martedì

ስደተኞች ለመኖርና ለመሻሻል የሚያደርጉት ጥረት


በስደት አገራችንን ጥለን በሰው አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ቁጥርችን በዚህ 10 ዓመታት ውስጥ ብቻ እጥፍ ድርብ ሆኗል:: ታዲያ በየትኛውም ምክንያት ቢሆን አገራችንን ለቀን በኢኮኖሚ ወደ አደጉት አገሮች ለመኖር ስንነሳ እያንዳንዳችን የምናልመው ነገር ይኖራል:: ይኸውም በትምህርትም ሆነ በስራ ከፍ ለማለት፣ በኢኮኖሚ ኑሮዋችን ለመሻሻል፣ ቤተሰቦቻችንን በኤኮኖሚ ለመደገፍ፣ ሌላም ሌላም። በእርግጥ ዕውነት አለን:: ከአጣች ከነጣች አገራችን ወደ ተረፋቸውና ወደተትረፈረፋቸው አገሮች ስንጓዝ ለምን የተሻለ ነገር አንመኝ? ይሁንና የተመኘነው አገር ስንደርስ እንዳለምነውና እንደተመኘነው ሳይሆን ነገሩ የተገላቢጦሽ ይሆንብናል:: በጣሊያንኛው «ሶቶ ሶፕራ» እንደሚባለው ማለት ነው::
ጣሊያን በመጨረሻዎቹ ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካና ከእስያ በመጡ ስደተኞች ምን ያህል ተጥለቅልቃ እንደመጣች እናያለን:: እነዚህም ስደተኞች ኑሮአቸውን ለማሻሻል፣ ተረጋግተው ለመኖር፣ የማይገቡበት ቀዳዳ እና የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም:: የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት፣ ዜግነት ለማግኘት፣ ወዘተ ... ብዙ የሚያደርጉት ነገር አለ:: የጣሊያን ዜግነት ካለው ጋር ይጋባሉ፣ የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘትም የተዋጣለት ልብ ወለድ ታሪክ ያቀርባሉ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ከአላቸው ጋር በገንዘብ የሃሰት ጋብቻ ይፈጽማሉ፣ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ካለው ወንድሟ ወይም እህቱ ጋር የሃሰት ጋብቻ ይሚያደርጉም ይገኙበታል ። ከዚህም አልፎ ተርፎ ያለአቻ ጋብቻ የሚያደርጉም አሉ:: ይህ እንኳን በሀገራችን ወገኖች ሲፈጸም አይታይም። በሀገራችን በኢትዮጲያ እራሳችን የወደድናትንና የመረጥናትን፣ ሴቷም እንደዚሁ ያፈቀረችውን የማግባት ልምዱ የዳበረ ባህል ነው:: ወንዱ ከእርሱ እድሜ ጥቂት ያነሰችውን ካልሆነ በስተቀር ከእርሱ እድሜ በላይ የሆነችውን የማግባት ልምዱ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር አይታይም:: ሌሎች የውጪ ሀገር ስደተኞች ግን ፍጹም የተለየ ነገር ሲያደርጉ ይታያል:: የ25 ዓመቱ ጎረምሳ የ50 ዓመት ፈረንጅ አሮጊት ያገባል:: ወይንም በአልኮልና በሃሺሽ አእምሮዋ የደነዘዘ እርባነ ቢስ ያገባል:: የ20 ዓመት ጉብሏም አባቷ ብቻ ሳይሆን አያቷ የሚሆነውን ሽማግሌ ፈረንጅ ማግባት የተለመደ ነገር ሆኖዋል:: የሚያሳዝነው ያለአቻ መጋባቱ ብቻ አይደለም:: የፈረንጅ ባህል ልቅ በመሆኑ ስንት በእኛ ያልተለመደ ድርጊቶች ሲፈጸም እናያለን:: ታዲያ ስደተኛው ይህን የሚያደርገው የፈረንጅ አባዜ ይዞት ወይም የዘር ሃረግ ስቦት አይደለም:: ሌላ ምክንያት የለውም፣ ነገሩ ግልጽ ነው:: የመኖሪያ ፈቃድ ወይንም ዜግነት አግኝቶ በሰላም ሰርቶ ወይም ተምሮ መኖር እንዲችል ነው::
ታዲያ ለዚህ ሁሉ ነገር መፈጠር ዋናው ምክንያት ዞሮ ዞሮ የዛ አገር መንግሥት የደነገገው የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ ህግ ነው:: ... ይቀጥላል ...
ይህ የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ ህግ እንደየሀገሩ ይለያይ እንጂ ማንኛውም ነጻ አገር ያለውና ሊኖረው የሚገባ ህግ ነው:: ይህ ህግ ለሃብታም አገራት ብቻ አልተሰጠም ድሃ አገሮችም በነጻነት የሚኖሩ እስከሆነ ድረስ የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ ህግ ይኖራቸዋል:: ይህ ህግ ከሌላቸው ቅጥ ያጣ፣ መረን የለቀቀ፣ የዜጎችን መብት የሚጋፋ አሰራር ይፈጠራል:: ዛሬ በየትኛውም አገር እንኳን የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ እንደልብ ማግኘት ቀርቶ ከአንዱ አገር ወደ ሌላው አገር ህጋዊ የመግቢያ ፈቃድ (ቪዛ) ሳይዙ መግባት አይቻልም:: ብዙ ጊዜ ይህን ነገር ስናስብ ህጋዊ የመግቢያ ፈቃድ የሚያስፈልገው ለአውሮፓ፣ ለአሜሪካና ለካናዳ ሊመስለን ይችላል:: ... ይቀጥላል ...
ስደተኛ በኢኮኖሚ በበለጸጉ አገሮች ብቻ የሚገኝ መስሎ ከታየን ፍጹም ተሳስተናል:: በሌሎች ደሃ በተባሉ አገሮች ስደተኞች አያጡም:: የድሆችም ደሃ በሆነችው አገራችን እንኳን በአሁኑ ጊዜ የሱዳን፣ የሱማሊያ ወዘተ ... ስደተኞች ይኖሩባታል:: ታዲያ ሀገሪቱ ድሃ ትሁንም አትሁንም ለስደተኛው የመኖሪያ ፈቃድም ሆነ ዜግነት በቀላሉ የትም ቦታ አይሰጥም:: ህግና ደንቡን ያሟላ ሲሆን ብቻ ነው ተቀባይነት የሚኖረው:: እዚህ ላይ «የድሃ አገር ዜግነት ተገኝቶስ ምን ሊጠቅም ምን ሊጎድል» የምንል በርካታ ነን:: ... ይቀጥላል ...


Nessun commento: