domenica

በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልዶች

……....ከምንወደውና ከሚናፍቀን ቤተሰብ መራቃችንና መለየታችን፣ የብቸኝነት ኑሮን ስለምንገፋ፣ የሩጫ ኑሮ ስለምንኖር፣ ኑሮው የማይደላ፣ እረፍት የሌለውና ለመንፈስ የማይሞላ በመሆኑ ድብርቱ እንዳለ እናውቀዋለን። በዚህም ምክንያት የሣቅ ችግር አለብን አይደል! ታዲያ ይህንን ድብርት ለማላቀቅ ባገኘነው ዘዴ በመጠቀም አንዳንዴም እንሣቅ እስቲ! ፈገግታ ጥሩ ነው። በስራና በትምህርት የተጨነቀን አዕምሮን አንዳንዴም ለማዝናናት ያህል ከማህደሬ ውስጥ ቆንጥሬ ያወጣኋቸውን ቀልዶች አንብቡና በእኔ ሞት እስቲ ሳቁልኝ:: ቀልዶቹ በሙሉ ጣሊያን ሀገር ያለነውን አበሻ ነው የምመልከተው

PimpingYourSpace.com. All you can need.


ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.)
***********************************************************************

.
……....ታዲያ እንዲሁ ሡርቶ ራሱን ለማስተዳደርና ድሃ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይጓጓ የነበረ ወጣት አበሻ ጸሎቱ ሰምሮ እዚሁ ጣሊያን ይመጣል:: ለመስራት ካለው ጉጉት የተነሳ ጣሊያንን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች እየሄደ ሥራ ማፈላለጉን ተያያዘው:: ዕድሉ አልቀና ብሎት ለረዥም ግዜ ያለሥራ መቀመጥ በመገደዱ ይጨነቅ ጀመር::
ይህንን ጭንቀቱን ያየ አንድ ጣሊያናዊ ለጎብኚዎች መዝናኛ ተብሎ የተሠራ የዱር አራዊት የሚገኙበት ቦታ (zoo) ሄዶ ሥራ እንዲያገኝና እንዲሞክር ይነግረውና እዚሁ ጣሊያን ሀገር በምትገኘው pistoia የምትባለው ከተማ ይሄዳል:: "zoo di pistoia" ውስጥ ገብቶም ሥራ አላችሁ ወይ ብሎ ይጠይቃል:: በአጋጣሚም ምንም የሥራ ልምድ የማይጠይቅ የግማሽ ሰዓት ሥልጠና ብቻ የሚያስፈልገው ሥራ ያገኛል::
……....ሥራውም የዱር አራዊት ምስል ማስኬራ (maschera) አጥልቆ በብረት አጥር ውስጥ ገብቶ እንደተመደበበት እንሰሳ መሆን ነው:: አጅሬም በአጋጣሚ የተመደበው እንደ ጎሬላ ዝንጀሮ ሆኖ እንዲሠራ ነበርና የተሰጠውን የ30 ደቂቃ ስልጠና በብቃት አጠናቆ እንደ ዝንጀሮ መንጎማለል፣ መጮህ፣ መፈናጠር፣ ብቻ ምን አለፋችሁ ሁሉን መሆን ችሎ ወደ ሥራው ተሰማራ:: ጠዋት ሄዶ እስከ ማታ በብረት አጥር ውስጥ ሲንጎማለል ውሎ ማታ ወደ ሰውነቱም ወደቤቱም ይመለሳል:: ረዥም ሰዓት ስለሚሠራና ክፍያውም ጥሩ ስለሆነ በአጭር ግዜ ውስጥ ይጓጓለት የነበረውን ሁሉ በእጁ ማስገባት በመቻሉ ጭንቀቱ ወደ ፈጹም ደስታ ተለውጠ:: ሥራውንም ተላመደው::
……....ታዲያ መቼም በየቀኑ ለ12 ሰዓት ከአራዊት መንጋ ጋር መዋል ቀላል አይደለም:: ከዚያ አለቃውም ጉብዝናውን አይቶ ስለተደሰተ ብር ጨምሮ ሰጠው። ይህቺን ሰርቼ ብር ከተጨመረልኝማ ሌላም ነገር ሰርቼ የበለጠ አገኛለሁ አለና በማግስቱ መገለባበጥ ጀመረ። አጅሬውም ሲገለባበጥ ሳያስበው አንበሶች ያሉበት ወስጥ ተገልብጦ ገባ። አንበሶቹን እንዳያቸው ደንግጦ "እመ ብርሀን ከዚህ ጉድ አውጪኝ አለቀልኝ" እያለ በልቡ ሲያወራ ወዲያው የውስጡ ሠራተኞች የሆኑት ቶሎ ብለው ገብተው ወዲያው ይለያይዋቸዋል።
……....ታዲያ አራዊት ያው አራዊት ነውና ሳት ብሎ የሾለከ ቀን አያድርስ ነው:: አጅሬም ያው እንደገና የፈራው አልቀረም አንድ ቀን በአንበሳውና በሱ መካከል ያለው በር ሳይዘጋ ተረስቶ ኖሮ አያ አንበሴ ጎልመም ጎልመም እያለ ወደ እሱ መጣበት። አጅሬም ዝንጀሮነቱን እረስቶ "ወይኔ ጉዴ ወይኔ ምነው በቀረብኝ" እያለ በጭንቀት የሚገባበት ጠፍቶት አንዱ ጥግ ብረት ላይ ይለጠፋል:: አፉን አውጥቶ እንዳይጮህ ጎብኝዎች ስላሉ ተቸግሮ በጭንቅ ውስጥ እንዳለ ሳያስበው "ገብርኤል አውጣኝ" ሲል አንበሳው አማርኛ ሲናገር ጊዜ ቆም ብሎ "እንዴ! አበሻ ነህ እንዴ? "ብሎት እርፍ:: አንበሳ ከመቼ ጀምሮ ያወራል ብሎ ሲደነግጥ ለካስ አያ አንበሴዎቹም የኛው ሰዎች ነበሩ::
- ድሮስ ለአንበስነቱ ማን ብሎን!!
- ዝንጀሮነቱም ቢሆን የእንእጀራ ነገር ሆኖ እንጂ::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.
አንድ ሚላኖ የሚኖር አበሻ ነው እናትና አባቱን ካገርቤት አስምጥቶ ከተማውን እያዞረ ያሳያቸው ጀመረ:: ታዲያ ወደ የግድግዳዉ ብቻ ጠጋ እያለ በbancomat ይኼንን euro ከግድግዳው ሲያስፈተልክ ያዩታል:: አባትዬው ግድግዳው ሁሉ ገንዘብ ሲተፋ አይተው በጣም ተገርመውና ተደንቀው ይሰነብታሉ:: ሳምንታት ያህል ቆዩና ወደ አገርቤት የመመለሻቸው ቀን ደረሰና እሳቸውን በመሸኘት ላይ እንዳለ ከአንዱ ግድግዳ ተጠጋና 500 euro አውጥቶ "ይህንን ለኪስዎ ብዬ ነው" ብሎ ይሰጣቸዋል::
አባትየውም በጣም አዝነው "ምነዉ ልጄ ዝም ብሎ ከየግድግዳው ዝም ብሎ ለሚብዋተተዉ ነፈግ ነፈግ የምታደርገው ለማን አስበህ ነዉ?" አሉ ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.
"እግዜር ሆይ!! እንደው ምናለበት totocalcio እንዳሸንፍ ወይም ሎተሪ እንኳን እንዲደርሰኝ ብታደርግ" እያለ ሁልግዜ በማማረር የሚጸልይ አበሻ ነበር:: ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ሳያቋርጥ እየደጋገመ በመሄድ ፀሎቱን እያለቀሰ ተያያዘው:: ታዲያ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማልቀስ የተለመደ አይደለም:: እናም የቤተክርስቲያኑ parrocco ሁልጊዜ ማልቀሱን አይተው ያሳዝናቸውና እግዜርን... "ይህ ሰው ሁልግዜ እየመጣ ይጸልያል:: ስምህንም እየጠራ ያለቅሳል:: ታዲያ ምን አለበት ጸሎቱን ብትሰማለት? ምኞቱን ብታሳካለት?" ይላሉ:: እግዜርም መልሱን ሲሰጣቸው "ሁልግዜ እየመጣ እንደሚጸልይ አውቃለሁ:: ታዲያ እኔ ምንላድርገው? መጀመሪያ totcalcioውን ይጫወታ!!!" አላቸው ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.
ሁለት carabinieri አንዱን አበሻ መንገድ ላይ ያስቆሙትና documento አሳየን ቢሉት
- አበሻው - "የለኝም"
- soggiornoህን አውጣ ሲሉት
- አበሻው - "እሱም የለኝም"
- "ፓስፖርትህን አሳየን"
- አበሻው - "እሱም የለኝም"
carabiniereው እንዴት አርጎ እዚህ አገር ያለመረጃ ሊኖር ይችላል ብሎ ያው CPT ክመወሰዱ በፊት ልምርመራ ቀርቦ እንዲጠየቅ ተድረገ።
carabinieri - "እድሜህ ስንት ነው?"
አበሻ - "28" ይላል::
carabinieri - "እርግጠኛ ነህ?"
አበሻ - "ቆይ ላስብበት" ይልና ቆይቶ " 28 አይደለም ተሳስቼ ነው። 24 ማለቴ ነበር" ይላል::
carabinieri - "ግን እርግጠኛ መሆን አለብህ" ሲባል
አበሻ - "አሁንም ላስብ ጊዜ ስጡኝ" ይልና "20" ይላል:: እንዲህ እያለ እየወረደ ቢያስቸግራቸው አንዱ ከሳሽ carabinieriው ብድግ ይልና "ክቡር giudice ሆይ! እኔ የምጠይቀው ነገር ቢኖር ይሄ ሰውዬ ተመልሶ ወደ እናቱ ማህጸን ከመግባቱ በፊት ያለው እድሜ ይመዝገብልኝ" አለ ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.
እዚህ ይኖር የነበረ አበሻ ለሁለት ዓመት ሶጆርኖ ጠብቆ ስላላገኘ ትንሽ በአእምሮ በጨጭ አርጎት ጓደኞቹ ግንዝብ አዋጥተው ውደ ሀገር ቤት ይልኩታል። ከእዚህ ከላኩት ጓደኞች አንዱ ከወራት በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ጤንነቱን ለማወቅ ብሎ ስልክ ይደውልና ከእናቱ ጋር ሲያወራ ...
ስልክ ደዋይ - "ተሻለው ወይ?"
እናትዮው - "እድሜ ለእናንተ ጓደኞቹ:: ተጋግዛችሁ ባትልኩልኝ ኖሮ ልጄ በስው ሀገር ሞቶ ይቀር ነበር"
ስልክ ደዋይ - "አይ! እዚህ እኮ መተዛዘን መረዳዳት የተለመደ ነው:: እንኳን ይሄ ቀርቶ ሌላም ይደረጋል"
እናትዬው - "ግን እኮ ወዲያው እንዳመመው ብትልኩልኝ ኖሮ በጣም ይድን ነበር" ሲሉት ጊዜ
ስልክ ደዋይ - "አይ እማማ ወዲያው እንደታመመ ይላክ ከተባለማ ጣሊያን ውስጥ ያለው አበሻ ሁሉ ይላክ ነበር" አላቸው::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************.
.
ሮማ ከተማ ለgay matrimonio ድጋፍ በወጡ በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ግብረሰዶሞች መሐከል አንዱ ሀበሻ የሀገራችንን ባንዲራ ከፍ አርጎ ይዞ እያውለበለበ ከፊት ረድፍ ሆኖ ሰልፉን ይመራል:: በዚህም ብቻ ሳይወሰን አጅሬው ሌሎቹ የሚሉትን መፈክር ቀደም ቀደም እያለ ድምጹን ከፍ አርጎ ያስተጋባል። ይህንን የአዩና የተበሳጩ አበሾች "ይህ የኛው ጉድ አይደል" ብለው ...
"አንተ ስማ! እንዴት የአገራችንን ባንዲራ ይዘህ ከomosesuale ጋር ሰላማዊ ሰልፍ ተወጣለህ? ቢሉት ...
"ሞኛችሁን ፈልጉ! ለgay መጋባት ከተፈቀድላቸው ደስታዬን አልችለውም" ...
"ታዲያ እነሱ ስለተጋቡ አንተን ይህን ያህል ያስደስተሃል እንዴ?" ...
"እንዴታ!! እኔም ወንድሜን አግብቼ ከኢትዮጵያ አስመጣው ነበር" ... ብሏቸው አረፈው::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሴትየዋ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ጣሊያን ይመጡና በዚሁ ቀርተው ጣሊያን መኖር ከጀመሩ ዓመት አለፋቸው:: በጠና ይታመሙና ሆስፒታል ገብተው ትንሽ ጊዜ ብቻ እንደቀራቸው ሀኪሞች ቁርጡን ነገርዋቸው። ያው እንግዴ ከመሞታቸው በፊት አንድ ቀን ልጆቻቸው እንዲህ ብለው ይጠይቋቸዋል:: እማዬ ድንገት ከሞትሽ የት እንቅበርሽ? እዚሁ ጣሊያን ውይስ ኢትዮጲያ ይሻላል? ብለው ሲጠይቁቸው እናትዬውም "አይ ምነው ልጆቼ! ያው ስሞት ሶርፕሬሳ (sorpressa) ብታረጉኝ" አሉዋቸውና ቁጭ::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
እናት ከአዲስ አበባ በተዘዋዋሪ ስልክ ሚላኖ ለሚኖረው ልጃቸው ደውለው ሲያወሩ ቆይተው
ልጅም ለቤተሰቦቹ ጤንነት ጠይቆ ሲያበቃ "ምነው እማዬ በደህና ደወልሽ ወይ?" ብሎ ቢጠይቃቸው
እናት ፡-"አይ ልጄ ትንሽ ገንዘብ ቸግሮኝ ነው"
ልጅ ፡- እንዳልሰማ መስሎ "አይሰማኝም ስልኩ ብልሽት አለው መሰለኝ" ብሎ ሲመልስ
ኦፐሬተሯ ፡- በመሃል ገብታ "ገንዘብ ላክልኝ ነው የሚሉህ" ብትለው
ልጅ ፡-"ዝም በይ! ደደብ! ታዲያ ገንዘብ አንቺ ካለሽ ስጫት" ብሎ ስልኩን ዘጋው::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
እናት ከሀገር ቤት በስልክ ጣሊያን ለምትኖረው ልጃቸዉ "እዚያ እናንተ ጋ erboristeria የሚባል ሱቅ ውስጥ ወጣት የሚያደርግ መድሀኒት አላቸው ይባላል:: እንዲያዉ ፈልገሽ ላኪልኝ" ብለዉ ሲያስጨንቋት ጊዜ ፈልጋ ፈልጋ በ pillola መልክ የሚዋጠውን ገዛችላቸውና ላከችላቸው:: በኋላም ስልክ ደዉላ "እማዬ ያልሽዉን ልኬልሻለሁ:: አወሳስዱም በቀን አንድ ብቻ ነዉ:: በምንም አይነት መንገድ ከአንድ በላይ እንዳትወስጂ" mi raccomando ብላ ታስጠነቅቃቸዋለች:: እንደተባሉትም መጠቀም ይጀምራሉ:: መድሀኒቱ እየሰራ የእናትየውን ወዝ እንደገና ሲመጣ ያዩት አባት "እኔም ይህን ኪኒን ካልዋጥኩ" ብለዉ ያስቸግሩ ጀመር:: እናት አወሳሰዱን አስረድተዉ አባትም ከመድሀኒቱ መዉሰድ ይጀምራሉ:: ከዓመታት በኋላ ልጃቸው ሀገር ቤት ስትመጣ ኤርፖርት ሊቀበልዋት ከመጡት ሰዎች መሀል እናትዋ የሀያ አመት ወጣት መስለዉና ልጅ አዝለው ጠበቋት:: የመድሀኒቱ መስራት እየገረማት እናትዋን ከሳመች በሁዋላ "አባዬስ?" ብላ ጠየቀች:: እናትም "አይይ እሱማ የላክሽልን ኪኒን አንድ አንድ ብቻ ነዉ የሚወሰደዉ ብዬ ብነግረዉ አልሰማ ብሎ አራት አራት እየዋጠልሽ ይኸዉ አዝዬዉ መጥቻለሁ" ብለዉ ያዘሉትን ማሙሽ አሳይዋት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንድ በችግር ላይ ያለ ሰው በጣሊያን ካለው ዘመዱ እርዳታ ፈልጎ ደብዳቤ በተደጋጋሚ ቢጽፍ መልስ አያገኝም:: በኋላም የሚለኝን ከቃሉ ለስማ ብሎ እንደምንም ብሎ ገንዘብ ተበድሮ ስልክ ይደውልለታል። በስልክ እንዳገኘውም ችግሩን ዘርዝሮ ነግሮ የሚለብሰው ሱሪ እንኳን ከቂጡ የተቀደደ መሆኑ ቢነግረው "ሱሪህ መቀደዱን ለምን ዞር ብለህ ታያለህ" አለው ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አባት ገጠር ሆነው ጣሊያን ካለው ልጃቸው ጋር በስልክ እያወሩ ነበር:: ግን ልጃቸው የአባቱን ድምጽ መስማት ተስኖት ስለነበር "አባዬ ድምጽህ አይሰማም ምንድነው ስልኩ ችግር አለው?" ብሎ ቢጠይቅ አባትም "አይ ልጄ! እንደዉ በሽታ ቢጤ ቢይዘኝ ነጭ ሽንኩርት በላሁና አፌ እንዳይሸትህ ብዬ ተሸፋፍኜ ነው የማናግርህ" ብለው ቁጭ::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
እኛ አፍሪካውያን እንዴት እንደምንኖር አንዳንድ ጣሊያኖች በደንብ አያውቁም። እናም አንድ ጣሊያናዊ አንዱን አበሻ ይተዋወቅና እንዲህ ብሎ ጠየቀው::
ጣሊያናዊ :- አፍሪካ ውስጥ እናንተ የምትኖሩት በዛፍ ላይ ነው አይደል? ብሎ ጠየቀው::
አበሻውም በንዴት "አዎ" አለው::
ጣሊያናዊ :- እንዴት ነው ዛፉ ላይ የምትወጡት?
አበሻውም :- "በ ascensore" አለው ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሴት ልጃቸውን ለመጠየቅ የመጡ እናት ናቸው አሉ:: ታዲያ ማታማታ ሲተኙ ከልጃቸው እና ከባለቤቱዋ መኝታ ቤት ውስጥ የሚሰሙት የማቃሰት ድምጽ ያሳስባቸዋል:: ታዲያ አንድ ቀን ምን ሰይጣን ነው እንዲህ የሚያረጋቸው ብለው ለማረጋገጥ ፈራ ተባ እያሉ ወደ ልጃቸው ምኝታ ቤት በዝግታ ይጠጋሉ በሩ በደንብ አልተዘጋም:: በቀዳዳ ያያሉ:: ደነገጡ :: ወደመኝታቸው ተመለሱና በማግስቱ ጠዋት ወዲያው ወደአገር ቤት ስልክ ደወሉ::
እናት - ሀሎ ደህና ሰነበታችሁ
ስልክ መላሽ - ደህና ነኝ
እናት - ሁሉን ስመጣ እናወራለን::
ስልክ መላሽ - ምኑን?
እናት - እረ ተውኝ::
ስልክ መላሽ - ምን ተፈጠረ?
እናት - አይ ይ ይ ይ!!!! "ልጄ ጥጃ ሁናለች" አሉ ይባላል።
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሴትየዋ ጣሊያን ብዙ ጊዜ ከርመው አገር ቤት በተመለሱ በሳምንቱ እድርተኛቸው የሆነ ሰው ስለሞተ ቀብር ለመድረስ ተቻኩለው ሰራተኛቸውን "ማነሽ እስቲ! ከበቡሽ! " ያንን ነጠላ አቀብይኝ እባክሽ!
ከበቡሽም ንጠላውን ስትፈልግ ስትዘገየችባቸው ጊዜ
ሴትዮዋ ይናደዱና አንቺ ልጅ ያንን cazzo ነጠላ አምጪልኝ ለቅሶ ደርሼ ልምጣ ቶሎ በይ ብዬሻለሁ።
አሁንም ስትዘገይብቸው ግዜ ይቺ ባፋንኩሎ ሶርዳ " ያሉትን የሰማ አለ?
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አበበ ቢቂላ እዚሁ ጣሊያን ሮማ ውስጥ ባለው stadio olimpico ውስጥ በባዶ እግሩ ማራቶን ያሸነፈ ጊዜ አንድ የተሸነፈ ሯጭ "ለምን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ ፈቀዳችሁለት?" "እሱ እኮ ያሸነፈው ሸክም ስለቀለለት ነው" ብሎ ክስ በማቅረብ ዳኞቹን ሲጠይቃቸው ጊዜ ምን ብለው መለሱለት መሰላችሁ? "አንተም ሸክም እንዲቅልልህ ከፈለግህ ለምን ራቁትህን ሮጠህ አታሸንፍም ነበር?" ብለው መለሱለት ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዱ እዚሁ ጣሊያን ሀገር ሆኖ እጮኛው ከሀግር ቤት ደብዳቤ ጻፈችለት:: "ከእንግዲህ ብኋላ የኔና ያንተ ነገር እዚሁ ላይ ቢያበቃ ይሻላል:: ከሌላ ልጅም ፍቅር ይዞኛል:: ደግሞም እስከዛሬ ድረስ የላኩልህን ፎቶግራፎቼን ቶሎ መልስልኝ" አለችው:: እሱም በጣም ይናደድና ወደ ጓደኞቹ ሄዶ እነሱ የማይፈልጓቸውን የሴት ፎቶግራፎች ሰብስቦ "መልክሽ ስለጠፋኝ ከነዚህ ፎቶግራፍ መሀል ምረጪና የራስሽን ወስደሽ ሌሎቹን እንድትመልሽልኝ አደራሽን" ብሎ ጻፈላት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሚላኖ የሚቀመጥ ለቤተሰቦቹ ስልክ እንኳን ደውሎ የማያውቅ ከብዙ ዓመት በኋላ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ አገር ቤት ሄደ። ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ አሽከር ተቀበለው። ከአሽከሩም ጋር እንደተገናኙ ስለቤተሰቦቹ ይጠይቀው ጀመረ።
አሽከርየውም "ሁሉ ደህና ናቸው ብቻ ..." ብሎ ዝም አለ።
ልጅዬውም "ምነው ምን ተፈጠረ?"
አሽከር "ትልቁ ውሻ ሞተ"
ልጁ - "ምን ሆኖ?"
አሽከር - "እሱማ የትልቁን በሬ አንጀት ሲጎትት ታንቆ ሞት"
ልጅ - "በሬውን ምን ነካው?
አሽከር - "በሬውማ ለእሜቴ አርባ ታረደ እኮ!"
ልጅ - በጣም ይደነግጥና "እማዬ ምን ሆና ሞተች?"
አሽከር "እሳቸውማ በጌቶች ሞት አዝነው ሞቱ" ብሎ ቁርጡን ነገረው።
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ባላገር የሚኖሩ አባት ሮም የሚኖረውን ልጃቸውን ለመጠየቅ እዚህ ከፉሚቺኖ aeroporto እየወጡ እያለ እቺ ጠጋ ሲሏት የምትከፈት የመስታውት በር ታጋጥመዋለች:: ሻንጣውን ቁጭ ያደርጉና ሊከፍቱ ጠጋ ሲሉ ክፍት ይላል:: እሰይ ብሎ ሻንጣ ሊያነሱ በሚመለሱበት ጊዜ ተመልሶ ይዘጋባቸዋል:: አሁንም ለመክፈት ሲመጡ እራሱ ይከፈታል:: ወደ ሻንጣው ሲመለሱ አሁንም ዝግት ሲልባቸው በንዴት ወደ ስዉ ይዞሩና "ጎበዝ ይሄ ምን ይቀልዳል?" ብለው ጠይቀው ነበር ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጋሼ ከበደ ቡና ቤት ሲገባ ሁል ጊዜ 3 ቢራ በአንድ ጊዜ እያዘዘ ነው የሚጠጣው:: እንደጨረሰም እንደገና በሌላ ዙር 3 ቢራ ያዝና ይጠጣል። መጠጥ ቀጂውም "ለምንድነው 1 ቢራ ከማዘዝ 3 ቢራ በአንድ ጊዜ የምታዘው?" ብሎ ሲጠይቀው ጋሼ ከበደም "አይ! ሁለት ጓደኞቼ ወደ ውጪ ሀገር ስለሄዱና ስለተለያየን ያው መጠጥ ስንጠጣ ለሶስተችንም እያዘዝን እንድንጠጣ ቃል ስለተገባባን ለዚህ ነው በየዙሩ 3 የማዘው" አለው:: እነሱም መጠጥ ሲያዙ እንደዚሁ ነው። ጋሼ ከበደም ብዙ ጊዜ እየተመላለሰ ደንበኛ ሆነ:: ታዲያ አንድ ቀን ወደ ቡና ቤት ይገባና 2 ቢራና 1 ለስላሳ ያዛል:: መጠጥ ቀጂውም "ምነው ዛሬ ቀየርክ?" ቢለው እሱም መልሶ "እኔ መጠጥ ትቻለሁ" አለው:: menomale ለስላሳ ማዘዙ! almeno ሁለተኛ ዙር ብሎ አይደግምም። እነዚያ የተከፈቱት 2ቱ ቢራዎች ግን አያሳዝኑም!! ይታያችሁ እንግዲህ!! ያው ወደ ጋሼ ከበደ ጠጋ ማለት ሳያዋጣ አይቀርም
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዷ አበሻ ለቢሮ ሥራ ለመቀጠር ወደ አንድ cooperativa ትሄድና ከሥራ ቀጣሪው ጋር ስለሥራው እየተነጋገረችና ጥያቄ እየተደረገላት ነበር...
ቀጣሪው - "ደሞዝ ስንስት ቢከፈልሽ ጥሩ ነው?"
ተቀጣሪዋ - "2000 ኤውሮ" አለች::
ቀጣሪው - "እንደውም 3000 ኤውሮ እናደርግልሻለን፣ ደግሞም አንድ ወር የዓመት ፈቃድ ከአዲስ መኪና ጋር ቢስጥሽ ምን ይመስልሻል?" አላት::
ተቀጣሪዋ - ደንግጣ "ቀልድዎን ነው አይደል?" ብትለው
ቀጣሪው - "አይ! ቀልዱን እኮ የጀመርሽው አንቺ ነሽ" አላት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጣሊያን ሀገር የሚኖር ዜግነቱን ግን ወደ ጣሊያናዊነት የለወጠ አበሻ ከ fiumicino ተነስቶ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከሻንጣ ፈታሾቹ ጋር አለመግባባት ይፈጥርና በሚሠሩት ስዎች ላይ ስለ ውጭ አገር ዜጋነቱ ይደነፋል:: ታዲያ ምን እንዳደረጉ ታውቃላችሁ? ዝም አሉና ልጁ የሚያርፍበትን አድራሻ ተቀብለው በሰላም ሸኙት:: ከዚያም እቤቱ ሄደው "በል በኢትዮጵያ ህግ መሰረት አንድ የውጭ ዜጋ ሌላ ሰው ቤት ማረፍ አይችልም":: ይህም ለውጪ ሀገር ዜጎች የተለየ ጥበቃና protection ደግሞም ለአንተ security ሲባል ከጸጥታ አንጻር ችግር እንዳይገጥምህ ተብሎ ነው:: ከዛ በኋላማ ምናለፋችሁ ጊዜውን በሙሉ ......
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጋሼ ከበደ እድላቸው ሆኖ አሜሪካ ገቡና ኑሮን ሲኖሩ sex ሳያደርጉ ብዙ ጊዜ ሆኗቸው ነበር:: ታዲያ አንድ ቀን አንድ ሁለት ተባብልው ይሳካላቸውና አንዷን አበሻ ይዘው እቤታቸው ይዘዋት ይመጣሉ:: ወደ አልጋ ይሄዳሉ ...
ታድያ ጋሼ ከበደ አሷን ከላይ አርገው አሳቸው ከታች ሆነው ፍቅር እየሠሩ ነበር:: ልጀትዋም ከላያቸው ሆና ጸጉርዋንም ስትሠራው ነበር:: ጋሼ ከቤም የምታደርገውን አዩና ከልባቸው ተበሳጭተው ..."ምን አያደርግሽ ነው?" ብለው ሲጠይቋት አሷም ስትመልስ "አሜሪካ እኮ ሁለት ሥራ ካልተሠራ መኖር አይቻለም" አለቻቸው ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንድ ሰውዬ ለስራ ጉዳይ ወደ ውጭ ሲሄድ ለቅርብ ጓደኛው የሚስቴን ነገር አደራ:: ችግር ካለም ፃፍልኝ ብሎት ሄደ:: ከትንሽ ሳምንት በኋላ እንዲ ብሎ ፃፈለት
ውድ ወንድሜ :-
1ኛ ) በጣልክብኝ አደራ መሠረት ባለቤትህን በየጊዜው እጠይቃታለሁ። በጣም ደህና ናት::
2ኛ ) ከብዙ ወንዶች ጋር ተዋውቃለች። እናም ሲያወጧት አይቻለሁ::
3ኛ ) እኔንም አሳስታኝ አውጥቻታለሁ::
4ኝ ) ስለ 3ኛው ጉዳይ ምን አስተያየት አለህ ?
ባልየውም ይህ ደብዳቤ እንደደርሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት
ውድ ጓደኛዬ :-
1ኛ ) ደብዳቤህ ደርሶኛል አመሰግናለው::
2ኛ ) ባለቤቴን ብዙ ወንዶች እና አንተም እንዳወጣሀት ገልፅህልኛል::
3ኛ ) ባለቤቴ ግን የሚጋባ በሽታ አለባት::
4ኛ ) አንተስ ስለ 3ኛው ጉዳይ ምን ትላለህ ?
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
የፈረንጅ ባህል ይዞ የተምታታበት አበሻ አገርቤት ለእረፍት ሄዶ ሳለ አንድ ቀን የታመመ ዘመድ ከጠየቀ በኋላ ሊሰናበት ሲል "በሉ እንግዲህ ወደሩቅ አገር ስለምሄድ ለቀብር አይመቸኝም" የሞተ እንደሆነ እናንተንም እግዚአብሔር ያጽናችሁ አላቸው ይባላል
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ብዙ ዓመት እዚህ የተቀመጠ አበሻ ሀገር ቤት እየሄደ ሚስት በማግባት ከአንዴም ሁለቴም ሶስስቴም እዚህ አስመጥቷል:: ነገር ግን ያመጣቸው ሚስቶች ትንሽ ወሮች ተቀምጠው ጥለውት ስለሚሄዱ በቃ ያለሚስት ተቀምጧል:: እናም አንድ ይህንን ችግሩን ያልየ አበሻ "አንተ ለምንድነው ሚስት የማታገባው?" ሲለው እሱም "አንተ ይህን አታውቅም እንዴ? እዚህ የሀገራችን ሴት ሁሉም የተያዘ ነው:: ያለኝ ተስፋ ያ በየግዜው ሚስት ከሀገር ቤት የሚያስመጣውን ዘዴ እየተጠቀምኩ እኮ ነው። አሁን ደግሞ 4ኛ ሚስት ለማስመጣት በፕሮሰስ ላይ ነኝ" አለው ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሶስት (3) ሰላዮች ይመረጡ ተባለና ኢትዮጲያዊ፣ ጣሊያናዊ፣ እንግሊዛዊ የዘመኑ ስላይ በመባል ተመረጡ። ከ እነሱም ውስጥ እስቲ ማነው የበልጠ ፈታንና ቀልጣፋ ተብሎ ፍየል አምጡ ተብለው ሲላኩ
እንግሊዛዊው - ወዲያው ከች አደረገ
ጣሊያናዊው - በንጋታው ከች አረገ
ኢትዮጲያዊው - ስድስት ቀን ቆይቶ አፍዋ ደም በደም የሆነች ውሻ ከች ሲያደርግ "ምንነካህ አንተ?" ሲባል አይ በቃ አምናለች እኮ አለ:: (ውሻዋን ደብድቦ ፍየል ነኝ ብላ አሳምኗታል)
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አዛውንቱ ጣሊያን ሀገር ብዙ ነገር አይተዋል:: ካዩዋቸው ነገሮች በጣም የወደዱት ቢኖር ግን የባለጊውን ፊልም ነው:: ታዲያ አንድ ቀን ፊልሙን በጥሞና እየተክታሉ ሳለ አንዷ ትመጣና እንዴ! አባባ! እርስዎ ትልቅ ሰው አደሉ እንዴ? ይህን የባለጌ ፊልም ያያሉ? ስትላቸው ባአባባሏ የበሸቁት አዛውንት "ዝም በይ! ምላሰኛ! ምላስ እዚህ ስንት ቁም ነገር ይሠራበታል መሰለሽ:: አንቺ ግን ዝም ብለሽ ታወሪበታለሽ" አልዋት ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሮማ ውስጥ ካሪታስ የሚመገቡ ሁለት ጓደኛሞች ሁልግዜ ምግብ ለመብላት በተራ በተራ ነው። የሚሄዱት እና ቀድሞ የበላው ምን እደሆነ የሚነግረው በምልክት ነው።
ያልበላው ፡- ምን ነበር ዛሬ?
በልቶ የመጣው ፡- "ዳ" ነው ይለዋል።
ያልበላው ፡- አሀ ዳቦ ነው ማለት ነው ይልና እሱም ሊበላ ይሄዳል።
በሌላ ቀን ያልበላው ፡- ዛሬስ ይለዋል
በልቶ የመጣው ፡- "ፓ" ነው ይለዋል
ያልበላው ፡- ፓስታ ማለት ነው። ብሎ ሊበላ ይሄዳል
በሶስተኛው ቀን ያልበላው ዛሬስ ሲለው
በልቶ የመጣው ፡-"ዝ" ነው ይለዋል
ያልበላው ፡- ደንግጦ ዝልዝል ተደርጎም አይታወቅም ብሎ ሲሮጥ ይሄዳል እዛም ሲደርስ ዝግ ነው ለካስ። "ዝ" ያለው ዝግ ማለቱ ነው
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንድ አባት ልጃቸውን ለመጠየቅ ጣሊያን ይመጣሉ:: ከዚያም ልጃቸው ሁሉግዜ ማታ ማታ ጥላቸው ወደ ውጭ እያመሸሽ ትመጣለች::
ይህንን ያዩ እና በሁኔታው የተቆጡ አባት "ልጄ ሆይ! ምነው ማታ ማታ ልክ እንደሀገሬ ሰካራም ሰው እያመሸሽ ትገቢያለሽ ጥሩ እኮ አይደለም" ሲሏት
ልጃቸውም "አባዬ ይህ እኮ አውሮፓ ነው:: ልትቆጣጠረኝ አትችልም" አለቻቸው::
ይህንን የሰሙ አባት እምምምም... ብለው ልጃቸውን ከጠየቁ ከወር በኋላ ወደ አዲስአበባ ተመለሱ:: ከዚያም ከአንድ ዓመት ብኋላ ደግሞ ልጃቸው ወደ ኢትዮጲያ ትሄዳለች:: ማታ ማታ ዙረት የለምደች ልጅ አምሽታ ቤት ስትገባ አባቷ ልክ እንደገባች በጥፊ ያልሷታል:: ከዚያም ጥፊ የቀመሰችው ልጅ አባቷን ምነው አባዬ ምን አደርኩ በጥፊ መታሃኝ ስትላቸው አባትም "ይሄ እኮ ኢትዮጲያ ነው" አሏት ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ልጆቻቸውን ለመጥየቅ ሮማ የመጡ ሁለት እናቶች አውቶቢስ ፌርማታ ጋ ይገናኛሉ:: አንዷ 5 ቁጥር አውቶቢስ ስትሆን ወደቤት የምትወስዳቸው የአንድኛዋ ደግሞ 8 ቁጥር አውቶቢስ ነበር የምትወስዳቸው:: እና አጋጣሚ ሆኖ 58 ቁጥር አውቶቢስ ትመጣለች:: ሴቶቹ አቤት መታደል ሁለታችን የምትወስድ አውቶቢስ በአንድ መጣችልን ይሉና ተሳፍረው ጥፍት አሉ:: ያው ቀኑን ሙሉ ብዛው አውቶቡስ እየዞሩ እያለ ያቺ አምስት ቁጥር የምትጠብቀዋ ረዥም ፎቅ አይታ ፎቁን ትቆጥር ጀመር:: 1 - 2 - 3 - 4 ... ሲቆጥሩ የሰማ አንድ ጩልሌ መጣና "ስንት ቆጠሩ?" ብሎ ጠየቃት:: "15" ብላ መለሰች:: ጩልሌው ሂሳብ አወራረደና 2 ኤውሮ ላንድ ፎቅ! 15 ፎቅ ስለቆጠሩ ሰላሳ ኤውሮ ይክፈሉ!" ብሎ ዓይኑን አጉረጠረጠባቸው:: እሷም "እሺ እሺ ብላ ከፍላ ተገላገልችው:: በኋላ ጓደኛዋን "ሸወደኩት እኮ!" አለቻት:: ጓደኛዋ "እንዴት?" ብላ ስትጠይቃት እሷም "25 ፎቅ ነበር የቆጠርኩት"
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ኢትዮጲያ ውስጥ ገጠር ትኖር የነበረች አንዲት ልጅ ጣሊያን ሀገር መጣችና አንድ ቀን አስቤዛ ለማድረግ ወደሱፐር ማርኬት ወጣ አለች። ከዚያም ገባችና የምትፈልገውን ነገሮች መፈለግ ጀመረች። ይህች ሰው በአይምሮዋ ያለውን ነገር ፈልጋ ማግኘት አልቻለችም ነበር። ከዚያም ገራ ተጋብታ ሳለ አንዱ ሠራተኛ ምን እያደረገች እንድሆነ ግራ ተጋብቶ ሲጠይቃት የምትፈልገውን እቃ በጣሊያንኛ ቋንቋ ማውቅ ስላልቻለች እጁን ጎትታ ወስዳ እንቁላሉን በእጇ ይዛ "dove la madre di questo uovo?" ብላ ቁጭ።
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዱ ገና ከአገርቤት እዚህ ጣሊያን እንደመጣ ለጭፈራ ከጓደኞቹ ጋር ወጥቶ "እባካችው እኔ ፈረንጅ መቅመስ እፈልጋለሁ እንደምንም አገናኙኝ" አላቸው:: እነሱም "እራስህ ሞክር አትፍራ" አሉት:: እሱም ፍለጋውን ተያይዞ ከአይናችው ተሰውሮ ያገኘውን ይዞ ሄድዋል:: ስሟም ሮዛ (Rosa) ነበር የምትባለው:: ታዲያ አልጋ ላይ ይዝዋት በሆድዋ ተኛችበት:: ከዛ እሱም ስራውን ይቀጥላል:: መብራት አጥፍቶ ስለነበር ሆድዋን እይዛለው ብሎ ከፊት ያለውን እቃዋን ይይዛል:: ከዛ ደንግጦ "ሮዚ በሳሁሽ ወይኔ በሳሁሽ" ማለት ለካስ ሮዚ ወንድ ኖርዋል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዱ በቅርቡ ጣሊያን ህገር ይመጣና ልክ በ1ወሩ 100 ኤውሮ ወደ አገርቤት ላከና አባቱን በል አባዬ ወደ ኢትዮ ብር ሲለወጥ 1000 ብር ይሆናልና አንድ ነገር አድርግበት አላቸው:: በ3ኛ ወሩ ሲደውል አባቱ ምነው ልጄ የት ጠፋህሳ?
አባዬ እኔ ያለሁበት ከተማ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ስለደረሰ ነው ይጠፋሁት።
አባትዬውም እህ የሞተና የተጎዳ ሰውስ አለ?
ልጃችውም አዎ 100 የሚሆኑ ሞተዋል
አባትዬውም ስለዚህ ወደእኛ ሲቀየር 1000 ሰው ሞቷል ማለት ነው?
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ዘበርጋ ማይክል ክሚባል ጛደኛው ጋር አሪዞና ውስጥ የሚገኘውን የግራንድ ካንየን ሽለቆ ለመጎብኘት ይሂዳል። ታድያ ሽለቆዉን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ማይክልን እየውልህ እንግዲህ አሁን ድምጺ ከፍ አድርገ ስሜን ብጣራ የገደል ማሚቶው ስሜን 10 ጊዜ ይደጋግመዋል ይለዋል ለዘበርጋ:: እንዳለውም ጮክ ብሎ ማይክል ሲል ሸለቆዎም ተከትሎ .. ማይክል.. ማይክል.. ማይክል.. አለ:: ይህን የተገነዝበ ዘበርጋም ለምን ታድያ እኒም አልሞክርም ይልና እሱም በተራው ጮሆ ዘበርጋ ብሎ ሲጮህ ግራንድ ካንየኑ ምን ብሎ መለሰለት መሰላችሁ "I beg your pardon?" ብሎ መለሰለት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************

አንዱ ክላንዴስቲኒ የአንገት ሀብል ቀምቶ በማምለጥ በጣም የታወቀ ነው። ይሄ ልጅ በጣም ስላስቸገረ ፖሊስ አንድ ማስታወቂያ አወጣ። ይህም ማስታወቂያ የሚለው፡- "በዚህ አካባቢ የምትኖሩ ሴቶችም ሆናችሁ ወንዶች እባካችሁን ግድ ካልሆነባችሁ በስተቀር አርቴፊሻል የአንገት ሀብል አድርጉ።" በእርግጥም ይሄ ማስታወቂያ ከወጣ በኌላ ሰላም ሆነ። የዚህ ጭልፊት ልጅ ገበያም ስለቀነሰ ሙሉ ትኩረቱን የእጅ ስልክ ላይ አዞረ። ታዲያ አንድ ቀን አንድ አባት የእጅ ስልካቸውን ይዘው ሲያወሩ ያስተውልና ግራ ቀኙን አየት አየት አድርጎ ከኌላቸው መከተል ይጀምራል። እኝህ አባት የዚህን ልጅ ዝና ሰምተው ስለነበር ወዲያውኑ እንዳዩት የሚያወሩትን ሰው እንኴን "ደህና ዋል" ሳይሉ ስልካቸውን ዘግተው ኪሳቸው ውስጥ ያደርጉና መንገዳቸውን ይቀጥላሉ። በዚህ ጊዜ ስልክ ኪሳቸው ውስጥ ሆና መጮህ ጀመረች። አባት ደግሞ እየሰሙ ዝም። አሁንም ትንሽ ቆየና ስልክ ጮሀች። እሳቸው ምናቸው ሞኝ ነው "እሲኪ ትፈነጂ እንደሆነ አይሻለሁ" ብለው ዝም። ለሶስተኛ ጊዜ ስልክ ጮሀች። በዚህ ጊዜ አጅሬ ከኌላቸው ሆኖ "አረ -ፋዘር! ስልክ ይጮሀል። ምናልባት ኢመርጀንሲም ሊሆን ይችላል የዛሬ ነገር እኮ አይታወቅም" ቢላቸው ሰውየውም መለስ አሉና" አይ የኔ ልጅ ግድየለህም ተውው እኔ ከምጮህ እሷ ብትጮህ ይሻላል።

. ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)

******************************************

ከሃምሳ ዓመታት በፊት ወደ ጣልያን ተጉዞ ፓስታ እየበላ የቆየ መምህር ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ስለ ምግብ ሲያስተምር “ምግብ ማለት ከሱፐር
ማርኬት የሚገዛ፣ የሚቀቀል፣ ስጎ የሚጨመርበት፣ ከዚያም በሹካ የሚበላ ማለት ነው” አለና ተማሪዎቹን አስተማረ፡፡ ከዚያም ተማሪዎቹን አንድ ነገር ጠየቀ “እንጀራ ከሱፐር ማርኬት ይገዛል?” “አይገዛም” አሉት፡፡ “እንጀራ ይቀቀላል”? “አይቀቀልም” “ስጎ ይጨመርበታል”?
“አይጨመርበትም” “በሹካ ይበላል”? “አይበላም” “እንግዲያውማ እንጀራ ምግብ አይደለም ማለት ነው” አላቸው ይባላል፡፡

. ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)

******************************************
አለሚቱ ከሀገርቤት ወዲያውኑ እንደመጣች ሰው ቤት ተቀጠረች። ቀጣሪዎችዋም እስቲ ወጣ ትበል ብለው ለመጀመሪያ ሙከራ ሱቅ ላኳት። ያው 5 ኤውሮ ሰጥተዋት “uovo” በይና እና እንቁላል ግዢ አሏት። ትንሽ እንደሄደች ጠፋባት። ለባለ ሱቁ በምን ትናገር? ለካ ቀጣሪዎቿ ለሀገሩ አዲስ ስለሆነች እንዳትጠፋ ብለው ከሁዋላ እየተከተሏት ነበር። እሷ ለባለሱቁ ለማስረዳት ግራና ቀኝ እጁን እያማታች “ኩኩ” ብላ ከሁዋላ የምትጥለውን ለማሳየት ያረገችውን እንቅስቃሴ አይተው ሳቃቸውን መቆጣጠር አቃታቸው።

. ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************ወይዘሮ ጌጤ እድሜ ጠግበው፣ የልጅ ልጅ አይተው፣ ለማንም የማይቀረው ሞት እሳቸውንም ይዞ ሊሄድ ባልጋቸው ዙሪያ መዞር ጀመረ:: እስቸውም ያቃስታሉ። ዙሪያቸውን ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸው የቅርብ ዘመድ እንዲሁም ለክፉም ለደጉም ቢሆን የሚናዘዙትም ካለ ተብሎ የነፍስ አባታቸውም ተገኝተዋል::
"እኅኅኅህ ....አረ ወይኔ! አይ ዘንድሮ! ባጭር ተቀጨሁ! አየዬ! አይ ሰው መሆን!!!" አሉ ጌጤ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆነው::

"አይዞሽ እማማ ምንም እኮ አትሆኚም" አለ ቾምቤ እያሉ የሚጠሩትና ከልጅ ልጆቻቸው ውስጥ በጣም የሚያቀርቡት አንዱ ልጃቸው::
"አዬ ቾምብዬ ተወኝ የኔ ነገር እማ በቃው ....ይሀው የናንተን .. የናንተን መጨረሻ እንኴን ሳላይ ይህው ተቀጠፍኩ:: ባጭር ቀረሁ" እንደ ማልቀስ ቃጣቸው::
ሁኔታውን በጽሞና ይከታተሉ የነበሩ የነፍስ አባታቸው ጊዜው አልፎ ነገሮች ከመቀየራቸው በፊት ደብተርና ኢስክሪፕቶ ይዘው ጠጋ አሉና "አይ ወለተ ወልድ አይዞኦ ....እመ -ብርሀን አቅፋ ደግፋ ልጇን እንዳሸገረችው እርሶንም በቅፏ ታሻግርዎታለች በርታ ይበሉ ደግ አይደለም እንደዚ ሲሆኑ ጻድቃን ይቀየማሉ ደስ አይላቸውም" ብለው ከተቆጣጧቸው በኌላ ....
"ይበሉ አሁን የሚናዘዙትን ይንገሩኝና በማስታወሻዬ ላይ ልጣፍ::" አሉ አባ ሞት እንዳይቀድማቸው በመስጋት::
"እሺ አባቴ በነጥብ በነጥብ ይያዙልኝ እንግዲህ::" ጌጤ ራሳቸውን እንደምንም ቀና አድርገው ወደ ነፍስ አባታቸው እያዩ መናዘዝ ጀመሩ ::
"ይጻፉ አባቴ::"
1. "ባንካ ዲ ሮማ 10000 ኤውሮ"
"እሺ አስር ሺህ" ቄሱም ጻፉ::
2. "ባንካ ዲ ላቮሮ 7000 ሺህ"
3. "ባንካ ዲ ኢታሊያ አስራአምስት ሺህ"
"ደግ ነው ወለተ -ወልድ! እንዴት ይከፋፈል ታዲያ?" አባ ጠየቁ::
"እዳዬ ነው ልጆቼ:: ያልጨርስኩት እዳ ነው:: ክፈሉት::"

. ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)

******************************************

ወይዘሮ ቀለሟ ልጃቸው ዳዊት በላከላቸው የግብዣ ወረቀት አስፈላጊውን የጉዞ ፎርማሊቲ ጨርሰው ወደ ጣሊያን ሊያቀኑ ቀን ቀርቷቸዋል:: ከገጠር ካመጧት የቤት ሰራተኛቸው ተናኘ ጋር እየተጋገዙ ድርቆሹን በሶውን በርበሬውን ሚጥሚጣውን ዳቦ ቆሎውን ምጥኑን ባይነት በመልክ በመልኩ እያደረጉ ሻንጣ ውስጥ ያስገባሉ:: ሁኔታቸውን ላየ ቀለሟ ጣሊያን የሚመጡ ሳይሆን ሊሸፍቱ በረሀ የሚገቡ ይመስላሉ:: የፈረንጅ በረሀ:: በዚህ መሀል ስልክ ተደወለ:: ደዋዩ ልጃቸው ዳዊት ነው::
"ምነው ልጄ ትናትና ደውለህ አልነበር ምን ችግር አጋጠመህና ዛሬ ደወልክ?" አሉ ቀለሟ::
" አይ እማዬ ቡዙ ነገር አትያዠ ሁሉም እዚህ አለ ሸክም እንዳታበዠ ብዬ ነው::"
"አይ የኔ ልጅ ታዲያ የኔ የእናትህን እጅ የሚያስበልጥ አለ እንዴ? እኔ እናትህ እንኴን ላንተ ለሌላም እተርፋለሁ አይዞህ አታስብ ቡዙም ነገር አልያዝኩ::"
"ጥሩ ነው እሺ እማዬ እንዳልሽው ይሁን... ብቻ አንድ ነገር ልንገርሽ....!!" አለ ዳዊት ልቡ ፈራ እያለ::
"ምንድነው ልጄ የምትነገረኝ" አሉ ቀለሟ ለመስማት ቸኮሉ::
"ይህእውልሽ እማዬ መቼም የጣሊያን ሀገር ኑሮ ውድ ስለሆነ የቤት ኪራይና አንዳንድ ወጭ እንድታግዘኝ ብዬ አስገብቻለሁ ::
"አግብቻታለሁ!!ማናት ደሞ እሷ?"
"ኖ ኖ እማዬ ደባል የምትሆነኝ ልጅ ማለቴ ነው:: የመብራቱንም የስልኩንም የውሀንም ኪራይ እየተካፈልን አብራኝ የምትኖር ደባል አለችኝ:: ከመምጣትሽ በፊት እንድታውቂው ብዬ ነው::"
ቀለሟ ነገሩ ቡዙ አልጣማቸውም:: "ከሴት ልጅ ጋር ደባልነት! እንዴት እሺ አለችህ ልጄ እንደው ያለ ፊርማም ያለ ወረቀትም ዝም ብላ ገባችልህ ማለት ነው?"
"አይ እማዬ እንደምታስቢው አይደለም እዚህ ስትመጨ ሁሉንም ነገር ታይዋለሽ:: ግኑኝነታችን ምንም ሌላ መልክ የለውም:: ለመረዳዳት ስንል ብቻ ያደረግነው ነው::"
ወይዘሮ ቀለሟ መልሱ ቡዙ ባያረካቸውም በልባቸው "ስመጣ ሁሉንም አይ የለ" ይሉና ልጃችውንም ላለማስደንገጥ ብለው "እሺ ይሁንልህ" ብለው ወደ ጣሊያን ያቀናሉ:: በርግጥም ሁሉ ነገር ለየብቻ ነው:: ልጃቸው ዳዊትና ደባሏ ማህሌት የሚተኙት በተለያየ ክፍል ነው:: ሁለቱም የራሳቸው የመታጠቢያ ቤት አላቸው:: በጋራ የሚጠቀሙት ማድቤቱንና የሳሎኑን ቤት ብቻ ነው:: ይሁን እንጂ የሁለቱ ባንድ ቤት ውስጥ መኖር ስሜታቸው ቡዙ ሳይወደው የእረፍት ጊዜአቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ:: በተመለሱ በሳምንቱ አንድ እሁድ ቀን ማህሌት ቡና ልታፈላ ቤቱን እንደ ባለ ትዳር ቤት ሞቅ ደመቅ ልታደርገው ፈልጋ ጀበናውን ብትፈልግ አጣችው:: ያልገባችበት ቦታ የለም ቤቱን ከዳር እስከ ዳር አሰሰችው:: ካገር ቤት በስንት ልመና ሰው አስቸግራ የመጣችው ጀበና ደብዛው ጠፋ:: እየቆየች ስትሄድ አንድ ክፉ ሀሳብ በአእምሮዋ ውስጥ መመላለስ ጀመረ::
"እንዴ ምናልባት ጀበናዬን የዳዊት እናት ወስደውት ቢሆንስ ? ወይ ጉድ የሚገርም ነው!! የሄዱት ኢትዮጵያ ምን አጥተው ነው የኔን ጀበና ይዘውብኝ የሚሄዱት?"
ጉዳዩ በጣም ስላበሳጫትም ስላስገረማትም ለዳዊት ነገርችው:: ዳዊት መጀመሪያ ነገሩን አላመነም::
"ሁሉም ጋ ፈልገሽ አጣሽው ማለት ነው?" አላት ለናቱ ምን ብሎ በስልክ እንደሚጠይቃቸው እያሰበ::
"ያልፈልኩት ቦታ የለም መቼም መርፌ አይደል" አለችው ማህሌት ፍጥጥ ብላ እያየችው::
ዳዊት ሲፈራ ሲቸር እናቱ ጋ ስልክ መታ::
ስለጤንነታቸውና አጠቃላይ ነገሮችን ከጠያየቃቸው በኌላ ቀልድ መሆኑን ለማሳወቅ ሳቅ እያለ.....
"እማዬ እንዴት ነው የቡና ጀበናችንን ይዘሽብን ሄድሽ እንዴ? ፈልገን እኮ አጣነው ...."አለ እየሳቀ::
"አጣችሁት?" አሉ ወይዘሮ ቀለሟ በምጸት::
"አዎ እማዬ ማህሌት ያልፈለገችበት ቦታ የላትም ቤቱን ከዳር እስከ ዳር አስስዋለች::
"በል የኔ ልጅ ስማኝ ይሀውልህ እቺን እቤትህ ያለችውን ኮማሪት እንዲህ በልልኝ::
"ምን ልበላት?" ዳዊት የልቡ ምት እየጨመረ ሲመጣ ታወቀው::
"ስሚ ምነው አልጋሽ አስጠላሽ በልልኝ.... ምነው እንደ ፌንጣ ካልጋ አልጋ ትዘያለሽ በልልኝ::"
"አረ እማዬ ምን እያልሽ ነው?" ዳዊት ግራ እየገባው ጠየቀ::
ወይ የኔልጅ ይልቁኑ እኔ እናትህ የምነግርህን በደንብ ስማና ንገርልኝ::" አንቺ መቁሊያ እግር በልልኝ::"
አረ እማዬ የምትይው ምንም አልገባኝም:: እኔ እኮ የምጠይቅሽ ስለጀበናው አንቺ ደግሞ የምታወሪው..... እያለ ሲቀጥል ቀለሟ በመሀል አቌረጡትና "አይ ልጄ እኔም የምነግርህ ስለ ጠፋው ጀበና ነው:: "ይልቁኑ ሰሞኑን ደውልልኝና እኔና አባትህ አንተን ራስህን ለጥብቅ ጉዳይ ልናነጋርህ እንፈልጋለን" ብለው ወይዘሮ ቀለሟ የዳዊት እናት ስልኩን ይዘጉታል::
ወይዘሮ ቀለሟ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ የተነሱ ዕለት ማህሌት መኝታ ቤት ገብተው ጀበናውን በጥንቃቄ አመቻችተው ትራሷ መሀል ማስቀመጣቸውን ግን ማንም አላስተዋለም ነበር::

ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)

******************************************


ከኢትዮጲያ ወደ ጣሊያን ለመምጣት በዝግጅት ላይ ነች:: ሁሉ ነገር ተጠቃሎ ይዛ የምትሄደው ሁሉ መኪና ውስጥ ከተጫነ በኌላ ጉዞ ወደ ቦሌ ይጀመራል:: በጉዟቸው ላይ እያሉ ከጎኗ ለተቀመጡት አባቷ
ልጅ = "መቼም አባብዬ በሰላም እዛች ሀገር ልግባ እንጂ ቀንም ማታም ሰርቼ የመጀመሪያ ፕሮግራሜ መጦሪያህ የሚሆንህን ታክሲ እልክልሀለሁ:: የዛ ሰው ይበለኝ እንጂ::"
አባት = "አይ የኔ ልጅ አንቺ ሰላምና ጤና ሁኚልኝ እንጂ ይደርሳል:: ይሄንን ማሰብሽ እራሱ እንዳደረግሸው እቆጥረዋለሁ" አሉ በልጃቸው ኩራት እየተሰማቸው::
ዐመታት አለፉ:: ቃል የተገባላቸው ታክሲ የውህ ሽታ ሆነ:: በዚህ መሀል አንድ አስገራሚ ነገር ተከሰተ:: ልጃቸው አንድ ያልታወቀ ቦዘኔ ወዳ አስወልዷት ያለበትን አድራሻ እንኴን ሳይነግራት ጥሏት ስለጠፋ የሚረዳት ስላጣችና ከስራ ጋር ስላልትመቻት በሁነኛ ሰው ልጇን ላባቷ ትልካለች:: ያልጠበቁት እንግዳ የመጣባቸውም አባትም መገረምም መደነቅም ይዟቸው ለልጃቸው ማስታወሻ ጽፈው ሰደዱላት::
የኔ ልጅ እንዴት ሰነበትሽ? ደህና ነሽ ወይ? ምነው ልጄ ታክሲው ሳይመጣ ወያላው ቀደመ?

.
. ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)

******************************************

ልጅ ጣሊያን ሀገር ውስጥ ኑሮውን ከጀመረ ጥቂት አመታትን አስቆጠረ:: ታዲያ ከኑሮ ውድነት ጋር የራሱም ንፉግነት ተጨምሮ ቀብቃባ እንዲሆን አድርጎታል:: ለቤተ ሰቦቹ እንኴን ሲደውል ጤንነትቻውን ለማወቅ ካልሆነ በስተቀር ስለሌላ ጉዳይ አያነጋግርም:: አንድ ቀን ሲደውል አባቱን አገኘ::
አባት: "እንዴት ነህ ደህና ነህ? ምነው ልጄ እንዲህ ትጠፋብናለህ ? እንደው እኮ ዝም ብለህ ስትጠፋ እኔም እናትህም ተጨነቅን::"
ልጅ: አባዬ ምን ላድርግ ብለህ ነው! ኑሮው እነደምታየው አስቸጋሪ ነው አይመችም:: ለዛ ነው:: በል አባዬ ዋናው ድምጽህን ከሰማሁ ይበቃል:: ይቆጥርብኛል" ይልና የአባቱን ይሁንታ ሳይጠይቅ ስልኩን ጆሯቸው ላይ ይዘጋል::
በሚቀጥለው ጊዜ ሲደውል እናቱን ያገኛል::
እናት: "ሀሎ ምነው ልጄ እንዲህ ጨከንክ? ሰው እንኴን አትናፍቅም?"
ልጅ: "ምን መሰለሽ እማምዬ አልመች እያለኝ እኮ እንጂ እኔማ ማሰቤ እኮ አልቀረም::"
እና: "እሺ ይሁና እኔማ ይሄ ልጅ ላመት ባሉ እንኴን ...ብለው ሳይጨርሱ የነገሩ አዝማሚያው የገባው ልጃቸው ፈጠን አለና "እማዬ ስልኩ ይቆጥርብኛል ሌላ ጊዜ በሰፊው አወራሻለሁ" ይልና ስልኩን ጆሯቸው ላይ ዝግት:: ይሄ ነገር ያሳሰባቸው እናትና አባት አንድ ቀን እቤት ተቀምጠው ሲወያዩ
እናት: "አንቱዬ እንዴት ነው ነገሩ ልጃችን እንደው የልባችንን ሳያናግረን እንደው ናፍቆታችንን እንኴን ሳንጨርስ ጆሯችን ላይ ስልኩን መዝጋቱ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?"
አባትም ሁኔታው ቢያሳስባቸውም ሚስታቸውን ለማጽናናት ሲሉ "አይ አይዞሽ አትዘኚ አመሪካን እንዲህ እንደኛ ሀገር አይደለም ዝም ብሎ ስልክ አይመታም:: ልጃችንም ያዝልቅለት እንጂ በዚህ ከቀጠለ ጥሩ የውሀና የመብራት ቆጣሪ ይወጣዋል" አያሉ ሚስታቸውን ሲያጽናኑ ስልክ ጮኽ:: ያው ልጃቸው ነው:: ስልኩን አባት ያነሱና
አባት: "ልጄ ሰላም ነህ ጤናህስ ደህና ነው?" ይሉታል::
ልጅም "ደህና ነኝ አባዬ ይህውልህ እንደውም ዛሬ እኛ ጋ በአል ስለሆነ ስራ የለም አንተንም እማዬንም በደንብ አወራችኌለሁ::
አባትም ደስ እያላቸው "ቀጥል እስኪ ልጄ"
ልጅ: ይኸውልህ አባዬ እዚህ አገር ውጭ እየሄዱ ምግብ መብላት በጣም ሰልችቶኛል:: በዚህ ላይ ምግባቸው ጤነኛ አይደለም:: ካሁን በኌላ ራሴ እየሰራሁ ለመብላት ወስኛለሁ:: ስለዚህ ከማዬ ጋር ተነጋገሩና 3 ኪሎ በርበሬ 3 ኪሎ ሚጥሚጣ አንድ 5 ኪሎ ቅቤ በሶ አንድ ሶስት ኪሎ የሚሆን ጭኮ 5 ኪሎ የኤልሳ ቆሎ ከተመቸ ደሞ ክሽን ተደርጎ የተሰራ ዶሮ በፍሪዝ አቀዝቅዛችሁ .....እንዲሁም አልጫ ....እያለ ሊቀጥል ሲል አባት ቀበል አደረጉና
"ልጄ የኔ ልጅ ቆይ ስማኝ ይሄንን ሁሉ ስታወራ እኮ ስልኩ ይቆጥርብሀል አሉትና ጆሮው ላይ ድርግም::

ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************

የጎረቤት ሴቶች ተሰብስበው ስለልጆቻቸው ወግ ሲያወጉ "የኔ ልጅ ያለችው ጣሊያን፣ ፈራንሳይ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ ነው" እያሉ ሲጫወቱ አንደኛዋ ብድግ ብላ "የኔ ደግሞ ያለችው ጅቡቲ ነው" ስትል አንዷ ብድግ አለችና "ምን ውጭ አገር ትያለሽ ጓሮ ነው ያለችው አትይም እንዴ!" አሏት ይባላል::

******************************************


አንዱ አበሻ ልጅ ዋና ለመማር piscina ይሄድና ሲዋኝ ይሰምጥና መውጣት ያቅተዋል። ከዚያ እዚያው ውሀ ውስጥ እየተንፈራገጠ በአጠገቡ ሰው እንዳለ ሲመለከት አንድ ጠና ያሉ ሰውዬ በpiscinaው አጠገብ ሲያልፉ ያያል። የሰጠመውም ልጅ "አባባ aiutare! ... Io morire! ... እያለ ሲጮህ ሰውዬው ደግሞ ዞር አሉና እንዲህ አሉት " ጣሊያንኛ ከመማርህ በፊት ዋና አትማርም ነበር?" አሉት።
Endale T/Mariam (Roma)

******************************************

እዚህ ጣሊያን ሀገር የሰለቸኝ...


* ልብስ ማጠብ ወይንም ላቫትሪቼ ማድረግ፣ ደግሞ እንዲደርቅ ፀሀይ ላይ ማስጣት፣ መተኮስ፣ ...
* ምግብ መስራትና ከዚያ የበላሁበትና የሠራሁበትን ሳህና ድስት እቃ ማጠብ ነው የሰለቸኝ። ይህንንም ፓርት ታይም ስራ ብዬዋለሁ። ወይም ሁለተኛ ስራ ሆኖብኛል። ምንም የእውነት እረፍት ቀን የለም እኮ!! ያችኑ እሁድ ቀንን እንዲሁ ስል ምንም ሳልቀመጥ ቀኗ ታልቃለች። ሀገር ቤት ላሉ ለቤት ሰራተኞች እጅግ አዘንኩላቸው። ያ ግፍ ይሆን እንዲህ እንድሆን ያደረገኝ? እናት አባቴ በሰፈሩበት መስፈሪያ እኔው እየከፈልኩት ነው። የሰራተኞቹ ጡር ነው መሰለኝ የደረሰብኝ።
* አንዳንዴ የእንጀራ በወጥ አምሮቴን ለመወጣት ብዬ ያው በመጥበሻ (padella) ላይ እንጀራ መጋገር፣ ቆንጆ ወጥ ለመሥራት አይኔ እስኪቃጠል ድረስ ሽንኩርት ስከትፍና ሳቁላላ መዋል ... ከዚህም አልፎ ተርፎ ወደውጪ ስወጣ ወጥ ወጥ እየሸተትኩ መውጣቱ። ይህ ችግር በኔው አፓርትመንቶ ውስጥም አለ። ክፋቱ ደግሞ ልብሱ አንዴ ከሸተተ ወድያው ላውንደሪ ካልተወረወረ አርማዲዮ ውስጥ ያለውን ሁሉ ይበክለዋል። እኔ የምለው - በዚህ ጉዳይ ምን ቢደረግ ይሻላል ትላላችሁ? አገር ቤት እያለሁ እንዲህ አይነት ችግር አልነበረም እኮ! ወይም አይታወቀንም ነበር መሰለኝ? ምክንያቱ ማድቤታችን ለብቻ ራቅ ያለ ስለነበር ነው እንዳልል የብዙዎቻችን ቤት መኝታ ቤቱም ሳሎኑም ኪችኑም አንድ ላይ ነው። ለዛውም በከሰል ወይም በናፍጣ በሚሰራ ምድጃ እየተጠቀምን...
* በጣሊያን ሀገር ከደባል ጋ መኖር የተለመደ ነው። በተለይ የምንከራየው አንድ አፓርታመንቶ ከሆነ አንዱን ክፍል ይዞ መኖር የተለመደ ነው። መቼም በአብሮ መኖር ላይ ስንት አይነት ፀባይ አለ መሰላችሁ። ብቻ ትግስት የሌለን ከሆነ…

* ሌላው ደግሞ ሱፐር ማርኬት መመላለሱ። መቼም እኔ እንደሱ የሚያስጠላኝ ነገር የለም። አንዳንዴማ በየጊዜው እየሄዱ አስቤዛ ከማድረግ ብዬ እንደው ምንም ሳልበላ ጾሜን የማድርበት ጊዜ አለ። ማን ምግብ ይቀቅላል። ተመልሼ አዲስ አበባ ሂጂ በሰራተኛ ለመኖር ጊዚው ነው የናፈቀኝ። ግን እኒ እንደ ቢተሰቦቼ አልሆንም። ችግራቸው በደንብ ስለግባኝ ሰራተኞቼን በደንብ እይዛቸዋለሁ።...
* ሌላው ስልቺት ያለኝ ወደ ሥራ ለመሄድ ጠዋት ጠዋት የእንቅልፍ መቀስቀሻው ሰዓት (la sveglia)። ጥዋት በ6 ሰዓት ላይ Kirrrrrrr እያለ የሚጮህው። በተለይ አምሽቼ ስተኛ ጥዋት ላይ ደስ የሚል ህልም እና እንቅልፍ ላይ እያለሁ ! እኔ እንደው ገሀነም ሲገባ እሳት ብቻ ሳይሆን የዚህች የተረገመች ሰዓት አላርም ሁሉ የሚንጫጫ ነው እሚመስለኝ። ... ይቀጥላል ...
* ሌላው ደግሞ የስለቸኝ እዚህ ያለውን የአበሻውን የተከፋ ፊት ማየት። ሳቅና ጨዋታ ያለበት ወይም መዝናኛ ያለበት ቦታ አለመኖሩ መሰለኝ!! በዚህም ምክንያት ይመስላል ሁል ጊዜ አበሻው የተከፋ ፊት ያለው ነው የሚመስለው። (በእረፍት ጊዜያችን እንኳ ይህ ነው የሚባል ዝግጅት ተባብረን ማድረግ ስለማንችል ይመስለኛል። አንዳንዶቹ አስተባብረው ለማድረግ ሲጥሩ ቋሚ ሕብረት ያጣሉ።
* ዋናውን እረስቼው!!! የዚህ ሀገር የአየር ፀባይ!!! ብርዱ ያው ብርድ ሲሆን፣ ሙቀቱ ደግሞ እሣት በመሆኑ። እኔ ያደግኩት umidita የሚባል ነገር የሌለበት ያማረ ጸሀይ ያለሀሳብ እየጠጣሁ ተፈጥሮ ያደላት ውብ አገር ውስጥ ነበር:: ታዲያ የዚህ አገር የአየሩ ሁኔታ 9 ወር ሙሉ ጥቅጥቅ ያለ ክረምት ነው። ክረምት ቢሉ ደሞ እንደኛ አገር በቆሎ እሽት በከስል እየተጠበስ መንገድ ላይ የሚሽጥበት እና ዝናቡ አንድ ጊዜ ብቻ ዘንቦ ወዲያው ጸሀይዋ ፈገግ ብላ በደስታ የምትወጣበት አይነታይደለም እኮ!!
እዚህ እኮ ግርም የሚለኝ አንዳንዴ ከጠዋቱ በ 8.00 ሰዓት ስነሳ ከምሽቱ በ 8.00 ሰአት የተነሳሁ የሚመስለኝ። ይታያችሁ እስቲ! ጠዋት በ8፡00 ሰዓት ገና ጨለማ የሚሆንበት አገር! ደግሞ በረዶ የጣለ ጊዜ ስትራመድ ጉልበት ላይ የሚደርስ ወይም ቅዝቃዜው አጥንት የሚስብር አይነት ክረምት ነው።
እንደምንም አይኔን ጠራርጌ ተነስቼ የምስራውን ስራርቼ ሳልጨርስ alle 4.00 di pomeriggio ድቅድቅ ያለው ጨለማ ይመጣል። ምን እሱ ብቻ ያንን ብርድ ለመከላከል ግማሽ ቁምሳጥኔን የያዘውን የክረምታቸውን ጃኬትና ለብርዱ ደግሞ ከሱሬዬ በታች ሌላ ቱታ ለብሼ ነው የምውለው።
ደግሞ እፎይ ጸሀይ ወጣልን ከመባሉ ከፈረንጆቹ ጋር buongiorno ስትባባል ወዲያው ስለአየሩ ቁንጅና ወሬ ይነሳል። እነሱም ያው በማጋነን ሲያወሩ ሁልጊዜ መስማቱ ስልችት ብሎኛል። ግን አይፈረድባቸውም። እራሳቸውም እዚሁ ተወልደው እዚሁ አድገውበት አለመዱትም መሰለኝ። ታዲያ እነሱ እዚሁ ያልለመዱትን እኛ እንዴት አድርገን?
ጉድ እኮ ነው ደሞ ይሄም ሙቀት ውበት ሆኖ!! እንዴ! ታዲያ ወበቁ አያስቆም፣ አያስቀም፣ አያስተኛ፣ በእዛ ላይ ቤቶቹ ከማርጀታችው የተነሳ ... ልክ በባዶ ድስት ወይም በእንፋሎት እንደተቀቀለ broccoli ሆኖ መዋል ነው።
አይ አለመታደል በዚያ ላይ የሚውዱት የበጋው ወቅታቸው ስትመጣ ቀኑ አጥሮ ቁጭ። ማታ ከስራ ደክሞኝ መጥቼ ዛሬ በጊዜ ለጥ ነው እላለሁ ብል ጸሀይዋ አትጠልቅ። እስከ ምሽቱ 9.00 ሰዓት ድረስ አይኔን እያጠናገረች። ያው ወደ 10.00 ሰዓት ላይ እንደው ገርበብ ሲል አይ የራሱ ጉዳይ ብዬ አይኔን እንደጨፈንኩኝ ከመቼው እንደሚነጋ አትጠይቁኝ። እንደምንም አይኔን እያሻሽሁ ስዓቱን ስመለከት ገና ከንጋቱ 4.00 ሰዓት ነው። ይሄ ታዲያ ኑሮ ነው ???
.
* እነዚህ ነጮች እንደው አንዳንዴ ጭንቅላታቸው እንደ ቂጣቸው ሊጥ ነው ልበል? አፍሪካ ሲባሉ ካለ ዝሆንና አንበሳ በቀር የት እንዳለች እንኳን ጨርሰው አያውቁም:: በተለይ ወጣቶቹ ከኢትዮጵያ ነኝ ስትላቸው የት ናት ይሉሀል። አፍሪካ ውስጥ ስትል አፍሪካ ያለችው ላቲን ውስጥ ነው? ብለው ሲጠይቁህ አንጀትህን ነው የሚቆርጡት:: እንደውም አዛውንቶቹ ይሻላሉ። በተለይ በሀይለስላሴ ወይም በአድዋ ጦርነት እንዲሁም ቅኝ ባለመያዛችን ለይተው ያውቁናል::
* አንዱ በጣም በዌስተርኑ አለም ከሚያስጠላው ነገር የራስን የቅርብ ጎደኛ ለሌላ ሰው ማማት፣ ሚስት ባልን ማማት ባል ሚስትን ማማት፣ በጣም አስጸያፊ ነገር ወሬና ወንድም እና እህት እንደትልቅ ጠላት መተያየት በትንሽ በትልቁ፣
* ሌላው ደግሞ በጣም ከሰለቸኝ ስም ሀበሻው ሁሉ በሌለው ስም መጠራት
* የአበሻ እድሜ ቀረጣ። ውጪ ከሚገኘው አበሻ መሀከል ብዙዎቹ እድሜያቸውን ቆርጠው ነው የሚናገሩት። አንዳንዴማ ፈረንጅ ፊት እድመያቸውን ሲገመድሉት ያስደነግጡኛል።
* ካልሳቅህ የፈረድብሃል የተባለ ይመስል ከድድ እስከ ድድ የሚስቅ አስመሳይ
* በየቀኑ በዜና ላይ እከሌ ሞተ፣ የከሌ ቤት ተቃጠለ፣ እከሌ ጠፋች ... አንድም ጥሩ ዜና የለም እኮ!!
* እዚህ ተዘፍዝፎ አገርቤት ያሉት ምን ማድረግ እንዳለባቸው መለፍለፍ ...
* በጠባብ ካሜራ ወይም በትንሽ አፓርታመንቶ ውስጥ ከሌላ ሰው ጋር ተከራይቶ መቀመጥ። ... ... ...
* እኔን በጣም ከሚገርሙኝ ነገር ደግሞ የአፓርታሜንቶ ጎረቤትን ያለማናገር አንዱ ነው። መፈራራት ነው መሰለኝ። ግፋ ቢል buongiorno ወይም buonasera ነው እንጂ ምንም ስለነሱ አታውቅም። እነሱም ስለአንተ አያውቁም። ለምን እንደሆነ አይገባኝም። ... ይቀጥላል ...
* ሌላው እዚህ አገር ስልችትና ድክም የሚያደርገኝ የቴሌ ማርኬቶች የስልክ ጥሪ FastWeb, Alice, Tele2 ... ወዘተ ... በተለይ ስልኩን ቶሎ ላለመዝጋት ብዬ ላዳምጣቸው ከአልኳቸውማ! በጥያቄ ራሴን ያዞሩኛል። ስልኩን እንኳን መዝጋት አልችልም። እስኪ ይህንን ምን ትሉታላችሁ?
* ሌላው "እዚህ ከመጣህ ስንት ጊዜህ ነው?" የሚለውና "ከየት ሀገር መጣህ?" የሚለው ደረቅ ጥያቄ ... ይቀጥላል ...
ሌላውን የሚሰለቸኝን ነገር በሌላ ጊዜ። እናንተም ጨማምሩበት ታዲያ! ........
እስከዛው ይመቻችሁ
ሚካኤል ስልቹው እስቲ በተቃራኒው እናንተ ደግሞ እዚህ ሀገር ደስ ከሚላችሁ ነገር በሚል አርዕስት ጫር ጫር አድርጉ ...

እዚህ ጣሊያን ሀገር ደስ ከሚለኝ


እስቲ መቼም እዚህ የሚሰለቸንን ያክል ደስ የሚል ነግርም ስለሞላ አንድ እንበል። እናንተም የምትወዱትንና በጣም የሚጥማችሁን ነገሮች እስቲ ጠቁሙ::
እኔ በበኩሌ በጣም ደስ ከሚለኝ ነገር ምግባቸው በተለይ ጣት የሚያስቆረጥመው ፓስታ አል ፎርኖ። ነፍሴ ነው።
ከሀገራቸው የወቅት ግዜያቸው estateውን በጣም ነው የምወድላቸው። ምክንያቱም የሚያማምሩ ሴቶች ጥብቆና ሚኒ አድርገው በተለይ ደግሞ ወደባህር ያለበት ሀገር ሄደህ በገፍ በኮስቱሜ እየሆኑ ወዲህ ወዲያ ሲሯሯጡና ሳያቸው ከክፍያ ነጻ መመልከትን የመሰለ ነገር የለም። ስትሪፕ ክለብ በአደባባይ ማለት እኮ ነው። እንደው ሲመቹ!
ሌላው ደግሞ ትንሽ ሊያስቃቹህ ይችላል ግን እዚህ ሀብታም ነኝ ድሀ ነኝ የሚል ልዩነት ሳይኖር ሁሉም በአንድ ማርኬት ውስጥ ባንድ ላይ የፈለኩትን ነገሮች ጋዛዝቼና (ያው ሀብታሙ የሚበላውን ምግብ ሁሉ ገዝቼ) እኔም መብላቴ። ታዲያ ይህ ይህ ነገሮች ሀገር ቤት እንደህልም ናቸው።

የነጮች አክብሮት ኢንፎርማሲዮኔ ወይም መንገድ አሳዩኝ ብለህ ስትጠይቃቸው ባያውቁኝም መልሳቸውና ሰላምታቸው እንዴት አደንቀዋለሁ መሰላችሁ። በሁሉም ቦታ ለሁሉም ነገር grazie የምትለው ትህትናቸው። የሌላውን አላውቅም እንጂ ይሄን ሀገር በሰውነቴ ተከብሬ ስለምኖርበት እውደዋለሁ

በግሌ ደግሞ ደስ የሚለኝ የራሴን ኑሮ መኖር መጀመሬ አገር ቤት ብሆን ኖሮ ይኼኔ ሥራ ሁላ ብሰራ ከአባቴ ቤት አልወጣም ነበር ሁልግዜ ልጅ እንደሆንኩ የምኖር የመስለኛል::

እኔ ደስ ከሚሉኝ ነገሮች ውስጥ የትም ውዬ ድክም ራብ ብሎኝ ስገባ እድሜ ለ congelati በትንሽ ደቂቃዎች micronde ክትቼው አብስዬ ስበላ .....አይ እናቴ ጉዴን አላየሽ ሽንኩርት መላጥ የለ መክተፍ የለ .......ግልግል እላለሁ:: ብቻ ሁል ጊዜ እሱን ስበላ ራሴው ላይ ምግቡ እንዳይበቅልብኝ ፈርቻለሁ።
አሁንም ሆዳም እንዳትሉኝ ስው እቤትህ ቢመጣና ምንም የሚበላ ነገር ከሌለ እድሜ ለ pizza d'asporto ወይም ለቻይና ምግብ። እዛው ቤትህ ቁጭ ብለህ ከዲቫኖ ሳትነሳ በስልክ ማዘዝና እንግዶችህን ማስተናገድ። ኤውሮህን ይጭነቀው እንጂ።

እዚህ ደግሞ ከፈረንጆቹም ጋር አብረህ ስትውል ጋብዘኝ ልጋብዝህ አንተ ክፈል እኔ ልክፈል የለ። የየራስህን ከፍለህ ሳትጨናነቅ በጋራ መዝናናት እያለ። ስለአንተ ማንም አያገባውም የፈለከውን ታረጋልህ :: ይሄ ከምንም በላይ የምወደው ነው :: ምን ያህል ዲሞክራሲና ነጻነት እንዳላቸው ያው እንደምታውቁት ነው እስከ አፍ ጢምህ ድረስ ነው ያለህ። ሀገር ቤት እያለሁ ገበያ አልችልም ነበር:: ገበያ ከሄድኩ ስለማልከራከር ከስሬ እመጣለሁ :: እዚህ ግን ቀንስ፣ መሸጫውን፣ መርቅ ... የለ። ዋጋውን እንቅጩን አውቀህ ወይ ትገዛለህ ወይ ትሄዳለህ። 4. የፈለከው ቦታ መብላት - ሆዳም እንዳትሉኝ ግን ብዙ ጊዜ ስለምቸኩል የሆነ ነገር እየበላሁ ጉዞ ጀምራለሁ :: ታዲይ ኢትዮጲያ ቢሆን ከ "አያፍርም ወይ " እስከ "ቡዳ ይበላሀል " የማይባለው ነገር የለም ::
ሌላው የገንዘብ አያያዛቸው ይመቸኛል። sconto ያለበት ሱቅ ሲያፈላልጉ ለጉድ ነው :: የሌላውን ባላውቅም ጣሊያኖች በዚህ የሚችላቸው ያለ አይመስለኝም :: አንዱ ኢንዶኔዥያዊ ጉዋደኛዬ የማያውቀው (በቅናሽ የሚሸጥበት) ሱቅ የለም :: እኔ ደሞ አሳ በጣም ነው የምጨፈጭፈው:: እና ልጁን "ባክህ ዓሳ ርካሽ የሆነበትን ሱፐር መርካቶ ነገረኝ " ስለው "ምን አይነት ዓሳ ነው የምትፈልገው " አለኝ :: እንግዴ ይታያችሁ ምን ያህል እንደሚያውቅ።


ዘመናዊ ትምህርት ለተሻለ የእድገት ደረጃ

ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

.......... የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በመሆን ለምትከታተሉን ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ከሁሉ በፊት እንዴት ሰነበታችሁ? አብርሃም ዘውዴ እባላለሁ ከዚህ ድሕረ ገፅ አዘጋጆች አንዱ ነኝ::

.......... ባለፈው ጊዜ በቦሎኛ ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ፣ በወለጋና በመቀሌ ዩኒቨርስቲዎች መካከል በጋራ ሊያሰራቸው የሚያስችል ሳይንሳዊ የቴክኖሎጂ ስምምነት መፈረሙን የሚያበስር ለሀገር የሚጠቅም ዜና ባጭሩ ለአንባቢያን ማቅረባችን ይታወሳል:: በጉዳዩ አስተያየቱን እንዲሰጠን ከፕሮጀክቱ አስተባባሪ ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ ጋር ያደረግኩትን ቃለምልልስ ከዚህ በመቀጠል አቀርብላችኋለሁ፣

.......... ጥያቄ፣ የቦሎኛን ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ማስተባበር ለምን አስፈለገ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ የቦሎኛን ዩኒቨርስቲ ከአዲስ አበባ፣ ከወለጋና ከመቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ማስተባበር አስፈላጊ የሆነበት ዋናው አብይ ምክንያት እንደምናውቀው በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች በተለይም ዩኒቨርስቲዎች አብዛኞቹ ከተቋቋሙ ረጅም እድሜ የሌላቸው እንደመሆናቸው መጠን በቂ የትምህርት መሳሪያና ብቁ የሰለጠነ የሰው ሀይል ስለሚያንሳቸው ይህ ስምምነት ለተሻለ እድገት አቅጣጫና መንገድ ይቀይሳል የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው::

.......... ጥያቄ፣ በጣሊያን ካሉት ሁሉ ዩኒቨርስቲዎች በተለይ የቦሎኛን ዩኒቨርስቲ እንዴት ልትመርጥ ቻልክ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ በመጀመሪያ ደረጃ የቦሎኛ ዩኒቨርስቲ ከአውሮፓ አንጋፋው ዩኒቨርስቲ በመሆኑ በይዘቱና በጥራቱ የታወቀ ስለሆነና በዚሁ ዩኒቨርስቲ በትርፍ ጊዜዬ በማስተማር ሙያ ላይ ስለተሰማራሁ የቦሎኛን ዩኒቨርቲ ለመምረጥ ብዙ ጊዜም አልወስውደብኝም:: በሌላ በኩል ደግሞ አብረውኝ የሚሰሩት የድፓርትሜንት ሀላፊዎች በፕሮጀክቱ ተካፋይ መሆናቸውን በመግለፃቸውና በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎችም በኩል ከፍተኛ ትብብር በማሳየታቸው ቦሎኛን መምረጥ ቻልኩ::

.......... ጥያቄ፣ ይህን ውጤት ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ወሰደባችሁ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ በርግጥ ፊርማው ላይ ልንደርስ የቻልነው ከበርካታ ጥረቶች በኋላ ነው፣ በዚህ በጣሊያን በኩል ውሳኔ ላይ ከመድረስ በፊት አንዳንድ ጥቃቅን ውጣ ውረዶች ገጥመውን ነበር፣ ሆኖም ፕሮጀክቱ ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሎ ስለታመነበት በትዕግሥት እስከመጨረሻው መከታተል አስፈላጊ በመሆኑ የሥራ ውጤቱ የሆነው ፊርማ ላይ ሊደረስ ተችሏል::

..........ጥያቄ፣ ስምምነቱ የተፈፀመው በዬትኛው የትምህርት መስክ ነበር?
ዶ/ር ዘለቀ፣ ስምምነቱ ለጊዜው የእርሻ፣ የሕግንና የታሪክ ትምህርቶችን ብቻ ይመለከታል::

.......... ጥያቄ፣ ለጊዜው ስትል በሌሎች ትምህርቶችስ ላይ የታሰበ ነገር አለ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ ከነዚህ ስምምነቱ ከተደረሰባቸው የትምህርት ዘርፎች ሌላ በሚቀጥለው ዙር ደግሞ በሕክምናና በእንጅኔሪንግ ትምህርቶች ላይ ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት ላይ እንገኛለን::

.......... ጥያቄ፣ በዚህ ፕሮጀክት በይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆነው ማነው?
ዶ/ር ዘለቀ፣ በፕሮጀክቱ ተካፋይ የሆኑት ሁሉም ከላይ የጠቀስኳቸው ዩኒቨርስቲዎች ከፕሮጀክቱ ወደፊት ሊገኙ በሚችሉት ጥቅሞች ሁሉ በጋራ እኩል ተካፋይ ይሆናሉ:: አንዱ እርዳታ ለጋሽ ሌላው ገንዘብ ለማኝ የሆነበት አይነት ስምምነት አይደለም::

……....ጥያቄ፣ ለወደፊትስ በተመሳሳይ ተግባር እዚህ በመሆን ለኢትዮጵያ ምን የሥራ እቅድ አለህ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ አዎን እኔ መደበኛ ሥራዬ ዩኒቨርስቲ ማስተማር ሳይሆን የሌላ ድርጅት ሰራተኛ ነኝ፣ እንደዚህ አይነቱን ተግባር የማከናውነው ካለኝ ትርፍ ጊዜ በመቆጠብ ነው፣ በኢትዮጵያ አንድ ጥሩ አባባል አለ “ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም”:: አንድ ሰው አገሩን ለመርዳት ፍላጎቱ ካደረበት በተለያየ መልክ ሊረዳ ይችላል፣ እኔም ኢትዮጵያን በሙያዬ የመርዳት ግዴታ እንዳለብኝ በሚገባ ተረድቼ ይህንኑ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እገኛለሁ:: በርግጥ ከሥራ መብዛት የተነሳ የተፈለገውን ያህል እንደሚታሰበው መሥራት አይቻልም አንዳንዴ የጊዜ ችግሮች ይገጥማሉ::

.......... ጥያቄ፣ በመጨረሻ ልታስተላልፍ የምትፈልገው መልእክት ካለህ?
ዶ/ር ዘለቀ፣ በኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎችን ብዛት ብቻ ሳይሆን ጥራታቸውንም ጭምር መጠበቅ ከምንጊዜም በላይ አስፈላጊ በመሆኑ በውጭ ሀገር የምንኖር ኢትዮጵያዉያንም ሆንን የውጭ ሀገር ዜጎች ዘመናዊ ትምህርት ለተሻለ የእድገት ደረጃ በማለት ተገቢውን ሁሉ ማካሄድ ይኖርብናል እላለሁ ፣ አብርሃም አንተንም አመሰግንሃለሁ::
ደህና ሁኑ


“ኢትዮጵያን እንርዳት”

ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
30/07/2009

……....ባለፈው ሣምንት በቦሎኛ ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ፣ በወለጋ፣ በመቀሌ ዩኒቨርስቲዎች መካከል በጋራ ሊያሰራቸው የሚያስችልና ረጅም ጊዜ የፈጀውን ክፍል አንድ ሳይንሳዊ ስምምነት ለመፈራረም በቅተዋል:: ስምምነቱንም የፈረሙት እያንዳንዱን ዩኒቨርስቲ በመወከል በመሥራት ላይ የሚገኙት የየዩኒቨርስቲዎቹ የዲን ሃላፊዎች ሲሆኑ ይህ ፕሮጀክት ለጊዜው ሁሎችንም የትምሕርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ያጠቃለለ ሳይሆን የተወሰኑትን የትምህርት ዘርፎች ብቻ የሚመለከት ይሆናል::

……....የአዲስ አበባና የቦሎኛ ዩኒቨርስቲ ስምምነት በታሪክ ትምህርት ላይ ያተኮረ ሲሆን በወለጋና በቦሎኛ ዩኒቨርስቲ መካከል ደግሞ የእርሻ ትምህርትን ይመለከታል:: በመቀሌና በቦሎኛ ዩኒቨርስቲ መካከል የተፈረመው ስምምነት ግን በሕግ ትምህርት ላይ ያተኮረ ይሆናል::

……....ምንም እንኳን ሃሳቡን የሰነዘርኩትና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ እኔ ብሆንም ይህ ስምምነት ከግብ ሊደርስ የቻለው ከእትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች በኩል በተባበሩኝ እትዮጵያውያንና ከቦሎኛ ዩኒቨርስቲ በኩል ደግሞ ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ተስፋቸውን ባለመቁረጥ እስከመጨረሻ በትዕግስት አብረውኝ በሰሩት የሙያ ባልደረባዎች ተባባሪነት በመሆኑ ሁሉንም በዚህ አጋጣሚ ላመሰግን እወዳለሁ::

zeleke_eresso@yahoo.itለማርኮ በየነና ለቤተሰቡ ወገናዊ የድጋፍ ደብዳቤ

የጣሊያን ዘረኞች ባይወዱትም ይስሙት

……....ሰሞኑን ናፖሊ ተብላ በምትጠራው አንዲት ታሪካዊ የጣሊያን ከተማ ውስጥ በማርኮ በየነ (አባቱ በትውልድ ኢትዮጵያዊ) የዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ላይ የተፈፀመውን ዘረኝነት የድብደባ ሙከራን አስመልክቶ የተፃፈውን ባነበብኩበት ወቅት በልጅነቴ የሰማሁት አንድ ነገር ትዝ አለኝ:: ነገሩም አያቶቻችን ይናገሩት የነበረው “ጣሊያኖች ፋሺስቶች ናቸው” የሚለው ተራ መሰል አባባል ነበር:: ይህም አነጋገር መሉ በሙሉ እውነትን ያዘለ ነው ብሎ ባይባልም መሉ በሙሉ ከውነት የራቀ ነው ለማለት ግን እጅግ በጣም ያዳግታል:: በተለይም በነዚህ በመጨረሻዎቹ አመታት አካባቢ በጣሊያን አገር ውስጥ ማለትም እንደተቀሩት የአውሮፓ አንዳንድ ከተሞች ሁሉ በውጭ አገር ዜጋው በተለይም በአፍሪካውያን ላይ ከቃላት ዘለፋዎች አልፎ ተርፎ የድብደባ ሙከራዎች በተግባር ሲከሰቱ ማየት ከተጀመረ ሰንበት ብሏል::

……....ለነገሩ ጣሊያናዊ ሁሉ ፋሺስት ወይም ተደባዳቢ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ; ጥቂት “ነጭ የበላይ ነው” የሚሉ እብድ ውሾች የአያቶቻቸውን ፋሺስታዊ አመለካከት እስካሁንም ያልተላቀቁ ሁሉ እራሳቸውን ቀና ቀና በማድረግ ህብረተሰቡ ለጦርነት እንዲነሳ የቅስቀሳ ሙከራቸውን በመዘርጋት ላይ ስለሆኑ “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል” የሚለውን የአባቶቻችን ተረት ማስታወሱ ለወደፊት ሊጠቅም ይችላል ባይ ነኝ::

……....በማርኮ በየነ ላይ የተፈፀመው ድብደባ ቁስሉ ከነገ ወዲያ ታክሞ ይድናል; ታክሞ የማይድነው ቁስል ግን ቢኖር ለምን? ምን አድርጌ ነው? እና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ ከማጣት የተነሳ በውስጥ የሚፈጠረውና መልስም የማይገኝለት የጨንጓራ በሽታ ነው:: ይህ ለሁላችን እንደምሳሌ ልንወስደው የሚገባ ትምህርት ሊሆን ይችላል ብዬ በመገመት ለማርኮና ለቤተሰቦቹ በዚህ አጋጣሚ ካጠገባችሁ ነን ብዬ በማለት ደህና ሁኑ እላለሁ::

ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
Zeleke_eresso@yahoo.it
"በወጣቱ ማርኮ በየነ ላይ የተፈጸመበት ወንጀል ከዘር ማጥፋት ወንጀለኛነትና ጥቃት ጋር የተያያዘ ነው" (አባቱ ፕሮፌሰር ያቆብ በየነ)
09 03 09

……....ማርኮ በየነ ነዋሪነቱ ናፖሊ፣ ትውልዱ እዚሁ ጣሊያን፤ አባቱ ኢትዮጲያዊ እናቱ ጣሊያናዊት የሆኑ የ22 ዓመት ጎልማሳና የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው። ከትናንት በስቲያ በተለመደው ቦታ ከጓደኞቹ ጋር በዋለበት የናፖሊ መሀል ከተማ ውስጥ የሚገኘው ፒያዛ (Piazza del Gesù) አካባቢ ዘረኝነትን ቤሚያራምዱ ግለሰቦች ስላደረሱበት በደል የጋዜጣዊ መግለጫ አድርጓል። በቃለመጠይቁ ላይ ከሰጠው መልስ ላይ “ከዚህ ጥፋ!! ቆሻሻ ባሪያ…!!” እያሉ እንደዘለፉትና ይባስ ብለውም ጥቃት እንደፈጸሙበት ሁሉ አብራርቷል። የማርኮ ቤተሰቦችም ይህንን ጉዳይ በሚሰማ ፍ/ቤት ክስ የሚያቀረቡ ከሆነ መሠረታዊ አዝማሚያው በወጣቱ ላይ ያደረሱበትን ጥቃትና የዘረኛነት ወንጀል ዝንባሌ ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። በዘር ማጥፋት ወንጀለኛነት እና በተሰነዘረበት ጥቃት ላይ ከተመረኮዘ ችሎቱ በቀጣይ መታየቱ የማይቀር ስለሆነ በአንክሮ እንከታተለዋለን።

……....ከዚህ በታች የሰፈረው ጽሁፍ የዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት አባቱ ፕሮፈሰር ያቆብ በየነ እና ለጥቃቱ ሰለባ የሆነው ልጃቸው ማርኮ በየነ በጋዜጣው ላሪፑብሊካ (La repubblica) ቃለመጠይቅ ላይ የሰጡትን ምላሽ የሚያሳይ ነው። ፕሮፈሰር ያቆብ በየነ በጋዜጣ መግለጫ መልሳቸው ላይ “ዘረኝነት በዚህ ዕድሜዬ ማየቴ እና ከዚህ በፊት ምንም አይነት የዘር መድልዎ ያልተፈጸመባት ናፖሊ ውስጥ አሁን መከሰቱ እጅግ አሳዝኖኛል” ብለዋል። ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ የወደፊቱ እርምጃቸው ምን እንደሚሆን ይዳስሳል።

አብራሃም ዘውዴ (ቦሎኛ)


አሳዛኝ ዜና!

……....በጀልባ ውቅያኖስን በማቋረጥ ወደ ጣሊያን ለመግባት በአደረጉት ሙከራ ቁጥራቸው 75 የሆኑ ኤርትራውያን ህይወታቸዉን አጡ። እነዚህን ስደተኞች ይዛ ከሃያ ቀን በፊት ከሊቢያ ከተነሣችው ጀልባ ነዳጅ አልቆባት ሲሲሊ ካናል ውስጥ ለብዙ ቀኖች ቆማ እንደነበረና በሕይወት ማግኘት የተቻለው 5ቱን ብቻ እንደሆነ ነው። ከእነዚህም ሁለቱ ከፍተኛ የጤና ችግር ላይ በመሆናቸው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተጠቁሟል።

……....እስካሁን ባህር ውስጥ ከተጣሉት ግለሰቦች ሬሳቸው መገኘቱ በየትኛውም የዜና ምንጮች አልተዘገበም። በኣጠገባቸው ያልፉ የነበሩ መርከቦች እርዳታ የመንፈግቸውም ጉዳይ ዋናው ምክንያት የጣሊያን መንግስት በመርከበኞች ላይም ሆነ በባህር ዳር ጠባቂዎች ላይ በተለያዩ ሁኔታዎች ተጽዕኖ በማሳደሩ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ ጉዳዩ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ ነገሩ ይህን ያህል አስደንጋጭ የሆነው ለምንድነው? ቢባል የኛው ወገን መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የአሟሟታቸው ሁኔታ ነው። በአንድ ጊዜ ጉዞ ብዙ መሞታቸውና ወደ ባህር መጣላቸውን፣ ለሞታቸው ምክንያት የሆነው ደግሞ በጥማት የባህሩን ውሃ ከጠጡ በኋላ በጠና እየታመሙ መሞታቸው ነው። በአሻጋሪዎቻቸው ተደብድበው ለሞት የተዳረጉም ሊኖሩ ይችላሉ” ብለው አንዳንድ የጣሊያን ህትመቶች ጥርጣሬያቸውን ጠቁመዋል።

……....መቼም ይህ ዜና የዘገነነና ጨካኝ በመሆኑ ብዙዎቻንን እያነጋገረን ይገኛል። ከምንገናኛቸው ወገኖች የመጀመሪያው ርዕስ አድርገን የምንጨዋወተው ይኽንኑ ሆኗል። ሁላችንንም ለጊዜው ሀዘን፣ ንዴትና ቁጭት፣ እልህና ወኔ ቢፈታተኑንም እንደየእምነታችን ልንጸልይላቸው ይገባናል። ከዚሁ ጉዞ በህይወት የተረፉትም እንኳን በጣሊያን ሀገር የተለመደው የስደተኞች መብት ችግር ላይ እንዳይወድቁ እንዲሆንላቸውይገባል። ማለትም በቅርቡ ጣሊያን በአፀደቀችው ሕግ ከአምስት እስከ አስር ሺህ ዩሮ ይቀጡና ተመልሶ ወደየመጡበት የመባረራቸው ሁኔታ ስለአለ ይህ ደግሞ እንዳይደርስባቸው የሕብረት ድምጻችንን ማሰማት የሚቀጥለው ተግባራችን ሊሆን ይገባል።

……....ሰለጠነ የምንለው ኅብረተሰባችን ገሃድ በሆነ ሁኔታ የውጭ ዜጎችን ያለመቀበል ስሜት እያሳደገ መምጣቱ ይታያል። ይህም ሌሎችን ካለማወቅ የመጣ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ለሌሎች ላለማካፈል ወይም ከአጉል ራስ ወዳድነት የመነጨ ነው። ምንም እንኳን መንግሥታት ስደትን የመቆጣጠር ሕጋዊ መብት ያላቸው ቢሆንም ስደተኞች ደግሞ የመዳንና አስቸኳይ ርዳታ የማግኘት የማይገርሰስ ሰበአዊ መብት አላቸው። ይህን መሰል አሳዛኝ ሁኔታዎች እየተደጋገመ ስለሚከሰቱ ይህንን የሚመለከት ጥብቅ የዓለም አቀፍ ፖሊሲ ያስፈልጋል ባይ ነኝ።... ከዚህም ላይ ተደምሮ ጸጥ ያለው የምዕራባዊያን ግድየለሽነትና ግድየለሽነት (indiferenza)...

አብራሃም ዘውዴ (ቦሎኛ)
22 08 2009


.

የበረሀውን ሳይሆን የባህሩን

……....የቅጽል ስሜ ደፋሩ ይባላል። በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ እገኛለሁ። ረጅሙንና የበረሀውን ታሪክና ጉዞ ወደ ኋላ እንጨዋወተዋለን። ለአሁኑ በጀልባ ላይ ሆኜ ያየሁት አሳር እና አበሳ በአጭሩ።

……...." ገና ከመነሻችን ላይ ጀልባውን የሚነዳውና የሚቀዝፈው ከእኛው መካከል መሆን እንደነበረበት ሲነግረን በጣም ነው የተደናገጥነው። ነገር ግን ምንም ምርጫ አልነበረንም። ቀዛፊው ደግሞ አሣ አጥማጅ ከመሆኑ በስተቀር ሌላ የሚያውቀው ስላልነበር ሁኔታው ለአደጋ የሚያጋልጠን ነበር።

……....ሕልሜን እውነት ለማድረግ 30 ከሚሆኑ ወጣት ጋር በእንጨት ጀልባ ተሳፍሬ ጉዞዬን ቀጠልኩ። የተሳፈርኩበት ጀልባ በምስማር በተመታ እንጨት የተሠራ ነበር። ርዝመቱ 5 ሜትር ነው። ጎኑ ደግሞ ያው ያበጠ ቅርፅ ስላለው መለኪያ የለውም። ባሕሩ ላይ እንዳለን የደረሰው ማዕበልና ሞገድ እጅግ ከባድ ነበር። ሞገድ በተነሳ ቁጥር ጀልባዋ በውሃ ስለምትሞላ ውሃውን እየጨለፍን ወደባህሩ ብንጨምርም ማዕበሉ መልሶ ስለሚያለብሰው ያገኘን ስቃይ ከ-እሰከ ተብሎ አይነገርም። ቅዝቃዜው አጥንት ውስጥ የሚገባ ነው። ሌሊትማ ያለው ቁር አያድርስ ነው። ሁልጊዜ ደግሞ እርጥበት ስለማይለየን ቆፈኑ አያላውስም። በውንም በህልምም የምንናፍቀው የሞቀ ልብስ መልበስ ነው። መተኛት የሚባለው ነገርማ እንደው የማይታሰብ ነው። ከዚህ ሌላ በጀልባው ውስጥ ያለው ቦታ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ እግር ዘርግቶ መተኛት አይቻልም። መቀመጫዎቹ ደግሞ ጠባቦች ነበሩ።

……....በሁለተኛው ቀን በዲዝል ሞተር የሚንቀሳቀሰው ጀልባ ቆመ። ሞተሩ በመጥፋቱ ሊንቀሳቀስ አልቻለም። ግማሽ መንገድ ላይ ያሰብንበት ሳንደርስ ባህር ውስጥ ልንሰጥም ነበር። ሆኖም ሌላ መልካም ዕድል ስለአጋጠመን የባህር አሳሽ መርከብ ደርሶ እኔንና አብረውኝ የተሳፈሩትን ጓደኞቼን ሊያተርፈን ችሏል። ምንም እንኳን ሁሉም ነገር አደገኛ ቢሆንም በሶስት ሌሊትና በአራት ቀን ጉዞ ከተመኘሁት ቦታ ደርሼአለሁ። አራት ቀን ሙሉ በአደረግንው ጉዞ የአትላንቲክ ባህርን አቋርጦ ላምፔዱሳ ደረስኩ። እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በሕይወት ዘመኑ እንደማልደግመው እርግጠኛ ነኝ። በእርግጥ እንደዚህ መሆኑን ባውቅ ኖሮ የማልሞክረው እንደነበርና እኔን ያየህ ተቀጣ የሚያሰኝ መሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ።

……....ለምን ወደ ጣሊያን መምጣት እንደፈለግሁ
…….... “በቤታችን ምንም ገንዘብ የለንም። እኔ የምፈልገው ሠርቶ ገንዘብ ማግኘትን ነው። በቀላሉ ለመናገር እኔ የምፈልገው ቤተሰቤን መርዳት ብቻ ነው። ምንም ይሁን ምን፣ የትም ይሁን የት ሥራ አግኝቼ መሥራቴ ነው ለእኔ ዋና ቁም ነገር። የሥራ ምርጫ በእኔ ዘንድ ቦታ የለውም” የሚለው ወጣት ደፋሩ ህልሙን እውን ለማድረግ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል።
……....በጀልባ እያሳፈሩ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለሚያስገቡ ነጋዴዎች አንድ ሺህ አምስት መቶ ኤውሮ እንደከፈለ ቢናገርም ገንዘቡን እንዴት እንዳገኘው ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም። የጀልባው ባለቤት አንድ ሺህ አምስት መቶ ኤውሮ እንደተቀበለው ተናግሯል። ይህ እንግዲህ ከእያንዳንዱ ተሳፋሪ መሆኑ ነው። ይህን ያህል ገንዘብ የሚጠይቀውም ጀልባውን ለመሥራት እንደሆነ ይነገራቸዋል። ታዲያ ይህ ገንዘብ ምግባቸውን ስለማይጨምር እያንዳንዱ የራሱን ምግብ መያዝ ነበረበት። ከዚህም ሌላ ጀልባውን የሚያንቀሳቅሰውን ሞተር ተሳፋሪዎቹ እራሳቸው መግዛት ነበረባቸው። ... ይቀጥላል ...

……....ከአራት ቀን ጉዞ በኋላ የደሴቷ ወደብ ደርስኩ
……....ስለ ወደፊት ሕይወቴ ምንም የማውቀው ነገር የለም። ስለዚህም ያለኝ ፍርሃት ከፍተኛ ነው። የቀይ መስቀል ከመጸወተኝ አሮጌ ልብስ ሌላ ምንም የለኝም። ወደ አውሮፓ ብገባም የተመኘሁት ሁሉ አልተሳካልኝም። መንግሥት ወደሀገሬ እንድመለስ ወስኖብኛል። መሥራትም አይፈቀድልኝም። እንዲያውም የስደተኞች ማጎሪያ ጣቢያ መቀመጥ ነበረብኝ። የትም መውጣት ስለማይፈቀድልኝ ያው እስረኛ ማለት ነው። እኔ መቼም ወደ ሃገርህ መመለስ አለብህ የሚሉኝ ሁኔታ በምንም መልኩ የማላስበው ነው። ከሃገር ስወጣ ለወላጆቼ ምንም የነገርኳቸው ወይም ያማከርኳቸው ነገር አልነበረም። ከደረስኩ ከሃያ ቀን በኋላ ግን በስልክ እንዳገኘኋቸውና መልካም ዕድል እንደገጠመኝ ስለነገርኳቸው ሁሉ ነገር ቀለል ብሎላቸዋል። ይሁንና የአውሮፓው ክፍለ ዓለም አንፈልግህም እንደሚለኝ ለወላጆቼ መግለጽ አልፈልግም። ከሁለት ያጣ ጎመን የሚያሰኝ ሆኖብኛል። ... ይቀጥላል ...

……....ከአካባቢው ስለዚሁ የሚሉት አላቸው
…….... “እኔ ፖሊስ ነኝ ሥራዬም በአውሮፓ ኅብረት የተቋቋመውን የአካባቢውን ጣቢያ በኀላፊነት መምራት ነው። ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ እረፍት የለኝም ማለት ይቻላል። የስደተኞች ችግር በፖለቲካ እስካልተፈታ ድረስ ችግሩ የሚያቋርጥ አይደለም። ብዙ የሥራ ባልደረቦች ቢመደቡልኝም ሥራው የሚገፋ አይደለም።”እኒህ ያካባቢው አዛዥ የሆኑት ፖሊስ ስለ ስደተኞች ያላቸው አመለካከት የሚወቀስ አይደለም ለሰብአዊ መብት ክብር ይሰጣሉ። እንደሚናገሩት እነዚህ የአፍሪቃ ስደተኞች ሰው አክባሪዎች ማንንም ማስቀየም የማይፈልጉ ናቸው። የተማሩም አሉባቸው። የመጡባቸውን አገሮች ለመጎብኘት አሳብ አላቸው። መጽሓፍ ገዝተው በማንበብ ላይ ናቸው። ወጣቶቹ ለምን እንደሚሰደዱ ማወቅ እፈልጋለሁ። የተማረውና ወጣቱ ትውልድ አገሩን እየለቀቀ ለስደት መዳረጉ ግንዛቤ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ይላሉ። ወጣቱ ትውልድ አገሩን ጥሎ ከፈለሰ ችግር አለባቸው። ይህንን ችግር በየትውልድ አገራቸው ሊፈታላቸው ይሚችል ሁኔታዎች መደረግ ግዴታችን መሆን ይገባዋል። ... ይቀጥላል ...
……....ለማጠቃለያ ያህል
……....
ስደተኞች ያሰቡበት እስኪደርሱ የሚደርስባቸው ችግር በቃላት ተዘርዝሮ አያልቅም።
……....ባህሩን በትንሽ የእንጨት ጀልባ አቋርጠው ከአሰቡበት የሚደርሱት በአሥር ጀልባዎች ከተሳፈሩት ውስጥ አራቱ ናቸው የሚደርሱት። ወጣቶች የአትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ክፍለ ዓለም በሚያደረጉት ሙከራ የሚደርስባቸው የማዕበልና የሞገድ ችግር ይህ ነው ተብሎ በቃላት መግለጽ አይቻልም። እነዚህ ወጣቶች ለዚህ ሁሉ ስቃይ የሚዳረጉት በሕጋዊ መንገድ ወደ አውሮፓ ክፍለ ዓለም መግባት ስለማይችሉ ብቻ መሆኑ ይታወቃል። የቱሪስት የጉዞ ሰነድ ወይም የሥራ ፈቃድ አግኝቶ ከአገራቸው መውጣት አይችሉም። እነርሱ የሚያስቡት በምንም መልኩ አውሮፓ ከደረሱ ሁሉ የተቃና፣ መልካም ዕድል እንደሚገጥማቸው፣ የአውሮፓ ኑሮ የገነት ኑሮ እንደሆነ፣ ወዘተ ... አድርገው ነው የሚያስቡት። ... ይቀጥላል ...
ሌላው ደግሞ ፈረንጅ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ይከበራል፡፡ እኛ ግን አሁን አሁን ወደ ምዕራብ ስንመጣ እንናቃለን። ብዙዎቻችን የአገሩ ዜጋ የማይፈልገውን ስራ እንሰራለን፡፡ ምሁሮችም እንኳን ብንሆን የኑሮ ጉዳይ ስለሆነ እራሳችንን ዝቅ አድርገን ያልፈለግነውን ስራ እንሰራለን፡፡ ያልጠበቅነውና ያልተመኘነው ህይወት ውስጥ እንኖራለን፡፡ በአጠቃላይ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያት ስደተኛ እህቶቻችን ያልፈለጉትን የጠረጋ ሥራ፣ ያልተመኙትን የሰው ቤት ሥራ ... ወዘተ ... ነው የሚሰሩት፡፡ የአውሮፓ ሀገሮችም ቢሆኑ በትናንሽ ጀልባዎች እየተሳፈሩ የሚገቡ ስደተኞችን እንዴት ማስቆም እንደሚቻል ግራ የገባቸው ይመስላል። ማንም ሰው በባህር ላይ አጥር ማጠር ስለማይችል ሁኔታው በቀላሉ የሚታይ ሆኖ አልተገኘም። ... ይቀጥላል ...
……....የበጎ አድረጊዎቹ ምክር ...
የሞቱ ሰዎች አስከሬን ባህር ላይ ሲንሳፈፍ በማውጣት የተሰባበሩ ጀልባዎችን ሰብስቦ በመከመር የሚያገለግሉት የበጎ አድረጊዎች ምክር ...
ስደተኞችን የመግታት እርምጃ መውሰድ ብቻ ሳይሆን አሁን አሁን አስፈሪ መሆኑንና አማራጩን ጭምር ነው የምንጠቁመው። ህይወትን ለማትረፍ ካልሆነ በስተቀር የተሻለ ኑሮ ለማግኘት ብሎ በህገወጥ መሰደድ ይቅርባችሁ። ፀፀት ውስጥ እንዳትገቡ። በዚያው በትውልድ አገራቸው ብትኖሩ እንደሚሻል አትጠራጠሩ።
* አውሮፓ ገነት ናት" የሚለውን አጉል አስተሳሰብ እንድታስወግዱትና ተጨባጩን ሀቅ እንድታውቁት ለማድረግ፣
* አውሮፓ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳያገኙ በመሸቀል ብቻ ኑሮን መግፋት የቱን ያህል እንደሚያደክም፣
* በቅርብ ጊዜ ከመጡት አፍሪካዊያት እህቶቻችን የነበራቸው ህልምና ገሐዳዊው ይዞታ ፍጹም የተለየ ሆኖባቸው በሴትኛ አደሪነት የተሠማሩ መሆናቸውን፣
* ...............................
* ...............................
ይህንንም በመገንዘብ ሐቁ ያልታያችሁ እንዲታያችሁ ይሁን። ... ይቀጥላል ...ማህበራዊ ኑሮአችን በጣሊያን


አብራሃም ዘውዴ


……....ሰላም... አንድ ሰሞን "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" የሚል አባባል እሰማ ነበር። ለእኔም ቢሆን አብራችሁኝ የውጪውን ሕይወት ፅዋ ከምትካፈሉት በስተቀር ማን ሊደርስልኝ። ችግሬንም ብሶቴንም አምቄ እስከመቼ? እናም የይሉኝታንና የሀፍረትን ድር በጣጥሼ ገበናዬን አውጥቼ ላጫውታችሁ። ግን ችኩል ፍርድ አትስጡኝ። ስህተቴንና የጥፋቴን መነሻዬን እንዲሁም መድረሻዬን አጢናችሁ ምክራችሁን ብትለግሱኝ ብዬ ነው።
በጣሊያን ለምንኖረው አበሻ…
……....1/ የአስተሳሰብና የአብሮ የመኖር ገጽታችንን ለማሳየት
……....2/ ከሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ካሉት ጋር በማነፃፀር የውጪ ሀገር ሕይወታችንና አኗኗራችን ለማሳየት
……....3/ ስለማህበራዊ ችግሮቻችን በጨረፍታ በማቅረብ ለወደፊት በጎ ራዕይ የሚያሳየንንና የሚበጀንን ወቅታዊ መፍትሔዎች ለመጠቆም
……....4/ በጣሊያን የውጪ ሀገር ዜጎችን በሚመለከት ወቅታዊ ችግሮችን በመዳሰስና ለውይይት ለማቅረብ
……....5/ የውጪው ህይወታችን ምን እንደሚመስል ግንዛቤ ለማድረግና ራሳችንን ለማስተዋል ...
……....6/ እኔንም ከገጠሙኝ ጨማምሬ በማውጋት በዛው ላይ የግሌን አስተያየት አያይዤ ለማከል
……....7/ ... ይቀጥላል ...
……....ለነገሩ የጣሊያን ሀገር ኑሮውን እዚህ እያለን ስለምናውቀው ከዚህ ጽሁፍ ብዙ አዲስ የሆኑ ነገሮችን አታገኙበትም። ግን "ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም" ይባል የለ! እናም ወደ ቁም ነገሩ ላምራ። መንደርደርያ ይሆነኝ ዘንድ ከዚህ በታች አንዳንድ ጥያቄዎችን አስፍሬ መልስ በመስጠት ለመጀምር ሙከራ ላድርግ።
……....* እኛ በምንኖርበት የባዕድ ሀገር ህዝብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ምግብ፣ አየር... ተላምደንና ተውህደን መኖር እንችላለን ወይ?
……....* በማህበራዊ ሁኔታዎችስ ምን ላይ እንገኛለን?
……....* ምን ይጎለናል?
……....* በቁጥርስ ምን ያህል እንደርሳለን?
……....እንዚህን ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ መመለስ ባልችል እንኳን እዚህ ያለነው በሙሉ ጠያቂና ዘመድ የሌለን ባዕድ ሀገር ውስጥ ብቻችንን የምንኖር፣ ወዳጃችን ሥራችን ብቻ መሆኑን እናውቀዋለን። በጣሊያን ቁጥራችን ከ20 ሺህ በላይ እንሆናለን ተብሎ ይገመታል። ሚላኖና ሮማ በቁጥር ብዙ ናቸው። በነዚህ ትላልቅ ሀገር በብዛት የሚኖሩበትን ቦታ "አበሻ ሰፈር" ተብለው የሚጠሩ ቦታዎችም አሉ። እኔ ባለሁበት ክፍለ ሀገር ምን ያህል እንዳሉ ሲነገርም ስላልሰማሁ ወይም ተጽፎ ስላላነበብኩ በግምትም እንኳን ይሄን ያህል እንደርሳለን ለማለት አስቸጋሪ ይሆንብኛል። ነገር ግን ቁጥራችን በጣም እየጨመረ መምጣቱን በሚገባ አውቃለሁ። በምኖርበት ከተማ እንኳን ከዛሬ አስር ዓመት ወዲህ በቁጥር እጥፍ ድርብ ጨምረናል የሚል ግምት አለኝ። ... ይቀጥላል ...
……....ታዲያ ለብዙዎቻችን መገናኛ የሚፈጥሩልን ዓመታዊ ክብረበዓላችንን ወይንም አውደዓመት ላይ የሀገር ምግብ ሰርተን፣ ቡናውን አፍልተን፣ ቄጤማና ሳር ባይገኝም ምንጣፉንም ቢሆን በመሬት ላይ አንጥፈን እንሰባብሰባለን። ሌሎች መገናኛ ሁኔታዎችን ከሚፈጥሩልን መካከል ለምሳሌ - በሰርግና በልደት፣ በችግርና በሀዘን ወዘተ ... ናቸው። በየቤታችንም በመገባበዝ እንገናኛለን። ኦሪጂናል የሀገራችንን ምግቦች እዚህ ለማግኘት ባንችልም እንኳን አእምሮታችንን ለመወጣት የፉርኖ ዱቄት እንጀራ በመጥበሻ ላይ ጋግረን ከዘመዶቻችን በሚላክልን የተፈጨ በርበሬና ቅቤ ወጥ አዘጋጅተን ባልንጀሮቻችንን ጠርተን አብረን እንውላለለን። ዳቦ በወጥ መልመድም ግድ ሆኗል። ዝነኛውንም የሽሮ ዶኬንም የማይወደው የለም። በተቃራኒው ደግሞ ከማንም ጋር ግኑኝነት የማያደርጉ በርካታ የሆኑ የተገለሉ፣ ያልታወቁ፣ የኑሮውንም ውጣና ውረድ መቋቋም ያቃታቸው፣ የብቸኝነት ስሜት ያላቸው፣ የህሊና ዕረፍት የማያደርጉ፣ ለራሳቸው የሚሆን መዝናኛ ነገሮችን እንኳን የማያደርጉ የሀገር ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ። በመንፈስ ጭንቀት ወይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት ብቻ ሊሠሩ ባለመቻላቸው ወደሀገር ቤት የሚመለሱም አይጠፉም። ለዚህም እንኳን የሥነ አዕምሮና የሥነ ልቦና ምክር ሊሰጥበት የሚችልበትን ማዕከል ለማግኘት የሚጠየቅበትን ሳያውቁ፣ የሚፈለገውን አገልግሎትና ህክምና ሳያገኙ ወደ ቤተሰባቸው የሚመለሱና የሚላኩ ጥቂቶች አይደሉም።
.
……....ታዲያ በጣም በተቀራረቡት ወይም በደንብ ከሚግባቧቸው ጓደኛሞች መሀከል ልዩ ፍቅርና ትሥሥርም አለ። ከትውልድ ሀገራችን ስለራቅን ነው መሰለኝ። አንዳንድ ግዜም ማኅበሮች ወይም ኮሙኒቲዎች በዓላት ላይ በሚያዘጋጃቸው ፌስታዎች አማካይነትም ተያይተን የማናውቃቸውንና እሩቅ ሀገር ያሉትን እንድንተዋወቅና እንድቀራረብ አድርጎናል። እናም በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች በሥራችን ላይ ያጋጠሙንን ችግሮች እያነሳን እንጨዋወታለን። ስለሀገር ናፍቆትና ትዝታ እናወራለን። እዚህ ሀገር ስለ እኛ በሚያስደንቁንና እንግዳ በሆንብን ነገሮች ዙሪያም እናወጋለን። እኛ የፈረንጆቹን አንዳንድ ልማድ በምናይበት ጊዜ እንደምንገረመው እነሱም ስለ እኛ ባህል እንግዳ በመሆናቸው ብተመጽዖ ሲያወጉበት አይተናል።
ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ1995 ዓም ሀገሬ ደርሼ ስመለስ የዘመዴን ሠርግ ከቀለበት እስከ ቅልቅል ያለበትን የቪዲካሴት ፊልም ለፈርንጆች ጓደኞቼ አሳይቼ ነበር። የምግቡና የሰው ብዛት፣ የሙሽራዋ ቬሎና የሚዜዎች ልብስ፣ ከዚያም በላይ ከተማዋንና ፎቁን ሲያዩ ሊያምኑ አልቻሉም። በተለይ የምግቡና የሰው ብዛት ስላስደነቃቸው "ሀብታም ናችሁ ወይ?" ብለው ጠይቅውኝ ነበር። "በሀገራችን ሀብታምም ሆነ ድሀ ልጁን ሲድር እንደዚህ ደግሶ ነው" ብዬ ነገርኳቸው። ጥሎሽ፣ መልስ፣ ቅልቅል እየተባለ ሲጨፈር፣ ሲበላና ሲጠጣ ሲያዩ ድሀ ብለው የደመደሙላት ሀገራችን ሳትደንቃቸው አለቀረችም። ጥሬ ስጋም እየተጎረደ ሲበላም አይተው በጥም ተደንቀዋል። እግረ መንገዳቸውን የእነርሱን ሁለት ሰዓት የማይፈጅ የሰርግ ዝግጅት እና ያለጥሎሽ እንዲያገቡ የሚያደርገውን ባህላቸውን ረግመውታል። ይህንንን ማለቴ ሀገራችን የተትረፈረፈባት ነች ብዬ ጉራ ለመንዛት አልነበረም። እንደው የእነሱ አመለካከት የተለየ በመሆኑ እንዲያስተውሉ ለማሳወቅ ነበር። እዚህ ላይ ሀገሪቱ የምትገኝበትን ችግር፣ ድህነት፣ የረሃብና የድርቅ ሁኔታዎችን በየጊዜው የሚስሙትን ከነበራቸው ሃሳብ ጋር ቅራኔዎችን አፍልቆባቸው ስለነበር በመሀሉ ብዙ ነገር ተጨዋውተናል።
……....ለማንኛውም እኔ ከተገነዘብኩት ነገር ጣሊያኖች ብዙ ነገሮችን አቅልለው የመመልከት ልምድ አላቸው። እኛም ብንሆን ከእነሱ በአንዳንድ ነገሮች ላይ መልካሙን ባህላቸውን ለይቶ መውስዱ ሊበጀን ይችላል ለማለት ነው። ... ይቀጥላል ...
……....አንዳንድ ጊዜ ፈረንጆቹ "ዘርህ ምንድነው? ከየት መጣህ? አሳማ ትበላለህ ወይ? ወዘተ ..." እያሉ ይጠይቁኛል። በዚህ አጋጣሚ ልቤ በኢትዮጲያዊነት ስሜት የተሞላ በመሆኑ ከመልሴ ጋር አያይዤ ሌላም ብዙ ነገር እንዲያውቁ ብዬ ጨማምሬ ሳወራላቸው በተመጽዖና በመገረም ያዳምጡኛል። ለምሳሌ - 13 ወር እንዳለን፣ ከ200 በላይ ፊደል እንዳለን፣ ያለንበት ዓመተምህረት በ7 ዓመት ወደኋላ እንደምንገኝ፣ ከ80 በላይ ቋንቋዎች እንዳሉን፣ ...ወዘተ ... ሌሎችንም እንደዚሁ ሳወራላቸው በቃ ግርም ነው የሚላቸው። ማንኛውንም ነገር ስለሀገራችን ለማወቅ አስተውለው ሲያዳምጡኝ፣ ሲጠይቁኝ፣ ከልብ አድናቆትን ሲያደርጉ በጣም ደስ ስለሚሉኝ አከብራቸዋለሁ።
በተቃራኒው ደግሞ የአንዱ ሀገር ባህል ልምድና ኑሮ ሊለያይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ የማይችለውና ያልተማረው ክፍል ተነስቶ ማንነቴን ሳያውቅ እኔን የመናቅና የማይሆን ድርጊት ከፈጽመብኝ በመናደድ ሳይሆን በራሱ አይን እያየሁት ትክክለኛውን መልስ እሰጠዋለሁ። ልሳሳት እችላለሁ ግን ጥቂቶችና ባልተማሩት ነጮች አካባቢ በእኛ ላይ የመሰልቸትና የእምነት ማጣት ሁኔታዎች ያሳያሉ።
……....እናም እኔን ከገጠሙኝ ነገሮች አንዷን ላጫውታችሁ እስቲ!!
……....እኔና የሥራ ጓደኞቼ ወደ ከተማ ወጣ ብለን ለመዝናናት ፈልገን አንድ ቡና ቤት ገባን። ታዲያ ወዲያው እንደገባን አንዷ ጣሊያናዊት እኔን ለይታ በትህትና ሳይሆን በንቀት እኔን sei di colore? ብላ ጠየቀችኝ። እኔም ቋንቋቸው እየተለመደ የመጣ ቃል በመሆኑ ብዙም ደንታ ስለሌለኝ የኔ ምላሽ "አዎ" ነበር። Di Colore ትርጉሙ "ቀለም ያለው ወይም የቀለመ" ማለት ነው።ግን ጥያቄዋ የንቀት በመሆኑ ስለከነከነኝ ብቻ ቀጥል በማድረግ Se sono di colore tu devi essere senza colore አልኳት። መቼም አብረውኝ የነበሩት ምን ማለቱ ብለው ሳይደነቁ አይቀርም። ብቻ ጣሊያናዊቷ ፊቷ ከመቅጽፈት ፍም ሲመስል አስተዋልኩ። አንድ ጊዜ በጥፊ ወለወለችኝ። እኔም ዞረብኝ እላችኋለው። እሷም ተመልሳ ደንግጣ እጇን አፏ ላይ ጭና ታየኝ ጀመር። ከዚያም የቡና ቤቷ ባለቤት ታውቀኝ ስለነበር አረጋጋችኝ። ለነገሩ እኔን ብትመታኝም አሷን ለመምታት እቅድም አልነበረኝም። ሊያውም ሴት በመሆኗ እንዴት ብዬ። መቼም እናንተም ለምን ዝም አልካት አትሉኝም። በማይረባ ነገር ምን ዱላ አስመዘዘኝ። ብቻ ያስደሰተኝ የሷ ፈዞ መቅረት ነው። Senza colore ተብላ የምታውቅ አይመስላኝም።
እስቲ እናንተው እራሳችሁ አስቡት። እኛ ከቀለምን የቀለማችን አይነት ምንድነው። ማንኛውም ቀለም ካለው ጋር ቆዳችንን ብናስተያየው አንድ አይነት አይደለም። Di Colore ከማለት ሌላ አይነት ቃል ቢፈልጉለት ይሻላል። ታዲያ እናንተንም Di Colore ቢሏችሁ እንደኔ አይነት መልስ አታድርጉ። ያው ቋንቋቸውና ልምዳቸው ሆኗልና። እኔም ቢሆን እኮ በንቀት ሳይሆን በትህትና ብትለኝ ይህ ሁሉ ችግር አይፈጠርም ነበር። በበኩሌ ጥቁርና ነጭ ይምንባባለውን እመርጣለሁ። ... ይቀጥላል ...
.
... ከዋናው አርዕስት እየወጣሁ ስለመጣሁ ወደመነሻዬ ልመለስ። ይህንን ጉዳይ በሌላ ጊዜ እንደምናነሳው አልጠራጠርም።
... ሰው ደካማ ጎን አለው። ከኛም መካከል የአብሮነት ጥቅም ስታስረዳው የማይገባውና የመረዳት ችሎታ የሌለው አይጠፋም። ይህንን ደካማ ጎኑን አይተን እንተወው ማለት አንችልም። ከዚህ የውጪ ሀገር ቅዠት ኑሮ ሌላ የአለው መጥፎ ፀባይና ልምድ ተደርቦበት አሻፈረኝ ቢል ብዙም አንፍረድበት። እዚህ አስካለ ድረስና ወገናችን እስከሆነ ድረስ የመኖር ትርጉም ጣዕም እንደአጣ ሆኖ መቅረት የለበትም። የሰው ሀገር ሰው ነውና መቼም ቢሆን እንደማይደላው ቢታወቅም አንዳንዴ በያዘው ባሕሪ የሚፈጽማቸውን ድርጊቶች ስናይና ስንሰማ አኛኑ ሊቆረቁረን ይችላልና ነው።
……....በተለይም ከሌሎች የውጪ ዜጎች መሀከል በጣም ጥቂት የሆኑት በሚፈጽሙት መጥፎ ድርጊቶች ምክንያት ፈረንጆቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጪው ዜጋ ላይ ያላቸው አመለካከት መጥፎ መልክ እየያዘ መምጣቱን ሳትገነዘቡ አልቀራችሁም። ሥነስርዓት የሌላቸው የተወሰኑ የውጪ ዜጎች ቅሚያና ድብድብ ላይ ስለሚገኙ እኛም ተደምረን ከሕብረተሰቡ እያራቀን ይገኛል። ለምሳሌ የዛሬ 10 ዓመት ፈረንጆቹ ሌባ ይሰርቀኛል ብለው አይፈሩም ነበር። ዘወትር በሚያዩት፣ በሚሰሙት፣ በሚደርስባቸውና በሚያጋጥማቸው ህገወጥ ድርጊቶች አማካይነት እኛንም በነሱ አይን እንድንታይ አድርጎናል። አንዳዶቻችንም አጋጣሚ ሆኖ አንዱ የውጪ ዜጋ መጥፎ ድርጊት በፈጸመበት አካባቢ በመገኘታችን ብቻ እንኳን አፍረት እንዲሰማን ሆነናል። ቢሆንም ሕገወጥና ማህበረሰቡ ከሚያገልለው ሁነታዎችን እስካልፈጽምን ድረስ፣ ስርዓትን አክብረን እስከኖርን፣ ከመጥፎ ልምዶች እስከራቅን ድረስ ምንግዜም ተከብረን እንደምንኖር ጥርጥር የለኝም።
በእርግጥም እኛ ኢትዮጲያዊያን ሕግንም ሰውንም በጣም እናከብራለን። የሀገሬ ልጅ ቁጡ፣ ብርቱና አትንኩኝ ባይ ነው። ሲነኩት እንደ አራስ ነብር ስለሚሆን በቀላሉ ከሰው ጋር ሊቀያየምና ሊጣላ ይችላል። ለእነዚህ አጋጣሚዎች በቅንና በጥሩ ልቦና መቅረብ ካልቻለ በኋላ መዘዞች እንዳይከተሉት በትዕግስት ማለፉ ይሻለው ይመስለኛል። ... ይቀጥላል ...
……....ክጣሊያን ወጣ ካልን ደግሞ በሌሎች የአውሮፓ ሀገር የሚኖሩት ኢትዮጲያዊያን ዜጎች በቁጥር ምን ያህል እንሆናለን። እንግሊዝ ወደ 50 ሺ፣ ጀርመን 35 ሺ፣ ስዊድን 40 ሺ፣ ወዘተ ይሆናሉ ይባላል። ሆላንድ ወይም ካናዳ ያሉት ቁጥራቸው ጣሊያን ካሉት በቁጥር የበለጡ መሆናቸውም ይነገራል። በነዚህም ሀገሮች ጠቀም ያለ ገንዘብ በሚያስግኙ አገልግሎት መስጫና የሥራ ዘርፎች ላይ ዕውቀታቸውን የሚያውሉ ብዙ ናቸው። እዚህ ጣሊያን ሀገር ግን የተማሩበትን ዕውቀት ወይም የሥራ ልምዳቸውን ተመርኩዘው ተቀጥረው የሚሠሩ ቢኖሩ ከአንድ መቶ ኢትዮጲያውያን/ት ውስጥ አንድ ቢገኝ ነው። ሁላችንም የምንኖረው በፊት ልምድ በሌሉን ሥራ ላይ ነው። የጉልበት ሥራ፣ የቤት ውስጥ አገልግሎት፣ የንጽህና፣ የህመምተኛና የሽማግሌ ጥበቃ ወዘተ ... በመሥራት ነው። በአጠቃላይ እዚህ ጣሊያን ሀገር አንድ የውጪ ህገር ዜጋ በሙያው አይደለም ሥራ የሚገባው። ተምሬአለሁና ይህንን እችላለሁ ብሎ ተወዳድሮ መግባት አይችልም። ብዙ መንከራተት አለ። ካላወቅንበት መሻሻል ቀርቶ ያለንም የሥራ ልምድም የሚያሽቆለቁልበት ሀገር ነው። ይሄ ሁሉ ሞራላችንን ነክቶታል።
አሁን አሁን ግን ነፃነት በማይሰጥበት ሰው ቤት ተወስኖ ላለመቅረትና እንደልብ ለመሆን የግል ንግድ የሚያደርጉ፣ ትንሽም ገንዘብ አጠራቅመው ምግብ ቤት፣ ፀጉር ቤት የከፈቱ፣ በአላቸው ችሎታም ሆነ ሙያ በግል በመሥራት በማደግ ላይ ያሉ ወገኖችን ማየት አሰይ" ያሰኛል። ... ይቀጥላል ...
……....በጣሊያን ስላለው ቆም ላድርግና በሌሎች ሀገር ኢትዮጲያውያን/ት የሚመለከት ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ልመለስ። አልሰማችሁ እንደሆን በኢትዮጲያዊያን መካከል በዓለም ደረጃ እርስበርሳችን መተባበርና መተሳሰብ ያለባቸው ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ እንቅስቃሴዎች ትጀምሯል ይባላል። ለምሳሌ - በአውሮፕ ደረጃ በአለፉት ዓመታት ስድስት የአውሮፓ ሀገሮች ውስጥ ያሉት ኢትዮጲያዊያን ተገናኝተው የስፖርት ውድድር አድርገዋል። የብዙ ሀገር ማዕከል በሆነችው በሆላንድ (አምስተርዳም) ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ግን ጣሊያን ያሉት ኢትዮጲያዊያን አልተሳተፉበትም። ቢሆንም እንደዚህ የመሳሰሉት አንዳንድ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው ይባላል።
……....በዓለም ደረጃ ደግሞ በኅብረት ከአደረጉትና ካስፈጸሙት ሌላው ምሳሌ ሊሆን የሚችለው - ባህሬን (አረብ ሀገር) ያለችው የሺወርቅ ስው ገደለች መባሉ ሲሰማ ኢትዮጲያዊያን ድምፃቸውን አሰምተው ከሞት ቅጣት እንድትድን ተደረገች። አንዲት ኢትዮጲያዊ ሴት ሥራ ቀጣሪዋንና አሰሪዋን ሀብታም አረብ የሆነውን ግድያ ፈጸመች መባሉ እኔንም በጣም አስገርሞኛል። ይህችው እህታችን በኢትዮጲያ ዜግነቷ ሊያውም በሰው ሀገር የሞት ፍርድ ሲፈርድባት ሁላችንንም ውጪ ይለነውን ልባችንን ነክቶት ነበር። በሴትነቷ ላይ ብዙ በደል ተፈጽሞባትም ይባል ነበር። በተለይ በዋሺንግተን የነበረው የአበሻ ማኒፌስቶ ታይቶም አይታወቅም ነበር ይባላል። ባህሬን የነበረውም የኢትዮጲያ ኤምባሲ ይደረገው ጥረት የሚደነቅ ነበር ይባላል፡፡ ... ይቀጥላል ...
……....ሌላው ደግሞ በአውሮፓና በአሜሪካ መካከል በሚገኙ ኢትዮጲያዊያን በኢንተርኔት መገነኛ ተፈጥሮ አበሾች ብዙ ግልጋሎትን የሚሰጥ ሥራዎች እየሰሩ ነው ያሉት ይባላል። በአሜሪካ ትላልቅ ክተማዎችም ውስጥ ቅን አስተሳሰብ ባላቸው ኢትዮጲያውያን አንዳንድ ማዕከል መስርተው ለበርካታ ኢትዮጲያዊያን የነፃ ትምህርትን የሚያገኙበትን፣ በኢትዮጲያዊያን የሕግ ጠበቃዎች፣ በኢትዮጲያዊያን የኢንሽራንስ ኩባኒያ፣ በህመምም ሆነ በድንገት ኢትዮጲያዊ/ት በሞት ቢለይ ውዲያው በትንሽ ክፍያ በጊዜውና በቶሎ አስከሬኑ ተለቅሶለትና በክብር ሀገር ቤት የሚላክበትን መንገድ ሁሉ ፈጥረዋል። ልዩ የህክምና ግልጋሎት በቀለለ ወጪ እንዲያገኙና ሌላም አሁን ላስታውስ ያልቻልኩት ብዙ ችግሮቻቸውን የሚያቃልል ሁኔታዎችን አድርገዋል። ይህ እንግዴ በማህበራዊው ኑሮአቸው እድገት ሲያድርጉ ይታያል።
……....እናም በጣሊያን ሀገር የምንኖረው ኢትዮጲያዊያን በማናቸውም የዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆናችንን እንኳን መገንዘብ አቅቶናልና ህሊናችንን የማረጋጊያ መሠረት ለመጣል መሞከር ይገባናል። ... ይቀጥላል ... ...
……....እዚህም ፕሮጀክት ላላቸው ማኅበሮች ብዙ አይነት ድጋፍና እርዳታ እንደሚያገኙ ታውቃላችሁ? የገንዘብ፣ የማቴሪያልና የሰው ሀይል ለintegrazione በየ regione ይመድባሉ። ብዙ የውጪ ሀገር ክሚኒቲዎች ይህንን አጋጣሚ እንደሚጠቀሙበት ሰምቻለሁ። እኛም በሥራ ክፍፍል አድርገን አንዱ ላይ ብቻ የሥራ ሸክም እንዳይበዛበት ተራ በተራ በመተጋገዝ ቀጥ ብለን ብንሠራ ማድረግ እንችላለን። ዘፋኞችና ተወዛዋዦች ብቻ ጠርቶ ምሽት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ፕሮጀክትና ፕሮግራሞችን በማዘግጀት የምፈጸሙ ሥራዎች አሉበት። የረቀቀ እቅድ እንድኖር ያስፈልጋል። እቅዱ ችግራችንን የሚቀርፍ፣ መንፈሳችንን የሚያፈካ፣ የስደተኛውን ስሜትና ፍላጎት ተንተርሶ የሚጓዝ መሆን አለበት። ከአለንበት አንድ እርምጃ ፈቀቅ የምንለው የስደተኛው ህልም ተከትሎ ሊሄድ የሚችል ማህበራዊ ፕሮግራም ሲኖረን ነው። እቅድ ወይም የፕሮጀክት ፕሮግራም ለማህበሮች ህልውና ተስፋና የማበብ ምልክት ነው። የማህበሮችን የአባላት በጎ ፈቃድና ተስትፎን ይጠይቃል። አቅጣጫውም እንዲያምር በህብረት መተጋገዝን ይጠይቃል። ... ይቀጥላል ...
……....ይህ አርዕስት ወደፊት ይቀጥላል።
*** *** *** *** ** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** *** ***
……....የዚህ ፅሁፍ ይዘት ምናልባት ብዙወቻችንን በቀጥታ ሊነካ ይችላል። አቤቱታ፣ ወቀሳና ትምህርት አለበት። ከልምድ አኳያ በብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚታዩና የሚነገሩ ናቸው። ችግሮች የታወቁ እና ብዙዎቻችንን ይወክላሉ። እውን እንጂ ፈጠራ አይደለም። ለማህበራዊ ህይወታችን ብቻ ሳይሆን ለግል ህይወታችንም እንዲጠቅም ታስቦበታል።
……....* ልማዶቻችንንና ባህሪዎቻችንን በይፋ በማወጣት የሚበጁንን መፍትሄወችን ለማግኘት፣
……....* የልብ ውህደትና የአዕምሮ አንድነት እንዲኖረን ለማድርግ፣
……....* አዕምሯችንን ለተገቢው ነገር እንድንጠቀምበት መንገድ ለማሳየት፣
……....* ከልዩነታችን ይልቅ ለአንድነትና ለደህንነታችን እንዲናተኩር ለማበረታታት፣
……....* ሃላፊነት ለሌላው ከሰጠን በኋላ ከመተባበር ወደኋላ ላለማለት፣
……....* ሃላፊነትን ክመውሰድ ላለመሸሽ፣
……....* የማሕበር ሕብረት ሥራ ወይም ትብብር ላይ ሳንገኝ ... ... ...
... ይቀጥላል ...
……....አንድ ጊዜ ሀገር ቤት ሄጄ ስመለስ ዘመድቼ ያሉኝን ምን እንደሆን ታውቃላችሁ።
"ኢትዮጲያውያን/ት በውጪው ዓለም ፍቅራችሁ ልዩ ነው ይባላል። እውነት ነው ወይ?" ብለው ሲጠይቁኝ
"አይደለም ሁሉም የተገላቢጦሽ ነው" ብያቸዋለሁ። ምክንያቱም እንደኔ ከሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ያሉት ሊታባበሩና ሊፋቀሩ ይችሉ ይሆናል እንጂ በጣሊያን እንደዚህ አለመሆኑን አውቀዋለሁ። "እንደውም ለምን እንደሆነ የማይገባኝ ነገር በአንዳንድ አጋጣሚ ማንንም በማናውቅበት ለላ የጣሊያን ከተሞች ሄደን በመንገድ ላይ ስንገናኝ አንገት ደፍተን ሰላምታን እንኳን ሳንለዋወጥ የምንተላለፍበትም ጊዜ አለ" ብዬ ለዘመዶቼ ነግሬአቸዋለሁ። የሚያስተሳስረን ነገር እንደሌለ አድርገን መተላለፉን እራሴን ስጠይቅ መልስም አላገኘሁለትም። ግን ለምን?
……....* ትኩረትን ውደ ሥራ ብቻ አድርገን ነው?
……....* ኑሮ ስለከበደን ነው?
……....* ስደተኛነታችን እንዳይታወቅብን ነው?
……....* የውጪ ሀገር ዜጎች በመብዛታቸው ያለመተማመን ተፈጠረ?
……....* የቤተሰብ ናፍቆት መብዛት ፀባያችንን እንዲለወጥ አደረገው?
……....* በአለመገናኘታችን ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታችን ተቀነሰ?
……....* የፈረንጁ ባህል የኛን እየቀየረብን ነው?
……....* አለመረጋጋት፣አለመተማመን፣ መናናቅ፣ ቅራኔዎች፣ ወሬ፣ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ መኮራረፍ፣ ሀሜት፣ በአጠቃላይ በምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። ብችግርም ሆነ በደስታ ሊደራረሱ የሚገባቸው የአንድ እናት ሀገር ልጆች ይህ እንኳን ሲሳናቸው ማየት ጥሩ ስሜት አይሰጥም።
……....ሌላው ደግሞ ሮማ ውስጥ ከገጠሜዎቹ አንዱ "ተጠንቀቅ አበሻ ዝም ተብሎ በመንገድ ሰላም አይባልም" ያለኝም አጋጥሞኛል። ይሄን ማለቱ ስለገረመኝ እኔም ቀጠል በማድረግ "እኔና አንተ አብረን ከመሆናችን በፊት ተያይተንም አናውቅም እኮ! በሰላምታ ብቻ አይደለም እንዴ የተቀራረብነው? እና ለምንድነው አበሻን ሰላም የማይባለው?" ለሚለው ጥያቄዬ መልሱንም አላገኘለትም። ለወትሮው እኛ ኢትዮጲያውያን/ት የምንታወቅበት በላምታችን ነበር። ክመተላለፍ አልፎማነህ? ከዬት መጣህ? እንዴት ነህ? መባባሉ እየተቀረ ነው መሰለኝ። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የጣሊያንን ምድር ስረግጥ በእርግጥ ቁጥራችን በጣም ጥቂት ነበር። የዛሬ ሃያ ዓመት ከማላውቀው ወገኔ ጋር መንገድ ላይ የተያየን እንደሆነ በርቀትም ሆነ በቅርበት ሰላምታ ስንለዋወጥ ለብዙ ዓመት አብረን አፈር ፈጭተን ያደግን እንመስል ነበር። ተቀራርበን ተጫውተን የስልክ ቁጥር መለዋወጡ ከተለያየን በኋላም መደዋወሉና የልባችንን አውግተን ቀጥዩን መገናኛ ቀጠሮ መውሰዱስ። የዛሬ 20 ዓመት ማታ ማታ ስንገናኝ አዲስ አበባ ሊያውም ቄራ ወይም መሀል አራዳ ያለን ይመስል ነበር። በዚያን ጊዜ እርስ በርሳቸው የሚደባደቡ የውጪ ዜጎችን ስናይ እንገረም ነበር። እነሱም የኛን መከባበርና ሥነስራዓት ሲያዩ መንፈሳዊ ቅናት ያድርባቸው ነበር። በአጠቃላይ እንደዛሬው ሳይሆን እኛ አካባቢ ሰላም ነበር። ... ይቀጥላል ...
……....ዛሬ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ የሌሎች የውጪ ሀገር ዜጎች በተለይም አፍሪካዊያን የሀገሩን ልጅ ቀርቶ ማንኛውንም የአፍሪካ ተወላጅ በመንገድ ሲያዩ ሰላምታን ይሰጣሉ። እነዚህም ዜጎች ሁኔታዎችን ፈጥረው ከመገናኘት ሲቦዝኑ አይቼ አላውቅም።
…….... እነሱ በእናንተ ክሙኒቲ ውስጥ ምን እየሠራችሁ ነው? ሕብረት አላችሁ ወይ? ብለው ሲጠይቁኝ መልስ ለመስጠት ሁሉ ተስኖኛል። ልምንድነው በተግባርና በሕብረታቸው ሊበልጡን ይቻሉት? እኛ እንደነሱ መተባበር ያቃተን ምክንያቱ ምንድነው?
……....ታዲያ እኔም ልሳሳት እችላለሁ ግን የውጪው ፍቅራችን የውሸት ነው። እንደውም እዚህ የመተከዝ ባህሪ ይታይብናል። ብንስቅም የውሸት ነው። (እውነተኛ ሳቅ ያለው በሀገር ነው) በመካከላችን መተማመን ያለ አይመስለኝም። ብዙዎቻችን መጠያየቅና መተዛዘንን እየረሳነው መጥተናል። አንዳንዶቻችንም ተኮራርፈንና ተደፋፍጠን ያለን እንመስላለን። ፍቅር ብዙም የለንም። ብትተክዝ ምን ሆንክ? ብታዝን ምነው? የሚለው ባህላችን እየተዳከመና እየቀረ መጥቷል። "በማር በወተት ያሳደግሽኝ እምዬ ኢትዮጲያ" እያልን ማንጎራግር፣ ስለሀገርና ስለቤተሰብ ናፍቆት ማውራትና እዚህ ስላለንበት ችግር ማሰቡን ብቻ ተያይዘነዋል። ሆዳችንም መባብቱንና ማልቀሱን ተያይዞታል። ችግራችንን ከልብ የሚያዳምጠን፣ የሚያጽናናን፣ የሚያጫውተን እውነተኛ ጓደኛ ስለማናገኝና በፊት ቀርበውን የነበሩት ሁሉ በወሬና በቅራኔ ስለራቁን በቃ ተለያይተን እንኖራለን። እርስ በርስችንም በወሬ ወገን እየፈጠርን በሌላው ላይ የመፍረድ ባህል እየተማርን ነው። "እንዲህ ሆነዋል፣ እንዲህ ያደርጋሉ" ሲባልና ሲሰማ ሰውን ከሰው ጋር ከማቀያየም ሌላ ምንም ነገር እንደማይጠቅም ማወቅ ያስፈልጋል። መቃቃርን በመፍጠር መለያየትን የምንወድ ከሆነ፣ መጠረቅ ባህላችን እየሆነ ከመጣ፣ የማይሆን ወሬ ማውራት ሱስ እየሆነብን ከመጣ በዚሁ መራራቃችን እንቀጥላለን ማለት ነው። አንገታቸውን ደፍተው ቤተሰብን ለመርዳትም ሆነ ራሳቸውን ለመቻል እየሠሩ ያሉትን ወገኖች መደባለቁም ጥሩ አይሆንም። "አይዟችሁ በርቱ፣ ቀን ያልፋል" ማለት እንጂ! "ከምን ጋር የዋለ ምንትስ" እያሉ ጨዋውን መርገምና መዝለፍ አይገባም። አንዱም በሌላው የቂም ጣት በመቀሰር የሚገኝ ጠቀሜታ እንደሌለ ማወቅ አለብን። ... ይቀጥላል ...
.
……....አስተውላችሁ ከሆነ ወይንም ገጥሞችሁ ከሆነ ነጮች ከፊታችሁ ጥሩ ፈገግታ ያሳዩና ዞር እንደተባለ ፊታቸውን ቅጭም ያደርጉታል። አሁንማ ይህንን ልማድ የኛዎች ጉደኞችም እየለመዱ ነው:: የሆነ ወቅት የኢትዮጵያን ሬስቶራንት ውስጥ ከጎኔ የተቀመጡት ወጣቶች እይተሳሳቁ ራት ከበሉ በሁዋላ ከመካከላቸው አንደኛው ከፍዬ ልሂድ ብሎ ይነሳል። የተቀሩት ሁለት ወጣቶች በጭራሽ እኛ ከሞትን በሀላ አይነት ግርግር ሲያነሱ ልጁ በሉ እንግዲህ በሰላም እደሩ grazie ብላቸው ተሰናብቶ ይወጣል:: የልጁ እግር ከሬስቶራንቱ እንደወጣ ልጁን ያላሉት ነገር አልነበረም:: ይሄ ሆዳም ዝም ብሎ በልቶ ይወጣል እንዴ? ክፈል ብንለው እኮ ያለቅስ ነበር እያሉ ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ:: ይህ ልጅ ማድረግ ሲፈልግ አታድርግ ብለውት በሁዋላ ላይ መነጫነጭ አኛን አይጠቅምም ነው:: ከንዲህ አይነት ጎደኛ ይሰውራችሁ!! አሜን... ይቀጥላል ...


ሐበሾች ሰላም አንባባልም


አብራሃም ዘውዴ


……....ይህንን ርእስ ሐበሾች ወደሚገኙበት መድረክ ማምጣቱ አስፈላጊ ሆኖ ስለታየኝ እዚሁ ገጽ ላይ አምጥቼዋለው:: ከዚህ በታች እንደምታዩት በዚህ አርዕስት ላይ የተለያዩ ግለሰቦች አስተያየቶቻቸውን አስፍረዋል። የአንዱ አስተያየት ከሌላው ምን ያህል የተለየ መሆኑንም እንድንገነዘብ ያደርገናል። እስቲ እርስዎም በሰላምታ ጉዳይ የደረሰባችሁ ገጠመኝ ከአልዎት እዚሁ ይተንፍሱ:: ብዙዎቹ ለምን መንገድ ላይ ሰላም ሳይባባሉ ይተላለፋሉ? አርዕስቱን ሳትለቁ ያላችሁን አስተሳሰብ ወይም ሀሳባችሁን ስጡ:: መፍትሄ ካላችሁም አንድ በሉ። .
……....እኔ ያለሁበት ሀገር እንደታዘብኩት ሐበሻ በውስጡ የዘር ክፍፍል ጥርጣሬ ዋነኛው በሽታው ነው:: አንዳንዱ በየዋህነት ተንደርድሮ ሰላም ሲል ሌላው ደግሞ በአጸፋው የግልምጫ መልስ ስለሚያገኝ ሁለተኛ አይለመደኝም አፌ ይቆረጥ ይልና ሌላ ቀን ሀበሻ ሲያይ ይሸሻል:: ይህ እንግዴ እኔ ላይ የደረሰብኝ ቢሆንም እንኳን የፈለገው ይሁን እኔ በእድሜ ገፋ ያሉ ሐበሾች ወይም ግራ የተጋቡ የሚመስሉ ሀበሻም ይሁኑ ሌሎች አፍሪካዊያን የሚመስሉትን ሰዎች ሳይ አላልፍም:: ቆም ብዬ ተመልሼ በትህትና “ልርዳዎት ወዴት ነው የሚሄዱት?” እያልኩ መጠየቅ፤ በመንገድ ላይም እንኳን ባገኛቸው የመኪና ሊፍት መስጠት ልማዴ ነውና:: ታዲያ አንድ ቀን እንደ ልማዴ በአንዱ ባስ ፌርማታ ላይ በእድሜያቸው በግምት 50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ባልቴት የሀበሻ ነጠላና ጥበብ ቀሚስ አርገው ግራ የገባቸው መስለው ስላየሁኝ እንደ ልማዴ መኪናዬን አስጠግቼ ቆምኩና "እማዬ ሀበሻ ነዎት አይደል ላድርስዎት ወይ? የተቸግሩት ነገር አለ?" ብዬ ስጠይቃቸው ሰትዬዋ አይናቸው ድንገት ተለዋወጠና በተሰባበረ ጣሊያንኛ "ምንድ ነው የምታወራው" እያሉኝ በግልምጫ ጢሜን አበረሩት:: በጣም ግራ ተጋባሁኝ በአቅራቢያው የነበሩ ሌሎች ታዛቢዎች ተገርመው ሲያዩኝ ስለነበር ፖሊስ እንዳይጠሩብኝ ብዬ ተከናንቤ ወደ ቤቴ አመራሁኝ እላችኋለሁ:: ሌላ ቀን ደግሞ ለሥራ ጉዳይ ሌላ ከተማ ሄድኩኝና አንዷን ሀበሻ የሀበሻ ሬስቶራንት እንድትመራኝ ብጠይቃት አማርኛ እንደማይገባት ከግልምጫ ጋር ሬስቶራንቱ ያለበትን አላውቅም እንደማለት አይነት መልስ ሰጠችኝና አሁንም እያዘንኩና በአዕምሮዬ ብዙ ነገር እየተመላለሰ ሄድኩኝና ሌሎች ሰዎች የሚገኝበትን ቦታ አስረዱኝና ሄድኩ። ይሄኛው ገጠመኜ ደግሞ ለጉብኝት ካለሁበት ከተማ ወደ ሮማ የሄድኩ ቀን ላይ ነበር:: መቼስ በተወሰኑ የሮማ ሬስቶራንት ውስጥ በተለይ ረፋድ ማታ ላይ የሀበሻ ብዛት ታውቁታላችሁ:: ከብዛታቸው የተነሳ እንደ መርካቶ መተሻሸት እንጂ ለሰላምታ አይታሰብም:: እንደ እውነቱ ከሆነ ሮማ ውስጥ ሃበሻው በአጠገቤ አልፎ ሰላም አላለኝም ብሎ ማማረር ማለት የአዲስአበባ መርካቶ ውስጥ ሄደው ሁሉንም ሰው ሰላም በሉ እንደማለት ይቆጠራል:: ግን ከፍትፍቱ ፊቱ ይባላልና ቢያንስ አንዳችን ለአንዳችን ጥሩ ፈገግታ የማሳየት ባህል አለመደብንም:: ይሁንና ወደ አንዱ ሱቅ ጎራ አልኩኝና ሻጯ ሀበሻ መሆኗን ሳውቅ ሰላምታዬን አስቀደምኩኝና ከፍ ብሎ የተሰቀለውን ልብስ አውርዳልኝ እንዳየው ጠየኳት:: በጣም እንዳስጠላኋት እየታወቀባት በጣም በቀስታ እየተራመደች ዘንግ ስታነሳ የሱቁ ስልክ አንቃጨለ:: ዘንጉን እንደያዘች ስልኩን አነሳችና በአማርኛ የቤቷን ጉዳይ ዝክዝክ አርጋ ከፊቴ ማውራት ጀመረች:: ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝና እኔው ይቅርታ አልኳትና እንድታስተናግደኝ በምልክት ለመንኳት:: ጭራሽ ዘንጉን ሰጠችኝና አውርድ ብላኝ ተዝናንታ ወሬዋን ቀጠለች:: ዘንጉን ቁጭ አደረኩላትና ውልቅ አልኩኝ:: ሌላው የታዘብኩት ነገር ደግሞ ሀበሻ ሬስቶራንት ውስጥ የንድ አስተናጋጅ የምግብ ዝርዝር (ሜኑ) ትፈልጋለህ ወይስ የምትበላውን ታውቀዋለህ ብላ መጠየቋ ነው። ይህን የመሳሰሉትን ነገሮች ስናይ እንደገባኝ ሀበሾች እርስ በርሳቸው መሰላቻቸታቸውን በግልጽ ያሳያል። በርግጥ የመሸሹ ጉዳይ የዘር ክፍፍል ያመጣው በሽታ ነው ብዬ ራሴን ለማሳመን ብሞክርም የመሰለቻቸቱና የመናናቁ ጉዳይ ለምን ይሁን ብዬ ራሴን ብጠይቅ ምንም መልስ ያላገኘሁበት ሆኗል።

***


…….... ምንም ይሁን ከዚህ በፊት የማላውቀው ሰው መንገድ ላይ ሰላም አላለኝም ብዬ ሆዴን አይቆርጠኝም:: ነገርግን አንድ አከባቢ የምትኖር ከሆነ ትውውቅ እና ንጹህ መግባባት ቢኖር ለመረዳዳት ይጠቅማል:: የተቸገረን ሰው ወይም ርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ከተቻለ ያለ ዘር እና ቀለም ማዳላት መርዳት ጥሩ ምግባር ይመስለኛል:: ከዚያ ውጪ መንገድ ላይ ያየሁትን ሰው አበሻ ይሆን? ሰላም ልበለው አልበለው? ምን አጨናነቀኝ:: ሀበሻ ከሌላው በምንም ዐይነት ልዩ የሚያደርገው ነገር እንደሌለው በብዙ ነገር ስላረጋገጥኩ ሰውን ሳላውቀው ማንንም ሰላም አልልም:: የማታውቀውን ሰው ገና ለገና ሀበሻ ነው ብሎ ሰላም ማለት የዋህነት ነው:: ድሮ ድሮ ሀበሻ የሚመስለውን ሁሉ ሳልረዳና ሳልጠይቅ እንዲሁም በአይኔ ሳልጠቅስ የማልፍበት ጊዜ አልነበረም:: ኋላ ኋላ ግን ለማላውቀው ሀበሻ ለሰአምታ መጨነቅ ካቆምኩ ዘመን አስቆጥርያለሁኝ:: ድሮ ድሮ ሀበሻ ሁሉ የእናቴ ልጅ ይመስለኝ ነበር:: አሁን ግን ተንኮለኛ ሀበሻ ብቅ ብቅ እያለ በሚያሳፍር ዜና በየጋዜጣው ፊት ገጽ ላይ ገጭ እያለ ነው:: የዘር ጥላቻ አዕምሮውን ያቆሸሸው ሀበሻም ስለበዛ::

***


……....አንድ ሰው ካገሩ ርቆ በባዕድ አገር ሲኖር ባይተዋርነት እንደሚሰማው ግልጽ ስለሆነና ይህን ለማስታገስ ያገር ልጆች በባዕድ አገር ሲገናኙ ሠላምታ መለዋወጥ ብርቅዬ ነው:: ኧረ ወግም ነው:: ሰዉ ባገሩ ምሉዕ ነው:: የስደት ኑሮ ግን ሁሌም ጉድለት አለው:: በስደት አለም ከሚኖሩ አፍሪካውያን ከሀበሻ በስተቀር አብዛኛዎቹ ይፈላለጋሉ፣ ይጠያየቃሉ፣ ከሩቅ በፉጨት ተጠራርተው ነው ሰላምታ የሚለዋወጡት:: እኔ ባለሁበት ሀበሻ ሳይ ተከትዬ ሠላም ብዬ አድራሻ ተለዋውጬ ነው የምለየው:: በምችለው ሁሉ ወጉን ጠብቄ አገራዊ ግዴታየን ለመወጣት እሞክራለሁ:: በተለይ ለአዲስ መጤ ሀበሻዎች በባዕድ አገር የአገር ልጅ ሰላምታ ለእነሱ ፈውስ ነው:: በእስካሁኑ ቆይታዬ የሸሸኝ ወይም የሸሸሁት የለም:: ይህን መሰል ምሬት ግን ከሌሎች ሰምቸዋለሁ:: "ሀበሻ በተፈጥሮ ድብቅ ነው:: ውስጡ እንዲታወቅበት አይሻም" ይህ ሽሽት ምናልባት አንዳችን የሌላውን ውስጥ ዘልቀን ለመፈተሽ ካለን ያለሳለሰ ጥረት ሊሆን ይችላል:: እያንዳንዱ ያለፈበት ሕይወት ራሱ አንድ ልቦለድ አይደል! ያ እንዲነበብበት አይፈልግ ይሆናል:: ሌላው ችግር ደግሞ ከሰላምታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ጨዋታ አለ:: የት ነው ምትኖረው? የት ነው ምትኖሪው? ስለ ስራ ሁኔታ መጠያየቅ አድራሻ መለዋወጥ መቀጣጥር:: መችም በባዕድ አገር ሁሉም ደስተኛ አይደለምና ጓደኝነትና ስራ የሚፈልግም ይኖራል:: ዜጋው ለዚህ ዝግጁ አይደለም:: ይህን ላለመስማት ሰላም አለማባባሉን ይመርጣል:: እኔ ሌላዉን ለመርዳት ወይም ለመጎዳኘት ካልፈለኩ በሠላምታ ብቻ ለመሸኘት ምንም አይቸግረኝም:: ልርዳ ካልኩም የሚያግደኝ የለም:: እኔ የማምነው ሞቅ ያለ ሠላምታም ራሱ እርዳታ ነው:: መተዋወቅም ጥቅም አለው:: ይህ ሁሉ የሚጀምረው ከሠላምታ ነው:: የዚህ አምድ ጥያቄ ከየዋህነት የመጣ ነው ካላችሁ እኔ አልስማማም:: ቶክዮ ወይም ለንደን ውስጥ አበሻ አይቼ ሠላም የማልልበት ምክንያት ጭንቀት እንጂ የዋህነት አይመስለኝም:: ምናልባት ጣሊያን የምንኖር ስሜታችንን እንደተረዳሁት ከረጅሙ አመታት ኑሮ በኋላ የሚመጣ የጣሊያዊነት ስሜት ይኖረናል። ይህ ስሜት ሀበሻነትን ሳናስበው ከውስጣችን ውስጥ እያሟሟ ይሄድና መንገድ ላይ ሰላምታ መለዋወጡ እውነትም እብደት ያስብላል:: ሐበሻዊነት ወኔና ስሜት እስካለን ድረስ እንዲሁም በባዕድ አገር እስከኖርን ድረስ ግን ሠላምታ መለዋወጡ ልዩ ምልክታችን ነውና አትዘንጉን አትዝጉን::

***


……....ስሜን ይጠይቀኛል፣ ከዛም ቁጥሬን ይጠይቀኛል ብሎ ሰላምታ አለመስጠት ደግሞ! በራስ የመተማመን ክፉኛ በሽታ ያለበት ነው:: ማንኛውም በሰላምታ ምክንያት ክሰ እንደማይደርስባቸው በአውራ ጣቴ እፈርምላቸዋለሁ:: እኔ አበሻን ሰላም እማልለው በበኩሌ አገር ቤት ብቻ ነው:: እሱን እማላደርገው ከህዝቡ ቁጥር አንጻር እያንዳንዱን ሰላም እያልኩ ለማለፍ ጊዜ ስለማይኖረኝ ነው:: ከዛ ውጪ አይተህን ሰላም ሳትለን አለፍክ እምትሉ ካላችሁ መካከለኛ ይቅርታ ጠይቄ የገንዘብ ካሳ እክፍላለሁ። ሀበሻ ስለሆኑ ብቻ ሰላም የምልበት ወይም ደግሞ ሀበሻ ስለሆኑ ፊቴን የማጠቁርበት ምክንያት የለም:: ከሰው ጋር አይን ላይን ከተገጣጠምኩኝ sorrido... non mi importa che persona è.

***


……....ለምን ሀበሻ ሰላም አላለኝም ብዬ ጠይቄም አላውቅም:: የማላቀው ሰው ሀበሻ ስለሆንኩ ብሎ ሰላም እንዲለኝ አልጠብቅም እኔም አልልም:: ይህ ጉዳይ ለምን እንደሚነሳ እራሱ አይገባኝም:: ይልቅ I would like to know ለምን ሀበሻ ሀበሻን ሲያይ ፊቱን እንደሚከሰክስ ነገርግን እንደዚህ ለማለት የቻልኩበት ገጠመኝ አለኝ:: ሁሌም ወደስራ ሳልፍ ቡና ገዝቼ የማልፍበት ቦታ አለ:: አንዲት ሀበሻ ልጅ ነበረች:: Barista ነች:: ከፊቴ ያሉትን በጥሩ ሁኔታ እያስተናገደች ነበር era il mio turno... Ho visto di come la sua faccia era cambiata... era ovvio che non era felice di vedere me tra la gente... ሌላ ግዜ ደግሞ ከፊት ለፊቴ የምትመጣ ልጅ ከኔ ጋር ከመተላለፍ በቀር ምንም አማራጭ አልነበራትም:: ልክ አጠገቤ ስትደርስ ፊቷን ክስክስ አድርጋ ስልኳን ማውራት ጀመረች (ስልኩ ጠርቶም አይመስለኝ):: በሰላም አገር እራስን ማጨናነቅ እስኪ ምን ይባላል። ሰላም አለማለት ባይኖር almeno በsorriso ማለፍ ሲቻል የማይሆን መጨናነቅና መኮሳተር እንዲሁም መሸሽን ምን አመጣው? ጎመን በጤና! እንዲያ በሩቁ ይሻላል።

***


……....ምኑ እንዳይቀርብኝ ነው ደግሞ ሰላም የምለው? ሴቷ ጫማ ጫማሽን ታያለች ወንዱ ደግሞ ፈገግ ካልሺለት ስምሽ ማነው ይላል? ስምሽን ከነገርሽው ደግሞ ስልክሽን አምጪ ይላል ወይ ስራሽን ያባትሽን ስም ዕድሜሽን ባንድ ቀን አጣርቶ መሄድ ይፈልጋል እንዲያው ልብ አውልቆች ናቸው:: ስለዚህ ሀበሻ ነሽ ብሎ የሚጠይቀኝ ሀበሻ በቀላሉ "አይደለሁም" ብዬ እገጨዋለሁ 2ኛ ቀና ብሎ ፊቴን አያያትም መንገድ እያቆራረጠ ሲፈረጥጥ እያየ....እዚህ እስከኖሩ ድረስ ቋንቋውን ይወቁ።


ምክር ብጤ


……....ቋንቋ የተፈጠረው ለመግባባት፣ ያሰቡትንና የሚፈልጉትን ነገር በትክክል ለመግለፅ ነው፡፡ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለመግባባት ወሳኝ የሆነና የብዙ ነገር መክፈቻ/መዝጊያ ዋናው ቁልፍ ነው ማለት ይቻላል። ቋንቋ በአንድነት ለመኖርና አንድ ቤተ ሰብ ለመሆን የመዋሃሃድ ቍልፍ ነው። እርስዎም በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ ንዋሪ እስከሆኑ ድረስ የማህበረሰቡን ቋንቋ ማወቁ ተገቢ ነው። የቋንቋ እድገት የዜጋን እድገት ከሚያመለክቱት ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ማወቁ በራሳችን እንድተማመን ያደርገናል፡፡ ማወቁ አንዱ የማደጋችን ምልክት ነው፡፡ ካላወቅንበት ግን ማደግ አንችልም፡፡ ከጎደለን ማንነታችንም አብሮ ይጎድላልና!! የምንፈልገውንና የሚሰማንን ነገር ለማስረዳት ከቸገረን ወይም የሚነግሩን ነገር ካልገባን በሀገሪቱ ማህበራዊ ኑሮአችን እንዲሁም በስራው ዓለም ጋር ከተያያዘው ሁኔታዎች ጋር አንድ ላይ መጓዝ ይቸግረናል፡፡ ሃሳብን ያለምንም በትክክል መግለፅ መቻል ማለት እራሱን የቻለ ጥበብ ነው፡፡ እውቀትና ኩራትም ነው፡፡ ለአንድ ማኅበረሰብ ባህል የሚያመጣው ተጽዕኖ ከፍተኛ ቦታ ስለሚይዝ ለማወቅ መጣርና መናገር ማለት ለሚያስተናግደን ማኅበረሰብም ክብር መስጠት እንደማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የአንድ ማህበረሰብ ማንነቱን፣ እሴቱንና ባህሉን የሚጠብቅበት ቁልፍ ስለሆነ ነው። የሌላ ማኅበረሰብን ቋንቋ ለመረዳት መሞከር ማለት የማኅበረሰቡንም ባህል፣ ኑሮ፣ ዘይቤ፣ ... ለመረዳት ጥረት እንደማድረግ ሊቆጠር ይችላል።

……....ነገሮችን ካለመረዳት ወይም ካለማስረዳት መቀያየም፣ መጣላት፣ አለመግባባት ሊኖር ይችላል፡፡ ምናልባት በቋንቋው እጥረት ምክንያት ሊሆን ይችላል ግጭት የሚፈጠረው፡፡ የቋንቋን ጠቃሚነት ባለማስተዋል እራሳችንን ምን ያህል ራሳችንን እንጎዳለን፡፡ ቋንቋውን መናገር ብቻ ሳይሆን ብዙዎቻችን መፃፉንም በቅጡ አንችልበትም፡፡

……....የውጭ ቋንቋ ለእውቀትም ሆነ የውጭ ንባባትን ለማዳበር ጠቃሚነቱ አይካድም። ቢሆንም ለሀገራችንም ቋንቋዎች ትኩረት መስጠት ይገባል። ሀገራቸውን በቅጡ ለማያውቁት በባዕድ ሀገራት ለተወለዱ ልጆቻችን የራሳችንንም ቋንቋ ማቀበል ይገባናል። ዛሬ ሁላችንም እንደምንረዳው በሰው ሃገር ላይ ቁጥራችን በእጅጉ እየበዛ መጥቷል። የተለያዩ እንቡጦችንም እያፈራን ነው። ለነዚህ እንቡጦች ዘር፣ ኃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ሳይባል ብዙ ቁም ነገሮችን እየቀሰሙ ስለ ቋንቋቸውን ብቻ ሳይሆን መጸረት የሆነውን ባህላቸውን፣ ሃገራቸውን፣ የዘር ግንዳቸውን እንዲሁም ዕውቀት የሚያገኙበትና እርስ በርስ እየተማማሩ ከራሳቸው አልፈው ዜጎቻቸውንና ሃገራቸውን የሚጠቅሙ ትውልዶችን ለማፍራት መሰረት እንኳን ጥለንላቸው ብናልፍ ልጆቻችንን ለፍሬ ማብቃት ይቻላል:: አንድን ተክል ከመሰረቱ ጀምረን እየኮተኮትን አስፈላጊውን ማዳበሪያና ውሃ እያደረግን ስናሳድገው ሊጣመም ይችላል። በወቅቱና በሰዓቱ በችንካርም ቢሆን ካልመለስነው እንደተጣመመ ይቀርና በኋላ ለመመለስ ያስቸግራል። ልመልስህም ቢባል ይሰበራል እንጂ አይመለስም። ጠማማ ተክል ሁልጊዜ መጨረሻው ለአበባም ለፍሬም ሳይታደል ያለጊዜው ተቆርጦ ይቀራል።የኛ ሰው በጣሊያንአብራሃም ዘውዴ


……....በጣሊያን ወደ ሃያ አምስት ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከነዚህም መካከል ብዙዎቹ በርዕሰ ከተማይቱ ሮማ እና ሚላኖ ነው የሚገኙት። ለትምህርት ወደዚህ የመጡት እጅግ በጣም ጥቂት ሲሆኑ አብዛኞቹ ግን በተለያየው የጦርነት ክስተት፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ አህጉራዊና ቤተሰባዊ ችግር የተነሣ የተሰደዱ ኛቸው።

……....ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ከመጡት ውስጥ ደግሞ በረሃንና ባህርን አቋርጠው ብዙ ችግር ገጥሟቸው የገቡ ይገኙበታል። ከእነዚህም መሀከል በፍልሰት ላይ እያሉ ሕይወታቸውን ያጡትን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች ነው። ታዲያ በመጡበት በመጀመሪያው ዓመታት ውስጥ በዶኩመንት፣ በኢንተግራዚዮኔ፣ በቋንቋና በኑሮዋቸው ላይ ችግር ያጋጥማቸዋል። እንደዚህ አይነት ችግሮቻቸውን ለማቃለል ወይም የሚረዳዱበትን መንገድ በመፍጠር እዚሁ በሚገኙ ወገኖች በአንዳንድ የጣሊያን ከተሞች ውስጥ ማኅበራት አቋቁመዋል። እነዚሁ ዜጎች ከአቋቋሙዋቸው ማኅበራት ውስጥ ...

……....1- የመረዳጃ ማህበር በማለት ለችግረኞች አስፈላጊ የሆኑትን ነግሮች ለምሳሌ ከድርጅቶችና ከመንግሥት መጠለያ፣ ምግብ፣ ... ወዘተ ... ለሟሟላት ይጥራሉ።

……....2- ወደተለያዩ በጎአድራጎት የሚያደርጉና ወደ የክፍለሀገሩ የውጪ ዜጎች እርዳታ ሰጪ ጽህፈት ቤቶች ... ወይም ወደ ካሪታስ እየተመሩ እንዲገለገሉ ያደርጋሉ።

……....3- ህግና ደንብ ባለው ማህበራቸውና በመንግስት በኩል ህልውና በተሰጠው ድርጅታቸው አማካይነት እርዳታዎችን እንዲያገኙ በማድርግ ጊዜያዊው ችግረኛ ወገናቸውን እስከሚቋቋም ድረስ ይደጉማሉ።

……....4- የጤና ህውከት ለሚኖራቸው ደግሞ ሙሉ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ... ... ...
5- ... ይቀጥላል ...

……....እዚህ ከሚኖሩት ወገኖች መካከል ከማንም ጋር ግኑኝነት የማያደርጉ፣ የተገለሉ፣ ያልታወቁ፣ የኑሮውን ውጣና ውረድ መቋቋም ያቃታቸው፣ የብቸኝነት ስሜት ያላቸው፣ የህሊና ዕረፍት የማያደርጉ፣ ለራሳቸው የሚሆን መዝናኛ ነገሮችን እንኳን የማያደርጉ የሀገር ልጆች ብዙ ናቸው። በመንፈስ ጭንቀት ወይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት ብቻ ሊሠሩ ባለመቻላቸው ወደሀገር ቤት የሚመለሱም አይጠፉም። ለዚህም እንኳን የሥነ አዕምሮና የሥነ ልቦና ምክር ሊሰጥበት የሚችልበትን ማዕከል ለማግኘት የሚጠየቅበትን ሳያውቁ፣ የሚፈለገውን አገልግሎትና ህክምና ሳያገኙ ወደ ቤተሰባቸው የሚመለሱና የሚላኩ ጥቂቶች አይደሉም። ... ይቀጥላል ...

……....ጣሊያን በሙያ የሠለጠኑና በቀለም ትምህርት የገፉ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር ናት። ይሁንና በጣሊያን የውጭ ሀገር ስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽንና የአንዳንድ የውጪ ሀገር ተወላጅ ኮሙኒቲዎች የትብብር ጥናት እንደሚጠቁመው ይኸው እኛኑ የሚያስተናግደን ሀገር ስለስደተኞች የሙያ ችሎታ ተመክሮ አላደረገም። አድርጎም አያውቅም። እዚህ ጣሊያን ከሚገኙት በግምት ቁጥራችን ከ20ሺ እስከ 25ሺ የምንደርሰው ኢትዮጲያውያን ነዋሪዎች፣ ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች መካከል 70 በመቶ የምንሆነው መደበኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችንን ያጠናቀቅን ነን። ከሀገር ከመኮብለላችን በፊት ብዙዎቻችን በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተን የተለያዩ የሥራ ልምዶች ያለንም አለን። ታዲያ የጣሊያን መንግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት አልመከረበትም፣ ችሎታቸንንም አልተጠቀመበትም። ከሌሎችም የውጪ ዜጎች መካከል በየሀገራቸው የዩንቨርስቲ ምሩቃን የሆኑና በሙያቸው የሰለጠኑትን ሁሉ ዕድሉ ቢሰጣቸው ለጣሊያን ብልፅግና የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ማበርከት አይሳናቸውም። ... ይቀጥላል ...

……....ጥናቱ እንደሚያመለክተው እስከ 2005 አጋማሽ ድረስ 25% የሚደርሰው ስደተኛ በሥራው regolare ያልሆነ ነው። ማለትም እዚህ ከሚገኙት እስከ 4 ሚሊዮን ከሚደርሱት የውጪ ሀገር ዜጎች 500 ሺ የሚሆነው clandestini ነው ተብሎ ይገመታል። ሌላው ይህንኑ የሚያክለው ደግሞ ዶኩሜንት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ቢኖረውም ምንም ዓይነት ሥራ ወይም ገቢ የሌለው ነው። አብዛኞቹ ለህልውናቸው ሲጨነቁ ሲጠበቡ ነው የሚታዩት።
እንደዛም ሆኖ በእዚህ በተጠለልንበት ሀገር ውስጥ የውጪ ዜጋዎች ለሆንን ደህንነታችን የቱን ያህል አስተማማኝ ነው? ዓለማቀፍ መብታችንና ስበዓዊ ክብራችን የቱን ያህል ይጠበቃል? ወዘተ...
ታዲያ በዚሁ የውጪ ሀገር የኑሮ ችግርና የአጠቃላዩን የእኛን ስደተኞች ኑሮ እራሳችንንም እንኳ ለመገንዘብ እንዲያስችለን እስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ እኛው ራሳችን መርምረን እንየው።

……....እንደሚታወቀው ለውጭ ዜጎች ፍልሰት መመሪያ ሰጪው ህግ ለብዙ ዓመታት ያህል ሲያከራክር ቆይቶ ነበር። ከውጭ ሀገር እየፈለሱ ወደ ጣሊያን ለሚገቡ ሰዎች መመሪያ ሰጪ የሆነው ይህ ረቂቅ ህግ በተቃውሞ ፓርቲዎች እስካሁን የስምምነት እልባት አላገኙለትም ማለት ይቻላል። ስምምነት ላይ የማይደርሱበት ምክንያት ለምን ይሆን? የህጉን ረቂቅ አንቀጾች በጥሞና መርምረው በድምጽ ብልጫ ተደርጎበት ከተስማሙበት በኋላ በብሔራዊው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት (parlamento) ፀድቋል። በተቃውሞ ፓርቲዎችም ባለመደገፉ በጣሊያን ኅብረተሰብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አገኘ ወይም አላገኘም ማለት ያዳግታል። ... ይቀጥላል ...

……....ይህም ሆኖ ግን ጣሊያን ሀገር ለሚኖሩ የውጭ ተወላጆች ...

……....* የወደፊት የኑሮ እቅዳቸውን ለማውጣትም ሆነ ለማስተካከል የሚረዳ መሆን አለበት።

……....* የሠለጠነ የሰው ኃይል ምንጊዜም ተፈላጊነቱ ስላለ በከፍተኛ የጣሊያን የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የውጭ ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች የተሻለ አማራጭ ዕድል ሊሰጣቸውና እኩል መብት እንዲኖራቸው ይገባል።

……....* የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታም መቃለል አለበት።

……....* ለማንኛውም ሥራ ፈላጊ ለሆነው የውጪ ሀገር ተወላጅ በሩ ክፍት መሆን ይገባዋል።

……....* ተገን ጥያቂ ሰዎችን ካገር ማስወጣት ሳይሆን ዓለምአቀፋዊ የፖለቲካ ጥገኝነት መብት እንዳይነፈጋቸው መሆን ይገባዋል ... ይቀጥላል ...

……....ጣሊያን በኤኮኖሚና በህዝብ ቁጥር አለመመጣጠን ሳቢያ ለሚፈልሱት የውጭ ተወላጆች ቁጥር ምጨመር ምክንያት የምታስተናግድበት አቋም ወደፊት እንደነበረው አይሆንም። በጣሊያን ሀገር በአሁኑ ጊዜ 4 ሚልዮን የውጭ ዜጎች ይገኛሉ። የጣሊያን መንግሥት ለጋስነትን የሚያሳይበት እርምጃ ነው የተባለበት አንድ ሌላ ጉዳይ በአለፉት ዓምታት በጣሊያን ምድር ለሚገኙ የውጭ ተወላጆች ከህብረተሰቡ ጋር በማኅበራዊ ኑሮ መዋሀድ የሚችሉበትን መንገድ (integrazione) ለማቃናት ሲል በመንግስት ብዙ ሚሊያርድ ተመድቦ ወጪና ሰበካዎች ሁሉ አድርጎ ነበር። ለዚህም ማካሄጃ የሚሆነው ወጪ የተደረገው ስደተኛው እራሱ ከሚከፈለው የመመዝገቢያና የታክስ ገንዘብ ገቢ ወጪውን እንደሚሸፍንላቸው በማወቃቸው ነው። በዚህም ምክንያት የውጪ ዜጎችን ማስተናገድና በሥራ ማሰማራት ለኢኮኖሚያቸው እድገት ምን ያህል አስተዋጽዖ እንዳለው አምነውበታል። ይኼ ሁሉ ጥቅም እየተገኘበት እንዴት ለውጭ ዜጎች ፍልሰት መመሪያ የሚሰጠው አዲሱን ህግ እልባት አያገኙለትም?

……....ለምሳሌ ያህል ... ተገን ጥያቂዎችን ካገር ማስወጣት ሳይሆን ዓለምአቀፋዊ የፖለቲካ ጥገኝነት መብት እንዳይነፈጋቸው መሆን ይገባዋል። በእርግጥ በኒዮርክ፣ በዋሺንግተን፣ ለንደን እንዲሁም በማድሪድ አሸባሪዎች ጥፋት ካደረሱ ወዲህ ጣሊያን ውስጥ የፀጥታ ጉዳይ ይበልጥ እንዲታሰብበት አስገድዷል። ቀደም ሲል አክራሪ ሙስሊሞችን፣ በአሸባሪነት የሚጠረጠሩትና የተከለከሉ የድርጅቶች መሪዎችን፣ በሃይማኖትም ሆነ በጎሣ ላይ ያተኮረ ጥላቻን የሚሰብኩ ወንጀለኞችን ካገር ማባረራቸው ደግ ነው። ነገር ግን የህጉን አተረጓጎም ለውጦ ሁሉንም ተገን ጠያቂዎችን እንዳይነካ መሆን ይገባዋል። ... ይቀጥላል ...

……....ወደ አውሮጳው ኅብረት ስለስደተኞች ጉዳይ ስንመጣ ደግሞ ኅብረቱ ያቀደው የጋራው መመሪያ እስካሁን በሁሉም አባላት ሀገሮች አማካይነት አላገኘም ማለት ይቻላል። ምክንያቱም አባላቱ ሀገሮች የሚያስተላልፏቸው ሕግጋት አንደኛ በጽንሰ ሃሳብ የተለያዩ ናቸው። ለምሳሌ ስደተኞቹ የፖለቲካ ተገን በመጠየቅ ማመልከቻ ለሚያቀርቡት ሁኔታ አንዱ ከሌላው አውሮጳዊ ሀገር የተለያየ እርምጃ ነው የሚወሰደው። አለቅጥ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

…….... በታቀደው አዲስ መመሪያ ረገድ ከፍተኛ ቅሬታ እንዲኖር ከሚያደርጉት አንደኛው "የፖለቲካ ተገን ጠያቂ አቤቱታው ተቀባይነትን በሚያጣበት ጊዜ ወደ መጣበት ሀገር ይባረራል" የሚባልበት ሁኔታ ነው። ይህም ለተገን ጠያቂው ደህንነት አስተማማኝ ላይሆን ይችላል። ይባስ ተብሎ ተገን ጠያቂዎቹ ስደተኞች ወዲያው ከድንበር እንዲመለሱ የሚደረጉበት ሁኔታም ይገኛል። እንግዴህ ይህ ነጥብ የሚያመለክተው የኅብረቱ መመሪያ ምን ያህል ግልጽነት የተጓደለበት መሆኑን ነው። ስደተኞች ከድንበር እንዲመለሱ የሚደረግ ከሆነ በዚሁ ርምጃ አንፃር በተገን ጠያቂነታቸው መብት ላይ ይግባኝ የሚሉበት መብት ሁሉ ይጓደላል ማለት ነው።

…….... የፖለቲካ ተገን ጠያቂዎች ከሚያቀርቧቸው ማመልከቻዎች መካከል ከ5 በመቶ የሚደርሱቱ ብቻ ነው ድጎማና ትውቅናን የሚያገኙት። በዚህ አኳኋን እንግዲህ ከድንበር መባረር የሚፀና ከሆነ የፖለቲካ ተገን መብት ያላቸው ብዙ ስደተኞች የይግባኙ ሥርዓት ፍፃሜ ከማግኘቱ በፊት ሊባረሩ ይችላሉ ማለትም 95 በመቶ ወደሀገሩ በሚመለስበት ጊዜ ዋስትና ላይኖረው ይችላል ማለት ነው። የዓለሙ ድርጅት አሁን የሚሠጋበት በፖለቲካ ስደተኛነት ሳይሆን እንዲያው በፍልሰት ወደ አውሮጳ የሚሸጋገሩትን ወገኖች የሚመለከተው እምቢታ ወደ ስደተኞችም እየተዛወረ የውነተኛ ስደተኞች መብት የሚፋለስበትን ዝንባሌ መታየቱን ነው። በዚህም ምክንያት የአውሮጳው ኅብረት ከስደተኞች ጉዳይ መርሕ ጎንለጎን እውነተኛ የፍልሰት መርሕም እንዲኖረውና የእውነተኛ ስደተኛነትም ሁኔታ የሚጣራበት ቋሚ ሥርዓት እንዲፈጥር አስፈላጊ ሆኖ ነው የሚታየው። ... ይቀጥላል ...

የአበሻ ቀጠሮ

አብራሃም ዘውዴ

"የሰው ቀጠሮ ቀርጥፎ የሚበላ" ተብለን በፈረንጅ አፍ እንዳንገባና ትምህርት ይሆነን ዘንድ ስለቀጠሮ ማንሳቱ አስፈላጊ ነው። ይተገበራሉ የምንላቸውን ነገር በቀጠሮ የሚያዙ ስለሆኑ ስለቀጠሮ ትንሽ ቢባል የሚያስከፋ አይሆንም። ወይም የወደፊት እቅዳችን በቀጠሮዎች የሚያዝ ስለሆነ ሊፈፀም ይችል ዘንድ ቀጠሮን ማክበር ይገባል። ጥላሁን ገሠሠ በአንድ የሙዚቃ ካሴቱ ላይ...

"አርቆ ማሰቢያ እያለው አዕምሮ
ሰው እንዴት ይሳነው ለማክበር ቀጠሮ"

በማለት የነቀፈበትን ባለሁለት ስንኝ ግጥም መንደርደሪያ አድርገን ትንሽ እንበል። መቼም ስለቀጠሮ ሲነሳ ስለ “ጊዜ” መነሳቱ የማይቀር ነው። አዎ! "ጊዜ ወርቅ ነው" ተብሎ በሚነገርበት ሀገር እየኖርን ወይም ስለጊዜ ክቡርነት በሚነገርበት አገር እያለን በቀጠሮ አለመገኘትና ሰዓት አለማክበር ወይም ማርፈድ የኢትዮጵያዊነት ምልክት ተደርጐ መወሰዱ ለምን ይሆን? በቀጠሮ ሰዓት ያልተገኘ ኢትዮጲያዊ ሰው ሲገጥመን "ድሮስ አበሻ አይደል" እንላለን። እውነት “የአበሻ ቀጠሮ” የምንለው የተለመደው አባባል እኛን ኢትዮጵያዊያንን ለቀጠሮ ደንታ ቢስነት መሆናችንን ያሳያል? “የአበሻ ቀጠሮ” ይሚባለው መለያችን ሆኖ ሊቀር ነው እንዴ? አባቶቻችን...

"ከቶ አይቀርም ሞቱ ምንም ቢዋትቱ"
"አያሳስትም ሰዓት ቀጠሮ ያከብራል ሞት"

በማለት ቀጠሮ አክባሪው ሞት ነው ሲሉ የሞትን አይቀሬነት ገልፀዋል። ... ይቀጥላል ...


አበሻን መቅጠር እፈራለሁ!

……....አበሻን መቅጠር እፈራለሁ! ታዲያ "ያረፍድ ይሆን" ብዬ አይምሰላችሁ "ይመጣ ይሆን" ብዬ እንጂ፡፡
በቀጠሮ ጊዜ የሚያረፍድ አበሻ እራሱ ቀጥሮ ቢቀሩበት "ምንም አይደል" ብሎ መመለስ ጀምሯል። እያረፈድን "ይሁን" ማለት ተለመደ። የቀጠረን ሰው እየጠበቀን እያለ መቅረትም አለ፡፡ ታዲያ የአበሻ ቀጠሮን እንደ ቅርስ ልንጠብቅ እየከጀለን ወይም አሜን ብለን እየተቀበልነው ነው እኮ! ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ እንደመምጣት በቀጠሮ ላይ የኛ ጉዳይ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ ሆኗል፡፡ ስለ ሌሎች አገሮች ባላውቅም እዚህ አካባቢ ግን ስላለው መናገር እችላለሁ፡፡

……....በቀጠሮ ላይ በሰዓቱና በቦታው የማይገኘውን ግለሰብ እንዴት እናየዋለን?
ብዙዎቻችን ዝርክርኮች ከመሆናችንም የተነሳ በቀጠሮ ጊዜ በቦታውና በሰዓቱ አንገኝም፡፡ በቀጠሮ የማይገኝ ወይም ያለበቂ ምክንያት የሚዘገይ ግለሰብ ከብጣሽ ወረቀት የበለጠ የቀለለ ግለሰብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በራሱ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ዕቅድ የሌለውና ለራሱም ሆነ ለቀጠረው ግለሰብ ክብር የማያሳይ፣ የተዝረከረከና ሊተማመኑበት የማይችል አጉል ዜጋ ነው፡፡
……....ቀጠሮ ስለ አንድ ግለሰብ ማንነት ማወቂያና መገምገሚያ ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቁምነገርኛ፣ የሰለጠኑ፣ የሚከበሩ ሰዎች ቀጠሮን ያከብራሉ። ቁምነገረኛ የተባሉብትና የተከበሩበትም ሁኔታ አንዱ ቀጠሮን አክብረው በተዘዋዋሪም የቀጠሩትን ሰው በማክበራቸው የተነሳ ነው። የተማሩትም ቀጠሮ ያከብራሉ ስንል ብዙኃኑ ቁም ነገረኞች በመሆናቸውና ለቀጠሩት ሰው ክብር ስለሚሰጡ ነው። እናም ቀጠሮ ሻይ ለመጠጣት፣ ለመጨዋወት የመሳሰሉትን ለማድረግ የምንቀጣጠረውን ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ - ስብሰባ ሲኖር ቀጠሮ እንይዛለን፡፡ ዝግጅት ሲኖር በሰዓቱ ለመጀመርና ለመጨረስ ቀጠሮ እናደርጋለን፡፡ ታዲያ አዘጋጁም በወቅቱ ተዘጋጅቶና ተካፋዩም በሰዓቱ ተገኝቶ ጉዳዩን ለመፈፀም ሲያዳግታቸው ይታያል፡፡ አዘጋጆችም ከሆንን ቀደም ብለን አስበንበት ስለማንዘጋጅና ሃላፊነት ስለማይሰማን ጉዳዬችን በጊዜው አንፈጽመውም፡፡
……....ቀጠሮ ማድረግ ማለት በወቅቱ ለመገኘት ቃል መግባት ነው፡፡ ብዙዎቻችን ግን ቃላችንን እናፈርሳለን፡፡ ቃልን ማፍረስና ማጠፍ ደግሞ ወስላታና ውሸታም መሆን ማለት ነው፡፡ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ወስላታና ውሸታም መሆናችን አይሰማንም፡፡ ቢሰማንም ጎጂ መሆኑን በቅጡ አናስተውለውም፡፡ ምክንያቱም ቀጠሮን ያለማክበር ሁኔታ ስለተደጋገመ እንደ ልምድ ሆኖ እየቀረብን መጣ፡፡
……....በእርግጥ ቀጠሮን በተመለከተ ጥቂቶች እንሁን እንጂ ጠንቃቃ የሆንን አለን፡፡ የሚደንቀው ነገር ግን አንዳንዶቻችን በሰዓቱ ደርሰን የዘገዩትን ለምን ዘገየህ ብለን በምንጠይቅና በምንወቅስ ጊዜ ይባስ ብሎ ምን መልስ እንደሚሰጠን ታውቃላችሁ? "እባክህ አንተ ደግሞ ፈረንጂ አትሁንብን - ይሄ እኮ ያበሻ ቀጠሮ እኮ ነው!" መባላችን ነው፡፡ ወይም ደግሞ "ዝናብ ነበር"፣ "መጓጓዢያ አልነበረም" እንላለን፡፡ መቼም ሰነፍ ምክንያት አያጣም! እንደውም ለምን ሰዓቱን እንዳላከበረ ስትወቅሱት "ሰለጠንኩ ብለህ ነው ወይ?" ብለው አዙረው አንተን ጥፋተኛ አድርገው የሚመልሱም አይጠፉም፡፡ እንግዲህ ዋናው የብዙወቻችን ኢትዮጵያኖች ስህተት፣ በሰዓቱ መገኘት ማለት የፈረንጆች ባህል ብቻ መሆኑን ማመናችን ነው፡፡ ይህ የማስተዋልና የዕቅድ ማውጣት ጉዳይ እንጂ ሰዓት የማክበርን ባለቤትነት የወሰደ ዜጋ ወይም ዘር የለም፡፡ ይህ መታወቅ አለበት፡፡
……....ምክንያትን በመፍጠር በቀጠሮ ላይ በሰዓቱ አለመድረስ ወይም ሰዓቱን ባለማክበርና በዚሁ ስንፍናችን ከቀጠልን መደንቆር እንጂ አንሻሻልም፡፡ የምንኖረው ኢትዮጵያም ውስጥ ይሁን ውጭ አገር ሰው አደርጋለሁ ካለ ማድረግ አለበት፡፡ ቀጠሮ ከመያዛችን በፊት መቼና በምን ወደ ቀጠሮ ቦታ እንደሚኬድ እቅድ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ በቀጠሮውም ሰዓትና ቀን ሌላ ጉዳዮች እንደሌሉን ከበፊቱ ማወቅ አለብን። አብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያዊያን በህይወታችን ውስጥ አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን እንደ ተራ ነገር እንቆጥራቸዋለን፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ቀጠሮን በተመለከተ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች እንደተጠቀሰው ብናደርግ እጅግ ይጠቅመናል፡፡

ቀጠሮን የሚያከብር ግለሰብ ...
……....ሀ) ለቀጠረው ግለሰብ ክብር ያሳያል፡፡
……....ለ) እራሱም ክብር እንደሚገባው በተግባር ያሳያል፡፡
……....ሐ) በተቃጠረው ጉዳይ ላይ ክብደት መስጠቱንና አስፈላጊነቱንም ያሳያል፡፡
……....መ) ጥንቁቅና ነገሮችን በዕቅድ የሚሰራ መሆኑን በተግባር ያሳያል፡፡ ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ቀጠሮ ሲኖረን የተጠቀሱትን ነጥቦች ብናስብባቸው አይከፋም፡፡ ... ይቀጥላል ...
ለምሳሌ ቀጠሮ በሰርግ ጥሪ ላይ...
በብዙ የሰርግ ጥሪ ወረቀቶች "ከቀኑ በ13.30 ሰዓት ላይ ለምሳ እንዲገኙልን" የሚሉ ግብዣዎች አሉ። ይባስ ብሎም "ቀጠሮ ያክብሩ" ወይም "በጊዜ እንዲገኙልን አደራ" የሚል ማሳሰብያ ጭምር ያዘለ ነው። ይሁንና በተባለው ሰዓት በቦታው ቢሄዱ ጭር ያለ ቦታ ነው። ሰርገኞቹ ሙሽሮቹን አጅበው ከሰዓት በኋላ በ15.00 ሰዓት ላይ “ጉሮ ወሸባዬ” እያሉ ወደ ዳስ ሲገቡ፣ ምሳ የሚቀርበው ወደ 16.00። ይህም ሁኔታ በጣሊያን ሀገር በምንገኘው ተደጋግሞ ይታያል። ቀጠሮ አክባሪነት በሃገራችን አጥብቆ እየተለመደ በመጣበት ዘመን፣ ጣሊያን ያለነው ምነው ቀጠሮ ማክበር ያቅተናል? መልሱ አጉል ልማድ… ነዋ! እራትማ ከሆነ ያው እኩለ ሌሊት መሆኑ ነው። እኩለሌሊት የሚቀርብ ከሆነ ደግሞ የጥሪውም ወረቀት ለእኩለ ሌሊት ተብሎ ይታረም። ካልሆነ ግን እራት ብሉ ተብሎ ጥሪ በተላከበት ሰዓት እራቱንም በወቅቱ ማቅረብ ይገባል። “ለ 20.00 ሰዓት እራት ድረሱ፣ አደራ” ብለው ሲያበቁ፣ እስከ እኩለ ሌሊት ሰውን አጉል ማስጠበቅና በረሃብ አለንጋ መግረፍ ተገቢ ነው ወይ?ይህ ሁኔታ ሊለወጥ ይገባዋል። እንግዲያውስ ለዛሬው እዚሁ ላቁም። ይህ የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ ነው በአደባባይ ሹክ ያልኳችሁ፡፡ ሌሎች አንባቢዎች የሚሉትንና የሚጽፉትን ለመስማት እጠባበቃለሁ። መታረም ስላለባቸው ብቻ ሳይሆን መልካም ስለሆኑት ልማዶችም አሞጋግሶ መጻፉ ተገቢ ነው።
... ይቀጥላል ...አውሮፓ ስደተኞች እንዳይጎርፉባት ራሷን ትጋርዳለች

ክፍል 1


23 06 08
አብራሃም ዘውዴ


……....በስትራስቡርጎ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ኃሙስ 17 06 2008 ጠዋት ላይ "ከሶስተኛው ዓለም ወደ አውሮፓ ዘልቀው የሚገቡት ሕገወጥ ስደተኞች ወደመጡበት ሀገር መመለስ አለባቸው" የሚለው መርሕ ላይ ድንጋጌ አደረገ። ይህ የጋራ ውሳኔ እያንዳንዱን የአውሮፓ ሕብረት አባላት ሀገሮች የውጪ ዜጎችን የሚመለከተው ሕጎቻቸው ተመሳሳይና አንድ ወጥ የሆነ መመሪያ እንዲይዙ የሚያደርግ ይሆናል። ከዚህ ድንጋጌ በኋላ እያንዳንዱ አባላት ሀገሮች የሰደተኛን ጎርፍ ለመግታት ደምባቸውን እያጠበቁና ብዙዎችን ለማስወጣት ጥረታቸውን እያጠናከሩ ነው የሚሄዱት። ከዚህ ቀደም ልል የነበሩት የስደተኛ መመሪያዎች እየጠበቁ ይመጣሉ። ወደፊት እያንዳንዱ የአባላት ሀገሮች የሚያወጡት ውስጣዊ መመሪያዎች ተቀማጭ ለሆኑት የውጪ ዜጎች የሚመች አይሆንም። ስለዚህ የተያዘው ሁኔታ አያምርም። እጅግም የሚያበረታታ ነገር የለውም። ለምሳሌ አንድ የፖለቲካ ጥገኛ ጠያቂ ከባህር ጀልባ ላይ ብቅ በሚልበት ጊዜ ወደመጣበት የሚባረር እንጂ ዓለምአቀፋዊ የተገን ጠያቂዎች መብትን የሚጠቀምበት ማንም ሀገር ሊኖር እንደሚችል እጠራጠራለሁ። በጉባኤው ምክር ላይም "የፖለቲካ ተገን የመጠየቁ መሠረታዊ መብት አስፈላጊ ላይሆን ይችላል" የሚል ይዘት ያለው አስተያየቶችም ተሰምተዋል። ይኼ ደግሞ የጀኔቫውን የስደተኛ መብት ጥበቃ የሚጻረርና በዚያን ጊዜ ሁሉም የአውሮፓ ሀገሮች ሳይቀሩ የፈረሙበትን ታሪካዊ ውል የሚያፈርስ ነው። አሁን ይህ ውል ምን አይነት መጨረሻ ይኖረው ይሆን? ለዚህም ነበር የሕብረቱ ስብሰባ ላይ ጉዳዩን ከማንሳት ይልቅ በስተጀርባ መተዉ የተመረጠው።
.
……....የአዉሮፓዉ ህብረት አባላት ስለተገን ጠያቂ ጉዳይ ለስብሰባ በጠረቤዛ ዙርያ ሲቀመጡ የመጀመሪያቸው ጊዜ አይደለም። የአለፉትን የጋራ ውሳኔዎች በትክክልና ሙሉበሙሉ ህጋዊ በሆነ መንገድ በማስፈጸም በስራ ላይ ያዋለ ሀገር አልነበረም ማለት ይቻላል። እያንዳንዱ አባላት ከድንጋጌዎች ውጪ የራሳቸው የሆነ መመሪያ ይዘው ነበር በድንበር አካባቢ ያለዉን የጥበቃ ስራ የሚያጠነክሩት። የመግቢያ ኬላዎችን በር በመቆጣጠር ለህገወጥ ስደተኞች በሩን ለመዝጋት ብዙ ጥረት አድርገዋል። ይኸውም 1ኛ ድንበር ላይ ጠንካራ ፍተሻ እና ጥበቃ ማድረግ በ2ኛ ደረጃ ደግሞ በድንበር ላይ ጥገኝነት ወይም ተገን የሚጠይቁት ላይ ብዙውን ጊዜ ሕጋዊነት የሌለው እርምጃ በመዉሰድ ነበር። አንድም ግዜ በስርቆት ወይም በሌላ ወንጀል ሳይከሰሱ በእስር ቤት ዉስጥ ተይዘዉ ለወራት ታስረዉ ይባስ ብሎ ወደ የመጡበት በግዳጅ የሚመለሱት ስደተኞች ሁኔታ ነበር። የእስራቱ መልክ ደግሞ ልክ አንድ ትልቅ ወንጀል እንደሰሩ ነበር የሚያዙት። ያን ጊዜ አለም አቀፍ የሰብአዊ ጉዳይ ተሟጋች ድርጅት (Amnesty International) የአዉሮፓዉ ህብረት ስለ ስደተኞች ጉዳይ ያለዉን ፖሊሲ ወይም ፖለቲካ ማለፍያ ቢያደርገዉም በሌላ በኩል በድንበር ላይ የሚፈጸመዉን ድርጌቶች አውግዞ እንደነበር ይታወሳል። እንደዛም ሆኖ ስደተኞች ወደ የመጡበት አገር መመለሳቸዉን ሙሉ በሙሉ አይነቅፉትም ነበር። ይህንን አስመልክቶ በሰላማዊዉ ዉቅያኖስ በኩል አዉሮፓ የሚገቡት ስደተኞች ጉዳይ የተነሳ የሰበዓዊ ጉዳይ ተሟጋች ቢሮን ጥርጣሪ ዉስጥ ጥሎት ነበር። ስደተኛዉ ከለላ የጠየቀበት አገር መቆየት የሚችለዉ በፖለቲካ ጉዳይ ተፈላጊ ብቻ መሆኑ ከታወቀ እና የሰዉ ነፍስን ለማትረፍ የታሰበ ከሆነ ብቻ ነበር ድጋፉን የሚስጠው። ቢሆንም "አውሮፓ ከለላ የመስጠቱን ተግባር የመጀመርያ መርሆዋ ማድረግ አለባት" ብለው ተከራክረዋል። በዚያን ወቅት በአዉሮፓ ህብረት ሐገራት ለሚኖሩ ስደተኞች በተለይ ስፓኛ፣ ስዊዘርላንድ ወዘተ... ተገን ጠያቂዎች በስደተኛ ቢሮ ያስገቡትን ማመልከቻ ዉድቅ ሲደረግባቸው "ትክክል አይደለም" ብለው ነበር።
.
……....የውጪ ዜጋዎች ሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየተጣበበና እየተሸረሸረ የመጣው እንግዲህ የጋራ ድንጋጌ ህግ ሳይከተሉ የየራሳቸውን የውስጥ መመሪያ አውጥተው ሕገወጥ እርምጃቸውን በተግባር ላይ እንዲውል በማድረጋቸው ነበር። እንደውም አንዳንዶቹ ሀገር ከሰብአዊ ርኅራሄ ውጭ የሆነ መመሪያዎችን እንዲጸድቅ በማድረግ አስከፊ ድርጊት የሚፈፀሙም ነበሩ። ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹ ይውስዱት የነበረው እርምጃቸውን እስቲ እንመልከት፦
በግሪክ
……....ግሪክ ለመግባት በሚሞክሩ ስደተኞች ላይ ይፈጸም የነበረው ኢሰበዓዊ ድርጊት ወሰኑን ያለፈ ነበር። አንድ ሰሞን የባህር ወሰን ጠባቂዎችዋ ወደ ወደቧ የደረሱትን ስደተኞች እንደገና መልሰው ወደባሕር ይወረውሩ ነበር ተብሏል። ይህ ድርጊት በመመሪያዋ ላይ ባይኖርም "የፍልሰቱ ጥበቃ ስላልተሳካላቸውና ሁኔታው ተስፋ ያስቆርጣቸው የድንበር ጠባቂዎቹ በራሳቸው ውሳኔ የፈጸሙት ነበር" ተብሎ ተደባብሶ ቀረ። በሰፊው ያነጋገረና እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነበር። ነገሩም እንዲህ በቀላሉ የሚታለፍ ስላልነበረ ሕብረቱ አንድ እርምጃ እንዲወስድ በውጪ ሀገር ዜጋዎች የተደረገው ትልቅ ማኒፌስት ተደርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በእስጳኛ
……....1ኛ- እስጳኛ ባሕር ላይ የተገኙ አፍሪቃውያን እንዳሉ ተለቅመው ወደመጡበት እንዲመለሱ ታደርግ ነበር። 2ኛ- የፖለቲካ ተገን ጠያቂዎችን ከኢኮኖሚ ስደተኞች ለመለየት ሙከራ አድርግለች። 3ኛ- የባህር ጠረፎቿ ላይ ዘጊ አጥር አድርጋ የስደተኛን ጎርፍ ለመግታት ያደረገችው ሙከራ አልተሳካላትም። በተለይም የጂብራልተርን ሁለት ጎኖች በመዝጋትና የባሕር መስመሯ ላይ ማዕቀብ በማድረግ ርምጃ ወስዳ እንደነበር የሚታወስ ነው። 4ኛ- የስደተኛውን ጉዳይ ከሽብር ጋር እያዛመዱ አግባብ የሌለው እርምጃዎችን ይወስዱ ነበር። 5ኛ- በዚያን ጊዜ የነበሩት የፖለቲካ መሪዎቿ ጎርፉን ለመግታት ባለመቻላቸው የፖለቲካ ተገን የመጠየቁ መሠረታዊ መብት አስፈላጊ አይደለም ብለው የዓለማቀፉን የተገን ጠያቂዎች መብት ጥበቃ ውል የሚጻረር ሁኔታ ያሳዩ ነበር።
በስዊዘርላንድ
……....በስደተኛ አቀባበልና የኗሪነት ጉዳይ የሚመለከተዉን ህግ ለሪፈረንደም (ለህዝበ ዉሳኔ) አቅርበው ድምፅ ተሰጥቶበት ስደተኞችን ላለመቀበል ወስነው 1ኛ- የስደተኞችን የኗሪነት ህግ እንዲጠብቅ አድርገው ነበር። 2ኛ- ማንነታቸዉን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ያልቻሉ ስደተኞችን ወይም ከለላ ጠያቂዎችን ከአገራቸዉ የማስወጣት ስልጣን አግኝተው ነበር። 3ኛ- የአዉሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ዜጎች ያልሆኑት ወደ ስዊዘርላንድ መግባት የሚችሉት ለስራ ጉዳይ ብቻ እንዲሆን አድርገው ነበር። 4ኛ- ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ ወሰናችንን አጠናክረን እንዲጠበቅ የሚል ውሳኔ አስተላልፈው ነበር። ይህ በስዊዘርላንድ ስደተኞችን ላለመቀበል የወጣው ሕግ ወደ ሌሎች የአውሮፓ አገሮች እንዲዛመት መንገድ ከፍቶ እንደነበር ይታወሳል።
በጀርመን
……....የጀርመን መንግሥት የውጭ አገር ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የሚያደርገውን የውስጥ ሕግ ለማጽደቅ የሚያደርጉትን እሩጫ አሁንም ቀጥለውበታል። 1 - የመኖሪያ ፈቃድ በየጊዜው እየታደሰላቸው የሚኖሩ ቋሚ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ከአገር እንዲወጡ የሚለው ሕግ ተነስቶ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሆን አለበት ብለው እስካሁን በመከራከር ላይ ናቸው። (ብዙ ዓመታት የኖሩ የመኖሪያ መብታቸው እንዲረጋግጥላቸው በመማጸን ላይ የሚገኙ አያሌ ኢትዮጵያውያን አሁንም አሉበት) 2 - ባል ወይም ሚስት ጀርመን አገር ውስጥ ኗሪ እስከሆኑ ድረስ አንዱ ሌላውን ወደ ጀርመን የማስገባት መብት እንዳይኖረው የሚያግድ ሕግ ነበረበት። 3 - ከሚወጡት ሕጎች ላይ የጀርመንኛ ቋንቋ የሚያውቅ መሆኑን ማስረጃ ያላቀረበ ሁሉ ወደ ጀርመን መግባት አይፈቀድለትም የሚልም ነበረበት...
..... .....እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ አባላት ሃገሮች ስለፍልሰት ከተደነገገው የጋራ መመሪያ ውጪ ይወስዱት የነበረውን እርምጃ እንደምሳሌ ወስጄ ያቀረብኳቸው ናቸው። ከዚህ በታች ደግሞ እኛን ስለምታስጠልለን ሀገር "ኢጣሊያ" በዚያን ጊዜ የነበረውን እና አሁን ያለውን ሁኔታ እንመልከት...
በኢጣሊያ
……....የኢጣሊያ መንግስትም ከሰሜን አፍሪካ ሀገሮች የሚፈልሱትን ስደተኞች መልሶ ለማባረር በቆይታ እሥር ላይ (CPT) የሚያውል ነበር። ይኼ ስደተኞችን የማከማቸት ሁኔታ ለመጀመሪያ በጣሊያን እንጂ በሌሎች የአውሮጳ ሀገር ሲፈጸም አልታየም ነበር። የአሁኑም የኢጣልያ ዋናውና የመሀል ቀኙ መንግሥት የተያያዘው ወደ ኢጣሊያ ለመግባት በአመት ሃያ ሺህ እንኳን የማይደርሱትን የሶስተኛው ክፍለ ዓለም ስደተኞችን ቁጥር በማጋነን "ተወረርን እያለ ማስተጋባት ነው። "በሀገሩ ያልተመቸው ሁሉ ወደ አውሮጳ መግባት የለበትም" የሚል አቋም የአለው ነው። ይህ መንግሥት አማራጭና መፍትሄ ነው ብሎ የሚያምንበት ሕገወጥ መጤዎችን እስከሚባረሩ ድረስ ጊዜያዊ መቆያ ጣቢያ (CPT) ውስጥ የማጎሩንና የማባረሩን የሚለውን ያራምዳል። ይኸው እንደሚታየውም ጊዜያዊ መቆያ እያከማቸ ከመቼውም በበለጠ መልሶ የማባረሩን ርምጃ ለመጀመር እየተዘጋጀበት ነው። እስከሚባረሩ ድረስ በመስፈሪያ ጣቢያ የሚያቆዩበትን ቀናት የተወሰነ እንዲሆን አድርገዋል። የስደተኞች ማከማቻ መፍጠርና መገደብ ለነገሩ ተቀባይነት ቢያገኝም እንኳን እርምጃው መውሰዱ ብቻ በአውሮፓ ጸንቶ የቆየውን የስደተኞች ተገን መብት ከመሠረቱ ሊለውጥ የሚችል ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ኢጣሊያ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ clandestini ወይም ሕገወጥ ስደተኞችን ወደ መጡባቸው ሀገሮች ትመልሳለች ከተባለ በአዳጋቹ የመርከብ ጉዞ ላምፔዱዛ የደረሱት ሁሉ ጉዳያቸው ሳይታይላቸው ሊባረሩ ይችላሉ። የትውልድ ሀገራቸውን ትተው የመጡበት ምክንያት ረሃብንና ጦርነትን ሸሽተው ወይም በፖለቲካ ምክንያት ተባረው ነፍሳቸውን ለማዳን የመጡ ሊሆን ይችላል። እንዚህን ደግሞ ወደመጡበት መመለስ ማለት ለሞት፣ ለአስጨካኝ ሁኔታዎችና ኢሰበአዊ ድርጊት መዳረግ መሆኑን የተገነዘቡ አይመስሉም። ይህ ሁኔታ አለማቀፋዊ መብት አስጥባቂውን ክፍልና የውጪ ዜጋዎች ብርቱ ቁጣን ቀስቃሽ እንደሚሆን አይጠረጠርም።
.
……....ከድህነት ለማምለጥና የተሻለ ኑሮ ሕልማቸውን ዕውን ለማድረግ አገራቸውን ለቀው ከሚሰደዱት መሀከል ባሕር ውስጥ እየሰጠሙ ማለቃቸውም አሁንም ቢሆን የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። የሜዴትራኒያን ባሕር ተዋሳኝ ከሆኑት የማግሬብ አገሮች፤ ከሊቢያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ ወዘተ…ተነስተው ውቂያኖሱን በጀልባ በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመዝለቅ የሚሞክሩት አፍሪቃውያንና የመካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች ተገን ለማግኘት ያላቸው ዕድል የመነመነ ሆኖ ነው የሚገኘው። ሌላው ችግር ደግሞ በአውሮፓ ውስጥ ከብዙ ጊዜ ተቀማጭ የነበሩ ሆነው እስከዛሬ ድረስ የተገን ማመልከቻቸው ተቀባይነት አጥቶ "ዛሬ ነገ ልንባረር ነው" ሲሉ ኑሮአቸውን በሰቀቀን የሚገፉት ስደተኞች ጥቂቶች አይደሉም። በዚሁ የአዲሱን የአውሮፓ ድንጋጌ ምክንያት ያላቸው ተስፋና መጨረሻቸው ምን ይሆን?... በዚህ ሰሞን ደግሞ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ከሰሜን አፍሪቃ የባህር ዳርቻ በትንንሾቹ መርከቦች በሜድትሬንየን ባህር ወደምትገኘዋ የኢጣልያ ደሴት ላምፔዱዛ መጓዝ ይዘዋል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በመርከብ መስመጥ አደጋ ቁጥራቸውን መገመት ያልተቻለ የመርከቡ ተሳፋሪዎች ሕይወታቸውን አልፈዋል። ጉዞው ተሳክቶላቸውና ከሞት ተርፈው የደረሱትን የላምፔዱዛ ስደተኞች መቀበያ ጣቢያዎች ሞልተዋል የስደተኞቹ መቀበያ ጣቢያ ከሺህ በላይ የሚይዝ አይደለም ስለተባለ ስደተኞቹን ወደ መሀል ሀገር ማሰበጣጠር ተጀምሯል። ማስፈሪያ ጣቢያ ጥቂት ጊዜ አቆይቶ ወደየመጡበት ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
.
……....የሀገር ውስጥ አስተዳደሪነትን ያህል ታላቅ ሀላፊነት የተሸከሙት ሮቤርቶ ማሮኒ እንኳን ሳይቀሩ “ሕገወጥ ስደተኛነት እንደወንጀል የሚቆጠር ነው” እያሉ በአደባባይ አሁንም የሚከራከሩ ናቸው። ወንጀለኞች ከተባሉ በአሁኑ ጊዜ በኢጣሊያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው የመኖሪያ ፈቃድና ቤት የሌለው ወንጀለኞች ናቸው ማለት ነው። ታዲያ እንደ ወንጀለኛነታቸው እስርቤት መግባት ሊኖርባቸው ነው? የትኛው እስር ቤትስ ነው ይህንን ሁሉ የሚይዘው? ይህ እንግዴህ ከዚህ በፊት ይሰራ የነበረውን ግን አሁን የስራ ኮንትራቱን ጨርሶ ሌላ ስራ ለመቀጠር በመፈለግ ላይ እያለ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሶጆርኖው የሚታደስለት ካልሆነ በድንገት የመንገድ ላይ ቁጥጥር ከተገኘ እንደ ወንጀለኛ እየተቆጠረ ሊታጎር ነው ማለት ነው። ከታጎረ ደግሞ ከሀገር መባረሩ ማለት ነው።
.
……....ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚቀመጡ እንደወንጀለኛ የመቆጠራቸው ጉዳይ ላይ (il reato di clandestinità) ብዙ ታዛቢውችና የአውሮፓ የፖለቲካ ሰዎች ትችት አድርገውበታል። በተለይ የስፓኛ መንግስት መሪ የሆኑት ዛፓቴሮ ስለአሁኑ የኢጣሊያ መንግስት በውጪ ዜጋዎች ላይ ያላትን አቋም በመቋወም ተችተው ነበር። "አሁን እየታዬ ያለው የዘረኛነት ጉዳይ ነው” ነበር ያሉት። የኢጣሊያ ጠ/ሚ ሲልቪዮ በርሉስኮኒ መልስ በሰጡበት ጊዜ ሊያስተባብሉ ሞክረው ነበር… ይኸውም “እንደኔ ከሆነ በሕገወጥ ጣሊያን የሚገቡትን፣ መኖርያ ፈቃድ ያላገኙትን፣ ሥራና መተዳደሪያ የሌላቸውን በሙሉ ወንጀለኞች ናቸው ለማለት ባልደፍርም ወንጀል ነክ በሆኑ ሁኔታዎች ላይ ለመጋለጥና አማካይ ሊሆኑ ይችላሉ ነው የምለው” ብለው ተናግረዋል። በመቀጠልም “ኢጣልያ በአሁኑ የአገዛዝዋ መርህ መሠረት የውጪ ዜጋዎች እዚህ መምጣትና ሥራ መሥራት የሚችሉት ጣሊያን ከመግባታቸው በፊት የሥራ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው። ወደፊትም ችሎታን መሰረት አድርጎ ብቻ ይሆናል ወደዚህች አገር ለመምጣት የሚቻለው። የሚመጡት በሙሉ ከመነሻ ሀገራቸው ማመልከቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከሁሉ በፊት ግን ምን ዓይነት ችሎታ ይዘው እንደሚመጡ ይታያል። ከዚያም ከአመልካቾች መሀል ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ብቻ መግባት ይፈቀድላቸዋል፣ ለትምህርትና ለከፍተኛ ምርምርና ጥናት ተካፋዮችም ማመልከቻቸው ተጠንቶ መሆን ይገባዋል" ነው ያሉት።
.
……....በአውሮፓ ዙሪያ ብቻ ለተሻለ ስራና ኑሮ የትውልድ አገራቸውን ለቀው የተሰደዱት ህዝቦች ቁጥር 40 ሚሊዮን ነው ተብሎ ይገመታል። ከእነዚህ ስደተኞችም አብዛኛዎቹ በተሰደዱበት አገር አነስተኛ ክፍያ በሚያስገኙና ዜጎች በማይፈልጉዋቸው ስራዎች ተሰማርተው ነው ህይወታቸውን የሚገፉት። በተሰደዱበት ሁሉ አድልዎና መገለልም የዕለት ዕጣቸው ነው። ብዙዎቹ ስደተኞች ህጋዊ የተባሉትም ሳይቀር እንደሀገሩ ዜጎች የስራ ዕድል አይኖራቸውም። ዜግነት ስለማይኖራቸው የስራ ሽሚያውም አይመለከታቸውም። በዲሞክራሲ መርሆ እንደሚመራ የሚነገርለት የምዕራባውያኑ ማኅበራዊ ኑሮ ለዘርና ለቀለም ልዩነት የተጋለጠ መሆኑ፣ የባህልና የሐይማኖት ልዩነቶች አልፎ ተርፎ ግጭት የሚፈጥሩ መሆኑ ...ውዘተ… እንግዴህ እነዚህ በአንድ ሀገር ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ነገር ግን ከእነዚህ መሀከል የሚከፋው የዘርና የቀለም ልዩነት ማቆጥቆጥ መታየቱ ነው። የገዢው የፖለቲካ በለስልጣናት በእነዚህ አብይ ጉዳይ ላይ ያላቸው አስተያየት “ሁኔታው ይትኛውም አውሮፓ ሀገር ውስጥ አልፎ አልፎ የሚከሰት በመሆኑ ይህን ያህል አሳሳቢ አይደለም” ብለው መደፋፈን ብቻ ነው። ብዙዎቹ የአውሮፓ ሀገራት ልዩ ልዩ ባህሎች ተቻችለው የሚኖሩበት ሁኔታ (integrazione) እንዲፈጠር ጥረት ሲያደርጉ ኢጣሊያ ግን ፈልሰው የገቡትን ከህብረተሰብ ጋር በቀላሉ እንዲዋሀዱ ምንም ጥረት አላደረገችም ማለት ይቻላል። ያለመዋሀዳቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ስደተኞች የራሳቸውን ባሕልና ልማድ ይዘው ስለሚገቡ ከባህሎቻቸው ጋር ተቻችለው የሚኖሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መዋቅር አለመጣላቸው ነው።
……....ወደ አዉሮፓ ለመግባት በባህርና በድንበር ሾልከዉ ሲገቡ ወይም ለማምለጥ ሲሞክሩ “ህገወጥ” እየተባለ በተደጋጋሚ የሚያሳየዉ የቴሌቭዝን ሆነ የራድዮ ዘገባ ሲሰራጭ በህብረተሰቡ ጭንቅላት ውስጥ ተቀርጾ አስተሳሰቡን እንዲለውጥ አድርጎታል። ስለስደት (Immigrazione) በበጎ መታሰቡም ሆነ መወራቱ እየቀረና መጥፎ ዝንባሌን እየታየ ነው። ሌላው ደግሞ ስለስደት ጉዳይ ሲነሳ ሁልግዜ ከጥበቃ እና ከጸጥታ ፖለቲካ ጋር ያያይዙታል። በዚህም ሰበብ ስደትን ከህግ ውጪ የሆነ ሁኔታ ጋር ብቻ ማያያዝ ጀምረዋል። ያ ማለት ስደተኛ የሚለዉ ቃል ከለላ ጠያቂ የሚለዉ ትርጉም መሰጠቱ ይቀርና ከህግ ውጪ የሆነ ዜጋ ይሆናል ማለት ነው። በዚህም ምክንያት በውጭ ዜጋዎች ላይ ያለው አመለካከት መቀየር እንደጀመረና አዝማሚያው ከዕለት ወደ ዕለት ወደጥላቻው እንደሆነ በገሀድ ይታያል። ብዙዎች የውጪ ዜጎች እራሳቸው በሕብረተሰቡ ውስጥ እንደወንጀለኛ የሚታዩና የሚጠረጠሩ እየመሰላቸው በስራ ላይም ሆነ በሚገኙበት ቦታ ስሜታቸውን አገልለው፣ እራሳቸውን ወደታች አውርደው ነው የሚገኙት። ከስራ የመባረር ፍርሃት ስላላቸው ህመም ላይ እንኳን ቢገኙ ልህክምናም ሆነ ለእረፍት ፈቃድ ስለማይጠይቁ ጤናቸውን እስከሚያጡበት ድረስ የሚደርሱ አሉ። ከዚህ የስደተኛው መሪር ኑሮ ላይ የብቸኝነት ስሜት ሲጣመር ብዙዎቹ የአእምሮ ህመም ውስጥ ገብተዋል። በአጠቃላይ ባለማወቃቸው የሚጠቁ ዜጎች ናቸው። ስለሆኑም ለትምህርትና ለጥንቃቄ አንዲሆናቸው የሚያውቁና ልምድ ያላቸው ምን ማድረግ እንደሚችሉ በማሳወቅ መረዳዳት ይገባናል።
.
……....የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መብት ጥበቃ ውል ከተፈረመ ሃምሣ ዓመታት አልፎታል። ይህም ውል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለስደት ለዳረጋቸው አውሮፓውያን ዕርዳታና ተገን ለመስጠት በጊዜው የተደረገው ጥረት ውጤት ነበር። ጀኔቫ ላይ ተቀማጭ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ መርጃ ተቋም አፈ-ቀላጤ ሩፐርት ኮልቪል መለስ ብላው እንደሚያስታውሱት ውሉን የተለየ ትርጉም የሚሰጠው በታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስደተኞች መብት ጥበቃ ዓለምአቀፍ ጽናት ያለው ሕግ ለማስፈን መብቃቱ ነው። ይህ ደግሞ ወሣኝ ጉዳይ ነበር። የስደተኞች መብት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊከበር የሚችለው የዓለም መንግሥታትን ግዴታ ላይ የሚጥል የጥበቃ ዋስትና ሲኖር ብቻ በመሆኑ። ይህ ሃቅ ትናንት ጽናት ነበረው። ነገር ግን ዛሬ ይኖረዋል ወይ?

……....የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ መብት ጥበቃ ውል በመጀመሪያ በአውሮፓ ብቻ ጸንቶ ከቆየ ከ16 ዓመታት በኋላ እ.ኢ.አ. በ1967 ነበር በዓለምአቀፍ ደረጃ ሊጸና የበቃው። እስከዛሬ 140 የዓለም መንግሥታት ሲያጸድቁት በጅምሩ ውሉ ላይ የሰፈሩት መሠረታዊ አንቀጾች፤ ለምሳሌ ያህል “ ስደተኛ ” የሚለው ቃል አተረጓጎሙ ራሱ ዛሬ ሳይቀየር እንደጸና ነው። በዚሁ ውል መሠረት ስደተኛ ተብሎ የሚቆጠረው በዘር፣ በሃይማኖት፣ በነገድ፣ በማሕበራዊና በፖለቲካ አሰላለፉ የመሳደድ ጭብጥ ፍርሃቻ ስላለው አገሩን መልቀቅ የተገደደ ማንኛውም ዜጋ ነው። "የትኛውም ስደተኛ አደጋ እስካለበት ድረስ ያለውዴታው ወደ ትውልድ አገሩ መጋዝ የለበትም” የሚለው አንቀጽም አንዱ እጅግ ጠቃሚና መሠረታዊ ዓላማ ሆኖ ይገኛል። ስደተኞች ተገን አግኝተው በሰፈሩበት አገር የመሥራት፣ ነጻ ሆኖ የመንቀሳቀስ፣ የትምሕርትና የሃይማኖት ነጻነት አላቸው" የሚለውም በማያሻማ ሁኔታ በአንቀጽ የተቀመጠ ነው። ነገርግን አሁን በዚህ ሳምንት በአውሮፓ የተደነገገው ይህን ሁሉ ሊገፋ የሚችል ነው።
……....እርግጥ ዛሬ የስደቱ መንስዔ ምክንያትም ሆነ የፈለሣው ባሕርይ ከቀድሞው እጅግ እየተለወጠ መጥቷል። ከሃምሣ ዓመታት በፊት የጀኔቫው ውል ሲሰፍን በመሠረቱ ያተኮረው በፖለቲካ ምክንያት በሚሳደዱ ተገን ፈላጊዎች ላይ ነበር። ዛሬም ቢሆን የፍትህ-አልባው የአገዛዝ ዘይቤ በፈጠረው ችግርና የፖለቲካ አመለካከታቸው የሚሳደዱ አይጥፉ እንጂ አብዛኛው ስደተኛ በረሃብ፣ በጦርነት እንዲሁም በኤኮኖሚ ችግር እየተነሣ አካባቢውን እየለቀቀ የሚፈልስ ሆኗል። ታዲያ አሁንም ቢሆን ቢያንስ ቢያንስ ሁለቱን የስደት ምክንያቶች የሚለያያቸውንም ሆነ አንድ የማያደርጋቸውን ጽንሰ ሃሳቦች በሚገባ በማጤን ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት መጣሩ የግድ ይሆናል። ጉዳዩ የሚመለከተው የበላይ ባለሥልጣን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ተቋም በአንድ በኩል መሠረታዊ ዓላማው እንዳይዛባ መታገልና በሌላ በኩል ለምሳሌ በአውሮፓ ሕብረት የተለወጠው ሁኔታ ላይ ያጤነ ተልዕኮውን መወጣት ይጠበቅበታል። ጉዳዩ ውስብስብ ሊሆን ይችላል። የሆነው ሆኖ ግን የስደተኞች ሰብዓዊ መብት ዛሬም ነገም እንደትናንት ሁሉ ሊታጠፍ የማይገባው ጉዳይ ነው።
……....የሰው ልጅ ክብር፣ መብት፤ ነጻነትና ፍትህ የዓለም የሰላም መሠረቶች ናቸው። ይህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ 1948 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ቻርታ ላይ ሰፍሮ የሚገኝ ነው። እነዚህ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ለዓለም ሕብረተሰብ ልማትና አብሮ መኖር መርሆች ሆነው መቀጠል አለባቸው። እነዚህን መንፈግ የሰውልጅን የሕልውና መሠረት ማሣጣት ነው። ሆኖም አሁንና ወደፊት ከብዙ ፍትህ-አልባ ሁኔታዎች መታየት ተነስቶ የተፈጠረው ይህ ድንጋጌ መልሶ የተረሣ መሆኑን ስለሚያሳይ ዛሬ የነጻነት መብቶች አደጋ ላይ ወድቀው ነው የሚገኙት። ዓለም ከመቼውም በላይ በተሳሰረበት በዛሬው ጊዜ የሰብዓዊ መብት ከበሬታ መርህ ሊሆን በተገባው ነበር። አዝማሚያው በምድራችን ላይ በሰላም አብሮ መኖር የሚቻልበት ሁኔታ እንዲያብብ አያደርግም። የዜጎች የፖለቲካ፣ ማሕበራዊና ሰብዓዊ መብቶች፤ የሃሣብ፣ የሰላማዊ ሰልፍ ነጻነት፣ የነጻ ምርጫ፣ የአካል ደህንነት ከበሬታ መብትና የማሰቃየት እገዳ፣ ወይም የምግብ፣ የትምሕርት፣ የመኖሪያን፣ የኤኮኖሚና የማሕበራዊ ዋስትና መብቶች፤ ከዚያም አልፎ በቆዳ ቀለም፣ በጎሣም ሆነ በጾታ የሚደረገውን ልዩነት የሚያግዱት መብቶች የአንድ መንግሥት ዕርምጃ መሠረት ሊሆን ይገባዋል።
……....በአውሮፓ ለፖለቲካም ሆነ ዛሬ በተለይ ቁጥራቸው ለተበራከተው የኤኮኖሚ ስደተኞች ጎርፍ ማየል ምክንያቱ ጭቆና፣ ድህነትና የልማት ዕጦት መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ይታወቃል። ለነገሩ የበለጸገው ዓለም በታዳጊ አገሮች ላይ የተጫነውን ዕዳ በማቃለል ለልማት አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥር በተደጋጋሚ ቃል ገብተው ነገርግን በጣም ጥቂትና የተወሰኑ ሀገሮች ጅምሮችንና ተሳትፎዎችን ሲያደርጉ ይታይ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት የሚሌኒየምን ዕቅድ ከፍ አድርጎ ያስቀመጠው የታዳጊ አገሮችን ልማት በማፋጠን ድህነትን በተወሰኑ ዓመታት በከፊል የመቀነሱን ዓላማ ነበር። ይሁን እንጂ ቃልና ተግባር የሚጣጣሙ ሆነው አልተገኙም። የዕዳ ምሕረቱን ጉዳይ ካነሣን አይቀር ይህ ከንቱ ውዳሴ መሆኑን የሰባቱ በኤኮኖሚ ልማት የበለጸጉ ቀደምት መንግሥታት የ G-8 መሪዎች ጉባዔ እንደገና አሣይቷል።
……....በአውሮፓ የኤኮኖሚ ስደተኞችን ጎርፍ ለመግታት ከተፈለገ እነዚሁ በሚመነጩባቸው አገሮች ጦርነትና ረሀብ እንዲወገድ፣ ሰብዓዊ መብቶች በውል እንዲከበሩ የዓለም ሕብረተሰብ መነሣት ይኖርበታል። ሕብረተሰባዊ ሰላምና የኤኮኖሚ ዕድገት ገሃድ መሆን እስካልቻለ ድረስ አሁንም ወደፊትም ስደተኛ ይኖራል። ወደ ምዕራቡ ዓለም የሚደረገውም ፈለሣ በየጊዜው መልኩን ይለዋውጥ እንደሆን እንጂ ቀጣይ ነው የሚሆነው። በየአካባቢው ማጎሪያ መሰል ሰፈር ማነጹ ስደተኞችን ከራስ ደጃፍ በማራቅ መፍትሄ ይገኛል ብሎ ማሰቡ ከንቱ ነው። እንዲህ ከሆነማ ዴሞክራሲ ሕብረተሰብ ነው ተብሎ የሚጠራው የምዕራቡ ሕብረተስብ ሞራል መስፈርት የሚጣጣምም አይሆንም።
……....ያለንበት ዘመን ዓለም ዓቀፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር ዘመን ስለሆነና ጊዜው የነፃ ገበያ ወቅት በመሆኑ ህዝቦች ከአንዱ አገር ወደ ሌላው ለስራ መሰደዳቸው ጤነኛ አካሄድ ነው። አውሮፓውያን መሪዎችና ፖለቲከኞች ስደተኛውን እንደ አደጋ ሳይሆን ጠቃሚ የልማት አስተዋፅኦ ሊያበረክት የሚችል ሀይል አድርገው መመልከት ይገባቸዋል። እራሳቸውም ቢሆኑ በተወሰኑ ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። ለምሳሌ በአስርና በአስራ አምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ እየቀነሰ እንደሚሄድ የሚገመተው ህብረተሰብ የሚተካው የሰራተኖች ጉዳይ ማስነሳቱ አልቀረም። በጉዳዩ ላይ የዓለም ስራ ድርጅት ኤክስፐርቶች አስተያየታቸውን እንደሰጡት "ወደፊት የተተኪው ትውልድ ቁጥር መቀነስ ችግር አሁኑኑ መፍትሄ ሳይበጅለት እንዳለ ከተተወ በመጪው ሀምሳ ዓመት ውስጥ የህዝቡ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን ካለው በሀያ ከመቶ ይቀንሳል" ብለው ነበር።

ክፍል 2


……....መቼም ስደት ስለሚያስከትለው መሪር የህይወት ገፅታ በደንብ ሊናገር የሚችለው ያው ራሱ በችግሩ ሰለባ የሚገኘው ስደተኛ ነው። የተወለድንበትን፣ ያደግንበትን፣ የደስታም ይሁን የሀዘኑን ለዛ ያጣጣምንበትን ሀገርና ወገንን ጥሎ መሰደድ ማለት ከውሳኔዎች ሁሉ የከፋ ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በባዕድ ሀገር ተበትነን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰባችን መሀል ተነጥለን ሀገራችንን ለቀን የተሰደድነው ያለአንዳች ምክንያት እንዳልሆነ ይታወቃል። ይደላናል ወይም ሀብት እናተርፋለን ብለን አይደለም። በተለይ በኢኮኖሚ ወደ አደጉት አገሮች ለመኖር ስንነሳ እያንዳንዳችን የምናልመው ነገር ይኖራል። እውነታው ካልተካደ በስተቀር ለአብዛኞቻችን ሠርተን ራሳችንን ችለን የቀኑ ነፍስ ወከፍ ገቢያቸው አንድ ዶላር እንኳን የማይሞላላቸው፣ ከኑሮዋቸው ጋር ግብግብ ለሚገጥሙት ቤተሰቦቻችን ከአለችን ቆንጥረን የመኖር ዋስትና እንዲኖራቸው ለመጦርና የዕለት ጉርሳቸውን እንዳያጡ ለማድረግ ነው። በረሃብ፣ በጦርነት፣ በጭቆና፣ በድህነት፣ በመብትና የልማት ዕጦት የተነሣ አካባቢውን እየለቀቅን የምንፈልስም አለን። እየሠራንም ቢሆን ትምህርት ለመማርና ከተዋጣልን ደግሞ ተመልሰን በእውቀታችንና በጉልበታቸው አገራችንን ለማሳደግ የምንሽም እንገኝበታለን። ሌሎች ደግሞ ግብና ዓላማ ሳንይዝ “መች ቪዛ አግኝተን ከሀገር በወጣን” ብለን የምናልም በሀገር ቤት ያለን የአሁኑ ትውልድ ዜጋዎች ብዙ ነን። በወጣት እድሜያችን በዚህ ፀለምተኛ ህልም መወጠራችን የሚያሳየው ምን ያህል ጨለማ የሆነ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ መገኘታችንን ነው። ከድሃዋ ሀገራችን ወደ ተትረፈረፋቸው አገሮች የምንጓዘው የተሻለ ሕይወት ስለምንመኝም ይሆናል። ይሁንና እዚህ አገር ስንደርስ ሁሉነገሩ እንዳለምነውና እንደተመኘነው ሳይሆን የተገላቢጦሽ ይሆንብናል። በጣሊያንኛው «ሶቶ ሶፕራ» እንደሚባለው ማለት ነው። ይኸው የመጣንባት አገር ከአፍሪካና ከእስያ በመጡ ስደተኞች ተጥለቅልቃ እናያለን፣ እዚህ እንደደረስን እጅ መስጠት፣ የተሰደድንበትን ምክንያት መናገር፣ ቆይቶም "አገር ለቀህ ውጣ!" መባል፣ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌለን ስራ መከልከል፣ ወደ አልፈለጉት ቦታ መመደብና... ብዙ የተለያዩ አስቀያሚ የሆኑ ገጠመኞች የሚከሰቱ ሆነው እናገኛለን። እነዚህን በመሳሰሉት ምክንያቶች ወደ አውሮፓ ሀገሮች በመፍለሳችንም “የኢኮኖሚ ስደተኞች” የሚል የወል ስም እንዲሰጠን አደረገ። “የኢኮኖሚ ስደተኞች” ተብለን በመጠራታችን የሚሸነቁጠንና ህሊናችንን እንደጦር የሚወጋ ቢሆንም በከፊል እውነትነት ያለው ነው። ትላንት የሰው ዘር መገኛ፣ የሥልጣኔ አሀዱ፣ የታሪክ መቅድም፣ የተፈጥሮ ሀብት አምባ የነበረችው ሀገራችን ዛሬ የድርቅና የርሀብ ተምሳሌት ተብላ በመኮነኗ ዘመን በማይከትረው የስደት ባቡር ተሳፍረን መንጎድ እንደቀጠልን ስለሆነ።
……....ዛሬ ባህር ማዶ ተሰደን መሪር የህይወት ገፈት የምናጣጥመው አንሶን ስብዕናችን በገዢው መንግስት ወንበር ላይ በተቀመጡ ሹሞች መዳፍ ስር ወድቋል። የስብዕናችን በአደጋ ላይ ውሎ ማደሩ “ኧረ የሕግ ያለህ“ ብሎ የሚያስጮህ ነው። የአሁኑ የኢጣሊያ ገዢዎች ብዙሃኑን የያዙና ዋናውን የፖለቲካ ክፍል ሸፋኞች በመሆናቸው ርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁበት ያለው የስደተኛውን ሰብአዊ ክብር የሚነካ መልክ የአለው ነው። ብዙ አመት ተቀማጭ ለሆኑትም እንኳን ስጋት ላይ የሚጥል ሆኖ ይገኛል። ከእንግዲህ ወዲህ የመኖሪያ ፈቃድ (ሶጆርኖ) ለማግኘትና ለማሳደስ ያስገባነው ማመልከቻ አንቀበለውም "አገራችንን ለቃችሁ ወጡ” የሚል የውሳኔ በትር ልያርፍብን ይችላል። ወይም ስራ ከሌለን ዶኩሜንት ከሌለን “ወደ ዘብጥያ (CPT) ውረዱ” ልንባል ይችላል። አንዴ ከወረድን ደግሞ ከሀገሪቷ መባረራችን ነው። “ለምን?” ብለን ብንጠይቅ “ይህን ሁሉ የምናደርገው በአውሮፓና በሀገሪቷ ሕግ መሠረት ነው” የሚል መልስ ሊሰጠን ይችላል። ታዲያ! ይህች እኛን የምታስጠልለን ኢጣሊያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታህሳስ 10 ቀን 1948 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፀደቀውን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌን ፈርማ አልተቀበለችምን? እናስ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ይህንኑ ድንጋጌ የሚጥሱ አይደሉምን?
……....በዚያን ጊዜ ፀድቆ የነበረውን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ለመጥቀስ ያህል…
…….... (እስርን በተመለከተ) ፥ አንቀፅ 9 “ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊያዝ ሊታስር ወይም ሊጋዝ አይችልም”
…….... (የመስራት መብትን በተመለከተ) ፥ አንቀፅ 23 “1. ማንም ሰው ስራ የመስራት፥ ስራውንም በነፃነት የመምረጥ፣ በትክክለኛና በአመቺ የስራ ሁኔታ ውስጥ የመስራትና ከስራ አጥነት የመዳን መብት አለው”
……....እንግዲህ እውነታው ይሄ ነው። ስለዚህ እኔ የምለው እንደነዚህ ባሉት ጠቃሚ የሆኑ የሰበዓዊ መብት የሕግ ጽንሰ ሃሳቦችና አንቀጾች ላይ ተመርኩዞ መከራከር ይቻላል ነው። ይህም መንግሥት የስደተኛውን መብት እንዲያከብር እነዚህን የመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ሕግጋት ያስገድዱታል። ባለንበት ክፍለ ዘመን ሰዎች ከዚህ ዓለም አቀፍ ህግ በላይ ጎልተው መታየት አይችሉም። አስካልታዩም ድረስ የሕጉን ልዕልና ክብር ማንም ሊነፍገን አይችልም። ሁላችንም ልንጎናጸፈውና ልንገዛበት የሚገባ ሕግ ነው። በዚህች የዲሞክራሲ ሰገነትና የሰብአዊ ርህራሄ ምድር እንደሆነች ይነገርላት በነበረችው አውሮጳ ውስጥ ያለን ስደተኞች ከእንግዲህ ወዲህ የሚደነገጉት መመሪያዎችና ሕጎች እልባት የማይኖራቸው፣ የሰውን ክብር የሚነኩ በመሆናቸው ከሕግና ከሥርዓት ውጭ በደል ሊፈጸምብን ስለሚችል ከአሁኑ አቤቱታችን እንዲያይል መሆን አለበት። እንግዲህ እዚህ የምንገኝ የአውሮጳ ስደተኞች የሆንን ሁሉ የምዕራብ አውሮፓ አገራት የስደት ፖለቲካዎች አመለካከት እየተቀየረ የመምጣቱ ግዳይ ላይ ግንዛቤ እንዲኖረን ይገባል። ሰብዓዊውን መከራ ለመግታትና መብታችንን ለማስከበር ድምፃችንን ማሰማት እጅግ ተገቢ ነው። እርምጃው በዚህ ብቻ ማብቃት የለበትም። በስደተኞች ላይ እያረፈ ያለውን የጥቃት በትር እንዲነሳና የዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ የሰፈሩትን የሰበዓዊ መብቶች እንዲያከበሩ ድምጻችን ይሰተጋባ። ብቻችንን ሳንሆን የችግሩ ሰለባ ከሆኑት የውጪ ዜጋዎች ጎን በመሰለፍ ጉዳዩን የዜና ማሰራጫዎች እንዲዘግቡልን በማድረግ፣ ከስደተኛ መብት ተቆርቋሪ ከሆኑት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ካለማለስለስ እንዲገነዘቡ አድርጎ በስደተኞች ላይ እየተካሄደ ያለውን ፖሊሲ እንዲቃወሙትና እንዲያስቀይሩት በማድረግ እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አማካይነት የህግ በላይነት እንዲከበር አጥብቀን እንጠይቅ።
……....በጣሊያን ውስጥ ያለነው ኢትዮጲያውያን ስደተኞች ታሪክ ውስጥ ድምጻችንን ስናሰማ ይህ የመጀመሪያችን ጊዜ አይደለም። ከዚህ በፊት በመብት ጉዳይ ላይ በመትመም የተቃውሞ ድምፃችንን ያሰማንበት ጊዜያት አሉ። አንድ ምሳሌ ሊሆን የሚችል… በቅርቡ በፓርማ ከተማ ተገን የጠየቁ ወጎኖቻችን መጠለያ ታገኛላችሁ ተብለው ብዙ ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩት ነገርግን እስካሁን ያላገኙ ኢትዮጲያውያንና ኤርትራዊያን በይሉኝታ ሳይታጠሩ አደባባይ ወጥተው ያደረጉት ማኒፌስት ምሳሌ የሚሆን ነው። ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ትክክለኛ ፍትሃዊ ብይን አስካሁን ስላላገኙ... ምንጭ … አንድ / ሁለት / ሶስት ። ሕብረት ያላቸውም ሌሎች የውጪ ሀገር ዜጋዎች ለመብታቸውና ህልውናቸውን ለማስከበር ያደረጉትን ለምሳሌ ያህል በአለፈው ወር የባንግላዲሽ ዜጋዎች ከሰራተኛው ተወካይ ማህበራትና ከግራው ክንፍ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር አንድ ላይ ሆነው አደባባይ በመውጣት ያደረጉት ማኒፌስት ሌላው ምሳሌ ነው። ሌሎችም መጥቀስ ይቻላል... እናም የወቅቱ ጥያቄ የሚያንገበግብ በመሆኑ ከሌሎች የውጪ ዜጋዎች ጎን ሆነን መታገልና የስደተኛውን መብት አስከባሪ ሆነው ከሚታገሉ ክፍሎችም ተጠግተን አምርሮታችንን እናሳይ። ዛሬ በኢጣሊያ ያሉ የውጪ ሀገር ዜጋዎች ማህበራት በስደተኛው ጉዳይ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አስቆጥቷቸው በግንባርም ይሁን በሰላማዊ ሰልፍ ጩኸታቸውን እያሰሙ ነውና ልንተባበራቸው የግድ ይለናል። ገዢው መንግስት ጫናና ግፊት የሚያደርገው ሀገር ለቀው ይውጡ የሚባሉት ህገወጥ ስደተኞች ላይ ብቻ አይደለም። ለተለያዩ ጊዜያት ቆይታ ያደረጉትም ነገርግን ሥራ ወይም ዶኩሜንት የሌላቸው በቅርቡ ከመጡት ጋር ተደባልቀው የእርምጃቸው ሰለባዎች ሊሆኑ ይችላሉና።
……....በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ እየዘነበ ያለውን የችግር ዶፍ ለማቆም ዝግጁ ለመሆን ከተፈለገ የሁላችን ህብረት ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ አለብን። ብሕብረት እንድንሰለፍ ከተፈለገ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ክፍትና አሰባሳቢ ማዕከላዊ መድረክ ያስፈልገናል። በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰፊው ለመምከር በኢትዮጲያ ኮሙኒቲዎች አስተባባሪነት በተለይ የኢትዮጵያዊያን ቁጥር በርካታ በሆነባቸው ከተሞች እንዲደራጁና ጉባዔዎችን በመጥራት ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ለመነጋገር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
……....ይህንን የምናደርገው ኢጣሊያ ውስጥ የስደተኛው ጥያቄ የሚታይበት አሰራር ድብቅ በመሆኑ፣ እንዲሁም ስደተኞች ለመብታቸው ለመከራከር እንዳይችሉ በቢሮ አሰራር እንጂ በፍርድ ቤት የሚታይ ባለመሆኑ እና ይህንን የአለም አቀፍ ሕግ የጣሰ አሰራር ላለመቀበል “አሻፈረኝ” ለማለት ነው። ይህንን የምናደርገው በሀገረ ኢጣሊያ ማን እንደሚባረር ማን እንደሚቆይ የሚወስኑት የጊዜው ሹሞች ይህ ስደተኛ መጠጊያና ከለላ አጥቶ በሚንከራተትበት ሰዓት ሰብአዊ መብቱን፣ ክብሩንና ህልውናውን በመንካት እንደ ወንጀለኛ ማሰራቸው አስቆጥቶን ነው። ይህንን የምናደርገው እየደረሰ ያለው ጫና እየከፋ መሄዱ፣ ወገኖቻችንን ያለምግብና መጠለያ የሚያስቀሩ ውሳኔዎች እየበዙ በመሆናቸው፣ መጠሊያ በማጣት ከመሬት በታች በሚገኙ ካንቲናዎች ውስጥ እንዲኖሩ የተገደዱ ወገኖች መኖራቸው ክስተት በመሆኑ ነው። በአጠቃላይ የዚህ ችግር ሰለባ ይሆናሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በርካታ እየሆነ በመምጣቱ ነው። የምንቃወመው ፍትሃዊ ያልሆነውን ጸረ ስደተኛ ፖሊሲ ነው። በመሆኑም ከራሳችን አልፈን ገና ወደፊት ለሚመጡትም እንኳን በራችውን በቁልፍ ክርችም አድርገው እንዲዘጉ መሆን የለበትም። ይህ ቢቀር አንዴ እግራቸው እዚህ ሀገር ገብቶ አብረውን ያሉትን የኢትዮጵያውያን የመብት ጥያቄ ለማስከበር እንደ አንድ ቤተሰብ በመሰባሰብ በጋራ መጋፈጥ አለብን። የመኖሪያ ፈቃድ ያለንም ብንሆን ቤት ተዘግተን መቀመጥ የለብንም። የወገን መብት ሲረገጥ ነጻነት አለኝ ማለት አይቻልም። የወገኔ ነጻነት የኔም ነጻነት ስለሆነ! ስለዚህ እነዚህ ከሀገር የሚባረሩ ናቸው ተብሎ ብያኔ የተጣለባቸው ወገኖች የትግል አጋር ያስፈልጋቸዋል። ብቻቸውን መጓዝ የለባቸውም። አጋር የሌለውና የብቸኛ ትግል ይሳካል ማለት ያዳግታል። የትግል አጋር መጨመር ጥበብ ነው፣ የትግል አጋርና አጋዥ ኃይል ማራቅ ያለመብሰል ውጤት ነው። ሰዎች ለመብት፣ ለነጻነትና አርነት የሚያካሂዱት ማንኛቸውም አይነት ትግል የጋራ ስለሆነ። በአጠቃላይ መብት እየተገፋ ተኝቶ መናቆር እጅግ አሳፋሪ እና በአዕምሮ ከበሰለ ዜጋ የማይጠበቅ ተግባር ነው። ስለዚህ የመኖሪያ ፈቃድ ያለውም የሌለውም አንድ ላይ አደባባይ ወጥቶ ስርዓቱን ማጋለጥ የዜጎች ሁሉ የጋራ ግዴታ ነው።
……....ከእንቅስቃሴዎች መካከል ዋነኛው ሰላማዊ ሰልፍ ያለማቋረጥ ማድረግ ሊሆን ይችላል። በእውነቱ ብሶትን ለማሰማት አደባባይ ደፍሮ መውጣት በእኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያልተለመደ ቢሆንም ሊበረታታ የሚገባው በጎ ጅምር ሊሆንልን ይችላል። ለሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ለመነጋገር ስለይዘቱንና ሂደቱ በሰፊውና በግልፅ ተወያይተንና በቅድሚያ ተስማምተን ቀኑና ቦታው ተወስኖ የሰብሰባ ጥሪ ይደረግ። የስብሰባውን ጥሪ በደብዳቤ፣ በሞባይል ስልክ መልዕክቶች፣ በኢንተርኔት በኢሜልና ዜና ማሰራጫዎች በመጠቀም ሊሆን ይችላል። በሰልፉ እለት ለተለያዩ ድርጅቶች ስለሚቀርቡት መፈክሮች እምነታቸንንና ብሶታችንን የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል። ከመፈክሮች መሀከል በጣሊያንኛ ቋንቋ ሆኖ፥ አኛ ስደተኞች እንጂ ወንጀለኞች አይደለንም! እስራት ይቁምልን! ወዘተ… የሚሉ ቀላል አረፍተ ነገሮች ብቻ! ደግሞም ይህ አግጦ ሊበላን ያለው ችግር በአንድ ሰላማዊ ስልፍ ወይም አቤቱታ የሚቆም እንዳልሆነ አሌ የሚባል ጉዳይ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። የአንድና የሁለት ቀን ሰላማዊ ስልፍ ብቻ ይህንን ውስብስብ የሆነውን የስደት ችግር እንደማይቀርፍ እንዲሁም በሀገሪቱ የተከሰተውን አዲስ የፖለቲካ አየር እንደማይቀይር ግልፅ ነው። ስለዚህም በየጊዜው በሚደረጉብን መንግስታዊ ተጽዕኖዎች በቆራጥነት መቋቋምና መፍትሄ እስከሚገኝ ድረስ በሞራልና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በፅናት የሚቀጥል መሆን አለበት።
……....የወቅቱን በስደተኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለሚመለከታቸው ክፍሎች ለማሰማት በተለይም በመንግስታዊ ድርጅትና በተባበሩት መንግስታት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ፊት ለፊት በመሰባሰብ ተቃውሞአችንን ማሰማት። የመብታችንን ጥያቄና በወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው በደል ስብአዊነት የጎደለውና የሚያሳዝን መሆኑን መግላጽ ለመንግስት እና ለስደተኞች ቢሮ በደብዳቤ ማቅረብ። የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑት እህትና ወንድሞቻችን የዚሁ ቅጥ አጣሽ ህግ ሰለባ በመሆናቸው ምስክርነት እንዲሰጡ ማስደረግ። የገዢው ሹሞች ሊፈጽሙ እየተዘጋጁበት ያለውት ሁኔታ የከፋና ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ ለተ.መ.ድ. የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ወይም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በተለያዩ መንገዶች አቤቱታችንን ማቅረብ ይኖርብናል። በአጠቃላይ ይህ ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ሜዳ ላይ የሚጥል ፖሊሲን አጥብቀን እንደምናወግዝ ማስታወቅ።

……....ዛሬ ወይም ነገ ልንባረር ነው" እያሉ ኑሯቸውን በሰቀቀን የሚገፉ፣ በሐሳብና በጭንቀት ዓለም እየባዘቱ በብቸኝነት ቤታቸው ተከርችመው ከእንባ ጋር ትንቅንቅ የሚገጥሙ ወገኖች ስንት እንደሆኑ ቤቱ ይፍረደው ብቻ!... ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ይበልጥ በማዳበር ሲወርድ ሰዋረድ በቆየው የመረዳዳት ባህላችን እየታገዝን በህብረት እንድንቆምላቸው ይሁን። የአያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ መብቱ ተከብሮለት መኖር አስካልቻለ ድረስ የመብት ማስጠበቅ ትግል እና የህብረት ድምፃችንን ሳናቋርጥ ማሰማት ይኖርብናል። እንደዚህ ሲሆን ነው እየተሰራ የአለውን ደባ መቋቋምና ከሚመጣው የችግር አረንቋ መራቅ የምንችለው። ለወገን ደራሹ ወገን ነውና ህሊናችንና ሀይላችን በአንድነት እንዲቆሙ በማድረግ ወገናዊ እርዳታችን እንዳይለያቸው ይሁን።
……....ችግሩ እየከፋ እንደሚሄድ በመረዳት ጥያቂያችን መፍትሄ ያገኝ ዘንድና የሚደረግብን ጫና እንዲረግብ ጊዜያቸውን መስዋእት በማድረግ ትልቁን የእንቅስቃሴ ጅምሮች ለሚያቀነባብሩትና ወገናዊ ፍቅራቸውን በተግባር ለሚገልፁት አስተባባሪዎች በላቀው አስዋፅኦዎቻቸው በቅድሚያ የተለየ ክብር የሚሰጣቸው ናቸው ብዬ አምናለሁ።

……....ይህን የግል የሆነውን ሃሳቤን በለሰለሰ ሁኔታ ለማስረዳት ጥረት አድርጌያለሁ። በደንብ የተቀነባበረ ባለመሆኑ ይቅርታ እየጠየቅሁ እርማት አድርጌ ለሁለተኛ ጊዜ እስከማወጣው ደርስ ቸር ሰንብቱ።


0 Comments:

Posta un commento

Links to this post:

Crea un link

<< Home

   Copyright © 2009 ethiopia

Notizie ed Eventi (gibe3.com.et/EEPCo.html)Reaction to Issues Raised by ‘South China Morning Post’ Concerning the Gibe III HEP

the sole reason that Ethiopia has shifted to China is that the international financiers have taken much more time in approving the fund ...

Read More ...

EEPCo signs accord with Chinese Company for Gibe III Project

The Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) and Dongfang Electric Corporation (DEC), Chinese state-owned company, signed a company, signed a contractual agreement amounting to about USD 500 million ...

Read More ...

Distorted Facts Vs the Reality The Actual Picture of Gibe III Hydroelectric Project

Needless to say, many deliberate and irresponsible reports are being fabricated regarding the Gibe III Hydroelectric Project (HEP).   

Read More ...

Gibe III HEP Launches Satellite Office at Jinka Town

The Gibe III Hydroelectric Project (HEP) Office opened an Environmental and Social Impact Management and Mitigation Team branch office at Jinka town on Feb 2010.    

Read More ...

Office performs Public Consultations, Disclosure with Project-Affected Communities

the Gibe III Hydroelectric Project Office carried out a wide range public Consultations & disclosures and complimentary discussions with the upstream communities of the Project    

Read More ...

Consultants Reaffirm Gibe III HEP Viable in economic, financial, technical terms

the joint venture international consultants reaffirmed that the Gibe III Hydroelectric Project is considerably viable    

Read More ...

Gibe III Hydroelectric Project said Best Option in Power Sector Development

The African Development Bank (AfDB) and the Work Bank (WB) experts acknowledged Gibe III Hydroelectric Project is the best option in the power sector developments    

Read More ...

EEPCo, TBEA sign Contract for Gibe III-Wolaita substation Transmission Line Project

The EEPCo and TBEA, a Chinese company, singed a contractual agreement on July 24, 2009, amounting to Birr 380,883,690.99 (USD 34,007,472.41) for the installation of power transmision line from Gibe III Main station to the new Wolaita substation.    

Read More ...

Office Establishes Environmental Advisory Panel

The Gibe III Hydroelectric Project Office established Environmental Advisory Panel (EAP) in a bid to consult on the environmental issues during the implementation project.

Read More ...

EEPCo looks to win West African contract

Capita, (26 July 2009, Addis Ababa)-The Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) recently participated in an international tender to manage the operation of the recently completed Bumbuna Hydroelectric Project (BHP) in Sierra Leone, which was constructed by Italian-based firm. Salini.

Read More ...

Kenya, Ethiopia to benefit from dam project

Kenya and Ethiopia are constructing a-multibillion hydroelectric project to benefit the two neigbouring countries, according to Kenyan officials.

Read More ... 


Newsfeeds (cyberzena.com)/

ቀን መቁጠሪያ

 
ቀን መቁጠሪያ