venerdì

በስደተኞች የአውሮፓው የጋራ ድንጋጌ


በየጀልባ እየተንጠላጠሉ በመሰደድ ባሕር ላይ እንዳሉ የተገኙ አፍሪቃውያን ተለቅመው ወደመጡበት እንዲመለሱ ወይም እንዲሳፈሩና ብዙ ሳይቆዩ እንዲመለሱ የተደረጉ ብዙ እንዳሉ የሚታወስ ነው። የኢጣሊያ መንግስትም በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች በኩል የሚፈልሱትንም ስደተኞቹ መልሶ ለማባረር በቆይታ እሥር ላይ የሚያውል ወይም በCPT (ማጎሪያ) ውስጥ የሚያከማች ነው። ይኼ ሁኔታ ግን በሌሎች የአውሮጳ ሀገር ሲፈጸም አልታየም።
የአውሮፓ ህብረት ራሷን ትጋርዳለች፣ ስደተኞች እንዳይጎርፉባት መሰናክል ተደነቅራለች፣ የሚለው አነጋገር እንደገና ቀስቅሶ ይገኛል። አውሮጳውያኑ በዚሁ ጉዳይ ረገድ መስማማት የተሳናቸው ሆነው ነው የሚታዩት። በርግጥ በዚሁ የስደተኞች ጥያቄ ረገድ የአውሮጳው ኅብረት የሚቀርብበት ሂስ ተገቢ ነው። ግን የችግሩ ፍሬነገር ሌላ ነው። የአውሮጳው ኅብረት ነባር አባላት የስደተኞች ጉዳይ መርሕ የሚቀሰቅሰውን ክርክር እያጓተቱ ነበር ያቆዩት። የኋላ ኋላም አባላቱ “የጋራ” ብለው የሰጡት ድንጋጌ በአትኩሮት ሲመለከቱት እምብዛም የጋራ መንፈስ አይታይበትም። በዚህ አኳኋን እያንዳንዱ ኣባል መንግሥት እስካሁን የሰራበትን መርሕ ሳይለውጥ ነው የቀጠለበት።
እዚህ ላይ በተለይ “አስተማማኝ 3ኛ ሀገሮች” የሚለው አነጋገር ነው አንድ ምሳሌ የሚሆነው። በዚህም መሠረት እያንዳንዱ የአውሮጳው ኅብረት አባል መንግሥት ሰብዓዊውን መብት ያከብራሉ ስለሚላቸው ሀገሮች እስካሁን የያዘውን ዝርዝር ወደፊትም ይሰራበታል። አንድ ቀን ታዲያ በእነዚሁ ሀገሮች አንድ የፖለቲካ ተገን ጠያቂ ብቅ በሚልበት ጊዜ ወደዚያው እንዲባረር የሚደረግ እንጂ አውሮፓዊ ብሎም ዓለማቀፋዊ የተገን ጠያቂዎች መብትን የሚጠቀምበት ማንም ሀገር የለም። ከአንዱ አባል ሀገር ሌላው መላ አጥ ሆኖባቸው ውጤት አልባነታቸውን ነው የሚያንፀባርቁት። እውነተኞቹን ተገን ጠያቂዎች ከኤኮኖሚ ስደተኞች ለመለየት ነው ሙከራ የሚያደርጉም ይገኙበታል። የኤኮኖሚ ስደተኞችን ለመጋረድ የሚደረገው ጥረት አንዳንድ የአውሮጳ ጠረፎች ዘጊ አጥር እያደረጉ ነው። በዚህ ረገድ እስፓኛ የባሕሩን መስመር የጂብራልተርን ሁለት ጎኖች የዘጋቸበት ርምጃ አንድ ምሳሌ ይሆናል።
አሁን እንግዲህ የአውሮጳው ኅብረት የስደት ጉዳይ መርሕ በየትኛው ኣቅድ መቃናት አለበት? ለፖለቲካ ተገን አሰጣጥ መስፈርቱ መወሰንና ለሁሉም የሚረጋ እንዲሆን መደረግ አለበት። ስደተኞች የሚነሱባቸውን ሀገሮች “አስተማማኝ” እና “አላስተማማኝ” በተሰኙት ምድቦች መለየት ብዙ የሚያራምድ አይደለም። አውሮጳ ውስጥ የነበሩት የቀውስ አካባቢዎች አሁን ሰላምን ማግኘታቸውና ለአውሮጳውም ኅብረት አባልነት ተሥፋን ማየታቸው የስደተኞችን ጎርፍ የገታው ይመስላል። ግን ይኸው የአውሮፓ ዕድል ለአፍሪቃና ለእስያም የሚረጋ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ አማራጩ ነው መፈለግ ያለበት።
የስደት ጥያቄ የኋላ ኋላ በጠንካራ የልማት ርዳታ መርሕ ብቻ የሚፈታ እንደሚሆን ዛሬ አውሮጳውያኑ ይገነዘቡታል። ግን የአውሮጳው ኅብረት እስካሁን እንዳደረገው ሚሊዮኑን ርዳታ ዝግጁ ማድረግ ብቻውን ትርጓሜ የለውም ትብብሩም ነው መጠናከር ያለበት እስካሁን ታዲያ በተለይ ከአፍሪቃ ጋር የሚደረገው ትብብር ነው መቃናት እየተሳነው ነው የተገኘው።
ይኸው የትብብር አለመቃናት ነው በሰው በመነገድ አፍሪቃውያኑን መሰል ስደተኞች በየሰባራ ጀልባዎች እያጨቁ ወደ ባሕር እንዲሰማሩ፣ ለሞት እንዲጋለጡና ወንጀለኞች እንዲበራከቱ ነው የሚያደርገው እንጂ ሌላ መንገድ አይሰጥም።
የአውሮጳው ኅብረት ከዓመታት በፊት በሴቪያ/እስጳኝ ዓቢዩን ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት የደረሰው ውሳኔ አፍሪቃውያኑ መሪዎች ወንጀለኞቹን በጋራ ርምጃ ለመግታት ይተባበሩ ዘንድ ግፊት እንዲደረግባቸው የሚጠይቅ ነበር። ግን ለትብብር ዝግጁ ባይሆኑት ሀገሮች ላይ ማዕቀብ በሚደነገግበት ጥያቄ ረገድ አውሮጳውያኑ ብዙ አልተራመዱም።
እንግዲህ አውሮጳ በስደተኞቹ አንፃር በሮቿን ዘግታ አጥርና ማኅፈድ እንዳትፈጥር ከተፈለገ ስደተኞቹ በሚነሱባቸው ሀገሮችና በአውሮጳው ኅብረት መካከል ትብብር መጠናከር አለበት። ርግጥ፣ ጦርነትንና ሰብዓዊውን መከራ ለመግታት መታገል እጅግ ተገቢ ነው ግን ርምጃው በዚህ ብቻ ማብቃት የለበትም። ... ይቀጥላል ...
.
በዓለም ዙሪያ ለተሻለ ስራና ኑሮ የትውልድ አገራቸውን ለቀው የተሰደዱት ህዝቦች ቁጥር ሰማንያ ስድስት ሚሊዮን አካባቢ ይገመታል። ከእነዚህ ስደተኞችም አብዛኛዎቹ በተሰደዱበት አገር አነስተኛ ክፍያ በሚያስገኙና ዜጎች በማይፈልጉዋቸው ስራዎች ተሰማርተው ነው ህይወታቸውን የሚገፉት። በተሰደዱበት ሁሉ አድልዎና መገለልም የዕለት ተዕለት ዕጣቸው ነው። ይህም የውጭ ዜጎች ጥላቻ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በሄደበትና ዜጎቻቸው ዝቅተኛ ክፍያ ከሚያስገኙ ስራዎች በሚሸሹት በምዕራብ አውሮፓ አገራት ያለ የወቅቱ ችግር ሆኖአል።
የምዕራብ አውሮፓ አገራት ፖለተካዊና ኢኮኖሚያዊ አመለካከታቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል። የትኛውንም ሞያ ይዞ የሚመጣ ስደተኛ በአጭርም ሆነ በረዥም ጊዜ በምዕራብ አውሮፓ በዕርግጠኝነት መፈለጉ አይቀርም ይላሉ የስደተኞችና የዘር ጉዳይን የተመለከተው የአምስተርዳሙ የጥናት ተቅዋም ባልደረባ ዩርዮን ዱመርኒክ። ጀርመንና ኔዘርላንድስ ግን ይህን ለመቀበል ይከብዳቸዋል። በብሪታኒያ በፊንላንድና በስዊድን የኢኮኖሚ ስደተኞችን መብት የሚጠብቅ ህግ አለ።
ዱመርኒክ በኔዘርላንድስ ያለውን ሁኔታ እንደገለፁት ችግሩ አሁን የተከሰተ አይደለም “ጠባሳው ከዛሬ ሀያ ዓመት አንስቶ ያለ ነው። በተለይ እ.አ.አ በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያዎቹ በስደተኛው ዘንድ የስራ አጡ ቁጥር ከፍተኛ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሞች ከህብረተሰብ ጋር አለመዋሀዳቸው በአውሮፓ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖዋል። ለምሳሴ በኔዘርላንድስ የሚገኙት ወጣት የሞሮኮ ስደተኞች ከህብረተሰቡ ጋር አለመዋሀዳቸው እንደ አንድ ችግር ነው የሚወሰደው። ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ ለስደተኛው መጥፎ አመሰካከት እንዲኖረው ያደርጋል። ይህም በኢኮኖሚ ስደተኛው ላይ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል።” ... continiua ...
.
“ችሎታን መሰረት ያደረገው አሰራር እንደሚለው ወደዚህች አገር ለስራ ለመምጣት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው ማመልከት አለበት። ከዚያም ማመልከቻው ይጠናል። ምን ዓይነት ችሎታ ይዞ እንደሚመጣ ይታያል። ከዚያም ከአመልካቹ ውስጥ ከፍተኛ ነጥብ ያለው ለመግባት ይፈቀድለታል”
ይሁንና እዚህ ላይ የሚደረገው ጥንቃቄ በአስርና በአስራ አምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ እየጨመረ እንደሚሄድ የሚገመተውን በዕድሜ የገፋውን ህብረተሰብ የሚተካውን ሰራተኛ ጉዳይ ማስነሳቱ አልቀረም። በጉዳዩ ላይ የዓለም ስራ ድርጅት ኤክስፐርት አስተያየታቸውን እንደሰጡት ችግሩ አሁን መፍትሄ ሳይበጅለት እንዳለ ከተተወ በመጪው ሀምሳ ዓመት ውስት የህዝቡ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን ካለው በሀያ ሁለት ከመቶ ይቀንሳል። ይህ ማለት የኢኮኖሚ ስደተኛው እንዳይገለልና ከመዋሀዱ ችግር አንፃር ከአሁኑ ግልፅ ህግ መውጣት አለበት።
በነገዋ ምዕራብ አውሮፓ ከወዲሁ ልዩ ልዩ ባህሎች ተቻችለው የሚኖሩበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት።
ቋንቋውን መናገር ለመቆየትም ሆነ ለመስራት እንደ ግዴታ መቀመጥ አይኖርበትም ሲሉ የዓለም ስራ ድርጅት ኤክስፐርት አስረድተዋል።
... ይቀጥላል ...

Nessun commento: