venerdì

አውሮፓና ስደተኞች


ሜዴትራኒያን ውቂያኖስን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመዝለቅ የሚጥሩት ስደተኞች ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ ነው የመጣው። የሜዴትራኒያን ባሕር ተዋሳኝ ከሆኑት የማግሬብ አገሮች፤ ከሊቢያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ ተነስተው ውቂያኖሱን በጀልባ በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመዝለቅ የሚሞክሩት አፍሪቃውያንና የመካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ከድህነት ለማምለጥና የተሻለ ኑሮ ሕልማቸውን ዕውን ለማድረግ አገራቸውን ለቀው ከሚሰደዱት ብዙዎቹም ባሕር ውስጥ እየሰጠሙ ማለቃቸውም አሁንም ቢሆን የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። ለዚያውም ጉዞው ቢሳካላቸው እንኳ የሰደተኛን ጎርፍ ለመግታት ደምባቸውን እያጠበቁና ብዙዎችን ለማስወጣት ጥረታቸውን እያጠናከሩ በሄዱት የአውሮፓው ሕብረት አገሮች ተገን ለማግኘት ያላቸው ዕድል የመነመነ ሆኖ ነው የሚገኘው። በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገሮች የተገን ማመልከቻቸው ተቀባይነት አጥቶ ዛሬ ነገ ልንባረር ነው ሲሉ ኑሯቸውን በሰቀቀን የሚገፉት ስደተኞች ጥቂቶች አይደሉም።
ኢጣሊያ ክ2004 ዓም ጀምሮ ወደ ደቡባዊ ጠረፏ ወደ ላምፔዱዛ ደሴት ከዘለቁት ስደተኞች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን መልሳ ወደ ሊቢያ ልካለች። በአውሮፓው ሕብረት አገሮችም በሰሜናዊው አፍሪቃ መሸጋገሪያ አገሮች ስደተኞቹን ገትቶ ለመያዝ የሚያስችል ማከማቻ ሰፈር እንዲቆም በጀርመን የአገር ግዛት ሚኒስትር አቶ ቺሌይ የቀረበው ሃሣብ በዚያን ዓመት ብዙዎችን ሲያከራክር ነበር። የስደተኛውን ጎርፍ ለመግታት በሰሜናዊው አፍሪቃ መከማቻ ሰፈር ማቆም ይቻላል ተብሎ የቀረበው ሃሣብ የአውሮፓውን ሕብረት ያነጋገረና ማከራከሩን ይታወስ ነበር። ሃሣቡ በኢጣሊያና በአውስትሪያ ተደግፍ ነበር። ነገርግን በተቀሩት የሕብረቱ ዓባል ሃገራት ለምሳሌ በፈረንሣይ ... ዘንድ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም ነበር።
ስደተኞቹን በሰሜናዊው አፍሪቃ አገሮች በማከማቸት ዓለም አቀፉ ደምብ ያስቀመጠውን የደህንነት መስፈርት ማስከበር ይቻላል ወይ?
የተጠቀሱት ሃገራት የሰብዓዊ መብት ይዞታስ እስከምን ድረስ ነው?
እነዚህ ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለማግኘት የሚችሉ ሆነው አይገኙም። በወቅቱ ጎልቶ የሚታየው ስደተኛውን በማከማቸት አጠቃላዩን የስደተኛ ጎርፍ ሊገታ መቻሉ አጠያያቂ መሆኑን ነው። የስደቱን ችግርና መንስዔ ከመሠረቱ ሊያስወግድ መብቃቱም ሲበዛ ያጠራጥራል። እርግጥ በመስከረም 2001 ዓ.ም. አሜሪካ ውስጥ የሽብርተኞች ጥቃት ደርሶ የዓለምን ገጽታ በሰፊው ከለወጠ ወዲህ በአውሮፓም የጸጥታ ጥበቃውና የሕብረቱን የውጭ ድንበር አስተማማኝ የማድረጉ ግፊት እየጠነከረ ነው የመጣው። ሆኖም ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች እንደሚያደርጉት የስደተኛውን ጉዳይ ሽብርን ከመቋቋሙ ጥረት ጋር ማዛመዱ ተገቢነት አይኖረውም።
ይህን መሰሉን አስተሳሰብ ከሚያራምዱት ፖለቲከኞች መካከል ለአውሮፓ ሕብረት ኮሚሢዮን በፍርድ ኮሜሣርነት የታጩት ኢጣሊያዊው ክርስቲያን ዴሞክራት ሮኮ ቡቲልዮኔ ይገኙበት ነበር። ቡቲልዮኔ የኮሚሢዮኑ ሥልጣን ጸድቆ ብራስልስ ውስጥ መቀመጫ ከያዙ ወደፊት የአውሮፓው ሕብረት የጸጥታና የድንበር ጥበቃ ጉዳይ ሃላፊም ሊሆኑ ይችሉ ነበር። ቀደምታቸው የፖርቱጋሉ ተወላጅ አንቶኒዮ ቪቶሪኖ በአንጻሩ እነዚህን ዘርፎች የጠቀለለ ሰፊ ሥልጣን አልነበራቸውም። የኢጣሊያው ወግ አጥባቂ ባለሥልጣን ሕገ-ወጡ የስደተኞች እንቅስቃሴ ሊገታ ይገባዋል ባይ እንደመሆናቸው መጠን በሕብረቱ ኮሚሢዮን ውስጥ ይህንኑ ዓላማቸውን ካራመዱ ክርክሩ ይበልጥ መጠናከሩ የማይቀር ነው። አውሮፓ ቢቀር በሃሣብ በጉዳዩ ለሁለት የመከፈል አዝማሚያ ነው የሚታይባት። ብራስልስ ውስጥ የሕብረቱ ዓባል ሃገራት የግራ ክንፍ ፖለቲካ ወገን የኢጣሊያው ዕጩ ኮሜሣርና የመሰሎቻቸው አመለካከት ገና ከጅምሩ እንዳልተዋጠለት ሰሞኑን በግልጽ አሣይቷል።
በጀርመኑ አገር ግዛት ሚኒስትር ኦቶ ቺሊይ የተቀሰቀሰው በሰሜናዊው አፍሪቃ ስደተኞችን ማከማቻ መፍጠርና በዚያው የመገደብ ሃሣብ ለነገሩ ላይ ላዩን ቀላል ነገር ቢመስልም ተቀባይነት ቢያገኝ በአውሮፓ ጸንቶ የቆየውን የስደተኞች ተገን መብት ከመሠረቱ ሊለውጥ የሚችል ነው። ራሳቸው ኦቶ ቺሊይ ያሰቡት ገቢር ቢሆን በዚህ በጀርመን የፖለቲካ ተገን የመጠየቁ መሠረታዊ መብት አስፈላጊ አይሆንም ሲሉ ነው የተናገሩት። ይህ ሃሣብ የጀኔቫውን የስደተኛ መብት ጥበቃ ውል የሚጻረር በመሆኑ በዚህ በጀርመን በብዙዎች ሲነቀፍ የአውሮፓው ሕብረት ኮሚሢዮንም ተቃውሞታል። ለዚህም ነበር የሕብረቱ አገር ግዛት ሚኒስትሮች በቅርቡ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ጉዳዩን ከማንሳት ይልቅ በስተጀርባ መተዉ የተመረጠው።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መብት ጥበቃ ውል ከተፈረመ ሃምሣ ዓመታት አልፎታል። ከዚያን በፊት ተመሳሳይ ያልታየለት ውል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለስደት ለዳረጋቸው አውሮፓውያን ዕርዳታና ተገን ለመስጠት በጊዜው የተደረገው ጥረት ውጤት ነበር። ጀኔቫ ላይ ተቀማጭ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ መርጃ ተቋም አፈ-ቀላጤ ሩፐርት ኮልቪል መለስ ብላው እንደሚያስታውሱት ውሉን የተለየ ትርጉም የሚሰጠው በታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስደተኞች መብት ጥበቃ ዓለምአቀፍ ጽናት ያለው ሕግ ለማስፈን መብቃቱ ነው። ይህ ደግሞ ወሣኝ ጉዳይ ነበር። የስደተኞች መብት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊከበር የሚችለው የዓለም መንግሥታትን ግዴታ ላይ የሚጥል የጥበቃ ዋስትና ሲኖር ብቻ በመሆኑ። ይህ ሃቅ ትናንት ጽናት ነበረው፤ ዛሬም ይኖረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ መብት ጥበቃ ውል በመጀመሪያ በአውሮፓ ብቻ ጸንቶ ከቆየ ከ16 ዓመታት በኋላ እ.ኢ.አ. በ1967 ነበር በዓለምአቀፍ ደረጃ ሊጸና የበቃው። እስከዛሬ 140 የዓለም መንግሥታት ሲያጸድቁት በጅምሩ ውሉ ላይ የሰፈሩት መሠረታዊ አንቀጾች፤ ለምሳሌ ያህል ስደተኛ የሚለው ቃል አተረጓጎም ራሱ ዛሬም ሳይቀየሩ እንደጸኑ ናቸው። በዚሁ ውል መሠረት ስደተኛ ተብሎ የሚቆጠረው በዘር፣ በሃይማኖት፣ በነገድ፣ በማሕበራዊና በፖለቲካ አሰላለፉ የመሳደድ ጭብጥ ፍርሃቻ ስላለው አገሩን መልቀቅ የተገደደ ማንኛውም ዜጋ ነው። የትኛውም ስደተኛ አደጋ እስካለበት ድረስ ያለውዴታው ወደ ትውልድ አገሩ መጋዝ የለበትም የሚለው አንቀጽም አንዱ እጅግ ጠቃሚና መሠረታዊ ዓላማ ሆኖ ይገኛል። ስደተኞች ተገን አግኝተው በሰፈሩበት አገር የመሥራት፣ ነጻ ሆኖ የመንቀሳቀስ፣ የትምሕርትና የሃይማኖት ነጻነት ያላቸው መሆኑም በማያሻማ ሁኔታ የተቀመጠ ጉዳይ ነው።
እንግዲህ በሰሜን አፍሪቃ መገደቢያ ሰፈር ለመትከል በአውሮፓ የተጸነሰው ሃሣብ ይህን ሁሉ መስፈርት ሳይጋፋ ሊያልፍ የሚችል አይሆንም። እርግጥ ዛሬ የስደቱ መንስዔ ምክንያትም ሆነ የፈለሣው ባሕርይ ከቀድሞው እጅግ እየተለወጠ መጥቷል። ከሃምሣ ዓመታት በፊት የጀኔቫው ውል ሲሰፍን በመሠረቱ ያተኮረው በፖለቲካ ምክንያት በሚሳደዱ ተገን ፈላጊዎች ላይ ነበር። ዛሬም በፖለቲካ አመለካከታቸው የሚሳደዱና ተገን የሚሹ የጭቆና ሰለቦች አይጥፉ እንጂ አብዛኛው ስደተኛ በኤኮኖሚ ችግር፤ ማለት በረሃብና በጦርነት የተነሣ አካባቢውን እየለቀቀ የሚፈልስ ሆኗል። ይሁን እንጂ ይህም ቢሆን የፖለቲካ ጭቆናና ፍትህ-አልባ የአገዛዝ ዘይቤ የፈጠረው ችግር ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም። ስደተኞችን መገደቢያና ማስፈሪያ ይታነጽባቸው በተባሉት ሊቢያን በመሳሰሰሉት አገሮችም ፍትሃዊ ሥርዓት አለ ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር አይደለም።
ለዚህም ነው ሁለቱን የስደት ምክንያቶች የሚለያያቸውንና አንድ የሚያደርጋቸንም ምክንያት በሚገባ በማጤን ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት መጣሩ ግድ የሚሆነው። ጉዳዩ የሚመለከተው የበላይ ባለሥልጣን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ተቋም በአንድ በኩል መሠረታዊ ዓላማው እንዳይዛባ መታገልና በሌላ በኩልም ለምሳሌ ከአውሮፓው ሕብረት ጋር የተለወጠውን ሁኔታ ያጤነ ትብብር በማራመድ ተልዕኮውን መወጣት ይጠበቅበታል። ጉዳዩ ውስብስብ ሊሆን ይችላል። የሆነው ሆኖ ግን የስደተኞች ሰብዓዊ መብት ዛሬም ነገም እንደትናንት ሁሉ ሊታጠፍ የማይገባው ጉዳይ ነው።
በአውሮፓ ለፖለቲካም ሆነ ዛሬ በተለይ ቁጥራቸው ለተበራከተው የኤኮኖሚ ስደተኞች ጎርፍ ማየል ምክንያቱ ጭቆና፣ ድህነት፣ የመብትና የልማት ዕጦት መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ይታወቃል። ለነገሩ የበለጸገው ዓለም በታዳጊ አገሮች ላይ የተጫነውን ዕዳ በማቃለል ለልማት አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥር በተደጋጋሚ ቃል ገብቷል። የተባበሩት መንግሥታት የሚሌኒየም ዕቅድም ከፍ አድርጎ ያስቀመጠው የታዳጊ አገሮችን ልማት በማፋጠን ድህነትን በተወሰኑ ዓመታት በከፊል የመቀነሱን ዓላማ ነው። ይሁን እንጂ ቃልና ተግባር የሚጣጣሙ ሆነው አይገኙም። የዕዳ ምሕረቱን ጉዳይ ካነሣን አይቀር ይህ ከንቱ ውዳሴ መሆኑን ሰሞኑን ዋሺንግተን ላይ ተካሂዶ የነበረው የሰባቱ በኤኮኖሚ ልማት የበለጸጉ ቀደምት መንግሥታት የ G-7 መሪዎች ጉባዔ እንደገና አሣይቷል።
በአውሮፓ የኤኮኖሚ ስደተኞችን ጎርፍ ለመግታት ከተፈለገ እነዚሁ በሚመነጩባቸው አገሮች ጦርነትና የፖለቲካ ጭቆና እንዲወገድ፣ ፍትህና ፍትሃዊ የአስተዳደር ዘይቤ እንዲሰፍን፤ በአጠቃላይ ሰብዓዊ መብቶች በውል እንዲከበሩ የዓለም ሕብረተሰብ ለስሙ ከሚሰነዘር ሃዘኔታ አልፎ በተጨባጭ ድርሻውን ለመወጣት መነሣት ይኖርበታል። ሕብረተሰባዊ ሰላምና የኤኮኖሚ ዕድገት ገሃድ መሆን እስካልቻለ ድረስ ግን ስደተኛ ይኖራል፤ ወደ ምዕራቡ ዓለም የሚደረገውም ፈለሣ በየጊዜው መልኩን ይለዋውጥ እንደሆን እንጂ ቀጣይ ነው የሚሆነው። በሰሜን አፍሪቃም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች ማጎሪያ መሰል ሰፈር ማነጹ ስደተኞችን ከራስ ደጃፍ በማራቅ ጊዜያዊ የሕሊና ዕረፍት ለማግኘት ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ይሆናል ብሎ ማሰቡ ከንቱ ነው። ከምዕራቡ የዴሞክራሲ ሕብረተሰብ የሞራል መስፈርት የሚጣጣምም አይሆንም።

1 commento:

Anonimo ha detto...

የእ /ግ ቃል በዘፍጥረት 42, 1+2 እንዲህ ይላል
ያቆብም በግብጽ እህል እንዳለ ሰማ ያቆብም ልጆቹን ለምን እርስ በእርሳቹህ ትተያያላቹህ ? አላቸው አለ እነሆ ስንዴ በግብጽ እንዲገኝ ሰምቻለሁ ወደዚያ ውረዱ እንድንድን እና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን አለ ይህንን ቃል በማነብበት ግዜ አንድ ነገር ወደ አይምሮዬ መጣ ያም ምንድነው በዚህ ዘመን ያልነው ቤተሰቦቻችንን ማለትም እናት አባት ወይንም እህት ወንድም ወይንም የአባት አባት እና የእናት እናት ያለን ሰዎች ሁሉ ልክ እንደያቆብ ቤተሰብ በስደት ላይ ነን ያለነው በሀገር ቤት በህጻንነትም ወይንም ትልቅ ሁነን ስንኖር የነበርነው ኢትዮፒያውያን በሙሉ ዛሬ ከቤተስቦቻችንን ተለይተን በየተለያየ የአለም ዙሪያ ተበትነን ነው ያለውን ብዙዎቻችን የመጣንበት አላማ የራሳችን ጉዳይ ሊመስለን ይችላል ብዬ አስባለሁ ይህም ምንድነው ከዘመኑ ጦርነት ነፍስን ለተወሰነ ግዜ ለማዳን ትምህርትን ለመማር እና ከሀገራችን የተሻለ ሂይውት ለመኖር ነው ይህ በኛ ልብ ውስጥ ይኑር እንጂ እውነቱ ሲታይ ግን ሌላ ነው አሁን ያለንበትን ዘመን በመንፈስ ስናስተውለው ምድር በዮሴፍ ዘመን የነበረችበትን ዘመን ይመስላል ባይ ነኝ ቃሉም ሲናገር እንዲህ ይላል በግብጽ ምድር የነበረውም የሰባቱ አመት ጥጋብ አለፈ ዬሴፍም እንደተናገረው የሰባቱ አመት አመት ራብ ጀመረ በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብጽ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበር ኦሪት ዘፍጥረት ምራፍ 41, 53+55 አሁን በዚህ ዘመን 7 አመት የጥጋብ ዘመን አልፎ 7 አመት የራብ ዘመን ያለ ይመስላል ሰውም ሁሉ ከነሱ (ካሉበት ) በኢኮኖሚ ወደተሻለ ሀገር እይፈለሰ ነው ያለው ነፍሱን ለማዳን እና ትውልድን ለማትረፍ ከነዚህም ህዝቦች መካከል የኛው ሀገር ይገኝበታል ዛሬ በተለያየ ምድር ተብትነው ያሉይ ኢትዮፒያዊያን ይህ ነው ተብሎ በትትክለኛ ቁጥር ባይነገርም ነገር ግን ከ -50-60 ሀገሮች ላይ በትንሹ ይኖራል የሚል የራሴ ግምት አለኝ ይህ ነው ብዬ በዝርዝር ባልናገርም በአውሮፓ , በሚድል ኢስት , በኖርዝ አሜሪካን , በአፍሪካ እንዲሁም በኤሲያ እንግዲህ ዘመናትን ከሩቅ በመንፈስ አሻግሮ የሚያይ ጌታ ወደተለያዩ ቦታዎች በትኖናል ይህም ምንድነው ካልን ራሳችንን ችለን ቤተሶቦቻችንን በትንሹም ቢሆን ነፍሳቸውን በሀገራቸው ላይ ለማቆየት ነው እንግዲህ ጌታ እ /ግ ለራሳችን ጥቅም , ለቤተሰቦቻችን , እንዲሁም ለሀገራችን እንኮን እንድንተረፍ ረድቶናል ያቆብ ልጆቹን ውደግብጽ ውረዱ እና እንዳንሞት ስንዴ አምጡ እንዳለ ዛሬ አምላክ ፈቅዶ ትንሽም ሆነ ትልቅ ስንዴ ወደቤተሰባችን የምንልክ ሰዎች ትንሽ አይደለንም አምላክ ዮሴፍን በግብጽ ንጉስ በሆነው በፈዖን ፊት ሞገስ እንደሆነው በዘመኑ ከመጣውም ራብ እርሱን እና ቤተሰቡን እንዳዳነ ሁሉ ዛሬም ለኛ በየተሰደድንበት ሀገር ሁሉ ክብር እና ሞገስ ሆኖን እስራኤልን በግዜው ከመጣው ረሀብ እንደታደገ እኛንም ታድጎናል ዛሬ በየተሰደድንበት ሀገር ስራ በመስራት ከምናገኛት ገንዘብ ላይ ጥነነት እና ጸጋውን አብዝቶልን ዮሴፍ አድርጎ ለቤተሰቦቻችንና እና ለሀገራችን ጦሪ ረጂ አድርጎናል የኢትዮፒያን ታሪክ ወደ ሁዋላ ዘወር ብለን ስንመለከት ሀገራችን ልክ እንደማቱሳላ የረጅም ግዜ እድሜ ያላት ሀገር ነች ቢሆንም በዘመናት ውስጥ ሀገሪቱ ባላት የማእድን ሀብትና ንብረት ተጠቅማ ሌላውን ለመጥቀም ስትችል በየግዚያቱ አምላክ ያልቀባው መሪ ባለማግኘቷ ለተለያዩ አስከፊ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋለች አሁንም እያለፈች ነው በዚህም የተነሳ እኛም ለስደት በቅተናል በአሁኑ ሰአት ቤተሰቦቻችንን የምንረዳ ሰዎች የምናደረገው አስተዎጾ በቀላሉ የሚገመት አይደለም ይህ የምናደርገው ሁሉ በሀገሪቱ ላለው ኢኮኖሚ እድገት ቦታ ይኖረዋል ብለን እናምናለን ,,,,
ምክንያቱም ከኢትዮፒያ ውስጥ በአብሬጅ ደረጃ ሲታዩ ከአንድ እስከ ሁለት ብጠሰብ በውጭ ሀገር በተለይ በኢኮኖሚ በሰለጠነው ሀገር ይኖራል ይህም ቤተሰቡን ከመርዳት አልፎ የሀገሪቱንም እኮኖሚ
(boost) ያደርገዋል በየግዜው ከውጭ የሚላከው ገንዘብ ብዙውን ግዜ የአሜሪካን ዶላር ነው ይህንንም ለ spending ብቻ ነው እንዲጠቀሙበት የሚያደረገው
በጠሰብ ረጂውም የሚልከው የአሜሪካንዶላር ወይንም ኢሮ የ exchange value rate ትልቅ ስለሆነ ገንዘቡም በፐርሰንት ደረጃ ይሄ ነው ተብሎ ባይግመትም ወይንም በጥናት ባይደረስበትም ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች , ከኖርዝ አሜሪካን , እንዲሁም ከሌሎች ከኢትዮፕያ በኢኮኖሚ ከተሻሉ ሀገሮች ቤተሰቡን እየረዳ ያለ ኢትዮፒያዊ በብዛት ይገኛል የሚል ትልቅ እምነት አለኝ እግዛብሄር በውስጣችን ስላስቀመጠው ማንም የሌለውን የመረዳዳት ፍቅራዊ መንፈስ በውስጣችን ስላደርገ ስሙ ለዘላለም ይመስገን , በተጨማሪም በሀገሪቱ ውስጥ ያለው inflation (የዋጋ ንረት )
ከ market fluctuation እንዲሁም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ገቢ ከወጭዋ ጋር (Income Not equal Expnese)
የተስተካከለ (balance) ስለሌለ ከሀገሪቱ Gross National Income product ዝቅተኝነት አልፎ እግዛብሄር ይህንን ህዝብ (ተበትኖ ) ያለውን የህዝብ ቅሬታ ልክ እንደዮሴፍ ሞገስ እና ክብር ሆኖት ካለው እያካፈለ ቤተሰቡን ባይረዳ ኑሮ አሁን ሀገራችን ምን ትመስል ነበር ?
በሰራተኛ , ትንሽ የወር ገንዘብ ማገኘት , በጡረታ መተዳደሪያ አለመብቃት , በነጋዴ አለመበልጸግ በተማረ ሰው ስራ ማጣት በአጠቃላይ በሀገርቱ ስላለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር አለመፈታት
ኢትዮፒያን አሁን ካለችበት እጅግ አስከፊ ሁኔታ የባሰ በሰጠመች ነበር ,, ነገር ግን የእስራሌን ህዝብ የታደገ አምላክ ይህንን 7 ዘመን የስቃይ ግዜ አይቶ
ዮሴፍ በግብጽ ሀገር እራሱን ጠቅሞ ቤተሰቡን እንደጠቀመ እና እንደረዳ እኛንም ራሳችንን ችለን ቤተሰቦቻችንን ሆነ ሀገራችንን እንደንረዳ አምላክ የአሁኑ ዘመን ከሩቅ በመንፈስ አይቶ ከሀገራችን ወደተሻለ ሀገር ለችግር ግዜ ረጂ አድርጎ አፍልሶናል
አንድ ወን የአብርሀምን ዘር ሁሉ በሀብት በብልጽግና ወደተስፋይቱ ሀገር የመለሰ አምላክ እኛንም በሀብት በብልጽግና አድርጎ በጤንነት አድርጎ ወደሀገራችን ይመልሰናል ባይ ነኝ
መጽሀፍ ቅዱስ ስለሀገራችን ኢትዮፒያ ከሌላው ምድር ህዝብ ይልቅ ስለኛይቱ ሀገር ለየት ያለ መልክት አለው ከተስፋውም አንዱ ቃል ይህ ነው
1)እናንተ የእስራኤል ልጆች ለኔ እንደኢትዮፒያ ልጆች አይደላቹህም ይላል ትንቢተ አሞጽ 9, 8
እ /ግ ለሀገራችን ያለውን ፍቅርና እንክብካቤ ያሳያል
የኢትዮፒያ ልጆች ልክ እንደእስራል ልጆች ናቸው
ይህች በተለያዩ ጭካኝ መሪዎች በኩል እየተጎዳች እና እየተገረፈች ያለችው ሀገር እ /ግ አምላክ ህዝቧን በመንፈስ እየጠገነ እና እያጽናና ይገኛል
በኢትዮፕያ ምድር እንደተስፋ ቃሉ መሰረት አንድ ቀን በሩቅም ይሁን በቅርብ አምላክ እውነተኛ ንጉስ ይቀባላታል የሚል ተስፋ እና እምነት አለኝ አምላክ እ /ግ ለሀገራችን ለየት ያለው አላማ አለው ጌታም እድሜ ከሰጠን ትልቆን ኢትዮፒያ አድጋ እና በልጽጋ የምናይበት ቀን እሩቅ አይሆንም ባይ ነኝ ጌታውን የጠበቀ እንደሚከብር ሁሉ ኢትዮፒያን ጌታ በብልጽግና ያከብራታል በተዋረደችበት ቦታ ሁሉ ታላቅ ክብርን ታገኝለች ,

2)እንባቆም በትንቢቱ እንዲህ ይላል ምራፍ 2+7
የኢትዮፒያ ድንኮኖች ሲጨነቁ አየሁ
በዚህ ዘመን በኢትዮፒያ ውስጥ ስንት ድንኮን ( ሰው )
ይጨነቃሉ በራብ , በዕርዛት , በጤና ማጣት እውነተኛ ፍርድ እና ፍትህ በማጣት የተጨነቁ ብዙ ናቸው ይህ እውነተኛ እና ሁላችንም የምናውቀው የሀገራችን ቁስል ነው ስንት ሰው የዕለት ምግቡም እንኮን አጥቶ ሳይጠግብ የሚያድር , ስንቱስ ህዝብ ነው በቀላሉ መታከም በሚችል በሽታ የምድርን ኑሮ ሳያጣጥም ወደ መቃብር የሚገባው በሀገራችን በሚደረገው ግፍ እና ስቃይ ሁሉ የሚመለከተውን ሰውን ሁሉ ከፍርድ ሊያስመልጠው አይችልም ሰው የዘራውን ያንን መልሶ ያጭዳል እና .
3)ኢትዮፒያ እጆቾን ወደ እ /ግ ትዘረጋለች
እንባቆም በትንቢቱ ላይ በሩቅ ሲጨነቅ ያየውን ድንኮን ( ህዝብ ) በፖለቲካው በኢኮኖሚው አለም እውነተኛ እና ልክክለኛ ፍርድ ስላጣ ከስህተቱ በመማር ዛሬ ወደቅን ፈራጅ ጌታ እጁን እያነሳ ይገኛል ለኢትዮፒያ ተስፋዋ እግዛብሄር ብቻ ነው ምክንያቱም የተስፋ ሀገር ስለሆነች አምላክም በምድር ላይ ብዙ ድንቅ እና ታምር ወደፊት ስለሚሰራባት በራስ ወደድ ወይንም በሰልፊሽ መሪ ወደፊት አትመራም
ለኛ ኢትዮፒአይዊያን ሁሉ አምላክ ስላደርግለን ታላቅ
ቸርነትና ለማያልቀው በጎነቱ በአስከፊው ሰባቱ የራብ ዘመን ለታደገን እና እየታደገን ላለ ለዘላለም አምላክ ክብር ይሁንለት

ጌታ ያለው አይቀርም