martedì

በጣሊያን የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ሰሞኑን አዲስ ሰርኩላር አስተላለፈ


ከዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
01 09 07
ካሁን ቀደም ማለትም በቅርቡ የስራ ቪዛ በማግኘት ብዙ የዉጭ ሀገር ዜጎች ጣሊያን ሀገር ለስራ እንደመጡ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ተነግሮ እንደነበር ይታወሳል::
ይህም ሊሆን የቻለዉ የ 2006 አመት መደበኛ ፕሮግራምን አስመልክቶ ሲሆን ችግሩ የተከሰተዉ ጣሊያን ሳይገቡ በፊት ሳይሆን በዚሁ በጣሊያን ምድር ላይ ነዉ::
አሰሪዉ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ሰራተኛ ለመቅጠር ማመልከቻ አስገብቶ በነበረበት ወቅትና ተቀጣሪዉ ጣሊያን በደረሰበት የጊዘ ገደብ መካከል ብዙ ቀናት በማለፉ በዚህ መካከል ቀጣሪዉ ወይም አሰሪዉ ሰዉ ሃሳቡን ቀይሮ ሰራተኛዉን ለመቅጠር ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘ የዉጭ ሃገር ዜጋው ችግር ላይ ይወድቃል መፍትሄዉስ ምን ሊሆን ይችላል?
የሀገር ዉስጥ ሚንስቴር ካሁን በፊት በ 07/07/2006 አዉጥቶ በነበረዉ ቁ. 2570 የዉስጥ ሰርኩላር መሰረት ከላይ ያነሳሁትን ጥያቄ ሊመልሰዉ ችሎአል::
የሰርኩላሩ ፍሬ ነገር ባጭሩ ይህን ይመስላል “አንድ የስራ ቪዛ በመያዝ ጣሊያን አገር የገባ የዉጭ አገር ዜጋ የስራ ኮንትራት ከመፈራረሙ በፊት አሰሪዉ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ሃሳቡን ቀይሮ አልቀጥርህም ካለና ሃሳቡን ከቀየረ የዉጭ ሐገር ዜጋዉ ግለሰብ የስራ ፈቃድ ወረቀት የማግኘት መብት አለዉ“ ይላል::
ተመሳሳይ ችግር የገጠማችሁ ካላችሁ በዚህ እድል በመጠቀም ችግራችሁን እንደምታቃልሉ ተስፋ አደርጋለሁ::


Nessun commento: