mercoledì

በጣሊያን የቀድሞውን የውጪ ዜጋዎች ፍልሰት ሕግ የሚያድስ ረቂቅ ተቀመረ


Da Bossi/Fini ad Amato/Ferraro?
(የረቂቁ ነጥቦች)

የሚገቡት ቁጥር ገደብ?
የሚገቡት ቁጥር ጣራ በየ 3 ዓመት አንድ ጊዜ ይወጣል። ከእነዚህም መሀክል በየዓመቱ የተወሰኑትን ያህል እንዲገቡ ይደረጋል። ምንም እንኳን በ 3 ዓመት አንድ ጊዜ የሚወሰነው መጠን ጣራ ቢኖረውም ይህ ቁጥር ገደብ ውስጥ የማይገቡ ወይም የማይመለከታቸው ይኖራሉ። ለምሳሌ ልዩ የዕጅ ሙያ ወይም ጥበብ ያላቸውን፣የጥናት ተቋማት ባለሙያተኞች የሆኑትን በsponser ወይም ተወክለው የሚላኩትን ልዩ ችሎታዎችና የተማሩ ወይም ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን፣...ወዘተ...
Nullaosta ለሌሎችም?
ጣሊያን ሀገር ሠርተው ለሚኖሩት በሙሉ Nullaosta መብት እንዲኖራቸው ይደረጋል። ይህ ..... ለኮልፍ እነ ለባዳንቲዎች (colf e badanti) የሚሰጥ ነበር።
የጣሊያን ዲቪ???
ጣሊያን ለሥራ ለመግባት ከመጣበት ወይም ከራሱ ሀገር መንግስት የግድ ማመልከቻ ያደረገ እና የተመዘገበበት መዝገብ ያለው ይሆናል። ይኸው መዝገብ ደግሞ እዛው በአመልካቹ ሀገር መንግስት ለሚገኙት የጣሊያን ዲፕሎማቲክ ጽህፈት ቤት የተላለፈላቸው መሆን ይገባዋል።
Sponsor
በኢኮኖሚ በቂ መተዳደሪያውን የሚችል ተወካይ ወይም ጋራንሲ የሚሰጠው ከአለው ወደ ጣሊያን ሊልከው ይችላል። ወካዩ ወይም ዋስ ሊሆኑ ከሚችሉት መሀከል አንዳንዶቹን ለምሳሌ ያህል ልንጠቅስ እንወዳለን። 1 - የመንግስት ድርጅቶች (በተወካዩ ሀገርም ሆነ በጣሊያን ሀገር)2 - የሠራተኞች ማህበር ጽህፈት ቤቶችና ድርጅቶች (sindacati) 3 - ፓትሮናቲ (Patronati)4 - የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች (Associazione...)5 - ግለሰቦች (በየዓመቱ አንድ ሰው ብቻ)6 - ...ወዘተ...
Autosponsorizzazione
ሀብትና ገንዘብ ያለው ወይም ራሱን የሚችልበትን መተዳደሪያ ያለው መሆኑን ካስመሰከረ እሱ ራሱ ለራሱ ወክልናና ዋስ ሆኖ መስራት ይችላል።(ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ)
ቪዛና የመቆያ ፈቃድ
ወደፊት ጣሊያን ለሚመጡት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ፈቃድ ለማውጣትና ላማሳደስ የነበረውን ውጣ ውረድ እንዳይገጥማቸው ብለው በማሰብ በቪዛው አማካይነት ፍቃዱም እንዲሰጣቸው ይደረጋል። ይህ ቪዛ የመግባት ፍቃድ ብቻ ሳይሆን እንደመቆያ ፈቃድም ሆኖ የሚያገለግል መሆኑ ነው። ቪዛው ለረጅም ጊዜ የመቆያና የመኖሪያ ፈቃድ ሆኖ የሚያገለግል ሊሆን ነው። በዚህም ምክንያት እንደ permesso di soggiorno በየጊዜው ለማሳደስ በሰለፍ የሚያንከራት አይኖርም ማለት ነው። በዚህ የመቆያ ፈቃድ አማካይነት ለመጀመሪያ ጊዜ የስራ ኮንትራት ለሚኖረው እንደኮንራቱ የጊዜ እርዝመት ታይቶ የመቆያው ፈቃዱን በማራዘምና ወሰን በማድረግ ነው። ለምሳሌ - ሀ/ የ 6 ወር የሥራ ኮንራት ላላቸው 1 ዓመት የመቆያ ፈቃድለ/ የ 1 ዓመት የሥራ ኮንትራት ላላቸው የ 2 ዓመት የመቆያ ፈቃድሐ/ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ኮንትራት ላላቸው ወይም የግል ድርጅት ለሚያንቀሳቅሱት በየ 3 ዓመት የሚያሳድሱት የመቆያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል።
ማሳሰቢያ- (የሥራ ኮንትራታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ሲያሳድሱ የመቆያ ፈቃድ በእጥፍ ይራዘምለታል)
ያለስራ ለተቀመጠ
ሥራ በመፈለግ ላይ ሆነው የመቆያው ጊዜ የወደቀባቸው ወይም ያለ ሥራ ለተቀመጡ የውጪ ዜጋዎች ደግሞ የመቆያው ፈቃድ እንዲራዘምላቸው የሚያደርጉ ሁኔታዎች አሉ።
ለምሳሌ -
* መተዳደሪያውን የሚችል ከሆነ
* Sponsor ወይም የመቆያውን ጊዜ ለማራዘም የሚያስችለው ዋስትና የሚሰጠው ወካይ ያለው ከሆነ፣
* በሰበዓዊ ተግባሮች የተሰማራ፣
* የወንጀለኛነት record የሌለው፣
* ባህሪው፣ መንፈሱና ፀባዩ ህብረተሰቡን የማያስከፋ ከሆነ፣
* ...ወዘተ...
የመቆያ ፈቃድ ለማውጣትና ለማሳደስ ዋናውን አገልግሎት የሚሰጠው የፖስታ ቤት መሆኑ ቀርቶ ወደ ማዘጋጃ ቤት ቢሮዎች ይሆናል። እንግዴህ መዝገቦቹ ከአንዱ ቢሮ ወደሌላው ሲተላለፉ ያው የተለመደው የጊዜና የሥርዓት ትራፊክ እንደማይገጥም ተስፋ እናደርጋለን። ...........
መብት
ጣሊያን የአውሮፓ ህብረት አባል እንደመሆኗ መጠን ሀብረቱም በStrasburgo ጉባዔ ላይ የወሰነውን በሥራ ላይ ታውላለች። በዚህም ምክንያት "ማንኛውም የውጪ ዜጋ በሚገኝበት ሀገር የማህበራዊ ኑሮ ላይ የመካፈል መብት እንዲሰጠው ይደረጋል። በተለይም ኑሮውን ከአምስት ዓመት በላይ ያደረገ ከሆነና በህጋዊ መንገድ በመስራት የኢኮኖሚ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ስለሚገኝ የሀገሪቱም የፖለቲካ ሂደት ላይም ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል)
ለምሳሌ ድምጽ የመስጠትና የመምረጥ መብት፣ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ እስካለው ድረስ ክህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ ውህደት ሊያረግ ይችላል። ለምሳሌ
* ሀገሪቱ ለዜጋዎቿ የምትሰጠው የጤና አገልግሎቶች፣
* ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ መብቶች
* የጡረታ አበልና ድጎማ የመሳሰሉትን ማግኘት
* ከሁለት ዓመት በለይ የተቀመጠ ከሆነ ለህብረተሰብ የሚሰጡት ማህበራዊ አገልግሎቶች አይነፈገውም
* የሚያስተዳድራቸው 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆቹ በራሱ የመኖሪያ ፈቃድ ሥር ይሆናሉ (ልጆቹ 18 ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ የመኖሪያ ፈቃዳቸው በቤተሰብ ምክንያት ይሚባለውን እንዲያወጡ ይደረጋል)
Rimpatrio
ወደ ሀገራቸው መመለሻ የትራንስፖርት ወጪያቸውን ለማይችሉ በሚወጣው ፕሮግራም ተመዝግበው ወደሀገራቸው ለሚላኩ ከሁሉም በፊት በድጋሚ ጣሊያን ሀገር የመመለስ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ነገርግን ለህብረተሰቡ አደገኛ የሆኑትን እንደሁኔታቸው እየታየ ወደመጡበት ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋል።
CPT
ብዙ አከራካሪና ስምምነት ያልተደረሰበት ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል።
1 - Struture aperte በተወሰኑ ስዓቶች መውጣትና መግባት የሚቻልበት (ማንነቱንለማወቅ በሚጠየቅበት ጊዜ የሚተባበር ከሆ)
2 - Struture chiuse ደንብና ሕግን ለማይከተሉና ለማይተባበሩ (ነገርግን 60 ቀን በላይ በውስጡ መቆየት የለባቸውም)
..................///..................

ይኸው የሮማኖ ፕሮዲ መንግስት ከተቃዋሚው ፖለቲካ ክርከር የሚይዝበትና አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ ያገኛቸው የውጪውን ዜጋዎችን የውስጥ መስተዳደሪያ ድንብ መለወጡ ሳይሆን እየፈለሰ ለሚገባው የስደተኛውን ቁጥር መወሰኑ ነው። አስተዳዳሪዎቹና መሪዎቹም የሚሉት ዋናውና ወቅታዊው ጥያቄ እየፈለሰ የሚገባውን ስደተኛ ቁጥር በየ 3 ዓመት የሚያስፈልጉትን ቁጥር በመወሰንና ከ እነዚህም ውስጥ በየዓመቱ እንዲገቡ ማድረግ ነው። እስከሚቻል ድረስ ስርዓትን በማሲያዝ መቀበል እንችላለን። የዓለም አቀፍን የሰበዓዊነት መብቶችን እንዲከበር ለማድረግ በሚቻለን መንገድ ከመጣር ወደኋላ አንልም።" ...........በተቃራኒው ደግሞ የተቃዋሚው የፖለቲካ መሪዎች "ይህ መንግሥት የሚከተለው የፍልሰት ፖሊሲ ወደፊት ሀገሪቷን አስጊ ሁኔታ ላይ ይጥላታል" እያሉ ንዝንዛቸውን ቀጥለዋል። እንደውም አንዳንዶቹ ባለሥልጣናት "በሀገሩ ያልተመቸው ሁሉ ጣሊያንመግባት የለበትም" የሚል አቋም ይዘዋል። የሀገር አስተዳደር ሚንስትሩ ወደ ሀገሩ የገቡ ስደተኞች አሀዝ ባለፈው ዓመት መቀነሱን አመልክተው ስድሳ ሚልዮን ወደ ሚኖሩባትና በየአመቱም አሥር ሺህ ክላንዴስቲኒ ስደተኞች ወደ ሚገቡባት ኢጣልያ ከሰሜን አፍሪቃ በጥቂት ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች መግባታቸውን ማጋነኑ ባልተገባ ነበር ብለዋል። በተጨማሪም ይህ የፍልሰትን የሚመለከተው አዲስ የሕግ ቅምር የያዘው አቋም ግልፅ መሆኑን በተደጋጋሚ ያስረዳሉ። ሌላው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ የሚገኘው የጥቁር ሥራን (Lavoro nero) የማስወገዱ ጉዳይ ነው። በየፋብሪካውና በቤተሰብ አገልግሎት ውስጥ ብቻ የጥቁር ሥራ እየሠሩ ያሉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስለሆኑ ሁሉም regolarizzare መደረግ አለባቸው። ይህንን በጊዘው ስራዓት ማሲያዝ ያስፈልጋል። ለዚህም በየክፍለሀገሩ የሚገኙት የጣሊያን ማዕከላዊ አስተዳደር ክፍሎች በጥቁር ሥራ ላይ የተሰማሩትን የውጪ ዜጋዎች ሙሉ በሙሉ በ regolare ሥራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ሁሉም ተሳትፎ ማድረግና ይሚቻለቸውን ግዴታ እንዲወጡት ብዙ ይጠበቅባቸዋል" ......።
ለማጠቃለል ያህል... ጣሊያን በአለፈው መንግስቷ ከሌሎቹ የአውሮፓ የጋራ መርሕ ወደኋላ ትገኝ እንድደነበረና ብዙዎቹ የአውሮፓ ሕብረት አባላት ሀገሮች ከሚከተሉት መርሆዎች ጋር አንድ አይነት መስመር እንድትይዝ መሆን አለበት። ያለንበት ዘመን ደግሞ ዓለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር የሚደረግበት ዘመን ስለሆነ እንዲሁም ጊዜው የነፃ ገበያ ወቅት በመሆኑ ህዝቦች ከአንዱ አገር ወደ ሌላው ለስራ መሰደዳቸው ጤነኛ አካሄድ ነው። አውሮፓውያን መሪዎችና ፖለቲከኞች ስደተኛውን እንደ አደጋ ሳይሆን ጠቃሚ የልማት አስተዋፅኦ ሊያበረክት የሚችል ሀይል አድርገው መመልከትና እንዲህም የውጭ ዜጎች ወደ አውሮፓ የሚገቡበትን ስርአት በደንብ ማስተካከል ይገባታል።...

Nessun commento: