lunedì

የኢትዮጲያ ባህላዊ ማህበር በኤሚሊያ ሮማኛ


ይህ ማህበር የተመሠረተው እ.ኤ.አ. በ1994 ዓም ነው፡፡ አመሰራረቱና ድርጅታዊ ቅርፁ በሚገባ የተዋቀረና የተማከለ እንደነበረ ከማህበሩ ጋር ቅርበት ያለው ሁሉ የሚያውቀው ነው:: ዓላማዎቹ በኤሚሊያ ሮማኛ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በማህበራዊና በባህላዊ ነክ ጉዳዮች አማካኝነት መሰባሰብንና መቀራረብን ለመፍጠር ነበር። በተመሠረተ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ ለዚህ ማህበር መጠናከር በርከት ያሉ ግለሰቦች ጥረት ያደርጉ ነበር። ነገር ግን በተግባር ለመተርጎም የግለሰቦች መልካም ፈቃድንና የህብረት ስራን የሚጠይቅ ስለነበር ከዚህም በላይ በተወሰኑ ሥራዎች ላይ የተባባሪዎች ቁጥር በማነሱ የተጠበቀውን ውጤት አላገኘም። በሥራ ክፍፍል ተደርጎ ሁሉም የድርሻውን ቢያደርግና ትብብር ቢያገኝ ውጤት ይኖረው ነበር ለማለት ነው፡፡ ... ይቀጥላል ........

.
የመጨረሻው የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ በተካሄደበት ጊዜ በቁጥር 9 የሚሆኑ አባላት ተመርጠው ነበር። ከእነዚህም ውስጥ ብዙኃኑ በማህበሩ የሥራ አስኪያጅነት አባላት የቆዩ ነበሩ። በአሁኑ ጊዜ በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የምንገኘው ከዚህ በታች ስማችን የተቀስነው ነን፡፡
1. ወ/ሮ ጥሩነሽ ----------------- ሊቀመንበር
2. አቶ ሴባስቲያኖ ባርቶሎትታ ---------- ምክትል ሊቀመንበር
3. አቶ አብርሃም ዘውዴ -------------------- ፀሃፊ
4. ወ/ት ሙሉመቤት ----------------- ቴሶሪየሪ
5. አቶ ታደለ እጅጉ ---------------------- አባል
6. ወ/ሮ መቅደስ ---------- ባህልና ሕዝብ ግንኙነት
7. አቶ ደረጀ አባተ --------------------- አባል
8. አቶ ማርኮ ቤሊስትሪ ----------- ባህልና ሕዝብ ግንኙነት
9. ----- .....................
... (ይቀጥላል) ........
.
በ29-01-2005 ...
ሶስት ሆነን (ሙሉመቤት፣ አብራሃም፣ መቅደስ) በአጋጣሚ ምክንያት ስለ ስማህበሩ አንስተን ጭውውት ከፍተን ...
" በአለፈው ዓመት ውስጥ የተደረገ ስብሰባና የተሰራ ነገር የለም፡፡ የጉዳዩ ባለቤቶች ስለሆንን እጃችንን አጣጥፈን እያወራን ብቻ መቀመጡ ከሞራልና ከስነምግባር አንጻር አሳፋሪ አይደለም ወይ? ለምን የአቅማችንን እንኳን አንድ ነገር አናደርግም? ሃላፊነትን ይዘን የሙጢኝ ለማለት የምንፈልግ ይመስልብናል፡፡ እኛም ብንሆን በራሳችን መካከል ለውጥን የምንሻ ስለሆንን አስፈላጊ ከሆነ አዲሶች እንዲተኩበት በማድረግ ተከታዮችም ልምድ ማካበት እንዲኖራቸው ማድረግም አለብን " ...
በማለት እራሳችን እየተቸን እና እየተወቃቀስን በሶስታችንም በኩል የሚንጸባረቅ አንድ የውሳኔ ሀሳብ ወሰንን፡፡ ምንም እንኳን ህጋዊ የማዕከል ስብሰባ ባይሆንም (ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በቁጥር ከግማሽ በታች ስለነበርን) አጋጣሚው ላይ ያልነበሩት የኮሚቴው አባላት በሙሉ በሀሳቡ የሚስማሙ መሆኑን ስላወቅን ሌላ ህጋዊ ስብሰባ ተጠርቶ አንድ ውሳኔ ለማድረግ ወሰንን፡፡
.
በዚሁ ዕለት ከተነሱት ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ነበሩ...
ማህበሩ ሙሉ ሥራውን እንዲጀምር ከተፈለገ ከሁሉም በፊት ግን መደረግ ያለበት በአሁኑ ጊዜ የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ በመነጋገርና በመመርመር የሚፈለገውን እርምጃ መውሰድና መፍትሄ ሃሳብ መገኘት አለበት፡፡ ስለዚህም ...
1- ከማህበሩ አባላት ውስጥ ግዴታቸውን የሚወጡት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ውስጥም ትንሽም እንቅስቃሴ ቢሆን የሚከናወነው በተወሰኑ አባላቶች ብቻ ስለሆነ ሃላፊነትና የስራ ጭነት አስከትሏል፡፡ ከላይ እንድተጠቀሰው ይህም ሊፈጠር የቻለው ከማህበሩ ኣባላትም ቢሆን ምንም አይነት ትብብርና እንቅስቃሴ ስለማያገኙ ነው፡፡ ስለዚህም ከልብ በመስራት ላይ የነበሩት የኮሚቴው አባላት የማህበሩን እንቅስቃሴና የስራ ዘርፍ ለመሸፈን የሰው ሃይል ስለሚያስፈልጋቸው ይህንንም ሃይል መጨመርና ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከአባላት ትብብርና የስራ ተሳትፎ መኖር በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ላይ የስራ መደራረብ እንዳይፈጠርበት ስለሚረዳ ...
2- በተለያዩ ምክንያት አገልግሎት ለመስጠትም ሆነ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት የማይችሉ የኮሚቴዎች አባላቶች ማለትም በጊዜ እጥረት፣ በሥራ፣ በቤተሰብ፣ የመኖሪያ አድራሻቸው ሩቅ ለሆኑም ሆነ በአዳዲስ ተመራጮች መተካት ስለሚያስፈልግ ...
3- በአሁኑ ጊዜ የማህበሩ ሊቀመንበር በተወሰኑ ምክንያቶች ሃላፊነቱንና ሥራውን ማካሄድ ስለማይችሉና በፍቃዳቸው ቦታውን መልቀቅ ስለሚፈልጉ ሌላ ሰው እንዲተካበት ምርጫ ማካሄድ ግድ ስለሆነ ...
4- በማዕከሉ አመራር የአባላት ቁጥር የጎደለ በመሆኑ ያሉት ክፍት ቦታዎችን የግድ መሸፈንና መመሟላት ስላለበት ማስመረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ...
5- "ማህበሩን ለማራመድ አንዳንዱን የአመራር ቦታ በአዳዲስ ተመራጮች ይተኩበት" የሚል አሳብም ስለቀረበ... ወዘተ ...
.
እነዚህንና የመሳሰሉትን ላይ በመነጋገር ለስራችንን አቅጣጫ የሚያስይዙ አንዳንድ እቅዶችን ነድፈን በማውጣት በአጀንዳ ይዞ ምክር ለማድረግ ወሰንን፡፡ ከእነዚህም እቅድ መካከል በተቻለ መጠን ከተለያዩ አቅጣጫወች ሃሳቦችን እንዴት ለማግኘት እንደሚቻል ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጥሩ ሃሳብ ሊያመነጩ ይችላሉ፣ ቅን የሆነም ሃሳብ ይኖራቸዋል፣ የማህበሩ መሥራቾችም ስለሆኑ በማህበሩ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲገነዘቡልን ይረዳናል ብለን ያመንባቸውን እንግዶች የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ጠርቶ ለማነጋገር ወሰነ፡፡
.
ፈቃደኛ የሆኑትን እንግዶች በመጋበዝ ያደረግናቸው ተከታታይ 3 ስብሰባዎችና የተወያየንባቸው አጀንዳዎች በከፊል
- 05/02/2005 (ወ/ት ሙሉመቤት፣ ወ/ሮ መቅደስ፣ አቶ አብርሃም፣ አቶ ደረጀ፣ አቶ ታደለ፣ ዶ/ር ዘለቀ፣ አቶ አሻግሬ)
- 19/02/2005 (ወ/ት ሙሉመቤት፣ ው/ሮ መቅደስ፣ አቶ አብርሃም፣ ዶ/ር ዘለቀ፣ አቶ አሻግሬ፣ አቶ ደረጀ፣ አቶ ታደለ)
- 12/04/2005 (ወ/ት ሙሉመቤት፣ ወ/ሮ መቅደስ፣ አቶ አብርሃም፣ ዶ/ር ዘለቀ፣ አቶ አሻግሬ፣ አቶ ደጀኔ )
.
በመጀመሪያው ስብሰባ ላይ ከሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ውስጥ በቁጥር አራት የሚሆኑትና ከተጋበዙት እንግዶች መካከል ደግሞ በቁጥር ሶስት የሚሆኑት ተገኙ። የተገኙት እንግዶች በቁጥር ያነሱ ቢሆኑም የበሰለ አስተሳሰባቸውና ምክራቸው ለሥራችን ጠቃሚና መሰረት ጣይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በአጠቃላይ ሥራችንን እንድንቀጥልበት የሚያደርገው ዋናው ምክንያት የነዚህ ጥቂት ሰዎች በተደረጉት ሦስት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ሊሆንልን ችሏል፡፡ ከሃሳብ መስጠትም አልፎ አይዟችሁ፣ በርቱ እያሉ ድጋፋቸውን፣ ምክራቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ስለለገሱን እጅግ በጣም የሚመሰገኑ ናቸው፡፡ "ወደፊትም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የሚችሉትን ከማድረግ ወደኋላ አንልም" በማለት ቃላቸውን ሰጥተውናል፡፡
.
በስብሰባው የተገኙት እንግዶቻችን ካቀረቧቸው ሃሳቦችና አስተያየቶች ውስጥ ...
* በሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ውስጥ ሆነው ማህበሩን የሚያንቀሳቅሱት ግለሰቦች ጊዚያቸውን መስዋዕት በማድረግ ለማህበሩ ለሚያደርጉት ትልቅ ሥራና ተሳትፎ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ዓላማዎቹን ከሞላ ጎደል ለማሟላት ይሆናል በሚሉት መንገድ ስራውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል:: እንግዲህ መልካም የሰሩት ሁሉ መመስገን ይገባቸዋል:: ማንም ሰው እንዲረዳው የሚፈልገው የማህበሩን መደራጀት በመሆኑና ይህም ከአባላቱ ሃሳብና ምኞት ጋር ግንኙነት ያለው ነው፡፡ ማንኛውም ነገር ሂደቱ የሚሳካው ከጅምሩ ጥሩ ሲሆን ነው፡፡ በመሆኑም ለአንድ ማህበር ህልውና የአመራር ሚና ወሳኝነት የሚያጠያይቅ አይደለምና ተባብሮ ለመስራት እንድያመች አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ውስጣዊ የሆነ ያደረጃጀት ለውጥ በማድረግ የኮሚቴው ይስራ ቅንጅት እንዲሻሻል ማድረግ ይቻላል፡፡ በሥራ አስኪያጅነት ብዙ ጊዜ መቆየት ደግሞ መዘናጋቶችን ሊፈጥር ይችላል። ከዚህም በላይ በማሀበሩ ውስጥ የስራ አስኪያጅ ለውጥ ማድረግ ማለት ማህበሩ በእንቅስቃሴው እየተዳከመ የመምጣቱን ሁኔታ አባላት ስለተገነዘቡት ያው እንዲነቃቃና እንዲንቀሳቀስ ለውጥ ለማድረግ ሊሆን ይችላል:: ሀላፊነትንም ይዞ ብዙ መቆየት ማህበሩን የግል ንብረት ስለሚያስመስለው ለሌሎች በበጎ ፈቃደኝነት መልቀቅና ሌሎች ደግሞ በአዲስ መንፈስ ስራውን እንዲያካሂዱት ማድረግ ይኖርበታል:: ይህንንም ማድረግ "ማህበሩ የከሌና የከሌ ነው እኮ!" የሚባል ጉዳዮች እንዳይፈጠር ይረዳል፡፡
* የዚህ ኮሚቴ ስራ አስኪያጅ ሆኖ መመረጥ ማለት ለኢትዮጵያዊያን ማህበር በነፃ ለመስራት ሃላፊነት መውሰድ ማለት ነው፡፡
* አንድ የኮሚቴ አባል ሲመረጥ መጀመሪያ ፍላጎቱ ቀጥሎም ማህበሩን በነፃ ለማገልገል ሃላፊነት መውሰዱ ሲረጋገጥ ቢሆን ይጠቅማል፡፡
* አመራረጡ ግልፅና ዲዎክራሲያዊ ይሁን፡፡
* አንድ መሪ ያለፈቃዱ መመረጥ የለበትም፡፡
* ፍላጎት ያለው ሰው ቢመረጥ ጥሩ ነው፡፡ ችሎታ ከፍላጎትና ከሃላፊነት መውሰድ በኋላ የሚመጣ ነገር ነው፡፡ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው በቅን ልቦና ጠለቅ ብሎ ካሰበ ነገሮችን ይፈጥራል፤ አዲስ ችሎታም ያዳብራል፡፡
* የኮሚቴው ቁጥር መብዛት ሳይሆን ጥራት ላይ ቢያተኩር፡፡ ስለዚህም ቁጥሩን መቀነስ ...
* ተሳታፊ ያልሆኑትን መሪዎች መቀየርና መተካት፡፡
* ተገቢ የሆነውን ሰው አመራር ላይ ማስቀመጥ፡፡
* በአመራር ኮሚቴ ውስጥ የአዲስ መጪዎችና የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ፡፡
* ሴቶች አመራር አባላት ውስጥ ቢጨመሩ ማህበሩ የበለጠ ሊጠነክር ይችላል፡፡
መሪዎቹ እርስ በርሳቸው ቢተባበሩ የበለጠ ውጤት ያመጣሉ፡፡
* አዳዲስ ዜጋዎች በተሳትፎ እንዲያገለግሉ የመምረጥ ሁኔታ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
ከዚህም ሌላ ደግሞ በሁለተኛውና በሦስተኛው የስብሰባ ቀኖች እንዲሁ ተገናኝተን ወደፊት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ነጥቦች ላይ በመወያየት የሚከተሉትን በአጭሩ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
.
1- የኮሚቴው ይስራ ቅንጅት እንዲሻሻል፡፡ የስራ ቅንጅት ስንል የማህበሩ ኮሚቴዎች የውስጥ ስራ ክፍፍልና እያንዳንዱም የኮሚቴ አባል የስራውን ድርሻ ሃላፊነት መውሰድና መወጣት ማለታችን ነው፡፡
2- የማህበሩን ሂደት በየተወሰኑ ጊዜዎች ለኢትዮጵያዊያን ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን ስለ ማህበሩ ሂደት ያላቸው ዕውቀት ዝቅተኛ ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡
3- ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ ከIstituzione, ከRegione, Comune, Provincia etc... ወዘተ ያለውን raporto በመገምገምና በማስተካከል ወቅታዊ ሂደቱን ከቆመበት ቦታ እንዲጀምር .... ..... ...
4- በግለሰብ ደረጃ የተለያዩ እንቅስቃሴና iniziative ሊያደርጉ የሚሹትንና የሚያደርጉትን መንከባከብ (ቋንቋን የሚያስተምሩ፣ ዝግጅቶችን የሚያቀርቡ፣ ባህላችንን አጉልቶ ለሚያሳዩ፣ በተለያዩ ችሎታቸውና ሙያቸው፣ በፈጠራዎች፣ በጉልበታቸውና በሞራላቸው ለመሳተፍ የሚፈልጉትን ወዘተ... ) ትብብርና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
5- ማሕበሩ ውስጥ ተመዝግበው ያለባቸውን ግዴታ ለሚወጡት በሙሉ ሙሉ መብታቸው እንዲጠበቅና በአስፈለጋቸው ጊዜ በማህበሩ መመሪያ መሠረት ትክክለኛው አገልግሎት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
6- አባል መሆንና አለመሆን ልዩነቱን(ግዴታውን፣ መብቱን፣ ጥቅሙ ንና ጉዳቱን፣ ወዘተ ...) ማስረዳት፡፡
7- የማህበሩን የውስጥ መመሪያ ደንብና ሕግ (STATUTO) አባላት የሆኑት ሁሉ እንዲረዱት ማድረግ። የውስጡን ደንብና ዓላማ በአለማወቅ "ማሕበሩ ለእኔ እንዲህ አላደረገልኝም" የሚባለው እንዳይመጣና ያለመግባባት እንዳይፈጠር በደንብ እንዲረዱት ማድረግ፡፡ ለዚህም ነው አሳጥሮ ወደ አማርኛ መተርጎም ያስፈለገው፡፡ በእርግጥ ዋናው መመሪያና ደንብ የተወሰኑ ገጾች ያለውና በጣሊያንኛ መሆን ይገባዋል፡፡ ነገርግን ለአባላት እንዲስጥ የሚደረገውን በአጭሩ በአንድ ገጽ ላይ ጨምቆ በአማርኛ መተርጎም፡፡ መተርጎሙ እና አሳጥሮ ማቅረቡ የማሕበሩን ዓላማ በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡
8- አባላት በማሕበሩ ያላቸው እምነት የበለጠ እንዲሆን ሂሳብ ነክ ነገሮችንና አስፈላጊ ወይም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው በማቅረብ ማሳወቅ፡፡
9- ለማህበሩ ከኪሳቸው የሚያውጡትና የሚሠሩትን ሰዎች (ቤንዚን፣ ስልክ፣ ጊዜ መስዋዕት ማድረግ፣ ወዘተ ...) ትክክለኛ የሆነ ድጓም እንኳን ባይደረግ ነገር ግን አገልግሎት ስለሚያደርጉ ብቻ ከምስጋና ሌላ ከአንዳንድ የማህበሩ መዋጮ ነጻ እንዲሆኑ ማድረግና ግዴታቸውን እንደሚወጡት የማህበሩ አባላት እኩል የሆነ መብትና ሙሉ አገልግሎት እንዲኖራቸው፡፡
10- በወቅቱ የሚነሱና ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎችን መከታተልና ሌሎችን በማስረዳትም ሆነ ከእነሱም በመረዳት መማማር ይቻላል፡፡
ለምሳሌ
* ለችግረኛ ስደተኞች አገልግሎት እንዲያገኙ informazione እና ልችግራቸው መፍትሔ እንዲያገኙ የሚረዳ ንዑስ ኮሚቴ፣
* የበጎ አድራጊዎች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ፣ sindacal የሆኑ አገልግሎትና መብት ... ፣ የጤና፣ የሕግ፣ ... አገልግሎት informazione እና ፣ የሽምግልና ኮሚቴ (መቀያየምና መጣላት ሲደርስ ይቅር ለማባባል፣ ለማስታረቅ) ወዘተ ...
* ማህበሩ ፕሮግራሞቹን ሁሉ በተግባር ቢያሳይ አዲስ አባላትን ሊስብ ይችላል፡፡
* ስለማህበሩ ጥቅምና እንቅስቃሴ በማብራራት አባል በመሆን ያላቸውን መብታቸውንና ግዴታቸውን ማሳወቅ፡፡
* ማህበሩ በብዙኃን ዘንድ እንዲታወቅ ቅስቀሳና ማብራሪያ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ የሰማው ላልሰማ እንዲነግር በማድረግ፣ ወረቀት በመበተን፣ የተለያዩ comunicazione በመጠቀም ፡- ደብዳቤ፣ ስልክ፣ እሜል፣ መረበ-ገፅ (internet) ...
* አሁንም ከቦሎኛ ውጪ ለሚገኙ አባላት ያለውንና የሚደረገውን እንዲያውቁና እንዲገነዘቡ ለማድረግ በተወካዮቻቸው አማካይነት ግኑኝነትን ማድረግ፡፡ ተወካዮች በሌሉበት ቦታዎች ሁሉ በቁጥር ሁለት እንዲኖር ማድረግ፡፡
* የስብሰባ ቀጠሮ ሲደረግ አብዛኛዎቹ (ከግማሽ በላይ) በሚፈልጉበት ቀንና ሰዓት እንዲሆን መሆን አለበት።- ኮሚቴው በአዲስ መንፈስ ተቻችሎ ለመስራትና ከነበረው ኮሚቴው ጥፋቶች ከአሉ አርሞ ለማለፍ መሆኑን አጥብቀን እንገልጻለን። በአዲስ መንፈስ ለማካሄድ የሚያደርገው ጥረት እንቅፋት እንዳይገጥመው
* በድምፅ ብልጫ የሚወሰኑ ጉዳዮች ላይም ብዙ እንዳይንዛዛ ፍሬ ነገሩን ወስዶ ችግሩ እንዲቃለል ማድረግ
* አዲሱ ኮሚቴ በመንቀሳቀስ ማህበሩን ሕጋዊና ህልውና እንዳለው ሆኖ መቀጠል አለበት፡፡
* በስደት ጥያቄ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ማህበሩ መፍትሔ እንኳን ባያገኝ ችግሮቻቸው እንዲቃለል ማህበራዊ ትግሎች ላይ በመሳተፍና ድምጽን በማሰማት እንዲቃለል ጥረት እንዲያደርግ (እስከዛሬ ግን ይህ ሁኔታ አልነበረም::)
* አባሎቹም በተወሰኑ ጊዜያት ሊታደሱ የሚችሉ ፎቶ ያለበት የመታውቂያ ደብተር ይኖራቸዋል::
* ከአሁን በፊት ያልተደረጉና አዳዲስ አሠራሮች ይጠቅማሉ ከተባለ እንዲፈጸም መሆን አለበት::
* የፈረንጆችም ሆነ የእኛ ዓመት በዓላት (የክርስቲያንም ሆነ የእስልምና ኃይማኖት) ሲያከብሩ የመልካም ምኞትን ይገልፃል:: እነዚህንም በዓላቶች ጊዜውና ቦታው ከፈቀደለት በሚመቸው ሁኔታ ሊያከብር ይችላል፡፡
* የኮሚቴው ሕጋዊ አካልነት እስከሚቀጥለው ምርጫ ጊዜ በአመራር ይቆያል:: የአመራር አባላት ምርጫ የሚካሄደውም በዋናው የአባላት አጠቃላይ ስብሰባ ተጠርቶ በአባሎች መራጭነትና ተመራጭነት ይሆናል::
* ሌላው ደግሞ የማህበርን ዓላማ ለግል፣ ለቡድን፣ ለድርጅት ለጥቅም ለማዋል በሚደረግ የግለሰቦች ጥረት መካከል ስህተት እንዳይሠራና እንዳይፈጠር፣ የማህበሩን ስም ማንም እንዳይጠቀምበት ማድረግ የሁሉም አባላት ግዴታ ነው:: የግል ጥቅምን በማህበር አሳቦ ለማራመድ እስካልተፈለገ ድረስ የሚሰራ ሁሉ ሊሳሳት ይችላል:: እንዚህንም ስህተቶች በየጊዜውና ወዲያው በማረም ወደፊት ይቀጥላል፡፡
* ማህበሩ የፖለቲካ ድርጅት አገልጋይ ነው እንዳይባልና አባላትም ጥርጣሬ እንዳያድርባቸው በቅርቡ ሆነው የሚከታተሉት ታዛቢዎቹ የራሱ አባላት ናቸው፡፡ ከማንም የፖለቲካ ፓርቲ መዳፍ አይንተራስም:: ከፖለቲካ ነፃ መሆን ማለትም ከፓርቲዎችና ከመንግስት ተፅእኖ የሚያገልለው መሆኑ ነው:: ከፖለቲካው ብቻ ሳይሆን ከዘርና ከኃይማኖትም እንቅስቃሴ ነፃ መሆኑን እያረጋገጠ ይሠራል::
* ጥሩዎቹ ነገሮች ባንዲት ነገር ጉድለት ምክንያት መፍረስ የለባቸውም፡፡
* ከእህት ማህበራት ጋር መነጋገርና ሃሳብ መቀያየር ይጠቅማል፡፡
* ለወደፊት ጥናት በማድረግ የሰውን ፍላጎት ለማወቅ መሞከር ጥሩ ነው፡፡
.
ማህበር ማለት ማንኛውም አይነት የጋራ ግብ የሰበሰባቸው አባሎች ውዴታዊ የኅብረት ህላዌ ነው። አላማውም አካሉ ለሆኑት አባሎቹ ጥቅም ባለማቋረጥ መሥራት ነው። የማህበርተኞቹን ግብና መሠረታዊ ጥቅሙ ዓላማ ግብሩ እንድሆን ያደርጋል። ማህበሩም ይኖር ዘንድ አባላቱ ለሕብረቱ የሚለግሱት አስተዋጽኦ መኖር አለበት። አባላት ምንም አይነት አስተዋጽኦ የማያደርጉ ከሆነና ወይም ማህበሩ የሚያስተባብርበት ምክንያት ከሌለው መንምኖ ይቀራል።

venerdì

ንዑስ ኮሚቴዎች


1 - የመጽሔት እንዴት ሰነበተች
የኢትዮጲያ ባህላዊ ማህበር ቤኤሚሊያ ሮማኛ በ2001 ዓም በየሁለት ወሩ አዘጋጅቶ የሚወጣ መጽሔት ማተምና ለአባላት ማደላደል ጀምሮ የመጨረሻውንና ስድስተኛውን ቁጥር አውጥቶ እንደቆመ ቀረ፡፡ ከዚህም በኋላ ምን ላይ እንደደረሰ ማወቅ ለሚሹት የግድ መልስ መስጠት ተገቢ ነው፡፡
.
ብዙኃን ተካፍለው አስተዋጽዖ ያደርጋሉ የሚል እምነት ስለነበረን ... ለሕትመት የሚደረገውን ወጪና ለስርጭት ወደፊት እራሱን የሚችል ስለሆነ ለመጀመር የግድ የተወሰነ ወጪ ስለሚኖረው ከማሕበሩ የተወሰነ ገንዘብ ወስዶ ሥራው ሊጀመር ይቻላል በሚል ተወያይተን ወሰንን፡፡ በመጀመሪያም ይህንን ለማድረግ ህጋዊ የሆነ ንዑስ ኮሚቴ (redazione) እንዲኖረው አደረግን። የኅትመት ኃላፊነቱ የተወሰነ እንዲሆን ብለን በቦሎኛ ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 7089 - 08/02/2001 በጋዜጦች ... በአልቦ ሕጋዊነት እንዲኖረው አደረግን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ገንዘብ ወጪ ተደረገ፡፡ ከዚያም አንባቢያን በተወሰነ ክፍያቸው በconto corrente postale (Bolettino) አማካኝነት እየከፈሉ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ሌላ ወጪ ተደረገ፡፡ የመጀመሪያዎቹን 3 እትሞች (ቁጥር 1/2/3/)ን ሁሉም እንዲያውቁልን ብለን በነፃ ካደላደልን በኋላ የመጨረሻዎቹን 3 እትሞች (ቁጥር 4/5/6)ን መላክ ስንጀምር እስከ መቶ ለሚደርሱ ክተላከላቸው ውስጥ በቁጥር 12 የሚደርሱ አባላት ብቻ abbonati ሆኑ፡፡ ለመጽሔቷ እድምተኛ የሚሆኑት በቁጥር ይጨምራሉ በሚል እምነት አሳትመን የምናወጣው በቁጥር አስከመቶ ይደርስ ስለነበረና ያም ብዙ ወጪ ስለነበረበት መጽሔቷ የተላከላቸውና የደረሳቸው ምንም አይነት ክፍያ ባለማድረጋቸው የሕትመቷ መቋረጥ አንዱ ምክንያት ሆነ፡፡ ዓመታዊውን ክፍያ አጠናቀው የከፈሉት 12ቱ .... ደግሞ የደረሳቸው ሦስት እትም ብቻ ነው፡፡ .... (ይቀጥላል ... )
.
ዋናው የመጽሔት ዓላማም ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች የተዘገቡት ነበሩ፡፡
* የመወያያ መድረክ በመሆን ልጆቻችንና ወንድሞቻቸን እህቶቻችን ለዚህ የውጪ ሀገር ኑሮ ለማዘጋጀት
* በውጪ ሀገር ስንኖር ሊያጋጥሙ ን በሚችሉ የጋራ ችግሮች ላይ በመተባበርና በመረዳዳት ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍታት እንዲቻል
* በምንኖርበት በጣሊያን ሀገር ህግና ደንብ መሠረት በዜጎች እኩልነት መርህ ላይ በመመሥረት የኩልነት መብቱን የሚጠበቅበትን መንገድ መዘርጋት እንዲቻል
* የኢትዮጲያን የባህል፣ ልምድ፣ የኑሮ ሁኔታና የመሳሰሉትን በምንኖርበት አካባቢ ማሳወቅ እንዲቻል
* ከአካባቢያችን ውጪ በተለያዩ ሀገሮች ከሚኖሩ አኢትዮጲያዊያንና ሌሎች የውጪ ሀገር ዜጎች ጋር ሃሳብ ለሃሳብ የመለዋወጥ ግንኙነት እንዲኖር
* የታሪክ ዘገባዎችን በአስተናጋጁ ሀገር ቋንቋ፣ እንዲሁም የአማርኛ ፅሁፎችን ቅኔዎችን፣ ግጥሞችንና፣ ማንኛቸውንም ቁም ነገር አዘልና ቀልዶችን ወዘተ ... ለአንባቢያን ለማቅረብ
* የኪነጥበብ፣ የስፖርት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና ለአደባባይ እንዲበቁ ማገዝ ...እንዲሁም ሌሎችም ... ... ... (ይቀጥላል)
.
2 - የእርዳታ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ
በአለፈው 2003 ዓም በሃገራችን ሰፊና አሰቃቂ ለነበረው በረሀብ የተጋለጡትን ወገኖች ለመርዳት እዚህ ያለነውን አሰባስበን ግዴታችንን ለመወጣት የእርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም ተደርጎ ነበር፡፡ እንግዲህ በወቅቱ ከነበረን ውይይትና ወገናችንን ለመርዳት ካለን ሙሉ ፍላጎት በመነሳት “ለወገኖቻችን እንድረስላቸው” በሚል ግብታዊ (spontaneous) በሆነ መንገድ ተሰባስበን ገንዘብ ማዋጣታችንና በማህበሩም አማካይነት የሙዚቃ ምሽት ተደርጎ ገንዘብ ማሰባሰባችን የታወቀ ነው፡፡ ይህንን የእርዳታ ማሰባሰብ ሁኔታ ለማካሄድ በቁጥር 3 አባላት የያዘ ጊዜያዊ የእርዳታ አስተባባሪ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ የፈጸማቸውን ጉዳዮች በሚመለከት ደግሞ በተደረግውን ከፍተኛ ትብብርና በሚያኮራ መንገድ ደምድሟል፡፡ ነገር ገን ከሚመለከተው ክፍል የምስጋናም ሆነየደርሶናል ዜና ማንኛችንም አልሰማንም፡፡ ይህንንም በሚመለከት ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴው የሚያቀርባቸውን መግለጫዎችን ለመስማት ብዙሃን አባላቶች የሚሹት ሆኖ በመገኘቱ.. ማብራሪያዎችን ቢሰጥበት ጥሩ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወደፊት ይህ ንዑስ ኮሚቴ ሌሎች ተመሳሳይና የተቀደሱ ሁኔታዎችን ለማድረግ ሃሳብ ከአላቸው ... (ይቀጥላል ...)

martedì

ስለ ማሕበሩ ያለንን ዕውቀት ማስፋት


በተለምዶም ይሁን በተፈጥሮ በማህበር ሆኖ አንድን ነገር በጋራ ለማድረግ ቅስቀሳ ያስፈልጋል፡፡ ግለሰቦችን ወደ ማህበሩ ለመሳብ የማህበሩን ዓላማና በጋራ የሚያስገኘውን ውጤትና ጥቅም ማወቅ አለባቸው፡፡ ይህንን ካወቁ ወደ ማህበሩ የመግባታቸው ዕድል የሰፋ ነው፡፡ አባል ከሆኑ በኋላም በፈቃዳቸው የተለያዩ ተሳትፎዎች ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የማህበራቸውንም ዓላማ ሲረዱ በተለያየ መልክ ሃላፊነት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ የቅስቃሳውም አላማና ውጤቶች እየታየ በመመርመር አንዳንድ መነሻ የሚሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ መንቀስቃስ ይቻላል። እስካሁን ከተገነዘብናቸው አንድ ነገር በኤሚሊያ ሮማኛና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስለእኛ ማህበር የሚያውቁት ነገር ትንሽ መሆኑን ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ "ማህበሩ መኖሩን አውቃለሁ ግን አባል አይደለሁም" ይላሉ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን "በማህበር መደራጀት ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም?" ሲባሉ ብዙዎቹ "ይጠቅማል" ነው የሚሉት፡፡ ይጠቅማል ብለው እየመለሱ አባል ያልሆኑበት ምክንያት ግራ ቢያጋባም ስለማህበሩ የበለጠ ቢያውቁ ኖሮ አባል የመሆናቸው ዕድል ትልቅ ሊሆን ይችል ነበር፡፡ ማህበሩ "ምንም አይነት ነገር ሲያደረግ አይቼ አላውቅም" የሚሉም አሉ፡፡ ወዘተ ... እንግዲህ በዚህ ምክንያት ስለ ማህበሩ ያላቸውን ዕውቀት ለማስፋት የገድ ቅስቀሳ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
.
የቅስቀሳ ማካሄጃ አሳቦች
ከላይ እንደተጠቀሰው የማህበሩን ዓላማዎች፣ መመሪያ ደንብና ህግ ባጭሩ ጨምቆ በጥቂት ገጾች ላይ በመፃፍ በማባዛት እዚህ ለሚኖሩት እንዲደርሳቸው ማድረግና ሁሉም አንብበው መረዳት እንዲችሉትም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም ማድረግ፡፡ ከተቻለም እንዲወያዩበትና እንዲሻሻል ማድረግ፡፡
* ሰው ለሰው እንዲያሰማ በሚቻሉት መንገዶች ሁሉ መጠቀም። የበለጠ ግኑኝነት እንዲኖረን ለምሳሌ በፖስታ ሳጥን ቁጥራችን፣ በኢሜል አድራሻችን በመጠቀም፣ ሩቅ ለሆኑ ደግሞ በተወካዮቻቸው አማይነት፣ በተለይም ደግሞ ማህበሩ የራሱ የሆነ ድህረ-ገፅ በመንደፍ በሩቅ የሚገኙት በድህረ ገጽ (internet) ስለማሕበሩ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲያውቁ ማድረግ፡፡
* ያድራሻ ወረቀት በመስራትና ኢትዮጵያዊያን ሲመጡ መስጠት፡፡ እርስበርሳችንም ያድራሻ ወረቀቱን ለሌሎች ለመስጠት መተባበር፡፡ ያድራሻ ወረቀቱንም ስንሰጥ ስለማህበሩ አጭር ገለፃ ጋር ወይም ማብራሪያዎችን ከሚይዝ ሰነድ ጋር ቢሆን ይመረጣል፡፡
* ማህበሩ ውስጥ ለሚመዘገቡ አባላት በሙሉ የፖስታ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ ኢሜል ያላቸው ደግሞ በጣም ጠቃሚነት ስላለው በመዝገብ እንዲያዝ ማድረግ ------------------------------------------
* ለአዲስ አባላቶች መመዝገቢያ የሚሆን ቅፅ መስራት፡፡ አዲስ አባላቶችም ከመመዝገባቸው በፊት ስለማህበሩ አላማና እንቅስቃሴ ባጭሩ መግለፅና ማሳወቅ፡፡
* የሁሉም የአባል መታወቂያ ጊዜው ስለወደቀበት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ከተወሰነበት እንዲታደስ ማድረግና ለአዳዲሶቹንም አባላት ጨምሮ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ ...
* የመሪነት ቦታው በሥራ አስኪያጅ አባል በጊዜያዊ ተመድቦ እንዲሠራ የመደረጉ ሁኔታም .......
* ማንኛውም ወገን የፆታ የብሔረሰብ የሃይማኖት የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ሳይገድበው በፈቃዱ የማህበሩ አባል ሊሆን እንደሚችል ... ይቀጥላል ...

giovedì

ጠቃሚ ሃሳቦችን የማሰባሰቢያ ቅፅ


የምናተኩረው በኤሚሊያ ሮማኛና በአካባቢዋ በሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ላይ ነው፡፡ የተገኙት ሃሳቦች ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን/ት ሊወክል እንደሚችል ተስፋ አለን፡፡ ይህንን ቅፅ ብቻውን አትመውት ሊሞሉት ይችላሉ። ወይም ደግሞ የእያንዳንዱን ጥያቄ ተራ ቁጥር አስቀምጠው ከፊቱ ላይ መልሱን አስቀምጠው comments ላይ አስፍረው እንዲደርሰን ለማድረግ ይቻላል፡፡ የ እርስዎን ስምና የመኖሪያ ከተማ ከስሩ እንዲያደርጉ ይሁን።
.
የተሻለ ውጤትም ለማምጣት እንዲረዳን በማሰብ ዕድሜና ፆታ ፡፡ ለምሳሌ ከሚጠየቁት ውስጥ ወንድና ሴቶችን እኩል በእኩል መጠየቅ፡፡ በተረፈ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለምናገኝ ገንቢ ሃሳቦች እንደምናገኝና ለማህበሩ እንደሚጠቅሙ ተስፋ እናደርጋለን።
1)
ሀ) ፆታ፤ ሴት - c - ወንድ - c
ለ) ዕድሜ፤ ከ 25 በታች - c - ከ 60 በላይ c
2)
በኤሚሊያ ሮማኛ ውስጥ የኢትዮጵያዊያን ማህበር አለ?
ሰምቼ አላውቅም፡፡ c
እንዳለ አውቃለሁ ግን አባል አይደለሁም፡፡ c
የማህበሩ አባል ነኝ፡፡ c
3)
ማህበሩ ባሁኑ ጊዜ በርካታ አባላት ቢኖረውም ተሳትፎ የሚያደርጉትና የሚገለገሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ምክንያት ምንድነው ብለው ያስባሉ?
... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ...
4)
ለወደፊቱ ምን ቢደረግ በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ማዕከሉ ይመጣሉ ብለው ያስባሉ?
... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ...
5)
ማህበሩን ለማጠንከር በግለዎ ማድረግ የሚችሉት ነገር ካለ ቢያካፍሉን?
... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ...
6)
ይህ የኢትዮጵያዊያን ማህበር ኤሚሊያ ሮማኛ ውስጥ በመኖሩ በአጠቃላይ እንዴት ያዩታል?
ይጠቅማል፤ c
ለውጥ የለውም፤ c
ጥቅም የለውም፤ c
7)
መጨረሻ ላይስ የግል አስተያየት አለዎት?
... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ... ...
.
ስም ..................................................
የመኖሪያ ከተማ .................................
.
ለትብብርዎ በጣም እናመሰግናለን!!!

martedì

የርክክብ ሥርዓት ሲደረግ

ማዕከላዊው ኮሚቴ ከአዲሱ ሥራ አስኪያጅ ጋር በሚደረገው የርክክብ ሥነሥርዓት ሲፈፀም ውጣ ውረዱ እንዳይበዛ እንዳይከብድ መሆን አለበት፡፡ የርክክርቡ ሥርዓት እየተጓተተ ከመጣ የስራ ድልድሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ማድረግ አይቻልም። ... ... ...
ሊኖሩ ከሚችሉት ዋና ዋና ዶኩሜንቶች፣ ንብረቶች፣ መዝገብና ሰነዶች
* የቨርባሌ መያዣ ደብተር (ያለፉትን የማህበሩ እንቅስቃሴዎች ሪፖርት የሚያሳየው መዝገብ)
* የአባላትን ስም ዝርዝር የሚያሳይ መዝገብ
* የተመዘገቡበትን ቀንና ዓመተ ምሕረት እንዲሁም መዋጮዎቻቸው ይሚያሳይ ሰነድ
* ጊዜያቸው ያልወደቀና ሊያገለግሉ ይሚችሉ ማንኛውም ዶሴዎች (የግለሰቦችና የድርጅቶች አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ ደብዳቤዎች፣ ወዘተ ...)
* የማህበሩ Statuto (ኦሪጂናል ሰነድ)
* Carta intestata- Partita Ivaየማህበሩ የፖስታ ሳጥን ቁጥርና ቁልፍንብረት
* ቁሳቁስ (በስጦታ የተገኙ እቃዎች፣ ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ... )
* የገንዘብ ዶኩመንትስ (የሂሳብ ደብተር፣ ተንቀሳቃሽ ገንዘብ፣ የባንክ ካርድና፣ የestratto conto ወረቀቶች
* የአለፉትን ጊዜያት የባንክ ገንዘብ ገቢና ወጪ የሚያሳይ የባንክ ወረቀቶች ... )
* ጊዜያዊ የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴም ተመሥርቶ ክትትል እንዲያደርግበት
* በአለፉት ዓመታት በተቆጣጣሪ ኮሚቴ የኦዲት ክትትል የተደረገባቸውና የሚያሳዩ ሰነዶች ከኖሩ
* የገንዘቡም ሆነ የዶኩሜንቶች ርክክብ የሥራ አስኪያጅ አባሎችና የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት እንዲፈፀም ...
* የባንክ ካርዱንና ተንቀሳቃሽ የሆነውን ገንዘብ ለአዲሱ ገንዘብ ያዥ ማስረከብ ...
.
አዲሱ የሥራ አስኪያጅ ክኮሚተው የተወሰኑ ዶኩሜንቶች ከተረከበ በኋላ ሥራውን የሚጀምረው እንደተለመደው አባሎች በሚያቀርቡት ቃለጉባኤ (አጀንዳ) በመያዝ አስፈላጊው ስብሰባ በማድረግና ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ይሆናል፡፡
*
የማሕበሩን ገንዘብ አያያዝና በሚመለከት
ቀደም ብሎ በተደረገው ያለኮሚቴ ውሳኔ ምንም አይነት የሂሳብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ስለተደረገና ባንክ ያለውም ገንዘብ እንዳይወጣ ስለተወሰነ ይህ ሁኔታ በዚሁ መቀጠል አለበት፡፡ የኢትዮጵያውያን ማህበር የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በአለፉት ሶስት ዓመታት ምንም አይነት ወጪና ገቢ የተደረገ ባለመኖሩ የሂሳብ ሰነድና የስራ ዘገባዎችን አቅርቦ ግምገማ ያደረገባቸው ጊዜያት የሉም። አስፈላጊ ስላልሆነ ነው፡፡ አዲሱ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ባለው የሂሳብ ደብተር ግልጽ የሆነ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት መመሥረት አለበት። ማንኛውም ወጪና ገቢ ይመዘገባል:: የፈለገው ቢሆን በግለሰብ ደረጃ በእጅ ገንዘብ አይቀበልም:: ማንኛውም ገቢ በማህበር ሂሳብ ገቢ ይሆናል:: መንግስታዊ እውቅና ስለአለው በአልቦ የተመዘገበ በመሆኑ የመንግስት የሂሳብ ተቆጣጣሪ ድንገት መመርመር ቢፈልግ እንኳን ምንጊዜም ዝግጁ መሆን አለበት:: ማንኛውም የገንዘብ ወጪ ከመደረጉ በፊት በማዕከላዊ የሥራ አስኪያጅ በማጆሪቲ የተወሰነበት ቢሆንና ከተወሰነ በኋላም ማህተምና ፊርማ የተደረገበት መሆን አለበት፡፡ ይህም ማለት በግለሰብ ውሳኔና ፈቃድ ምንም አይነት ገንዘብ ወጪ እንደማይደረግ ... ያለኮሚቴ ውሳኔና ያለ ስምምነት ከባንክ ገንዘብ ማውጣት አግባብ ካለመሆኑ ሌላ በሕግ ሊያስቀጣ ይችላል፡፡ ሂሳብ ነክ ነገሮችንና ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ላባላቱ በማቅረብ ማሳወቅ ... ይቀጥላል ...
etiopiainitalia.com