martedì

በጣሊያን ሀገር የአጭር ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማሻሻያ ሕግ ወጣ


05 06 07
ዶ/ር ዘለቀ እሬሶ
ካሁን ቀደም ማንኛዉም ግለሰብ ለጉብኝት፣ ለንግድ ወይንም ለትምህርት ጣሊያን ሀገር በሚመጣበት ወቅት የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የመጠየቅና የማግኘትም ግዴታ ነበረበት:: በአዲሱ ሕግ ማለትም ቁጥር 68 በ 01/06/2007 በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 126 ( Disciplina dei soggiorni di breve durata degli stranieri per visite, affari, turismo e studio) ላይ ታትሞ በወጣዉ ሕግ መሰረት ግን ማንኛዉም የዉጭ ሀገር ዜጋ በጣሊያን ሀገር የመቆያ የጊዜ ገደቡ ከሶስት ወራት በላይ ካልሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት የማዉጣት ወይንም የመጠየቅ ግዴታ የለበትም ይላል:: ለምሳሌ አንድ ሰዉ ከሆነ ሀገር ወደ ጣሊያን ለቱሪዝም ወይንም ለጉብኝት የሶስት ወራት ቪዛ አግኝቶ ቢመጣ ጣሊያን ሀገር በሚገባበት ወቅት ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት ማሳወቅ (dichiarazione di presenza) ብቻ ይኖርበታል:: በመሆኑም የመኖሪያ ፈቃድ ወረቀት ጠይቆ ለማግኘት ጊዜዉን፣ ጉልበቱንና ገንዘቡንም ጭምር አያባክንም ማለት ነዉ::
በአለፈው አርብ በ "Gazzetta Ufficiale" የወጣውና ከ 2/06/07 ጀምሮ የፀደቀውን አዲስ ሕግ ግልባጭ ከዚህ ማውረድ ይችላሉ


Nessun commento: