domenica

የዘርና የቀለም ልዩነት በምዕራብ ሀገሮች


የዘርና የቀለም ልዩነት መስፋፋት በምዕራብ ሀገሮች እንደ ሰደድ እሳት እየቀጠለ የሚሄድና አሳሳቢነቱም እየጎላ መምጣቱ ታውቋል። ከምን ተነስቶ ከምን እንደደረሰ ግምገማ ተደርጎበታል።
በተባበሩት መንግሥታት ማኅበር በኩል የተደረገው ጥናት በተለይም በዲሞክራሲ መርሆ እንደሚመራ የሚነገርለት የምዕራባውያኑ ማኅበራዊ ኑሮ ለዘርና ለቀለም ልዩነት የተጋለጠ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ለሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ድርጅቶችና ጥናቶች አሳሳቢነቱን በግልጽ አስምረውበታል። ይሁንና የምዕራቡ ሀገር ፖለቲከኞች ሁኔታው አልፎ አልፎ የሚከሰት የቀለምና የዘር ልዩነት እንዳለ ቢናገሩም ይህን ያህል አሳሳቢ ነው ብለው ለመቀበል ፈቃደኞች አይደሉም።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት መከበር ተጠሪ የሆኑት የሴኒጋሉ ተወላጅ አፍሪቃዊው ዱኦዶ ዴኔ ስለ ጉዳዩ ብዙ የሚሉት አላቸው። በቅርቡ ከተከሠተው ከፈረንሣዩ ሁኔታ በመጀመር፥ በእስፓኝ የተደረገውን ያስታውሳሉ። በእስፓኝ አገር “እንዳሉሲን” በተባለው ክፍለ ሀገር አንድ የሞሮኮ ተወላጅ አንዲት ሴት በመግደሉ ወዲያው የሞሮኮ ተወላጅ የሆኑ አረቦች ሁሉ እንደ ዱር አውሬ ታድነው ተያዙ አንዳንዶችም ተገደሉ። በሆላንድ አገር በአምስተርዳም ከተማ የተፈጸመው ከዚህ የተለየ አይደለም። ቫን ጎኅ የተባለው ፊልም አዘጋጅ በመገደሉ ብዙ የሞሮኮ ተወላጆችና አረቦች ተንገላተዋል። ይህ የሚያመለክተው ችግሩ እንደ ሰደድ እሳት እየተያያዘ በመሄድ በተለያየ ቦታ እየተዳረሰ መሆኑን ነው። የሚገርመው ግን ይላሉ ዱኦዶ ዴኔ አንድ እራስ በተቆረጠ ቁጥር ሌላ እራስ እያቆጠቆጠ መሄዱ ነው።
እንደዚህ ያለውን መሠረታዊ ግጭት የሚፈጥሩት ሶስት ጉዳዮች እንደሆኑ ተመራማሪዎች በጥናት ደርሰውበታል። አንደኛ የዘርና የቀለም፥ ሁለተኛው የባሕል፥ ሦስተኛው የሃይማኖት ልዩነት ነው። እነዚህ ሁኔታዎች በአንድ አገር ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ከሁሉም የሚከፋው ግን የዘርና የቀለም ልዩነት መሆኑን የሴኒጋሉ ተወላጅ ዱኦዶ ዴኔ ይናገራሉ።
የዓለም ማኅበረሰብ በዘርና በቀለም ልዩነት የሚመጣውን አሳሳቢ ግጭት ቀደም ብሎ ስለተረዳው የቀለምና የዘር ልዩነት የሚወገድበትን መንገድ ለመቀየስ የተቻለውን ሁሉ አድርጓል። ጉዳዩን በኃላፊነት ወስዶ እየተከታተለ የዘርና የቀለም ልዩነትን የሚያስወግድ ድርጅት እስከማቋቋም ደርሷል። ይሁንና ድርጅቱ ተቋቁሞ፥ መመሪያውም ተዘጋጅቶ በሥራ እንዲተረጎም ጥረት በሚደረግበት ጊዜ አንዳንድ ውጤቶች ቢመዘገቡም ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ ውሏል ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም።
በአሁኑ ጊዜ በተባበሩት መንግሥታት ማኅበር አስተያየት በምዕራባውያን አገሮች ዘንድ የሰብአዊ መብት የተከበረበት ዲሞክራሲ ሰፍኗል እየተባለ ቢለፈፍም በአንዳንድ አገሮች በሚታየው የዘርና የቀለም ልዩነት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ከሌሎች አገሮች እየፈለሱ ወደ ምዕራባውያን አገሮች የሚገቡ ስደተኞችም ሆኑ ሠራተኞች የራሳቸውን ባሕልና ልማድ ይዘው ስለሚገቡ ሌላ አዲስ መዋቅር መጣል ይኖርበታል። ... ይቀጥላል ...


3 Comments:

At 08:04, Anonymous ሀይሌ ከሮማ said...

እዚህ እስከኖሩ ድረስ ቋንቋውን ይወቁ። ከጎደልዎት ማንነትዎም አብሮ ይጎድላል፡፡

የቋንቋ አለመቻል ያመጣው ችግር?
ቋንቋ የተፈጠረው ለመግባባት፣ ያሰቡትንና የሚፈልጉትን ነገር በትክክል ለመግለፅ ነው፡፡ ቋንቋ የብዙ ነገር መክፈቻና መዝጊያ የሆነ ዋና ቁልፍ ነው፡፡ ከዚያም አለፎ ሃሳብን ያለምንም በትክክል መግለፅ እራሱን የቻለ ጥበብ ነው፡፡ እውቀትና ኩራትም ነው፡፡ የቋንቋ እድገትም ያገርና የዜጋን እድገት ከሚያመለክቱት ነገሮች አንዱ ነው፡፡ እዚህ ብዙ ጊዜ ተቀምጠን በቅጡ አንችለውም፡፡ ማወቁ በራስ እንዲተማመኑ ያደርጋል፡፡ ካላወቅንበት ማደግ አንችልም፡፡ ካወቅንበት አንዱ የማደጋችን ምልክት ነው፡፡
የቋንቋ አለመቻል የምንፈልገውንና የሚሰማንን ነገር ለማስረዳት ይቸግረናል፡፡ ምናልባት በቋንቋ እጥረት ምክንያት ሊሆን ይችላል ግጭት የሚፈጠረው፡፡ ወይም ደግሞ ቀስ ብሎ ቋንቋን በመጠቀም ነገሮችን ከማስረዳት ይልቅ መጣላትን እንመርጣለን፡፡ የቋንቋን ጠቃሚነትም ባለማስተዋል እራሳችንን እንጎዳለን፡፡

ቋንቋውን መናገር ብቻ ሳይሆን ብዙዎቻችን መፃፉንም በቅጡ አንችልበትም፡፡ ... ይቀጥላል ...

 
At 08:32, Anonymous Anonimo said...

Mukera ... amariNa

 
At 08:58, Anonymous ስም የለኝ said...

የዘር ልዩነት እያቆጠቆጠ በመሄድ ላይ ነው። የዘር ጥላቻን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ነው የሚያመለክተው።
የውጭ አገር ሰዎች ጎርፈው በመግባታቸው በአሁኑ ጊዜ በጣሊያን ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ የሚሆን የውጭ አገር ዜጋ ይገኛል። በመሆኑም በታሪክም ሆነ በባህል እንዲሁም በሃይማኖት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ቀላል ባለመሆኑ በየጊዜው አንዳንድ አለመግባባት እየተከሰተ በመሄድ ላይ ነው። በየጊዜው ምርጫ በመጣ ቁጥር የውጭ አገር ሰዎችን ምክንያት አድርጎ መራጩን ሕዝብ ከመከፋፈል ይልቅ አስቀድሞ አንድ መፍትሔ ይፈለግለት የሚሉ የጣሊያን ዜጎች ጥቂቶች አይደሉም። ፓርቲዎች የገዛ ዓላማቸውን ለማራመድ ሲሉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በውጭ አገር ሰዎች ላይ መጥፎ ስሜትና ግምት የሚያሳድር ነው። ብዙዎች እንደሚያምኑበት የዘር ልዩነቱ የሚያነጻጽረው በመስጊዶችና በእስላም ሃይማኖት ላይ ብቻ ሳይሆን ዕለት ከዕለት በሚደረገውም የኑሮ ውህደት ወይም የintegrazione ሁኔታ ላይ ነው።
አንድ የጣሊያን ዜጋ ከአንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ጋር ሲነጋገር ብዙውን ጊዜ ስሜቱን ሲደብቅ የሚታይባቸው ጊዜ አለ። የዘር ልዩነት በውስጡ እንዴት ተደብቆ እንደሚገኝ ማወቅ ይችላል። አንዳንዴም የዘር ጥላቻው በተለየ ሂደት ሊታወቅ ስለሚችል በተለይም ንግግሩም፣ ቀልዱም ከዘር ልዩነት ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ በስተጀርባው የተደበቀውን ለይቶ ማወቁ እስከዚህ ከባድ ሊሆን አይችልም። ወደፊት የደረሰብኝን አንዳንድ ሁኔታዎችን እጽፍ ይሆናል ...

 

Posta un commento

Links to this post:

Crea un link

<< Home

   Copyright © 2009 ethiopia

Notizie ed Eventi (gibe3.com.et/EEPCo.html)Reaction to Issues Raised by ‘South China Morning Post’ Concerning the Gibe III HEP

the sole reason that Ethiopia has shifted to China is that the international financiers have taken much more time in approving the fund ...

Read More ...

EEPCo signs accord with Chinese Company for Gibe III Project

The Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) and Dongfang Electric Corporation (DEC), Chinese state-owned company, signed a company, signed a contractual agreement amounting to about USD 500 million ...

Read More ...

Distorted Facts Vs the Reality The Actual Picture of Gibe III Hydroelectric Project

Needless to say, many deliberate and irresponsible reports are being fabricated regarding the Gibe III Hydroelectric Project (HEP).   

Read More ...

Gibe III HEP Launches Satellite Office at Jinka Town

The Gibe III Hydroelectric Project (HEP) Office opened an Environmental and Social Impact Management and Mitigation Team branch office at Jinka town on Feb 2010.    

Read More ...

Office performs Public Consultations, Disclosure with Project-Affected Communities

the Gibe III Hydroelectric Project Office carried out a wide range public Consultations & disclosures and complimentary discussions with the upstream communities of the Project    

Read More ...

Consultants Reaffirm Gibe III HEP Viable in economic, financial, technical terms

the joint venture international consultants reaffirmed that the Gibe III Hydroelectric Project is considerably viable    

Read More ...

Gibe III Hydroelectric Project said Best Option in Power Sector Development

The African Development Bank (AfDB) and the Work Bank (WB) experts acknowledged Gibe III Hydroelectric Project is the best option in the power sector developments    

Read More ...

EEPCo, TBEA sign Contract for Gibe III-Wolaita substation Transmission Line Project

The EEPCo and TBEA, a Chinese company, singed a contractual agreement on July 24, 2009, amounting to Birr 380,883,690.99 (USD 34,007,472.41) for the installation of power transmision line from Gibe III Main station to the new Wolaita substation.    

Read More ...

Office Establishes Environmental Advisory Panel

The Gibe III Hydroelectric Project Office established Environmental Advisory Panel (EAP) in a bid to consult on the environmental issues during the implementation project.

Read More ...

EEPCo looks to win West African contract

Capita, (26 July 2009, Addis Ababa)-The Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) recently participated in an international tender to manage the operation of the recently completed Bumbuna Hydroelectric Project (BHP) in Sierra Leone, which was constructed by Italian-based firm. Salini.

Read More ...

Kenya, Ethiopia to benefit from dam project

Kenya and Ethiopia are constructing a-multibillion hydroelectric project to benefit the two neigbouring countries, according to Kenyan officials.

Read More ... 


Newsfeeds (cyberzena.com)/

ቀን መቁጠሪያ

 
ቀን መቁጠሪያ