giovedì

ከመሰለፍህ በፊት መሰለፊያዉን እወቅ


ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
በጣሊያን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት (permesso di soggiorno / carta di soggiorno) ለማሳደስም ሆነ አዲሱን ለመዉሰድ የሚያስችለዉን ማለትም ባለፈዉ ጊዜ የወጣውን አዲስ መመሪያ በተመለከተ ሰሞኑን ብዙ ሰዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ስልክ ደዉለዉ ይጠይቁኛል::
ጥያቄዎቹን ሙሉ በሙሉ በዚህ መድረክ ለመመለስ ጊዜ ቢያጥረኝም ለጥቂቶቹ መልስ ይሆናሉ በማለት የመመሪያዉን ይዘት ከዚህ ቀጥሎ አጠር ባለ መልኩ ለአንባቢያን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ:: በመጀመሪያ ደረጃ ከመሰለፍ በፊት ዬት መስሪያ ቤት ሄዶ መሰለፍ እንደሚገባ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል::
በጣሊያን ለመኖር የሚያስችል የዉጭ አገር ዜጎች ጉዳይ ሁሉም በፖስታ ቤት አይጠናቀቅም:: ይበልጡ አጅ በፖስታ ቤት ሲከናወን ጥቂቱ በፊት እንደነበረዉ በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ እንደነበረዉ ይቀጥላል:: አጉልና ከንቱ የማያልቅ ሰልፍ ተሰልፎ ጊዜና ጉልበት እንዲሁም ገንዘብን ከማጥፋት ሌላ የአእምሮ ህመም በሽታ ከመሸመት መጠንቀቁ ተገቢ ነዉና በተቻለ መጠን ጠይቆ ትክክለኛ መረጃ (እንፎርሜሽን) ማግኘት ያስፈልጋል::
.
በፖስታ ቤት ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ማሳደስ (permesso di soggiorno);
- ልጅ አስመጥቶ ማሳደግ;
- ጣሊያን ተወልዶ ወላጆቹ ሊያሳድጉት ያልቻሉ ልጅ;
- የማደጎ ልጅ አስመጥቶ ለማሳደግ;
- የፓስፖርት ለዉጥ;
- ስራ አጥ ስራ ፈላጊ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት እድሳት;
- የመኖሪያ ወረቀት ለአዉሮፓ ህብረት ዜጎች (carta di soggiorno cittadini U.E.);
- የመኖሪያ ወረቀት ለዉጭ አገር ዜጎች (carta di soggiorno cittadini stranieri);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት መቀየር (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (permesso di soggiorno);
- የመኖሪያ ወረቀት ኮፒ መጠየቅ (carta di soggiorno);
- ቤተሰብ;
- ቤተሰብ እድሜያቸዉ ከ 14 እስከ 18 አመት;
- የግል ስራ (lavoro autonomo);
- የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato);
- በተለያዩ ምክንያቶች የስራ ፈቃድ;
- ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ (lavoro subordinato - stagionale);
- ጉዞ ወደ ዉጭ አገር;
- ሃይማኖት;
- የፖለቲካ ምርጫ;
- ትምህርት;
- ጉብኝት;
- የሙያ ማሻሻይ ስልጠና ወዘተ ...

በኩዌስቱራ የእሚግሬሽን ቢሮ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳዮች ዝርዝር:-
- ንግድ ወይም ብዝነስ ነክ ስራዎች;
- ህክምና;
- እስፖርት ዉድድር;
- እርዳታና ማስተባበርያ;
- የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ;
- ህግና ፍትህ;
- ከ 14 አመት በታች እድሜ ያላቸዉ ልጆች;
- ከጣሊያን አገር ዉጪ ሰዉ በዋስትና ማስመጣት::

በዝርዝሩ ላይ ማብራርያ ካስፈለገዎት በሚከተለዉ የመገናኛ ዘዴ መጠየቅ ይቻላል::
zeleke_eresso@yahoo.it
Tel. 3395764139


1 commento:

Anonimo ha detto...

ሙኡከራ