martedì

ስለ ማሕበሩ ያለንን ዕውቀት ማስፋት


በተለምዶም ይሁን በተፈጥሮ በማህበር ሆኖ አንድን ነገር በጋራ ለማድረግ ቅስቀሳ ያስፈልጋል፡፡ ግለሰቦችን ወደ ማህበሩ ለመሳብ የማህበሩን ዓላማና በጋራ የሚያስገኘውን ውጤትና ጥቅም ማወቅ አለባቸው፡፡ ይህንን ካወቁ ወደ ማህበሩ የመግባታቸው ዕድል የሰፋ ነው፡፡ አባል ከሆኑ በኋላም በፈቃዳቸው የተለያዩ ተሳትፎዎች ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የማህበራቸውንም ዓላማ ሲረዱ በተለያየ መልክ ሃላፊነት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ የቅስቃሳውም አላማና ውጤቶች እየታየ በመመርመር አንዳንድ መነሻ የሚሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ መንቀስቃስ ይቻላል። እስካሁን ከተገነዘብናቸው አንድ ነገር በኤሚሊያ ሮማኛና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስለእኛ ማህበር የሚያውቁት ነገር ትንሽ መሆኑን ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ "ማህበሩ መኖሩን አውቃለሁ ግን አባል አይደለሁም" ይላሉ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን "በማህበር መደራጀት ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም?" ሲባሉ ብዙዎቹ "ይጠቅማል" ነው የሚሉት፡፡ ይጠቅማል ብለው እየመለሱ አባል ያልሆኑበት ምክንያት ግራ ቢያጋባም ስለማህበሩ የበለጠ ቢያውቁ ኖሮ አባል የመሆናቸው ዕድል ትልቅ ሊሆን ይችል ነበር፡፡ ማህበሩ "ምንም አይነት ነገር ሲያደረግ አይቼ አላውቅም" የሚሉም አሉ፡፡ ወዘተ ... እንግዲህ በዚህ ምክንያት ስለ ማህበሩ ያላቸውን ዕውቀት ለማስፋት የገድ ቅስቀሳ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
.
የቅስቀሳ ማካሄጃ አሳቦች
ከላይ እንደተጠቀሰው የማህበሩን ዓላማዎች፣ መመሪያ ደንብና ህግ ባጭሩ ጨምቆ በጥቂት ገጾች ላይ በመፃፍ በማባዛት እዚህ ለሚኖሩት እንዲደርሳቸው ማድረግና ሁሉም አንብበው መረዳት እንዲችሉትም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም ማድረግ፡፡ ከተቻለም እንዲወያዩበትና እንዲሻሻል ማድረግ፡፡
* ሰው ለሰው እንዲያሰማ በሚቻሉት መንገዶች ሁሉ መጠቀም። የበለጠ ግኑኝነት እንዲኖረን ለምሳሌ በፖስታ ሳጥን ቁጥራችን፣ በኢሜል አድራሻችን በመጠቀም፣ ሩቅ ለሆኑ ደግሞ በተወካዮቻቸው አማይነት፣ በተለይም ደግሞ ማህበሩ የራሱ የሆነ ድህረ-ገፅ በመንደፍ በሩቅ የሚገኙት በድህረ ገጽ (internet) ስለማሕበሩ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲያውቁ ማድረግ፡፡
* ያድራሻ ወረቀት በመስራትና ኢትዮጵያዊያን ሲመጡ መስጠት፡፡ እርስበርሳችንም ያድራሻ ወረቀቱን ለሌሎች ለመስጠት መተባበር፡፡ ያድራሻ ወረቀቱንም ስንሰጥ ስለማህበሩ አጭር ገለፃ ጋር ወይም ማብራሪያዎችን ከሚይዝ ሰነድ ጋር ቢሆን ይመረጣል፡፡
* ማህበሩ ውስጥ ለሚመዘገቡ አባላት በሙሉ የፖስታ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ ኢሜል ያላቸው ደግሞ በጣም ጠቃሚነት ስላለው በመዝገብ እንዲያዝ ማድረግ ------------------------------------------
* ለአዲስ አባላቶች መመዝገቢያ የሚሆን ቅፅ መስራት፡፡ አዲስ አባላቶችም ከመመዝገባቸው በፊት ስለማህበሩ አላማና እንቅስቃሴ ባጭሩ መግለፅና ማሳወቅ፡፡
* የሁሉም የአባል መታወቂያ ጊዜው ስለወደቀበት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ከተወሰነበት እንዲታደስ ማድረግና ለአዳዲሶቹንም አባላት ጨምሮ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ ...
* የመሪነት ቦታው በሥራ አስኪያጅ አባል በጊዜያዊ ተመድቦ እንዲሠራ የመደረጉ ሁኔታም .......
* ማንኛውም ወገን የፆታ የብሔረሰብ የሃይማኖት የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ሳይገድበው በፈቃዱ የማህበሩ አባል ሊሆን እንደሚችል ... ይቀጥላል ...

Nessun commento: