lunedì

ሰሞኑን በጣሊያን ሚ/ምክርቤት የውጪ ዜጎችን በሚመለከት


03 12 06
በጣሊያን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰሞኑን የፀደቁትን የውጪ ዜጎችን የሚመለከቱ ሁለት አዲስ ሕጎችና የውስጣቸውን ደንብ ፍሬ ነገሮቹን ብቻ መርጠን ከዚህ በታች አስፍረናል። ሁለቱ ዋና ዋና አዲስ ሕጎችም በአለፈው የበጋ ወቅት በጠረቤዛ ላይ ለውይይት ቀርበው ከነበሩት መካከል ይገኛሉ። እነዚህም
1)የካርታ ዲ ሶጆርኖ
2)የቤተስብን ማስመጣት የሚመለከቱ ናቸው።
ከሚያፀድቋቸው ሌሎች ህግጋትና አንቀፅ ጋር በአንድላይ በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት ከላይ የተጠቀሱትንና ያፀደቁትን የሁለቱን አስቀድመን አጭር ይዘታቸውን እናቀርባለን።
.
Carta di Soggiorno - (ካርታ ዲ ሶጆርኖ)
1 - በጣሊያን ከ5 ዓመት በላይ የመኖሪያ ፈቃድ የነበረው ማመልከቻ ከአስገባ ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንደሚሰጠው እና ይህም በሁሉም የአውሮፓ ሕብረት ኣባላት ሀገሮች ውስጥ ሥራ የመሥራት ዕድል የሚክፍትለትና በኣባላት ሀገር እንደፈለገው የመዘዋወር ፍቃድ እንዲኖረው ያደርገዋል።
2 - ቤተሰቦቹን ካርታ ዲ ሶጆርኖ እንዲኖራቸው ለማድረግ ማመልከቻ የሚሲያስገባ ከሆነ ቤተሰቦቹን በአስተዳዳሪነት የሚያስተናግድበት የመኖሪያ ቤት ሁኔታ በክፍለሀግሩ የተደነገገውን መመዘኛ ማሟላት አለበት። ይኸውም የሕብረተሰቡን የጤናአጠባበቅ ሥራዓት ይዞ የሚከታተልና ደንቡን የሚጠብቅ መሆን ሲገባው ይኸውም ግዴታውም ጭምር ሆኖ ይገኛል።
3 - ሌላው ደግሞ ይኸው መኖሪያ ቤት ለሕይወት አስጊነት የሌለው፣ በውስጡ መኖር የሚቻልበትን ሁኔታዎችን የሚያሟላ መሆኑን መረጋገጥ አለበት። ማሳሰቢያ
4 - ይህን ካርታ ዲ ሶጆርኖ ለማግኘት ተመኑ የተወሰነ የዓመት ገቢ እንዲኖረውና ለዚህም አስፈላጊውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርበታል።
5 - በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የነበሩ፣ በወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸውን እንዲሁም የሕብረተሰቡን ፀጥታን ያጎደሉና ከዚህ በፊት precedenza ያለባቸው ይህንን የcarta di soggiorno ፈቃድ ማግኘት አይችሉም።
.
Recongiungimento familiare (ቤተሰብን ለማስመጣት)
1 - ልጅ ያለው እድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ለማስመጣት ብዙ ማስረጃዎችን እንዲያሳይ አይጠየቅም። እንደገናም ወላጆቹን ለማስመጣት በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆን ይገባቸዋል። (65 ዓመት ...) ይህ ደግሞ ብዙ ጥያቄና ክርክር ይሚያስነሳ ይመስለናል። ለማንኛውም እዚህ ካስመጣ በኋላ (a carico suo) ወይም የአስተዳዳሪነቱን ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ መሆን አለበት።
2 - ከዚህ በፊት በመኖሪያ ቤት ስፋትና ጥራት ይወስን እንደነበረና ንገርግን አሁን ይህ ሁሉ እንዲቃለል ተደርጎ ASL የሚጠይቀውን requisiti ማሟላት አለበት
3 - በየክፍለሀገሩ የተተመነውን የዓመት ገቢ ለማሳየት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል።
4 - ልጅ ያለው ማንኛውም የውጪ ዜጋ እዚህ በአለው የጤና አጠባበቅ ስርዓትና ክትትል በማድረግ ግዴታውን እንዲወጣ መሆን አለበት።
5 - ጥገኝነት ጠያቂ ( refugiato ) ከሆነ የዓመት ገቢና የመኖሪያ ቤት የግድ እንዲኖረው አይጠየቅም። ነገርግን ፈልሶ የመጣበት ሀገር እና የጣሊያን የድንበር ስምምነት ወሳኝነት ሊኖረው ይችላል።

Nessun commento: