራችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነው:: የሚሊኒየሙን በአል በተመለከት ሰፋ ያለ ቦታና አዝናኝ ዝግጅቶች ይዘጋጁ እንጂ ማንም ከየትም ሊመጣ የሚችል ይመስለኛል:: የበአሉን ትልቅነትና ልዩ መሆን በማሰብ.........በተጨማሪም ይህንን ድህረገጽ ለማስተዋወቅ ሰፋ ያለ ጥረት ብናደርግ በአጭር ጊዜ ብዙ ተከታታይና ተሳታፊዎችን ለማግኘት እንችላለን ባይ ነኝ::

ለምሳሌ ያህል ሃበሻ በብዛት ባለባቸው ከተሞች በራሪ ወረቀቶችን በማሰራጨት....አንዳችን ለአንዳችን በመንገር የመሳሰሉት:: ይህም የበአሉን ዝግጀት በተመለከት የብዙዎችን ትኩረት የሚያስገኝ ይመስለኛል:: በዚህ ላይ አዘጋጆቹ ምን አስባችሁአል? ለሁሉም በእኔ በኩል ለማውቀው ሰው ሁሉ እየነገርኩ ነው::

መልካም ጊዜ

ያሚ ከፊሬንዜ

****************************************************************

ለ2ሺ ዓም ዘመን መለወጫ እንኳን አደረሳችሁ...
ይህንን ታላቅ በዓል ለማክበር የሚያስፈልገው ባዶ ቃላትና ምኞት ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ ተስፋ ሰጭ የሆኑ ጅምሮች ከአሁኑ ሊታዩ ይገባል... ደግሞ ሁላችንን በአንድ ቦታ የሚያሰባስብ ያማረ ፌስታ እንዲሆን ለማድረግ የምታስቡ ከሆነ ከአሁኑ ዝግጅቱ ተጠናክሮ መካሄድ አለበት... ይህ ካልሆነ ግን ዋጋ የሌለው ወሬ ነው እላለሁ... ጊዜውም በጣም ያጠረ መሰለኝ... ምክንያቱም ዝግጅቱ አሁን መጀመር ሲገባው ምንም ተንቀሳቃሽ ነገር አላየሁም... የሚደረግበት ከተማ - አስተባባሪዎች - ለዝግጅቱ አስፈላጊ የሆኑ - ቦታ - ወዘተ... ወዘተ... ማቀነባበር... እኔ እንደሚመስለኝ ወኔ ያላቸው ሰዎች እዚህ ጣሊያን ሀገር ማግኘት? ....... ለሁላችንም ግልጽ መሰለኝ...
እስቲ ይመቻችሁ

GG



giovedì

ሚሌኒዩምን እንዴትና ለምን ማክበር ያስፈልጋል?


የግል አስተያየት
እንዴትና ለምን ማክበር?
ኢትዮጲያ የራሷ የሆነ ቀን መቁጠሪያ አላት። በዓለም ውስጥ ልዩ ያደርጋታል። ዘመን መቁጠሪያችንን ዘመናትና ነገሥታት ሳይሽሩት ቀደምት አባቶቻችን ያስተላለፉልን ቅርስና የኢትዮጵያዊነት አንዱ መግለጫችን ነው:: ታዲያ ዓመት አልፎ አመት ሲመጣ "እንኳን አደረሳችሁ"..."መጭው ዓመት የስላም የጤና የስራ ዓመት ይሁን"... ብለን ተባብለን አመቱን በደስታ እንቀበላለን እናሳልፋለን።
.
መቼም እንደሚታወቀው የሚቀጥለው እንቁጣጣሽ ካለፉት ሁሉ የተለየ ነው:: ይኸውም ከተለመደው ከአመት ወደ አመት መሸጋገር ወይም ከዘመን ዘመን መሸጋገሪያ ሌላ ለየት የሚያደርገው የምዕተአመቱ መለወጫ (ሚሊኒየም ወይም የ1000 ዓመት ለውጥ) በመሆኑ ነው። ከሺህ ዓመት በኋላ አንድ ጊዜ ብቻ የሚመጣ በመሆኑና ከአለፉት ብዙ ትውልድ መሐከል በእኛ ትውልድ ላይ መጋጣጠሙ ነው። በዚህም ምክንያት ለእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ሎተሪ እንደደረሰው ያህል ነው የሚቆጠረው። ለዚህ ሚሌኒይም የደረሰው የእኛው ትውልድ ብቻ ስለሆነና ለዚህም በሕይወት በመገኘታችን እንኳን ደስ አለን።
.
ይህንን ልዩ የሆነውን የምዕተ አመት ለውጥ በሌላ ጊዜ ለማክበር ሌላ አንድ ሺ አመት ስለሚያስጠብቀን ይሄ እድል ሳያመልጠን ተጠቅመንበት ቁምነገሮች ልንሰራበት የሚገባ ይመስለኛል:: ስለዚህም በፀዳ ሁኔታ በባህል፣ በታሪክ፣ በኃይማኖትም ሆነ የተለያዩ ዘርፎችን ያካተተ እንዲሆን አድርጎ፣ አስተባባሪ አቋቁሞ ተሰባስበን በመተጋገዝ በዓሉን ለማክበር ከአሁኑ በጋራ ብንዘጋጅ ጥሩ ነው::
.
በእርግጥም በጣሊያን የሚገኙትን ኢትዮጲዊያን የሚያሰባስብ አህጉራዊ የሆነ ዝግጅት ለማድረግ በጀት (ገንዘብን) የሚጠይቅ ብቻ አይደለም። ጊዜን፣ መተባበርና ታጥቆ መሥራትን፣ እውቀትንና ጉልበትን፣ ቁሳቁሶችን ወዘተ... የሚጠይቅ ነው። አስተዋጽዖ የሚያደርጉ በጎ ፈቃደኞች ያስፈልጋሉ። ከዚህም በላይ ጠንካራ የኢትዮጲያ ኮሚኒቲዎች ካሉ በያሉበት ህብረተሰቡን በማስተባበርና ለዝግጅቱ ተሳትፎ እንዲኖር በማድረግ የሚጠበቅባቸውን የዜግነት ድርሻና ግዴታ እንዲወጡት መሆን አለበት።
የዚህ አይነት ዝግጅትን ለማስተባበርና ለማቀነባበር ልምድ ያላቸው ኮሚኒቲ ካላደረጉት በስተቀር ለሌሎች አስተባባሪዎች ወይም አዘጋጆች ከወራት
በፊት ይሚጀምሩትና ቀደም ተብሎ የሚታሰብበት ጉዳይ ይመስለናል። ማለትም «የኢትዮጲያ ሚለኒየም ፌስቲቫል በጣሊያን» ተብሎ የተሰየመ ደማቅ በዓል ለማዘጋጀት ከተፈለገ ሁሉንም በሚያሰባስብ አዳራሾች፣ ድንኳን፣ የእንግዶች መስተንግዶ፣ ..... ...... ..... ......
በአጠቃላይ በጊዜ እጥረት ምክንያት አህጉራዊ ፌስቲቫል ለማዘጋጀት ፕሮጄክቶችን በማቀድና በማጽደቅ ቀደም ተብሎ መሠራት የሚገባቸው ነገሮች ነበሩና። ...... (ይቀጥላል...)
.
ቢሆንም መለስተኛ የሆነ ዝግጅቶችን ለማቀነባበር ሕጋዊነት ያላቸው የኮሙኒቲ ማህበራት ከአሁኑ ጀምረው በማስተባበር ሊያደርጉት ይችላሉ። አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ በሥሩ ደግሞ የተለያዩ የሥራ ክፍፍል ያለው ንዑስ ግሩፕ በማቋቋምና መለስተኛ በዓል ለማድረግ። የደመቀ እንዲሆን ለማድረግ ደግሞ የኢትዮጲያን ገፅታ በማስረጃዎች ለማሳየትና በማቅረብ ከዚህም ጋር ሀገራችንን በይበልጥ ማስተዋወቅ የሚረዳን ስለሆነና ልዚሁም ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ ሁሉም ለበዓሉ መከበር የዜግነቱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ይደረግ ....
.
ለምን

- ለዚሁ ለሚያስተናግደን ሀገር ህዝብ የተለያዩ የአገራችንን ቅርሶች፣ ታሪክና ባህል ለማስተዋወቅ የምንችልበት አጋጣሚ ጊዜ ስለሚሆን...
- ኢትዮጲያ ከተቀረው ዓለም ሚሌንየሟን ከሰባት ዓመት በኋላ የምታከብርበት ምክንያት ከጁልየስ ቄሳር ተመሳሳይነት ባለው የቀን መቁጠሪያ የምትጠቀም መሆኑን ለማሳወቅና ያለንበት ዓመተምህረት በ7 ዓመት ወደኋላ እንደምንገኝ፣ 13 ወር እንዳለን፣ ከ80 በላይ ቋንቋዎችና ብዙ ብሔሮችን አቅፋ ... ፣ ከ200 በላይ ፊደልና ልዩ ቁጥሮች (አኃዝ) ...ወዘተ... እንዳለን፣
- በኢንቬስትሜንት እንድትለማ ማስረጃዎችን በማቅረብ አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን።
- የሀገራችንን የቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግ... (የሰው ልጅ መገኛና የሶስት ሺህ ዓመት ታሪክ ያላት መሆኗን ለማስገንዘብ... የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ገና ያልተነካ መሆኑን የሚያሳዩት በሀገሪቱ ያሉትን የአክሱም ሃውልት፣ የአጼ ፋሲለደስ ቤተ መንግስት፣ የላሊበላ አብያተክርስቲያን፣ በጣና ሃይቅ ውስጥ የሚገኙትን ድንቅ አብያተክርስቲያን፣ የባሌው ሼክ ሁሴን ፣ የነጋሽ መስጊድ፣ የሐረር ጀጎል፣ የሶፍ ዑመር ዋሻ፣ የጅማው አባ ጅፋር እንዲሁም በአገሪቱ ብቻ የሚገኙ ድንቅ እንስሳትና የተለያዩ አዕዋፋት ...ወዘተ... እንደሚገኙባት ለማሳወቅ...)
- የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት መሆንዋን ለማስገንዘብ...
- እኛም እራሳችን ብንሆን ስለሀገራችን የማናውቀውን የምንማርበት አጋጣሚ ስለሚሆንልን...
- በተለያዩ የጣሊያን ክፍል የምንገኝ ኢትዮጲያዊያን/ት እርስ በእርሳችን ትውውቅ የምናደርግበትና የሚያስተሳስር አንድ ማህበረሰብ ለመመሥረት ወርቃማ አጋጣሚ ይሆንልናል።

እንዴት

- አነስተኛ ባዛሮችንና ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት...
- የኢትዮጲያ ብሔረስብ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ የስራ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ ፎቶግራፎች፣ ....
- የፌስቲቫል የሙዚቃ ኮንሰርት በማድረግ...
- የተለያዩ የስፖርት ዝግጅቶች እንዲከናወኑ በማድረግ (ምሳሌ - ሀገራዊ ሻምፒዮን የእግር ኳስ ቡድኖችን የሚያሳትፍ ዝግጅቶችን በማቀነባበር። ለዚህ ደግሞ ጊዜው ማጠሩ ብቻ ብቻ ሳይሆን ቀደም ያሉ ዝግጅቶችም ያስፈልጉ ይመስለኛል)
- በጣሊያን ድርጅቶችና በመንግሥት ቅርንጫፎች ድጋፍና እርዳታ እንዲገኝ በማድረግ...
- ደግሞ ከተለያዩ የጣሊያን ክፍሎች ለሚመጡት የግሩፕ መጓጓዣ እንዲኖር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና መስተንግዶ እንዲኖራቸው ማድረግ፣...
- ኢትዮጲያውያን ብቻ ሳይሆኑ ኅብረተሰቡም በሚሌኒየሙ እንዲገኝልን ቅስቀሳ ማድረግ አለብን። በመገናኛዎች ማስታወቂያና ጥሪዎችን በማሰራጨት ፈረንጆቹም ለሚሌኒየሙ እንዲገኙ ለመጋበዝ ኢትዮጲያውያን/ት በሙሉ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ብዙ ይጠበቅባቸዋል።
- በዚህ ረገድ ኮሚኒቲዎች እንዲሰባሰቡና የጋራ ልምዳቸውን መሰረት አድርገው እንዲያስተባብሩ፣
- አህጉራዊ በዓል የሚዘጋጅ ከሆነ ከተለያዩ የጣሊያን ከተማዎች ለሚመጡት የግሩፕ መጓጓዣ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ጥሩ መስተንግዶ እንዲያገኙ፣
- ወጣት ኢትዮጲያውያን/ት በሙሉ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ብዙ ይጠበቅባቸዋል።
.
በዓሉ የዘመናት ታሪካችን የሚዘከርበትን ሁኔታ እንዲኖረው ያስፈልጋል:: ኢትዮጵያችን በዓለም ታሪክ ውስጥ ልዩ ሥፍራ የሚሰጣት የቅኝ ገዥዋን አንበርክካ በራሷ ነፃነቷን ጠብቃ ለዘመናት የኖረች ብቸኛ አፍሪቃዊት አገር መሆኗ ነው:: ስለዚህም ይህ የሚሊኒየም አውደዓመታችን ያለፈውን ታሪካችንን በማስታወስ በተለይም ጣሊያን የቅኝ አገዛዝዋን ሙከራ በመስበር ያሽነፍንበት ዘመን መሆኑን ለማሳደስ። ሌሎቹንም ታሪካችንን የምናድስበት፣ አንድነታችን የምናጠናክርበት፣ ያለፈውን አዝጋሚ ጉዞ መለስ ብለን የምንዳስስበትና መጪውን ጎዳና የምንመለከትበት አጋጣሚ ሊሆን ይገባል።
.
የዛሬ ሰባት ዓመት ፈረንጆች ሚሌኒየማቸውን ሲያከብሩ ሁሉም አንድ ላይ ነበሩ። እኛም ልክ እንደነሱ ወደ ሦስተኛው ሚሊኒየም ስለምንሸጋገር እጅ ለእጅ ተያይዘን ማክበር እንችላለን። ይህ አውዳመት ሀገራችን የሁለትና ሦስት ሺ ዘመን ጉዞ እንዳደረገች ለምናምነው ዜጎቿ ልዩ ትርጉም ይኖረዋል:: በዚሁ በጣሊያን ሀገር ሕግና የዲፕሎማሲ መርህ መሠረት ... (ይቀጥላል...)
አብራሃም ዘውዴ Gugno 2007


mercoledì

በጣሊያን ለሚገኙ የውጪ ሀገር ዜጎች ጠቃሚ ማስረጃዎች


ከሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የተቀነባበሩ ማስረጃዎች (በጣሊያንኛ)
24 06 07
ይህ መመሪያ ለውጪ ዜጎች የሚያገለግሉ ጠቃሚ ኢንፎርሜሽንና ቀላል ማስረጃዎችን በተለያዩ አርዕስቶች ተከፋፍሎ የቀረበ ነው። አዳዲስ እና ብዙ ጠቃሚነት ሊኖራቸው የሚችሉ ይዘቶች አሉት። ከታች ከሚገኙት አገናኞች (link) ላይ የፈለጉትን አርዕስት መርጠው በመክፈት ማንበብ ይችላሉ። ወይም ደግሞ የሚያስፈልጉዎትን አርዕስት መርጠው በመክፈት print ሊያደርጉ ይችላሉ። ይኸውም በተረጋጋ መንገድ አንብቦ ለመረዳት ስለሚረዳ ነው። ሌላው print የማድረጉ ጉዳይ ደግሞ ኮምፒተር ወይም ኢንተርኔት ለማይጠቀሙ ወገኖቻችን በወረቀት በማሰራጨት ማስረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ስለምንችል ነው። የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሰራተኞች ይህንን መመሪያ በሚቀጥሉት ወራት ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎምና በማስተርጎም እዚሁ ጣሊያን ሀግር በሚወጡ የውጪ ዜጎች የጋዜጣ ህትመቶቻቸውና ድረገጾች ላይ እንዲወጣ ያደርጋሉ።
1 - ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ መቀጠር - prima assunzione


በጣሊያን የቀድሞውን የውጪ ዜጋዎች ፍልሰት ሕግ የሚያድስ ረቂቅ ተቀመረ


Da Bossi/Fini ad Amato/Ferraro?
(የረቂቁ ነጥቦች)

የሚገቡት ቁጥር ገደብ?
የሚገቡት ቁጥር ጣራ በየ 3 ዓመት አንድ ጊዜ ይወጣል። ከእነዚህም መሀክል በየዓመቱ የተወሰኑትን ያህል እንዲገቡ ይደረጋል። ምንም እንኳን በ 3 ዓመት አንድ ጊዜ የሚወሰነው መጠን ጣራ ቢኖረውም ይህ ቁጥር ገደብ ውስጥ የማይገቡ ወይም የማይመለከታቸው ይኖራሉ። ለምሳሌ ልዩ የዕጅ ሙያ ወይም ጥበብ ያላቸውን፣የጥናት ተቋማት ባለሙያተኞች የሆኑትን በsponser ወይም ተወክለው የሚላኩትን ልዩ ችሎታዎችና የተማሩ ወይም ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን፣...ወዘተ...
Nullaosta ለሌሎችም?
ጣሊያን ሀገር ሠርተው ለሚኖሩት በሙሉ Nullaosta መብት እንዲኖራቸው ይደረጋል። ይህ ..... ለኮልፍ እነ ለባዳንቲዎች (colf e badanti) የሚሰጥ ነበር።
የጣሊያን ዲቪ???
ጣሊያን ለሥራ ለመግባት ከመጣበት ወይም ከራሱ ሀገር መንግስት የግድ ማመልከቻ ያደረገ እና የተመዘገበበት መዝገብ ያለው ይሆናል። ይኸው መዝገብ ደግሞ እዛው በአመልካቹ ሀገር መንግስት ለሚገኙት የጣሊያን ዲፕሎማቲክ ጽህፈት ቤት የተላለፈላቸው መሆን ይገባዋል።
Sponsor
በኢኮኖሚ በቂ መተዳደሪያውን የሚችል ተወካይ ወይም ጋራንሲ የሚሰጠው ከአለው ወደ ጣሊያን ሊልከው ይችላል። ወካዩ ወይም ዋስ ሊሆኑ ከሚችሉት መሀከል አንዳንዶቹን ለምሳሌ ያህል ልንጠቅስ እንወዳለን። 1 - የመንግስት ድርጅቶች (በተወካዩ ሀገርም ሆነ በጣሊያን ሀገር)2 - የሠራተኞች ማህበር ጽህፈት ቤቶችና ድርጅቶች (sindacati) 3 - ፓትሮናቲ (Patronati)4 - የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች (Associazione...)5 - ግለሰቦች (በየዓመቱ አንድ ሰው ብቻ)6 - ...ወዘተ...
Autosponsorizzazione
ሀብትና ገንዘብ ያለው ወይም ራሱን የሚችልበትን መተዳደሪያ ያለው መሆኑን ካስመሰከረ እሱ ራሱ ለራሱ ወክልናና ዋስ ሆኖ መስራት ይችላል።(ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ)
ቪዛና የመቆያ ፈቃድ
ወደፊት ጣሊያን ለሚመጡት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ፈቃድ ለማውጣትና ላማሳደስ የነበረውን ውጣ ውረድ እንዳይገጥማቸው ብለው በማሰብ በቪዛው አማካይነት ፍቃዱም እንዲሰጣቸው ይደረጋል። ይህ ቪዛ የመግባት ፍቃድ ብቻ ሳይሆን እንደመቆያ ፈቃድም ሆኖ የሚያገለግል መሆኑ ነው። ቪዛው ለረጅም ጊዜ የመቆያና የመኖሪያ ፈቃድ ሆኖ የሚያገለግል ሊሆን ነው። በዚህም ምክንያት እንደ permesso di soggiorno በየጊዜው ለማሳደስ በሰለፍ የሚያንከራት አይኖርም ማለት ነው። በዚህ የመቆያ ፈቃድ አማካይነት ለመጀመሪያ ጊዜ የስራ ኮንትራት ለሚኖረው እንደኮንራቱ የጊዜ እርዝመት ታይቶ የመቆያው ፈቃዱን በማራዘምና ወሰን በማድረግ ነው። ለምሳሌ - ሀ/ የ 6 ወር የሥራ ኮንራት ላላቸው 1 ዓመት የመቆያ ፈቃድለ/ የ 1 ዓመት የሥራ ኮንትራት ላላቸው የ 2 ዓመት የመቆያ ፈቃድሐ/ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ኮንትራት ላላቸው ወይም የግል ድርጅት ለሚያንቀሳቅሱት በየ 3 ዓመት የሚያሳድሱት የመቆያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል።
ማሳሰቢያ- (የሥራ ኮንትራታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ሲያሳድሱ የመቆያ ፈቃድ በእጥፍ ይራዘምለታል)
ያለስራ ለተቀመጠ
ሥራ በመፈለግ ላይ ሆነው የመቆያው ጊዜ የወደቀባቸው ወይም ያለ ሥራ ለተቀመጡ የውጪ ዜጋዎች ደግሞ የመቆያው ፈቃድ እንዲራዘምላቸው የሚያደርጉ ሁኔታዎች አሉ።
ለምሳሌ -
* መተዳደሪያውን የሚችል ከሆነ
* Sponsor ወይም የመቆያውን ጊዜ ለማራዘም የሚያስችለው ዋስትና የሚሰጠው ወካይ ያለው ከሆነ፣
* በሰበዓዊ ተግባሮች የተሰማራ፣
* የወንጀለኛነት record የሌለው፣
* ባህሪው፣ መንፈሱና ፀባዩ ህብረተሰቡን የማያስከፋ ከሆነ፣
* ...ወዘተ...
የመቆያ ፈቃድ ለማውጣትና ለማሳደስ ዋናውን አገልግሎት የሚሰጠው የፖስታ ቤት መሆኑ ቀርቶ ወደ ማዘጋጃ ቤት ቢሮዎች ይሆናል። እንግዴህ መዝገቦቹ ከአንዱ ቢሮ ወደሌላው ሲተላለፉ ያው የተለመደው የጊዜና የሥርዓት ትራፊክ እንደማይገጥም ተስፋ እናደርጋለን። ...........
መብት
ጣሊያን የአውሮፓ ህብረት አባል እንደመሆኗ መጠን ሀብረቱም በStrasburgo ጉባዔ ላይ የወሰነውን በሥራ ላይ ታውላለች። በዚህም ምክንያት "ማንኛውም የውጪ ዜጋ በሚገኝበት ሀገር የማህበራዊ ኑሮ ላይ የመካፈል መብት እንዲሰጠው ይደረጋል። በተለይም ኑሮውን ከአምስት ዓመት በላይ ያደረገ ከሆነና በህጋዊ መንገድ በመስራት የኢኮኖሚ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ስለሚገኝ የሀገሪቱም የፖለቲካ ሂደት ላይም ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል)
ለምሳሌ ድምጽ የመስጠትና የመምረጥ መብት፣ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ እስካለው ድረስ ክህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ ውህደት ሊያረግ ይችላል። ለምሳሌ
* ሀገሪቱ ለዜጋዎቿ የምትሰጠው የጤና አገልግሎቶች፣
* ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ መብቶች
* የጡረታ አበልና ድጎማ የመሳሰሉትን ማግኘት
* ከሁለት ዓመት በለይ የተቀመጠ ከሆነ ለህብረተሰብ የሚሰጡት ማህበራዊ አገልግሎቶች አይነፈገውም
* የሚያስተዳድራቸው 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆቹ በራሱ የመኖሪያ ፈቃድ ሥር ይሆናሉ (ልጆቹ 18 ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ የመኖሪያ ፈቃዳቸው በቤተሰብ ምክንያት ይሚባለውን እንዲያወጡ ይደረጋል)
Rimpatrio
ወደ ሀገራቸው መመለሻ የትራንስፖርት ወጪያቸውን ለማይችሉ በሚወጣው ፕሮግራም ተመዝግበው ወደሀገራቸው ለሚላኩ ከሁሉም በፊት በድጋሚ ጣሊያን ሀገር የመመለስ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ነገርግን ለህብረተሰቡ አደገኛ የሆኑትን እንደሁኔታቸው እየታየ ወደመጡበት ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋል።
CPT
ብዙ አከራካሪና ስምምነት ያልተደረሰበት ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል።
1 - Struture aperte በተወሰኑ ስዓቶች መውጣትና መግባት የሚቻልበት (ማንነቱንለማወቅ በሚጠየቅበት ጊዜ የሚተባበር ከሆ)
2 - Struture chiuse ደንብና ሕግን ለማይከተሉና ለማይተባበሩ (ነገርግን 60 ቀን በላይ በውስጡ መቆየት የለባቸውም)
..................///..................

ይኸው የሮማኖ ፕሮዲ መንግስት ከተቃዋሚው ፖለቲካ ክርከር የሚይዝበትና አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ ያገኛቸው የውጪውን ዜጋዎችን የውስጥ መስተዳደሪያ ድንብ መለወጡ ሳይሆን እየፈለሰ ለሚገባው የስደተኛውን ቁጥር መወሰኑ ነው። አስተዳዳሪዎቹና መሪዎቹም የሚሉት ዋናውና ወቅታዊው ጥያቄ እየፈለሰ የሚገባውን ስደተኛ ቁጥር በየ 3 ዓመት የሚያስፈልጉትን ቁጥር በመወሰንና ከ እነዚህም ውስጥ በየዓመቱ እንዲገቡ ማድረግ ነው። እስከሚቻል ድረስ ስርዓትን በማሲያዝ መቀበል እንችላለን። የዓለም አቀፍን የሰበዓዊነት መብቶችን እንዲከበር ለማድረግ በሚቻለን መንገድ ከመጣር ወደኋላ አንልም።" ...........በተቃራኒው ደግሞ የተቃዋሚው የፖለቲካ መሪዎች "ይህ መንግሥት የሚከተለው የፍልሰት ፖሊሲ ወደፊት ሀገሪቷን አስጊ ሁኔታ ላይ ይጥላታል" እያሉ ንዝንዛቸውን ቀጥለዋል። እንደውም አንዳንዶቹ ባለሥልጣናት "በሀገሩ ያልተመቸው ሁሉ ጣሊያንመግባት የለበትም" የሚል አቋም ይዘዋል። የሀገር አስተዳደር ሚንስትሩ ወደ ሀገሩ የገቡ ስደተኞች አሀዝ ባለፈው ዓመት መቀነሱን አመልክተው ስድሳ ሚልዮን ወደ ሚኖሩባትና በየአመቱም አሥር ሺህ ክላንዴስቲኒ ስደተኞች ወደ ሚገቡባት ኢጣልያ ከሰሜን አፍሪቃ በጥቂት ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች መግባታቸውን ማጋነኑ ባልተገባ ነበር ብለዋል። በተጨማሪም ይህ የፍልሰትን የሚመለከተው አዲስ የሕግ ቅምር የያዘው አቋም ግልፅ መሆኑን በተደጋጋሚ ያስረዳሉ። ሌላው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ የሚገኘው የጥቁር ሥራን (Lavoro nero) የማስወገዱ ጉዳይ ነው። በየፋብሪካውና በቤተሰብ አገልግሎት ውስጥ ብቻ የጥቁር ሥራ እየሠሩ ያሉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስለሆኑ ሁሉም regolarizzare መደረግ አለባቸው። ይህንን በጊዘው ስራዓት ማሲያዝ ያስፈልጋል። ለዚህም በየክፍለሀገሩ የሚገኙት የጣሊያን ማዕከላዊ አስተዳደር ክፍሎች በጥቁር ሥራ ላይ የተሰማሩትን የውጪ ዜጋዎች ሙሉ በሙሉ በ regolare ሥራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ሁሉም ተሳትፎ ማድረግና ይሚቻለቸውን ግዴታ እንዲወጡት ብዙ ይጠበቅባቸዋል" ......።
ለማጠቃለል ያህል... ጣሊያን በአለፈው መንግስቷ ከሌሎቹ የአውሮፓ የጋራ መርሕ ወደኋላ ትገኝ እንድደነበረና ብዙዎቹ የአውሮፓ ሕብረት አባላት ሀገሮች ከሚከተሉት መርሆዎች ጋር አንድ አይነት መስመር እንድትይዝ መሆን አለበት። ያለንበት ዘመን ደግሞ ዓለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር የሚደረግበት ዘመን ስለሆነ እንዲሁም ጊዜው የነፃ ገበያ ወቅት በመሆኑ ህዝቦች ከአንዱ አገር ወደ ሌላው ለስራ መሰደዳቸው ጤነኛ አካሄድ ነው። አውሮፓውያን መሪዎችና ፖለቲከኞች ስደተኛውን እንደ አደጋ ሳይሆን ጠቃሚ የልማት አስተዋፅኦ ሊያበረክት የሚችል ሀይል አድርገው መመልከትና እንዲህም የውጭ ዜጎች ወደ አውሮፓ የሚገቡበትን ስርአት በደንብ ማስተካከል ይገባታል።...

domenica

ቃለ መጠይቅ ለኢትዮጲያዊቷ ደራሲ ጋብርኤላ ጋር


la regalita di appartenersi
Barbara Romagnoli

Ex libris - "Regina di fiori e di perle", ultimo lavoro di Gabriella Ghermandi, racconta dell'occupazione italiana in Etiopia, ma anche del percorso di una donna dalle molte identità. Ne abbiamo parlato con l'autrice...

Condividere la memoria che riguarda due popoli, senza omettere nulla né puntare il dito, ma far parlare le contraddizioni e, oltre quelle, guardare al futuro. Questo si pensa dopo aver terminato il bel romanzo di Gabriella Ghermandi (Regina di fiori e di perle, Donzelli editore, 264 pag., 21 euro) dedicato all'occupazione italiana in Etiopia. Nel leggerlo sembra di stare attorno a un tavolo ad ascoltare qualche vecchio di famiglia. Nella finzione letteraria la protagonista che raccoglie le storie, dopo averlo promesso al vecchio Jacob, è Mahlet, bimba cresciuta in Etiopia e divenuta donna in Italia. Ricorda un po' la vita dell'autrice, che ci spiega come è nato questo romanzo, una sorta di musica scritta per essere cantata a più voci.

"Regina di fiori e di perle" è il tuo primo romanzo, ma tu non sei nuova alla scrittura. Perché hai abbandonato il racconto breve?
Nel momento in cui ho sentito l'esigenza di raccontare del colonialismo italiano con la voce della nostra gente, mi sono resa conto che un racconto o uno spettacolo non sarebbe stato sufficiente. Continue storie sorgevano dentro di me, come un vulcano risvegliato all'improvviso. Esplodevano nella mia immaginazione come fuochi d'artificio multicolori. Storie che avevo ascoltato da bambina e altre che mi sono state raccontate, per caso, ma forse non lo era, da alcuni anziani guerrieri che ho incontrato nel mio ultimo viaggio in Etiopia, nel gennaio 2006. Tante storie che avevano bisogno del ritmo lento della mia terra, e quindi un romanzo.

La tua narrazione si svolge sul registro dell'oralità, qualcosa che appartiene profondamente alla cultura tradizionale africana. Il racconto orale è ancora importante o la modernità ha tolto il gusto per la parola ascoltata e tramandata?
La situazione è alquanto complessa. Innanzitutto bisogna parlare delle varie forme di oralità, una di queste nella tradizione etiope è veicolata attraverso il canto, le parole delle canzoni sono la voce del popolo. Il canto racconta dell'attualità, critica, denuncia in una forma molto antica piena di metafore. Oggi questa tradizione è mantenuta dai giovani artisti. Poi esiste la tradizione dei cantori, i cosiddetti "Azmari", improvvisatori di versi, che attualmente hanno aperto locali ad Addis Abeba, molto frequentati. Infine esiste ancora grande rispetto per gli anziani e gli eremiti, i quali sono i detentori della "storia" tramandata attraverso l'oralità. Quindi, anche se in un modo che potremmo dire "adattato alla modernità", la tradizione orale è ancora uno dei pilastri della cultura etiope.

C'è una forte presenza di Dio in questo racconto. Lo stesso Dio degli italiani colonizzatori, eppure appare diverso, forse per via di come il tuo popolo si intrattiene con esso. Qual è il tuo rapporto con la religione?
Io non ho rapporti con la religione ma con la spiritualità. Il mio padre spirituale, un eremita che oggi ha 91 anni, mi ha cresciuta ricordandomi che il rapporto di ciascun uomo con Dio è privato, che la spiritualità è uno sostegno per compiere il proprio percorso e non un ostacolo e che per avvicinarsi ad essa bisogna allontanarsi dal moralismo. Nel mio percorso spirituale ho incontrato lama tibetani e maestri indiani che mi hanno aiutato ad aprire la mente, a trovare nuovi punti di osservazione. Il mio cuore resta vicino al cristianesimo, perché quella è la mia strada anche se non può esserla per tutti. Sono molto grata ai tanti maestri che ho incontrato per avermi aiutato a percorrere un pezzo di strada.

Tante le donne, accanto a Mahlet, protagoniste di questo romanzo corale. Che "peso" ha nella tua vita la differenza/ identità di genere?
Oddio, che domanda difficile. Non ho mai sentito il peso di essere una femmina e neppure il peso di essere mista. Per un certo tempo, nella mia infanzia, ho provato ad essere solo italiana. Così avrebbe voluto mia madre che aveva subìto il colonialismo e sperava che noi, io e mio fratello, non dovessimo vivere le sue stesse pene. Poi sono arrivata in Italia e ho compreso la naturale regalità dell'appartenere a me stessa e alla mia complessità di donna e di incontri di culture. L'essere femmina mi ha aiutato, sono stata coccolata da tutti gli anziani e le anziane di casa e sono sempre stata incoraggiata ad andare avanti. Soprattutto dagli uomini. Ho potuto incarnare il mio animo da guerriera e seguire, seppure in un modo diverso, ossia con l'arma della scrittura, la stessa strada delle tante donne della resistenza di cui parlo nel mio romanzo.

Grazie al lavoro di storici e scrittori come te si è sfatato il mito degli italiani brava gente in Africa, eppure non è ancora diventato patrimonio di memoria collettiva. Cosa bisogna fare secondo te?
Bisogna continuare a parlarne, magari facendo circolare pellicole come "Adwa" di Hailè Gerima, Italian legacy - documentario britannico - o il film "Il leone del deserto" (che in Italia ha subìto una scandalosa censura n.d.r). E poi scrivere le storie di quei tempi, perché, a differenza di un libro storico che permette il distacco emotivo, i film, i romanzi, i racconti, portano gli spettatori ad una emozione empatica che ne risveglia le coscienze sopite. Comprendere di avere sbagliato aiuterà gli italiani a non sentirsi superiori e migliori di altri colonialisti.

Da anni vai in giro con una intensa attività teatrale: spettacoli che parlano di identità multiple e collettive. Che rapporto c'è tra l'essere figlia di più culture e la scrittura?
La scrittura è l'arma magica che mi ha permesso di armonizzare tra loro le mie differenze. Mescolare la lingua italiana agli odori delle spezie del mio paese, ai suoni, ai canti, ai modi di dire è per me fonte di un infinito piacere sensoriale e dell'anima. Attraverso la scrittura io non sono divisa tra le mie differenze, ma quadruplicata, dentro di me si crea spazio per poter essere al contempo italiana, etiope, eritrea, bolognese, senza togliere nulla alle mie diverse identità.

In un tuo racconto dicevi che arrivata in Italia ti aveva colpito quanto gli italiani "programmassero" la vita, incuranti di ciò che accadeva loro attorno. Pensi sia ancora così o c'è altro adesso che noti e che è molto diverso dalla tua cultura di origine?
L'Italia sta cambiando, la programmazione sta sempre più cedendo il passo alla precarietà. Ed è una precarietà molto pesante perché aggravata dalla mancanza di qualcosa che nel mio paese c'è e permette a tutti di continuare a vivere: la solidarietà tra la gente.


martedì

በጣሊያን ሀገር የአጭር ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማሻሻያ ሕግ ወጣ


05 06 07
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
ካሁን ቀደም ማንኛዉም ግለሰብ ለጉብኝት፣ ለንግድ ወይንም ለትምህርት ጣሊያን ሀገር በሚመጣበት ወቅት የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የመጠየቅና የማግኘትም ግዴታ ነበረበት:: በአዲሱ ሕግ ማለትም ቁጥር 68 በ 01/06/2007 በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 126 ( Disciplina dei soggiorni di breve durata degli stranieri per visite, affari, turismo e studio) ላይ ታትሞ በወጣዉ ሕግ መሰረት ግን ማንኛዉም የዉጭ ሀገር ዜጋ በጣሊያን ሀገር የመቆያ የጊዜ ገደቡ ከሶስት ወራት በላይ ካልሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማዉጣት ወይንም የመጠየቅ ግዴታ የለበትም ይላል:: ለምሳሌ አንድ ሰዉ ከሆነ ሀገር ወደ ጣሊያን ለቱሪዝም ወይንም ለጉብኝት የሶስት ወራት ቪዛ አግኝቶ ቢመጣ ጣሊያን ሀገር በሚገባበት ወቅት ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት ማሳወቅ (dichiarazione di presenza) ብቻ ይኖርበታል:: በመሆኑም የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ጠይቆ ለማግኘት ጊዜዉን፣ ጉልበቱንና ገንዘቡንም ጭምር አያባክንም ማለት ነዉ::
በአለፈው አርብ በ "Gazzetta Ufficiale" የወጣውና ከ 2/06/07 ጀምሮ የፀደቀውን አዲስ ሕግ ግልባጭ ከዚህ ማውረድ ይችላሉ


giovedì

በጣሊያን የኢትዮጲያዊቷ ደራሲ መጽሀፍ ታትሞ ወጣ
Regina di fiori e di perle


Finalmente è uscito un romanzo sul colonialismo italiano raccontato dal punto di vista di noi etiopi. Un libro per Donzelli editore, dal titolo
"Regina di fiori e di perle".

.....Debre Zeit, cinquanta chilometri da Addis Abeba, 1987: una grande famiglia patriarcale; un legame speciale tra il vecchio Yacob e Mahlet, la più piccola di casa. Lui la conosce meglio di chiunque altro: la guarda negli occhi, mentre lei divora le storie che lui le narra. Così, un giorno si mette a raccontarle del tempo degli italiani, venuti ad occupare quella terra, e degli arbegnà, i fieri guerrieri che li hanno combattuti. Quel giorno, Mahlet fa una promessa: da grande andrà nella terra degli italiani e si metterà a raccontare...
Un lungo viaggio nel tempo e nello spazio, in cui scorrono la vita e le vicissitudini di una famiglia etiope nel periodo della dittatura di Mengistu Hailè Mariam, e nel decennio successivo dell'emigrazione. Un romanzo che percorre oltre cento anni di storia, dal tempo di Menelik ai giorni nostri. Una narrazione che, come scrive Cristina Lombardi-Diop nella postfazione, «non riguarda solo la dimensione del passato etiopico, ma è anche un modo di interrogarsi sull'idendità della memoria coloniale italiana».
...A cavallo tra lingue ed etnie, tra nazioni e continenti, tra occupazioni militari e guerre fratricide, si dipanano le mille storie di questa Shahrazade dei nostri tempi, fiera delle sue origini etiopi ed eritree, e insieme capace di usare la lingua italiana con l'intensità e la precisione di un bisturi.
...Gabriella Ghermandi è nata ad Addis Abeba nel 1965, e si è trasferita in Italia nel 1979, dove vive a Bologna, città di origine del padre. Seguendo l'arte della metafora tipica della tradizione culturale etiope, scrive e interpreta spettacoli di narrazione che porta in giro sia in Italia che in Svizzera. Conduce laboratori di scrittura creativa nelle scuole, sulla ricerca della «identità unica di ciascun individuo» da contrapporre alle «identità collettive» come percorso di pace. È stata per due anni direttrice artistica del Festival Evocamondi, rassegna di narrazione e musiche dal mondo, organizzato dalla rivista «El Ghibli», a Bologna. La sua intensa attività teatrale e teorica sul tema della multidentità e della scrittura è da anni oggetto d'interesse per molti studiosi anche all'estero, e l'ha portata di recente a compiere un tour in alcune delle più importanti Università degli Stati Uniti.
...Ha detto di sé: «Per i bianchi non ero bianca e per i neri non ero nera. Mia madre ha vissuto e subìto il colonialismo e voleva che io e i miei fratelli ci sentissimo il più possibile italiani. Voleva cancellare la sua identità e la sua lingua: oggi io parlo benissimo l'amarico e lo capisco meglio di lei... La nostra era una vita mista, fatta di quattro lingue diverse: l'amarico e l'italiano erano quelle di tutti i giorni, il bolognese e il tigrino erano le lingue della festa».


sabato

ያለማወቅ ከምንም አያድንም


ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ (ከቦሎኛ)
...... ሰላም ለአንባቢያን እንዴት ሰነበታችሁ?
..... በቅድሚያ ሰለቸኝና ደከመኝ ሳይል ቀንና ሌሊት በመድከም ይህንን መድረክ በማዘጋጀት የተጠቃሚነት እድል ለሰጠኝ ለአቶ አብርሃም ዘውዴ ልባዊ የሆነ ምስጋናዬን እቀርባለሁ::
...... ቀጥሎም እትዮጵያን በውጭዉ ዓለም ሁሌ በጥሩ ስም ለማስጠራት ለሚደክሙትና ይህቺ ዌብ ሳይት አምራ ደምቃና ከግብ ደርሳ ማየት እንድንችል ለተባበሩትና ወደፊትም ለሚተባበሩት ሁሉ መልካም ስራ፣ አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ግፉበት የድካማችሁ ውጤት ስራችሁ ነዉ እላለሁ::
...... በመሆኑም ነዉ አባቶች ሲተርቱ እንዲህ ያሉት "ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም":: ይህ በቅርቡ የተከፈተዉ እትዮጵያ በጣሊያን በመባል የታወቀዉ የኢንተርነት አድራሻ ማንኛችንም በጣሊያን ሃገር ነዋሪ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ትምህርት የምንቀስምበት መድረክ ከመሆን አልፎ አንዱ ከሌላዉ ጋር ሀሳብ ለሀሳብ የሚለዋወጥበት ጥሩ ዘመናዊ የመገናኛና የመወያያ ዘዴ ነዉ::
...... ለዚህም ነዉ "ያለማወቅ ከምንም አያድንም" በማለት ሀሳብ መስጠት የጀመርኩት:: በእርግጥ ብዙዎቻችን የጊዜ እጥረትና የስራ ሁኔታዎች ያለመመቻቸት ችግር ሊኖረን እንደሚችል ማወቅ ተስኖኝ ሳይሆን ከዚችው ካለችን ጊዜ የተወሰነችዋን ጠቃሚ በሆነዉ በትምህርት ላይ ብናዉላት የአዕምሮ እረፍት እናገኛለን የሚል የጠና እምነት ስላለኝ ነዉ::
.
ይህ የእትዮጵያ በጣሊያን ኢንተርኔት ዌብ ሳይት ለምን ለምን ይጠቅማል? ማንንስ ይመለከታል?
...... ከመልሶቹ በጥቂቱ:-
1. የጣሊያንኛ ችግር ላለባቸዉ ግለሰቦች ሁሉ በአማርኛ የመጻፍና የማንበብ እድል ይሰጣል;
2. በጣሊያን ሀገር የእኛን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዜና ያቀርባል;
3. ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ተቀይሮ የነበረዉን የስልክ ቁጥር ችግር በማቃለል በአሮጌዉ ምትክ አዲሱን ፈላልጎ ማግኘት ይቻላል;
4. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋን የሚመለከት የመኖሪያ ፈቃድ ህግን በተመለከተ ማብራሪያ ያቀርባል;
5. በጣሊያን የእትዮጵያ ኤምባሲን አድራሻና የስልክ ቁጥር ከመጠቆም አልፎ ለኤምባሲዉ ባለጉዳዮች ምን ሰነዶች እንደሚያስፈልጉ ያስረዳል;
6. በጣሊያን ሀገር ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእናት ሀገሩን የተለያየ ወቅታዊ ዜና በሚፈልገዉ ማግኘት ይችላል;
7. በጣሊያን ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ ማህበራት ዝርዝርና አድራሻ ያቀርባል;

8. የአዉሮፓ የቀን አቆጣጠርን ወደ ኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር በቀላሉ መቀየር ይቻላል;
9. የተለያዩ የሀገር ባህላዊ ዘፈኖችን መስማትና ድራማዎችን መከታተል ይቻላል;
10. የተለያዩ አስተያየቶችን መላክና መቀበልም ጭምር ይቻላል::
11. ...ይቀጥላል ...


giovedì

የጣሊያን የምንስትሮች ምክር ቤት አዲስ የኢምግሬሽን የሕግ ረቂቅ አወጣ


(ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ)
.....በጣሊያን አገር የሰሞኑን የኢምግሬሽን የሕግ ለዉጥ በተመለከተ የተለያዩ ህሳቦች በተለይም ከእዉነት የራቁ ወሬዎች ከየአቅጣጫዉ ይሰነዘራሉ:: በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የሕግ ረቂቂ እንጂ ተግባራዊ የሆነ ሕግ አለመሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ:: በአንድ አገር አንድን ሕግ ተግባራዊ ሕግ ነዉ ሊያሰኘዉ የሚችለዉ የአገሪቱ ፓርላማ አፅድቆት በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣ በኋላ ነዉ:: ከዚህ ሁሉ የዉጣዉረድ ጉዞዉ በኋላ ሕጉ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሕግ ነዉ ብሎ ማለት ይቻላል:: ይህ ሕግ ገና ብዙ መሰናክሎችን ያላለፈ እንደመሆኑ መጠን ተጠቃሚዉን ክፍል ችግር ላይ ጥሎት ሰሞኑን አንዳንድ ግለሰቦች... "አዲስ ሕግ ወጥቷል ብለዉ የሆኑ ጣሊያኖች ሲያወሩ ሰማሁ እዉነት ነዉ?" "የዜግነት ጥያቄስ አሁኑኑ ማቅረብ እችላለሁ?" ... እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ:: በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከተዉና በጣሊያን አገር ነዋሪ የሆነዉ የዉጭ አገር ዜጋ በተለይም የአማርኛን ቋንቋ አንብቦ መረዳት የሚችል ሁሉ ትክክለኛዉን መልእክት ማግኘት ይችላል ብዬ በማመን የሕጉን ለዉጥና መንፈስ አጠር ባለ መልኩ ከዚህ በታች ላስቀምጥ እሞክራለሁ::

FLUSSI DI INGRESSO
ካሁን በፊት በየአመቱ የዉጭ አገር ዜጎች ወደ ጣሊያን አገር በመምጣት መስራት እንዲችሉ የተወሰነ ቁጥር ገደብ ተደርጎ ፕሮግራም ይወጣል በአዲሱ ህግ ግን ይህ ቁጥር በሶስት አመት አንድ ጊዜ ይወሰናል ቁጥሩም እንዳስፈላጊነቱ ሊጨምር ይችላል::
.
LAVORATORI ALTAMENTE QUALIFICATI
ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸዉ የዉጭ አገር ዜጎች ጣሊያን አገር መጥተዉ ለመስራት ጥያቄ ካቀረቡ የመምጣት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ይላል ካሁን ቀደም የነበረዉ ህግ ግን የጉልበት ስራን ብቻ ይመለከት ነበር::

LISTE DI COLLOCAMENTO
ማንኛዉም የዉጭ አገር ዜጋ ጣሊያን አገር ገብቶ ስራ ለመስራት ባለበት አገር የጣሊያን አምባሲ በሚገኘዉ የስራ ፈላጊዎች ዝርዝር ሰነድ ላይ መመዝገብ ይኖርበታል::

AUTOSPONSORIZZAZIONE
አንድ የዉጭ አገር ዜጋ በራሱ ሃላፊነት የራሱን ወጪ ችሎ ዋስትናዉን እራሱ ከሸፈነ ጣሊያን አገር ገብቶ ስራ የመስራት መብት አለዉ:: ለምሳሌ በዚህ አንቀጽ መሰረት አንድ ግለሰብ በቂ ገንዘብ አለኝ ለጣሊያን ቪዛ ይሰጠኝ ብሎ ቢጠይቅ ቪዛዉን የማግኘት እድል አለዉ ማለት ነዉ::

VISTI D’INGRESSO
አንድ የዉጭ አገር ዜጋ ጣሊያን አገር ለመምጣት ቪዛ በሚጠይቅበት ወቅት ያለአንዳች ቢሮክራሲና ዉጣዉረድ ለጥያቄዉ መልስ ባስቸኳይ ሊሰጠዉ ይገባል:: ጣሊያንም ከመጣ በኋላ ካሁን በፊት እንደነበረዉ የመኖሪያ ኮንትራት (contratto di soggiorno) የመፈረም ግዴታ አይኖርበትም::

DURATA DEI PERMESSI
የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የጊዜ ገደብ ካሁን በፊት ከነበረዉ የረዘመ ይሆናል:: ለምሳሌ የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ አነስተኛ ከሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ ለስድስት ወር ይሰጠዋል:: የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ ከስድስት ወር በላይ ከሆነ ግን የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ የሁለት አመት ይሆናል:: የስራ ኮንትራቱ የጊዜ ገደብ የሌለዉ ከሆነ የሶስት አመት የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ይሰጠዋል:: የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱ በሚታደስበት ወቅት የጊዜ ገደቡ እጥፍ ይሆንና የስድስት ወር የነበረዉ ለአንድ አመት፣ የሁለት አመቱ ለአራት አመት ይታደስለታል ማለት ነዉ::
.
PERMESSI PER MOTIVI UMANITARI
የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት በስራ ብቻ ሳይሆን በሰባዊ መብት ምክንያትም ለአንድ አመት ሊሰጥ ይችላል:: የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀቱንም ለማሳደስ ግለሰቡን ሊያኖር የሚችል የገቢ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል::
.
PASSAGGIO DELLE COMPETENZE AI COMUNI
ይህ ሕግ በተግባር ሲተረጎም የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማሳደሱ ተግባር ሃላፊነቱ የፖሊስ ጽ/ቤት ሳይሆን የማዘጋጃ ቤት ይሆናል:: ይህም በየፖሊስ ጽ/ቤቶች በራፍ ሲደረግ የነበረዉን የሰዉ ልጅ የማያልቅ ሰልፍ ሊያስወግድ ይችላል::

INSERIMENTO DEI MINORI STRANIERI
በጣሊያን አገር ነዋሪዉ የዉጭ አገር ዜጋ ህጻናትም ጭምር ከህብረተሰቡ ተዋህዶ አምራች ዜጋ መሆን እንዲችል የስራ፣ የትምህርት፣ የህክምና፣ የመኖሪያ ቤት፣ የጡረታ እኩልነት መብቱ ሁሉ ይከበርለታል::

ELETTORATO ATTIVO E PASSIVO ALLE AMMINISTRATIVE
በወንጀል ያልተነካካ በጣሊያን አገር በህጋዊነት ለአምስት አመት ያህል ነዋሪ የሆነ ማንኛዉም የዉጭ አገር ዜጋ በሚኖርበት ክፍለ ሀገር በሚደረገዉ የአስተዳደር ምርጫ በመራጭነትም ሆነ በተመራጭነት የመካፈል መብት ይኖረዋል::

PROGRAMMI DI RIMPATRIO E ASSISTITO
በተለያዩ ምክንያቶች በጣሊያን አገር መኖር የማይችሉት የዉጭ አገር ዜጎች ፕሮግራም ይዘጋጅና በወጣዉ ፕሮግራም መሰረት እርዳታ ተደርጎላቸዉ ወደየመጡበት አገራቸዉ እንዲመለሱ ይደረጋል:: አገራቸዉም ከገቡ በኋላ እንደገና ተመልሰዉ ጣሊያን አገር በስራ የመምጣት እድል ቅድሚያ ይሰጣቸዋል::

MODALITA’ DI ALLONTANAMENTO
አንድ በጣሊያን አገር የሚኖር የዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል ከተገኘበት እንደየወንጀሉ ክብደት፣ ቀላልነትና አደገኛነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ይታሰራል ወይንም አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ይደረጋል::

CENTRI DI PERMANENZA TEMPORANEA
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጣሊያን አገር የገቡ የዉጭ አገር ዜጎች ተይዘዉ ማንነታቸዉ ተረጋግጦ ወደያገራቸዉ እስከሚመለሱ ድረስ እስከ ስልሳ ቀናት ያህል ይቆያሉ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ይደረጋል:: የማረፊያ ቤቶቹም ቁጥር ካሁን ቀደም ከነበረዉ አነስተኛ ይሆናል::
ለማጠቃለል ያህል ይህ የሕግ ረቂቅ ከሞላ ጎደል ሲታይ የሰዉን ልጅ መብት የሚያስከብር ሌሎች በዴሞክራሲ የበለጸጉ አገሮች ካላቸዉ የኢሚግሬሽን ሕግ ጋር የሚቀራረብ ይመስለኛል ሆኖም አንዳንድ የጣሊያን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉ እንዳይጸድቅና ግቡን እንዳይመታ ከመፈለጋቸዉ የተነሳ ጣሊያን በዉጭ አገር ዜጋ ልትወረር ነዉ፣ አገሪቱ የወንጀለኛ ማጠራቀሚያ ልትሆን ነዉ፣ እና ወዘተ በማለት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር በመንዛት ፍርሃት በመፍጠር ላይ ይገኛሉ:: ጉዳዩ "አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ" እንደሚለዉ የአባቶች ተረት እንዳይሆን የጣሊያን መንግስት ጥንቃቄ ሊያደርግበት ይገባል ብዬ እላለሁ::
Bologna, 30/04/2007


domenica

በጣሊያን በጥገኝነት ለሚኖሩ - Richiedenti asilo


በጣሊያን ጥገኝነት (የተገን መብት) ለማግኘት ማመልከቻ ላስገቡት ለየት ያለ የመኖሪያ ፍቃድ ...
27 04 06
እንደ አማራጭ እድል ሊወሰድ ይችላል ግን.....
ከዚህ በፊት በጣሊያን የተገን መብትን ለማግኘት ወይም በጥገኝነት ለመኖር ማመልከቻ ያቀረቡ ከኮሚሲዮኑ መልስ ሳያገኙ ለዓመታት በቁማቸው የቀሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የውጪ ዜጋዎች እንዳሉ ይታወቃል። የዛሬ ሁለት ዓመት (21 Aprile 2005) የተለየ መመሪያ ወጥቶ ብዙ ሺህ የሚሆኑ ተገን ጠያቂዎች ይህንኑ ማመልከቻ አቅርበው እስካሁን መልስ ያላገኙ ናቸው። "አጠራጣሪ ተስፋ ይዘው ከሚቀመጡ ሌላ አማራጭ እድል ይኑራችው" በማለት ከእዚህ በታች ያለውን ለየት ያለ መንገድ ፈጥረዋል።
ይኸውም፡- ማመልከቻቸውን ለሚያነሱ ወይም rinunciare ለሚያደርጉ ለየት ያለ ሰበዓዊ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጥ በማድረግ ነው። (ይህ ፍቃድ Permesso di soggiorno per Motivo Umanitari ተብሎ የሚጠራና ለየት ያለ ይዘት እንዳለው ደግሞ ማወቅ ይገባል። ምክንያቱም ማመልከቻ ጥያቄዎን ከማንሳትዎ በፊት አንዳንድ ሁኔታዎቹን መመርመር አይከፋም ለማለት ነው) ከዚህ በኋላ ግን ሁኔታውን መርምረው rinunciare ለማድረግ ውሳኔ ላይ ለደረሱት ወይም ይህ አማራጭ እድል ለሚስማማቸው ፎርሙን በቀጥታ ከዚህ አገናኝ አውርደው (scaricare አድርገው) ፎርሙን ከሞሉ በኋላ ለማዕከላዊ ኮሚሲዮኔ FAX መላክ አለብዎት። ይህም ኮሚሲዮኔ permesso umanitari ሊያገኙ እንደሚገባዎት ለኩዌስቱራ ያሳውቃል። እርስዎም እንደ አመልካችነትዎ ይህንን ማግኘትዎንና መብትዎት የሚከበርልዎት ዜጋ መሆኑዎን ለJudice Istruttore ያሳውቃሉ።
የተገን ጠያቂዎችን የሚመለክተው ማከላዊው የምክር ፅህፈት ቤትም ይህ እርምጃቸው በጣም የሚያረካቸው ሆነው አግኝተውታል። የጽህፈትቤቱ ዳይሬክተር የሆኑት Christopher Hein ሲናገሩም ከ 2002 ዓም ጀምሮ መልስ እስኪሰጣቸው ድረስ ይሚጣባበቁ አሁንም እንዳሉ በማስረዳት "ብዙዎቹ ይህንን እድል በመጠቀም በጣሊያን የመኖርና የመሥራት ፈቃድ የሚያገኙበት በመሆኑ በጣም ደስ ብሎናል" ብለዋል። እራሱን ይህን አማራጭ እድል በተግባር ላይ ለማዋል በስብሰባቸው ውሳኔ ላይ መድረሳችን ብቻ የሚያኮራን ነው ይላሉ።
.
ማስገንዘቢያ
በመሀል ተንጠልጥለው የሚቀሩ ጥያቄዎች አይጠፉም
ለምሳሌ
* ይህ permesso umanitario በየጊዜው ለማሳደስ ከበድ ሊል ይችላል
* ከ permesso di soggiorno የሚያንስ ጊዜ ያለው ነው
* Ricongiungimento familiari የማግኘት መብት አይሰጥም
* ...ወዘተ...
በእነዚህ ምክንያቶች ውሳኔ አድርገው ፎርም ሞልተው ፈርመውና ፋክስ ከማድረግዎ በፊት ሁኔታውን በደንብ ይመርምሩ።
etiopiainitalia@yahoo.it


giovedì

የጣሊያን መንግስት ለሰማኒያ ሺህ የዉጭ አገር ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ፍቃድ ሊሰጥ ነዉ


80 MILA STAGIONALI NON COMUNITARI
8 03 2007
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
Il prossimo 12 marzo 2007 sarà pubblicato, in gazzetta ufficiale, il decreto che ha stabilito le quote massime di ingresso di lavoratori non comunitari per l’anno 2007. Sono ammessi in Italia per motivi di lavoro subordinato, i cittadini stranieri non comunitari residenti all’estero, entro una quota massima di 80000 unità, da ripartire tra le regioni e le province autonome”. A partire dalla stessa data quindi sarà possibile presentare le domande per far entrare in Italia e assumere lavoratori stagionali extracomunitari.
Ci si può rivolgere alle associazioni di categoria o spedire la richiesta d'assunzione per raccomandata al Ministero dell’Interno.
Gli 80mila nuovi ingressi autorizzati dal nuovo decreto flussi sono riservati a stagionali provenienti dai seguenti paesi:
Serbia, Montenegro, Bosnia-Herzegovina, ex Repubblica Jugoslavia di Macedonia, Croazia, India, Pakistan, Bangladesh, Sri Lanka, Ucraina, Tunisia, Albania, Marocco, Moldavia, Egitto e altri.
Indipendentemente dalla nazionalità, potrà inoltre entrare chi è stato titolare di un permesso per lavoro stagionale negli ultimi tre anni. I datori di lavoro potranno presentare le domande attraverso le associazioni di categoria o spedendole per raccomandata semplice al ministero dell'Interno. La prima strada dovrebbe garantire tempi più brevi per il rilascio del nulla osta, dal momento che la procedura è completamente informatizzata. Gli sportelli delle associazioni di categoria possono infatti compilare le domande ondine e inviarle subito allo Sportello Unico per l'Immigrazione, che le inoltra alla Direzione provinciale del Lavoro.
Per presentare invece la domanda per posta si deve scaricare il modulo 07-STAG (non si possono utilizzare fotocopie) dal sito internet del Ministero dell'Interno, compilarlo e inserirlo in una busta insieme alla fotocopia dei documenti del datore di lavoro e del lavoratore straniero. Sulla busta va incollato o ricopiato il modello di frontespizio pubblicato dal Ministero dell'Interno, presso il quale è stata creata una task force che digitalizzerà la domanda e la inoltrerà allo Sportello Unico per l'Immigrazione.

Dai seguenti link potete scaricare moduli e istruzioni
(Cliccate col tasto destro e scegliete "salva oggetto con nome..."):
8 marzo 2007 Elvio Pasca


sabato

በጣሊያን አገር ሰራተኛ ከስራዉ ሲሰናበት ተጠራቅሞ ቆይቶ በመጨረሻ ላይ የሚከፈለዉን ገንዘብ የሚመለከት የህግ ለዉጥ


TFR
Che cos’è?
01 02 2007 ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ

ይህን በተመለከተ በቅርቡ የጣሊያን መንግስት አዲስ መመሪያ አዉጥቷል:: የመመሪያዉን ይዘት ከዚህ ቀጥዬ ባጭሩ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ::

እያንዳንዱ ማለትም ጉዳዩ የሚመለከተዉ ግለሰብ ሁሉ የጊዜዉ ገደብ ከማለፉ በፊት በመከታተልና ጠይቆ በመረዳት አስፈላጊዉን ፎርም መሙላት ይኖርበታል::

በመጀመሪያ ደረጃ TFR ማለት ምን ማለት ነዉ?

በጣሊያንኛ Trattamento di Fine Rapporto (TFR) ወይንም በዘልማድ አነጋገር Liquidazione በመባል የሚታወቀዉ የስራ መሰናበቻ በጀት አንድ አሰሪ ግለሰብ ወይንም ድርጅት ሰራተኛዉን በሚያሰናብትበት ወቅት ተጠራቅሞ የቆየዉን ለሚያሰናብተዉ ሰራተኛ የሚከፍለዉ የገንዘብ መጠን ነዉ:: ሰራተኛዉ ለብዙ አመታት በስራዉ ላይ ተሰማርቶ ከሆነ የገንዘቡም መጠን በዚያዉ ልክ ከፍ ይላል:: የስራዉ ጊዜ አነስተኛ ከሆነ ግን ገንዘቡም አነስተኛ ይሆናል:: ካሁን ቀደም የነበረዉን ህግ ከተመለከትን እንዲህ ይላል - አንድ ሰራተኛ ከስራዉ በሚሰናበትበት ወቅት ከደመወዙ ተቀናንሶና ተጠራቅሞ የቆየዉ ገንዘቡ ባንድ ጊዜ ለሰራተኛዉ ይከፈለዋል::

ባዲሱ ህግ ግን አንድ ሰራተኛ እስከ 30/06/2007 ባለዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ፎርም በመሙላት ገንዘቡ በአሰሪዉ እጅ እንዲቆይለትና መጨረሻ ላይ እንዲከፈለዉ ወይንም በሌላ የእንቨስትመንት መልክ ወደ ጡረታ በጀት እንዲዛወርለት የመምረጥ ግዴታ አለበት:: ከሁለቱ አንዱን ካልመረጠ ግን እንደችላ ባይ ተቀባይ ተቆጥሮ አሰሪዉ ይህንኑ ገንዘብ ወደ ጡረታ በጀት እንዲዘዋወር ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ያስተላልፋል:: ይህ አዲስ ህግ ለጊዜዉ የመንግስት ሰራተኛንና በቤት ሰራተኛነት ተቀጥረዉ የሚሰሩትን የቤት ሰራተኞችን (colf e badanti) አይመለከትም::

Che cos’è il TFR?
Il trattamento di fine rapporto (anche conosciuto come “liquidazione”) è la somma che viene corrisposta dal datore di lavoro al lavoratore al termine del rapporto di lavoro dipendente.

Come si determina?
Il TFR si determina accantonando per ciascun anno di lavoro una quota pari al 6,91 % della retribuzione lorda. La retribuzione utile per il calcolo del TFR comprende tutte le voci retributive corrisposte in dipendenza del rapporto di lavoro, salvo diversa previsione dei contratti collettivi. Gli importi accantonati sono rivalutati, al 31 dicembre di ogni anno, con l'applicazione di un tasso costituito dall'1,5% in misura fissa e dal 75% dell'aumento dell'indice dei prezzi al consumo Istat. Al momento della liquidazione, il TFR è tassato, in linea generale, con l’applicazione dell’aliquota IRPEF media del lavoratore nell’anno in cui è percepito. Per la parte di TFR che si riferisce agli anni di lavoro decorrenti dal 1° gennaio 2001, l’amministrazione finanziaria provvede poi a riliquidare l’imposta, applicando l’aliquota media di tassazione del lavoratore degli ultimi 5 anni.

La scelta sulla destinazione del Tfr
In base a quanto previsto dal disegno di legge finanziaria, dal 1° gennaio 2007 ciascun lavoratore dipendente può scegliere di destinare il proprio Trattamento di Fine Rapporto (TFR) maturando (futuro) alle forme pensionistiche complementari o mantenere il TFR presso il datore di lavoro. In relazione all’anzianità contributiva maturata presso gli enti di previdenza obbligatoria si aprono diverse possibilità di scelta per i lavoratori.

Lavoratori dipendenti iscritti ad un ente di previdenza obbligatoria dal 29 aprile 1993.

La scelta del lavoratore sulla destinazione del TFR riguarda l’intero TFR maturando e può essere manifestata in modo esplicito (dichiarazione espressa) o tacito (silenzio-assenso all’adesione).

Modalità Esplicite
Entro il 30 giugno 2007 per i lavoratori in servizio al 1° gennaio 2007, o entro 6 mesi dalla data di assunzione, se avvenuta successivamente al 1° gennaio 2007, il lavoratore dipendente può scegliere di: •
destinare il TFR futuro ad una forma pensionistica complementare; • mantenere il TFR futuro presso il datore di lavoro. In tal caso, per i lavoratori di aziende con più di 50 dipendenti, l’intero TFR è trasferito dal datore di lavoro al Fondo per l’erogazione del TFR ai dipendenti del settore privato, gestito, per conto dello Stato, dall’INPS.

Modalità Tacite (Silenzio - Assenso)
Se entro il 30 giugno 2007 per chi è in servizio al 1° gennaio 2007, o entro 6 mesi dall’assunzione, se avvenuta successivamente al 1° gennaio 2007, il lavoratore non esprime alcuna indicazione relativa alla destinazione del TFR, il datore di lavoro trasferisce il TFR futuro alla forma pensionistica collettiva prevista dagli accordi o contratti collettivi, anche territoriali, o ad altra forma collettiva individuata con un diverso accordo aziendale, se previsto. Tale diverso accordo deve essere notificato dal datore di lavoro al lavoratore in modo diretto e personale.



mercoledì

ጣሊያንና የዉጭ ዜጎችዋ


ከጠብ ወደ ፍቅር ወይንስ ከፍቅር ወደ ጠብ
ቃለ መጠይቅ

የተያያዝነዉ አዲስ ዓመት የሰላም፣ የደስታና የብልጽግና ይሁንልን በማለት እራሴን ላስተዋዉቅ።
አብረሃም ዘዉዴ እባላለሁ:: ከሁሉም በፊት በየዕለቱ ይህንን ድረገፅ የሚጎበኙት (በውጪ ሀገራት የሚኖሩት) ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እና ይህች ድረገፅ የራስዋ ግብ ላይ ለመድረስ ስለተቃረበች አዘጋጅና ተባባሪዎች የሆንን በሙሉ ደስታ ተሰምቶናል። ለዚህም እኔም ከልብ አመሰግናለሁ::
ከዚህም በመቀጠል ለዚህ መድረክ ዝግጅት መሳካት ተባባሪ ከሆኑት አንዱ ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ ጋር በጣሊያን የዉጭ አገር ዜጎችን በተመለከተ አጠቃላይ ሁኔታ ያደረግሁትን ቃለ መጠይቅ (ጥያቄና መልስ) ባጭሩ ከዚህ በታች አቀርብላችኋለሁ::

ጥያቄ:- ... በቅርቡ አለም አቀፍ የስደተኞች ቀን (Immigration Day) በጣሊያንም አገርም ተከብሮ ነበር:: ይህን በተመለከተ በጣሊያን ለሚኖሩት ኢትዮጵያዉያንም ሆነ ከጣሊያን ዉጪ ለሚከታተሉን ሁሉ ምን መልዕክት ያስተላልፋሉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... ይህን ጥያቄ በብዙ መልኩ መመለስ ይቻላል:: ለምሳሌ የጣሊያን ፕሬዝደንት የተከበሩት ጆርጆ ናፖሊታኖ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰሞኑን እንዲህ ብለዉ ነበር: በጣሊያን ነዋሪዉ የዉጭ አገር ዜጋ ለኢኮኖሚያችንና ለባህላችን እድገት መሰረት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፣ ልዩነታችን የብልጽግናችን መሰረት ነዉ:: በታሪክ እንደሚታወቀዉ ሁሉ እኛ ጣሊያኖች በመሰደድ የመጀመሪያዎች ነበርን ዛሬ ግን የዉጭ አገር ዜጎች ስራ ለመፈለግ በራችንን በሚያንኳዋኩበት ባሁኑ ወቅት የማስተናገድ ችሎታችንም ያን ያህል ከፍተኛ መሆን አለበት:: ሁሉም የዉጭ አገር ዜጋ እንደወንጀለኛ መቆጠርና መታየት የለበትም:: በህጋዊ መንገድ ሰርቶ የሚኖር፣ ህጋችንን የሚያከብር የዉጭ አገር ዜጋ ሁሉ መብቱ ሊከበርለት ይገባል ያሉት ተስፋ የሚሰጥ ይመስለኛል::

ጥያቄ:- ... ባለፈዉ 21/12/2006 የጣሊያን ፓርላማ የ 2007 የአመት በጀቱን አጽድቋል:: በዚህ ህግ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጋን የሚመለከቱ ጉዳዮች ወይም አንቀጾች ካሉ በተለይ በጣሊያን ለሚኖሩ አንባቢያን ሊጠቅም ስለሚችል ባጭሩ ቢገልጹልን?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... አንዳንድ ጥቃቅን ጉዳዮች አሉበት ለምሳሌ የዉጭ አገር ዜጋን የስራና የመኖሪያ ችግር ለማቃለል ተብሎ የተወሰነ ያህል በጀት ተመድቧል፣ በቤት አገልጋይነት የዉጭ አገር ዜጋን ቀጥሮ የሚያሰራ ማንኛዉም አሰሪ ግለሰብ የግብር ቅነሳ ይደረግለታል፣ አዲስ ኮምፕዩተር ለሚገዛ ወይንም ያለዉን ለሚቀይር የዋጋ ቅናሽ ይደረግለታል፣ የያዘዉን አሮገ የቤት መኪና በአዲስ ለሚቀይር ድጎማ ይሰጠዋል፣ የግል ድርጅት ለማቋቋም ለሚፈልጉ አማካሪ ድርጅቶችን ይመድባል የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል:: በወረቀት ላይ ያሰፈሩት ተግባራዊ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ አንዳንዴ ህጎች ይጸድቁና ተግባራዊ ሳይሆኑ ይቀራሉና ተከታትሎ ዉጤቱንም ማረጋገጥ ያስፈለጋል::

ጥያቄ:- ... ለመሆኑ በጣሊያን ፓርላማ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጎች አሉ? ካሉ ቁጥራቸዉስ ምን ያህል ነዉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በጣሊያን ፓርላማ ዉስጥ በመጨረሻዉ ምርጫ የተመረጡት በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጋ በዜግነት ጣሊያናዊ የሆኑት ተመራጮች ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ:: ባልሳሳት አራት ወይም አምስት ቢሆኑ ነዉ:: ይህ የሚያሳየን በጣሊያን የዉጭ አገር ዜጋዉ በፖለቲካ የተጠናከረና የተደራጀ አለመሆኑን ነዉ:: ምንም በፓርላማ ባይመረጡም በየክፍለሃገሮችና በየማዘጋጃ ቤቶች ያስተዳደር ምርጫ በመካፈል የሚመረጡት በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጎች ቁጥር ግን እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፣ ይህም ያበረታታል ብዬ አምናለሁ::

ጥያቄ:- ... በጣሊያን አገር በግምት ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ የዉጭ አገር ዜጎች እንደሚኖሩ እንሰማለን በፖለቲካና በማህበራዊ ኑሮዉ ሙሉ በሙሉ የተካፈሉት ጥቂቶች ናቸዉ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በመጀመሪያ ባንድ አገር የፖለቲካና ማህበራዊ ኑሮ ሙሉ በሙሉ ለመካፈል የዚያን አገር ቋንቋ፣ ባህል፣ የኑሮ ዘዴ፣ እና የመሳሰሉትን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል:: አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከጣሊያን ዉጪ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ በመፈለግ ጣሊያንን እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ አድርገዉ ስለሚወስዱ ቋንቋውን ለማጥናትም ሆነ አልፎ ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ብዙም የዉስጥ ፍላጎት አይኖራቸዉም፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ኑሮዉ ተካፋይነታቸዉም እየቀነሰ ይመጣል:: አንዳንድ ጊዜ የቁጥር መብዛት ብቻዉን በቂ ሊሆን አይችልም:: በሌላ በኩል ደግሞ ከጣሊያን የመንግስታዊ አካል በኩል ለብዙ ጊዜ የዉጭ አገር ዜጎች ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቆይቷል፣ ችግሮች ከመከሰታቸዉ በፊት ፕሮግራም አይወጣም ይህ ደግሞ ለቁጥጥር አመቺ አይሆንም እንክርዳዱን ከስንዴዉ ለመለየትም ያዳግታል::

ጥያቄ:- ... የጣሊያን ጋዜጠኞች ብዙ ጊዜ ስለዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል ብቻ ሲጽፉ እናያለን የዉጭ አገር ዜጋዉ ሁሉ ወንጀለኛ ነዉ ማለት ነዉ ወይንስ ይህ ጉዳይ እንዴት ነዉ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... አዎን ጋዜጦች ለምዶባቸዉ ነዉ መሰለኝ የዉጭ አገር ዜጋዉን ሁሉ ከወንጀል ጋር ያዛምዱታል፣ ይህ በኔ ግምት የፕሮፌሽኒስት ወይም የባለ ሙያ ጋዜጠኛ ስራ አይደለም ምክንያቱም እየቆየ ሲሄድ ከፍቅር ይልቅ ወደ ጠብ ያመራል:: እዚህ ላይ አንድ የማስታዉሰዉ ነገር አለ ባለፈዉ ጊዜ አንድ የሴኔጋል ተወላጅ ለረፍት ባህር ሄዶ ከሌሎች ጋር ዋና በመዋኘት ላይ እንዳሉ አንድ ጣሊያናዊ ህጻን ይሰምጥና የሰመጠዉን ልጅ አድናለሁ ብሎ ገብቶ ሰምጦ ሞተ:: ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት ይህን ያህል አልተወራም ነበር:: እንደዚህ አይነት ተግባር ቢታይም ለህብረተሰቡ በተገቢዉ መንገድ አይቀርብለትም:: ይህ ብቻ አይደለም በጣሊያን ሰሜናዊ ክፍል ለፍተዉ የግል ድርጅቶች በመክፈት የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጎሳ፣ የቀለም ልዩነት ሳይሉ ጣሊያኖችንም ጭምር ቀጥረዉ የሚያሰሩ በትዉልድ የዉጭ አገር ዜጎች በብዛት እንዳሉ መዘንጋት የለብንም:: ይህ ደግሞ ከጠብ ወደ ፍቅር ሊያመራ የሚችል ትክክለኛ መንገድ ነዉ::

ጥያቄ:- ... በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?

ዶ/ር ዘለቀ:- ... በሺህ በሚቆጠሩ በተለያዩ ምክንያቶች ከትዉልድ አገራችን ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ “አንድነት ሃይል” መሆኑን ሳንዘነጋ በጋራ ችግሮች ላይ እኛን ከመሰሉት ሌሎች የዉጭ አገር ዜጎች ጋር መቀራረብና መነጋገር ይኖርብናል:: እያንዳንዱ ግለሰብ የሚያዉቀዉን ለሌላዉ ለማያውቀዉ ወገኑ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት አዉቆ ተገቢዉን ቢያንስ የሞራል እርዳታን መለገስ ይኖርበታል:: የማናዉቀዉን ጉዳይ ከሚያዉቁት ጠይቆ ከመረዳት ወደ ኋላ አለማለት፣ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጥ:: ...



giovedì

ከመሰለፍህ በፊት መሰለፊያዉን እወቅ


ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
በጣሊያን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት (permesso di soggiorno / carta di soggiorno) ለማሳደስም ሆነ አዲሱን ለመዉሰድ የሚያስችለዉን ማለትም ባለፈዉ ጊዜ የወጣውን አዲስ መመሪያ በተመለከተ ሰሞኑን ብዙ ሰዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ስልክ ደዉለዉ ይጠይቁኛል::
ጥያቄዎቹን ሙሉ በሙሉ በዚህ መድረክ ለመመለስ ጊዜ ቢያጥረኝም ለጥቂቶቹ መልስ ይሆናሉ በማለት የመመሪያዉን ይዘት ከዚህ ቀጥሎ አጠር ባለ መልኩ ለአንባቢያን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ:: በመጀመሪያ ደረጃ ከመሰለፍ በፊት ዬት መስሪያ ቤት ሄዶ መሰለፍ እንደሚገባ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል::
በጣሊያን ለመኖር የሚያስችል የዉጭ አገር ዜጎች ጉዳይ ሁሉም በፖስታ ቤት አይጠናቀቅም:: ይበልጡ አጅ በፖስታ ቤት ሲከናወን ጥቂቱ በፊት እንደነበረዉ በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ እንደነበረዉ ይቀጥላል:: አጉልና ከንቱ የማያልቅ ሰልፍ ተሰልፎ ጊዜና ጉልበት እንዲሁም ገንዘብን ከማጥፋት ሌላ የአእምሮ ህመም በሽታ ከመሸመት መጠንቀቁ ተገቢ ነዉና በተቻለ መጠን ጠይቆ ትክክለኛ መረጃ (እንፎርሜሽን) ማግኘት ያስፈልጋል::
.
በፖስታ ቤት ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ማሳደስ (permesso di soggiorno);
- ልጅ አስመጥቶ ማሳደግ;
- ጣሊያን ተወልዶ ወላጆቹ ሊያሳድጉት ያልቻሉ ልጅ;
- የማደጎ ልጅ አስመጥቶ ለማሳደግ;
- የፓስፖርት ለዉጥ;
- ስራ አጥ ስራ ፈላጊ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት እድሳት;
- የመኖሪያ ወረቀት ለአዉሮፓ ህብረት ዜጎች (carta di soggiorno cittadini U.E.);
- የመኖሪያ ወረቀት ለዉጭ አገር ዜጎች (carta di soggiorno cittadini stranieri);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት መቀየር (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (carta di soggiorno);
- ቤተሰብ;
- ቤተሰብ እድሜያቸዉ ከ 14 እስከ 18 አመት;
- የግል ስራ (lavoro autonomo);
- የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato);
- በተለያዩ ምክንያቶች የስራ ፈቃድ;
- ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato - stagionale);
- ጉዞ ወደ ዉጭ አገር;
- ሃይማኖት;
- የፖለቲካ ምርጫ;
- ትምህርት;
- ጉብኝት;
- የሙያ ማሻሻይ ስልጠና ወዘተ ...

በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- ንግድ ወይም ብዝነስ ነክ ስራዎች;
- ህክምና;
- እስፖርት ዉድድር;
- እርዳታና ማስተባበርያ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ;
- ህግና ፍትህ;
- ከ 14 አመት በታች እድሜ ያላቸዉ ልጆች;
- ከጣሊያን አገር ዉጪ ሰዉ በዋስትና ማስመጣት::

በዝርዝሩ ላይ ማብራርያ ካስፈለገዎት በሚከተለዉ የመገናኛ ዘዴ መጠየቅ ይቻላል::
zeleke_eresso@yahoo.it
Tel. 3395764139


martedì

ከኩዌስቱራ ወደ ፖስታ ቤት


ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
Bologna (Italy) 28/11/2006

በእጣሊያን አገር ለመኖር የሚያስችለዉን የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት (permesso di soggiorno e carta soggiorno) አዲሱን ለማዉጣትም ሆነ አሮጌዉን ለማሳደስን በተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መመሪያ ተላለፈ::
ካሁን ቀደም በፖሊስ - በኩዌስቱራ - ሲሰጥም ሆነ ሲታደስ የነበረዉ የመኖሪያ የፈቃድ ወረቀት ከሚቀጥለዉ ሰኞ 04/12/2006 ጀምሮ በፖስታ ቤት እንዲከናወን የእጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስትሩ በአለፈው ጊዜ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ:: በመሆኑም ፖስታ ቤቶች ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ተጨማሪ ማስተናገጃዎችን ለማዘጋጀት በመሮጥ ላይ ይገኛሉ:: ለዚህም ዉሳኔ ሊደረስ የተቻለዉ ከ 06/11/2006 ጀምሮ በፕራቶ፣ በአንኮና፣ በፍሮስኖኔ፣ በብርንድሲ እና በመሳሰሉት ጥቂት የእጣሊያን ትናንሽ ከተሞች የተካሄደዉ ጊዜያዊ ሙከራ ባስገኘዉ ጥሩ ዉጤት መሰረት ነዉ ይባላል::
.
ለማሳደስም ሆነ አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት:-
1) በአቅራቢያ በሚገኘዉ ማንኛዉም ፖስታ ቤት በመሄድ ፎርም መቀበል;
2) ፎርሙ አዲስ መጠየቂያ፣ ማሳደሻ፣ መቀየሪያ፣ ማስተካከያ፣ ወዘተ ለመሳሰሉት ይጠቀማል;
3) የመኖሪያዉ ፈቃድ ለስራ (ቅጥረኛ ወይም የግል)፣ ለቤተሰብ፣ ለትምህርት፣ ለቱሪዝም፣ ለሃይማኖት እና ለመሳሰሉት ሁሉ ይጠቅማል;
4) የሰራተኛ ማህበር ተወካዮችም (patronati) አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል;
5) ፎርሙ ተሞልቶ ፖስታ ቤት መረከብ አለበት;
6) ፖስታ ቤቱ ለአስረካቢዉ ደረሰኝ ይሰጣል;
7) ፖስታ ቤቱ የተረከበዉን ጥያቄ ወደ ኩዌስቱራ ይልከዋል;
8) ኩዌስቱራም መዝገቡን አጣርቶ የመጀመሪያ ጥያቄ ከሆነ ግለሰቡን ለአሻራ ይጠራዋል ነገር ግን ለማሳደስ ከሆነ ቀርቦ እንዲወስድ ይጠራዋል::

.

ይህ ቀላል ለዉጥ አይደለም ቀደም ተብሎ በየዜና ማሰራጫዎች በሰፊዉ መነገር የነበረበት ጉዳይ ነዉ:: እንደሚታወቀዉ የእጣሊያን መንግስት የዉጭ አገር ዜጋ ጉዳይ ሲሆን ሁሌ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይደል? ይህን ለዉጥ ስንቶቹ የዉጭ አገር ዜጎች ሰምተዉታል? ምን ያህልስ ተግባራዊ ይሆናል? ዉጤቱን ለማየት ያብቃን::

.

የክፍያ ጉዳይ ማንኛዉም ጠያቂ እያንዳንዱ € 30,00 ለፖስታ ቤት የአገልግሎት ዋጋ ይከፍላል:: ለቴምብር € 14,62; € 27,50 ደግሞ ለፎርም የመክፈል ግዴታ አለበት:: መመሪያዉ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከሰኞ 11/12/2006 መሆኑን በዚህ አጋጣሚ በጣሊያን ለሚኖሩ አንባቢያን መግለጥ እወዳለሁ::



lunedì

ሰሞኑን በጣሊያን ሚ/ምክርቤት የውጪ ዜጎችን በሚመለከት


03 12 06
በጣሊያን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰሞኑን የፀደቁትን የውጪ ዜጎችን የሚመለከቱ ሁለት አዲስ ሕጎችና የውስጣቸውን ደንብ ፍሬ ነገሮቹን ብቻ መርጠን ከዚህ በታች አስፍረናል። ሁለቱ ዋና ዋና አዲስ ሕጎችም በአለፈው የበጋ ወቅት በጠረቤዛ ላይ ለውይይት ቀርበው ከነበሩት መካከል ይገኛሉ። እነዚህም
1)የካርታ ዲ ሶጆርኖ
2)የቤተስብን ማስመጣት የሚመለከቱ ናቸው።
ከሚያፀድቋቸው ሌሎች ህግጋትና አንቀፅ ጋር በአንድላይ በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት ከላይ የተጠቀሱትንና ያፀደቁትን የሁለቱን አስቀድመን አጭር ይዘታቸውን እናቀርባለን።
.
Carta di Soggiorno - (ካርታ ዲ ሶጆርኖ)
1 - በጣሊያን ከ5 ዓመት በላይ የመኖሪያ ፈቃድ የነበረው ማመልከቻ ከአስገባ ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንደሚሰጠው እና ይህም በሁሉም የአውሮፓ ሕብረት ኣባላት ሀገሮች ውስጥ ሥራ የመሥራት ዕድል የሚክፍትለትና በኣባላት ሀገር እንደፈለገው የመዘዋወር ፍቃድ እንዲኖረው ያደርገዋል።
2 - ቤተሰቦቹን ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንዲኖራቸው ለማድረግ ማመልከቻ የሚሲያስገባ ከሆነ ቤተሰቦቹን በአስተዳዳሪነት የሚያስተናግድበት የመኖሪያ ቤት ሁኔታ በክፍለሀግሩ የተደነገገውን መመዘኛ ማሟላት አለበት። ይኸውም የሕብረተሰቡን የጤናአጠባበቅ ሥራዓት ይዞ የሚከታተልና ደንቡን የሚጠብቅ መሆን ሲገባው ይኸውም ግዴታውም ጭምር ሆኖ ይገኛል።
3 - ሌላው ደግሞ ይኸው መኖሪያ ቤት ለሕይወት አስጊነት የሌለው፣ በውስጡ መኖር የሚቻልበትን ሁኔታዎችን የሚያሟላ መሆኑን መረጋገጥ አለበት። ማሳሰቢያ
4 - ይህን ካርታ ዲ ሶጆርኖ ለማግኘት ተመኑ የተወሰነ የዓመት ገቢ እንዲኖረውና ለዚህም አስፈላጊውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርበታል።
5 - በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የነበሩ፣ በወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸውን እንዲሁም የሕብረተሰቡን ፀጥታን ያጎደሉና ከዚህ በፊት precedenza ያለባቸው ይህንን የcarta di soggiorno ፈቃድ ማግኘት አይችሉም።
.
Recongiungimento familiare (ቤተሰብን ለማስመጣት)
1 - ልጅ ያለው እድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ለማስመጣት ብዙ ማስረጃዎችን እንዲያሳይ አይጠየቅም። እንደገናም ወላጆቹን ለማስመጣት በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆን ይገባቸዋል። (65 ዓመት ...) ይህ ደግሞ ብዙ ጥያቄና ክርክር ይሚያስነሳ ይመስለናል። ለማንኛውም እዚህ ካስመጣ በኋላ (a carico suo) ወይም የአስተዳዳሪነቱን ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ መሆን አለበት።
2 - ከዚህ በፊት በመኖሪያ ቤት ስፋትና ጥራት ይወስን እንደነበረና ንገርግን አሁን ይህ ሁሉ እንዲቃለል ተደርጎ ASL የሚጠይቀውን requisiti ማሟላት አለበት
3 - በየክፍለሀገሩ የተተመነውን የዓመት ገቢ ለማሳየት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል።
4 - ልጅ ያለው ማንኛውም የውጪ ዜጋ እዚህ በአለው የጤና አጠባበቅ ስርዓትና ክትትል በማድረግ ግዴታውን እንዲወጣ መሆን አለበት።
5 - ጥገኝነት ጠያቂ ( refugiato ) ከሆነ የዓመት ገቢና የመኖሪያ ቤት የግድ እንዲኖረው አይጠየቅም። ነገርግን ፈልሶ የመጣበት ሀገር እና የጣሊያን የድንበር ስምምነት ወሳኝነት ሊኖረው ይችላል።

mercoledì

አሳዩን አትንገሩን


ዶክተር ዘለቀ እሬሶ
...... አንድ ጸሐፊ በቅርቡ የአገራችን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት “አሳዩን አትንገሩን” በሚል አርስት የሚከተለውን አስፍሮ ነበር:: በአለምም ሆነ በአንድ አገር ታሪክ ዉስጥ የአገር መሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች አዛዉንቶች፣ ህዝብና ሌሎች ሌሎች የሚፈተኑበት ልዩ ወቅት ይከሰታል:: ያም ወቅት አብዛኛዉን ጊዜ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ይሆናል:: ያን ችግር ለመፍታት በሚያደርጉት አዎንታዊ እንቅስቃሴ፣ ያን ችግር ለማባባስ በሚጫወቱት ሚና ወይም በሚይዙት የአያገባኝም ወይንም ደንታቢስነት ሚና ማንነታቸዉ ይለካል:: መልክቱ ባጭሩ ተግባራዊ እንሁን ማለቱ ይመስለኛል::
...... በኢጣሊያን አገር የሚኖሩትን የዉጭ አገር ዜጎች የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ ሰሞኑን ከምን ጊዜዉም በበለጠ የተለያዩ ወሬዎች ይነፍሳሉ አልፎም ይተረካሉ:: ይህ ዜና አዎንታዊ እንቅስቃሴ? ወይንስ ችግር የማባባስ ዘመቻ? መልሱ እንደፊደል ምርጫ ጥያቄ ሁሉም ሊሆን ይችላል::
...... የመጀመሪያዉ የዉጭ አገር ዜጋዉ ከገጠሙት የቢሮክራሲ ዉጣ ዉረድ እንዲላቀቅ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳይኖረዉ፣ የስራና የህክምና ችግሮች እንዳይገጥሙት ማለትም ግዴታዉን ተረድቶ መብቱ ተከብሮለት አምራች ዜጋ እንዲሆን አስፈላጊዉን ሁሉ ለማድረግ ቢያንስ የሚሞክሩትን አነስተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያጠቃልላል::
...... ሁለተኛዉ ደግሞ በሰዉ ቁስል እንጨት ስደድበት አይነት ነገር ነዉ:: የዉጭ አገር ዜጋዉን ከወንጀል ጋር በማጣመር ሁሉንም ወንጀለኛ በማድረግ የዉጭ አገር ዜጎች ገደሉ፣ ሰረቁ፣ አጭበረበሩ፣ ቀጠፉ፣ ደፈሩ፣ አቆሸሹ፣ ወዘተ በማለት የዉጭ አገር ዜጋዉ ከህግ ዉጭ እንደሆነና የተመቻቸ ኑሮ እንዳለዉ አስመስለዉ በማቅረብ እንዲያዉም ይባስ ብሎ የመንግስት እርዳታ ሁሉ የሚሰጠዉ ለዉጭ አገር ዜጋ ብቻ ነዉ በማለት የአገሬዉን ህዝብና የዉጭ አገር ዜጋዉን ለማጣላትና ለማጋጨት ከፍተኛ ቅስቀሳ በስዉር እየተካሓደ ነዉ::
...... ይህንንም ስል ሁሉም የዉጭ አገር ዜጋ ወንጀል አይሰራም ለማለት ፈልጌም አይደለም:: እንዲያዉም ሰርቶ ከመኖር ይልቅ ሀገ ወጥ በሆነ መንገድ ሐብታም መሆን እንደሚቻል መጥፎ ትምህርት በማስተማር ላይ የሚገኙም እንዳሉ ተስኖኝ አይደለም:: ታዲያ እንክርዳዱን ከስንዴ መለየት አስፈላጊ በሆነበት ባሁኑ ሰአት አብዛኞች የኢጣሊያን አገር የዜና ማሰራጫዎች የሚጽፉአቸዉ ጽሁፎችና አርስታቸዉ ከመለያየቱ የተነሳ ሕግ አክባሪዉንና ወንጀለኛዉን የዉጭ አገር ዜጋ እንኳን በአግባቡ ለይቶ ማወቅ አልተቻለም::
በጠቅላላዉ ለመዝጋት ያህል ሰሞኑን በአንዳንድ የኢጣሊያን አገር ጋዜጦች ላይ የዉጭ አገር ዜጋን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ አርስቶች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፣ ለዉጭ አገር ዜጋዉ ግን ምንም የተቀየረለት አንዳችም ነገር አይታይምና ወሬዉ በተግባር መተርጎም እንዳለበት የሚመለከተዉን ክፍል ከመጠየቅ ወደ ኋላ ማለት አይገባም::
...... ስለ ጽሁፉ አስተያየት ካለዎት zeleke_eresso@yahoo.it

lunedì

ITALIA: Il governo cambia che cosa si aspetta lo straniero?


(dr.Zeleke Eresso)
... Secondo la stima della Caritas-Migrantes nell' anticipazione del rapporto annuale sull'immigrazione, relativo al 2005, gli immigrati regolari presenti in Italia all'inizio di quest'anno hanno superato, seppure di poco, la quota dei 3 milioni.
... L'immigrazione in Italia è ormai un fenomeno strutturale e politico. Secondo molti studiosi del campo, più di tre milioni di cittadini stranieri risiedono regolarmente in Italia e la loro presenza, sia come lavoratori che come imprenditori, contribuisce in modo determinante allo sviluppo economico. Quasi mezzo milione di bambini stranieri stanno crescendo in Italia al fianco dei loro coetanei italiani e hanno tutte le carte in regola per diventare insieme a loro i cittadini di domani.
... Il cittadino straniero, regolarmente residente in Italia, partecipa alla vita civile, politica, economica e culturale del paese è una risorsa positiva, la base su cui costruire l'integrazione. Un impegno che investe tutti gli aspetti della società e richiede quindi un approccio unitario e significativo ma non soluzioni superficiali, teoriche e complicate come spesso purtroppo accade.
... Quale è realmente l’intenzione del nuovo governo di centrosinistra in materia di immigrazione? per il momento non si sa nulla e l’unica cosa certa è qualche dichiarazione di principio, generico, da parte di qualche componente dell’attuale maggioranza. Nelle ultime settimane si è parlato molto di modifiche sostanziali, tanto attese dagli stranieri residenti in Italia, della legge Bossi-Fini.
... Il problema ormai cronaca dell’immigrazione non si risolve solo cambiando o modificando l'attuale politica sull'immigrazione che è rigida e "discriminatoria", ma dando priorità ai bisogni principali delle persone che lavorano e producono nella società.
Che cosa occorre fare fondamentalmente? andiamo per ordine:
* Il diritto di voto agli immigrati: un tema molto delicato, politico, “non esiste inclusione sociale senza partecipazione alla vita amministrativa nella città in cui si vive” visto che non si paga solo le tasse, come giusto che sia, ma si partecipa alla crescita collettiva;
* Questione di cittadinanza: le nuove regole di cittadinanza sono l’adeguamento di un paese alle regole di civiltà quindi occorre una riforma della quale fanno parte vecchi e nuovi cittadini;
* Regolarizzazione: in primo luogo occorre una verifica sulle richieste di regolarizzazione con l’obiettivo di regolarizzare coloro che svolgono attività lavorativa sotto forma di usa e getta.
... In conclusione, se si comincia a dare delle risposte adeguate, al meno a queste priorità, vorrà dire che lo straniero non è un oggetto da usare quando serve e gettare in un altro momento, ma è una persona che lavora e vive in un paese normale e civile.