lunedì

ግጥም ብጤ


ፖሞዶሮና ፓስታ ቅርጭም አደርግና
አንድ ጣሳ ቢራ ጭልጥ አደርግና
ተመስገን እላለሁ ኑሮ ይባልና።
.
ስፐር ማርኬት ቡስጣ ስሸከም እውልና
ስህን ሬስቶራንት ሳጥብ አመሽና
በኩራት እተኛለሁ ነገም ሌላ አለና።
.
ከቀናኝ ፊሶ ሥራ አገኝና
ወይም ሽማግሌ ጠባቂ እሆንና
ትላንትን እደግማለሁ ዛሬም እንደገና።
.
ጊዜው ሲገሰግስ ዘመኑም ሲረዝም
ሥራዬን ለዘመድ ለወዳጅ አልነግርም
እርዳኝ ባይ ጠያቂ በጭራሽ አልወድም
አገር ግባ የሚለኝ ምክርም አልፈቅድም።
.
ባገር ያለ ሁሉ ከንቱ ይመስለኛል
የፈረንጁ ነገር ክሱም ይደንቀኛል።
.
እንደመልካም ነገር ተሰደድኩ እላለሁ
ግን ክብር ያለሀገር እንደሌለ አውቃለሁ።
.
ዛሬ አያችሁ እንጂ ሳድር በሰው ሀገር
ከዋሉ ካደሩ ለእኔም አለኝ ምድር።
.
ሰው ያለሀገሩ ቢበላ መቅመቆ
መከበር አለበት ሰውነቱ ታውቆ።
.
ሰው ክለሀግሩማ ካለቦታው
ብሳና ይሆናል ሸንኮራ አገዳው
መህይም ይመስላል ብዙ እውቀት ያለው።
.
ካገሩ የወጣ ሀገሩ እስኪመለስ
ኑሮውን ይገፋል ክብሩን በማስገሰስ።

Nessun commento: