giovedì

70 የአለቃ ገብርሃና ቀልዶች


ከህይወት ታሪካቸው ስንጀምር አንዳንዶች የአባታቸው ስም ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ። ምናልባት አንዱ የአለም ሌላው ደግሞ የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናባጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ 1814 ዓ .ም ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኃላ ወደ ጎጃም ተሻግረው ቅኔን ተቀኙ። ከዚያም ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሰው ከመምሕር ወደ አብ ወልደ ማርያም ጽዋትወ ዜማ፤ ከባሕታዊ ገብረ አምላክ አቋቋም፤ ከዐቃቤ ስብሃት ገብረ መድሕን ትርጓሜ መጽሐፍትን እንዲሁም ድጓን ተምረዋል። በዚህ የሰፋ እውቀታቸው የተነሣ በ 26 ዓመታቸው ጎንደር ሊቀካህናትነት ተሾመው ነበር። በዚህም ሹመት ለሰባት ዓመት ማገልገላቸው ይነገራል። በፍትሐ ነገሥት ሊቅነታቸው ደግሞ በዳኝነት እየተሰየሙ አገልግለዋል። አለቃ ገብረ ሐና ጨዋታ አዋቂነታቸው እየታወቀ የመጣው በዚህ ወቅት ነበር። በዚህም እውቀታቸው የትንሹ ዓሊ አጫዋች ሆኑ። አጼ ቴዎድሮስ ሥልጣኑን ሲይዙ አለቃን በቤተ መንግሥት አገኟቸው። አለቃ የቤተ መንግሥቱን ሰዎች በቀልዳቸው ሸንቆጥ ስለሚያደርጉ መስማማት አልቻሉም ነበር። እንዲያውም ዐጼ ቴዎድሮስ «ገብረ ሐና ፍትሐ ነገስቱን ጻፍ፤ ፍርድ ስጥ .. ገንዘብ ያውልህ፤ ቀልድህን ግን ተወኝ።» ሲሉ ተናግረዋቸው ነበር ይባላል። አለቃ ግን አላቆሙም። በተለይም ደግሞ በንጉሡ ባለሟል በብላታ አድጎ ላይ «አድግ / በግእዝ አህያ ማለት ነው /» እያሉ በሚሰነዝሩት ትችት በተደጋጋሚ ተከሰው ዐጼ ቴዎድሮስ ዘንድ ቀርበዋል። በመጨረሻ ቴዎድሮስ ክስ ሲሰለቻቸው ምላስ ቀርቶ ታገሉና ተሸናነፉ ብለው ፈረዱ። በዚህም ትግል ምሁሩ አለቃ ተሸነፉ። ንጉሡም እንግዲህ ምን ይበጅህ ? ሲሉ ጠየቋቸው አለቃም «ድሮስ ትግል የአህያ ሥራ አይደል» ብለው በመመለሣቸው ከአካባቢያቸው ለማራቅ ሲሉ ንጉሡ ገብረ ሐናን ለትግራይ ጨለቆት ሥላሴ አለቃ አድርገው በመሾም ወደ ትግራይ ላኳቸው። ወደካቶሊክነት የተቀየረውና ከአንቷን ዳባዲ ጋር በዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን ስለሆነው ሁሉ ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው የዋድላው ሰው ደብተራ አሰጋኽኝ ጥር 1858 ዓ .ም . ለአንቷን ዳባዲ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ይህን ሁኔታ ገልጦት ነበር «አለቃ ገብረ ሐናን ንጉሥ መቱዋቸው። ወደ ትግሬ ወደ ላስታ ተሰደዱ። እጅግ ተዋረዱ እኔም በዋድላ አገኘኋቸው ወደ ቆራጣም ሄዱ» ሲል ጽፏል። ደስታ እንዳለ ሁሉ መከራም ያለ ስለሆነ ሁለቱንም በጸጋ መቀበል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ ነው። ካህናት በአጼ ቴዎድሮስ ላይ ባመጹ ጊዜ በአድማው ካሉበት ካህናት መካከል አንዱ ገብረ ሐና መሆናቸው ስለታወቀ ዐጼ ቴዎድሮስ በአለቃ ገብረ ሐና ላይ አምርረው ሊቀጧቸው ዛቱ። አለቃም ሸሽተው ጣና ሐይቅ ሬማ መድኃኔዓለም ገዳም ገቡ። በዚያም ባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ የተባሉ የአቋቋም ሊቅ አገኙ። ሁለቱም ተወያይተው በጎንደር አቋቋም ስልት የመቋሚያውን የአካል እንቅስቃሴ ጨምረው ዝማሜውን አዘጋጁት (በኋላ ተክሌ አቋቋም እየተባለ የሚታወቀው ነው )። ባህታዊ ጸዐዳ «ከእንግዲህ እኔ ወደ ዓለም አልመለስም፤ አንተ ይህንን ስልት አስተምር» ብለው አለቃ ገብረሐናን አደራ አሏቸው። ከዐጼ ቴዎድሮስ ሞት በዃላ በ 1864 ዓ .ም . ዐጼ ዮሐንስ ሲነግሡ ከገዳም ወጥተው ወደ ትግራይ አቀኑ። በመቀጠልም በቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ የሚያውቋቸው ምኒልክ በሸዋ መንገሣቸውን ተከትለው ሸዋ መጡ። ዐጼ ምኒልክ በዐጼ ቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ አለቃ ገብረ ሐናን ስለሚያውቋቸው በደቡብ ጎንደር የሚገኘውን የአቡነ ሐራን ገዳም ሾሟቸው። በዚያም ጊዜ በአካባቢው ከባድ ርሃብ በመከሠቱ አለቃ ከገዳሙ ብር አንድ ሺ አውጥተው ለገበሬዎች አከፋፈሏቸው። በዚህም ተግባራቸው ተከስሰው ወደ አዲስ አበባ መጡ። የፍርድ ሚኒስቴር የነበሩት አፈ ንጉሥ ነሲቡ ስሕተት ነው ብለው ፈርደውባቸው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ በምኒልክ ዘንድ ስለተሰማ ወደ ዙፋኑ ችሎት ተሻገረ። ዐጼ ምኒልክም ይህ ተግባር ያሸልማል እንጂ አያስቀጣም ብለው በመፍረዳቸው አለቃ ነጻ ወጡ። ንጉሥ ምኒልክ አለቃን የእንጦጦ ራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። እርሳቸውም ትርጓሜ መጻሕፍትን ያስተምሩ ነበር። ጥቂት ጊዜ በአዲስ አበባ እንደ ተቀመጡ እንደገና ወደ ጎንደር ተመልሰው፤ ድንግልናቸውን አፍርሰው ወይዘሮ ማዘንጊያን አገቡና ተክሌ የተባለ አንድ ወንድ ልጅና በፍታ የተባለች ሴት ልጅ ወለዱ። አንዳንድ ሊቃውንት አለቃ ገብረ ሐና ሊቅ፤ መልከመልካምና የነገሥታቱ ወዳጅ በመሆናቸው በዚያ ዘመን የነበሩ ሴቶች ወዳጅነት ለማበጀት ይሻሙባቸው ነበር ይላሉ። አለቃ ድንግልናቸውን ያፈረሱት ሆን ብለው ሳይሆን እኔ አስፈርሰዋለሁ በሚል የወይዛዝርት ውድድር የተነሣ ነው ይባላል። የአለቃ መንፈሳዊ ሕይወት የተናጋው ከዚያ በዃላ ነው ይባላል። ተክሌ ለትምህርት ሲደርስ ከሌላው የቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር እርሳቸው ከባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ ጋር ሆነው ያዘጋጁትን ዝማሜ አስተማሩት። አለቃ ገብረ ሐና ደርቡሽ ጎንደርን ሲወርር ልጃቸውን ወደ ወሎ ልከው እርሳቸው ጎጃም ውስጥ ዘጌ ገዳም ገቡ። በዃላም ዐጼ ምኒልክ ደርቡሽን ለመውጋት ወደ ፎገራ መምጣታቸውን ሲሰሙ፤ ከተደበቁበት ወጥተው ንጉሡን ተከትለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ምኒልክም እንደገና የራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። ልጃቸው አለቃ ተክሌ ወሎ ንጉሥ ሚካኤል ዘንድ እያሉ የተንታ ሚካኤል በዓል ሲከበር ከአባታቸው የተማሩትን ዝማሜ በተመስጦ አቀረቡት። ንጉሥ ሚካኤልም በዚህ ተደንቀው በዚያው በተንታ እንዲያገለግሉ አደረጉ። የተክሌ ዝማሜ በይፋ የተጀመረው ያኔ ነው ይባላል። በዃላ ራስ ጉግሣ የአለቃ ተክሌን ዝና ሰምተው ንጉሥ ሚካኤልን በማስፈቀድ ወደ ደብረ ታቦር አምጥተው የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሾሟቸው። አለቃ በአዲስ አበባ እያሉ ከመኳንንቱ ከመሳፍንቱ ጋር ያላስማሟቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። የመጀመርያው ትንባሆ ይጠጣሉ ተብሎ የተነገረው ሐሜት አንድ ቀን በቅኔ ማኅሌት ፒፓቸው ወድቆ በመጋለጣቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአድዋ ጦርነት ታላቅ ጀብዱ ለፈጸሙት ለደጃዝማች ባልቻ ዐጼ ምኒልክ የሚወዷትን ጎራዴያቸውን ሲሸልሟቸው «ወይ ጎራዴ ወይ ጎራዴ ከቤቷ ገባች» በማለት በሽሙጥ በመናገራቸው ባልቻ እገላለሁ ብለው ተነሡ። ይህም አልበቃ ብሏቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በነገር ተኳረፉና መላ የቤተመንግሥቱ ሰው አደመባቸው። ዐጼ ምኒልክ አለቃን ምን ቢወዷቸው በተለይ ከደጃች ባልቻና እቴጌ ጣይቱ ጋር የፈጠሩትን ጠብ አልወደዱላቸውም። በዚህ ምክንያት አለቃ ገብረ ሐና ከአዲስ አበባ ለቅቀው እንዲወጡ ተወሰነባቸው። በጎንደርና በወሎ ጥቂት ጊዜ ከሰነበቱ በዃላ ልጃቸውን ገብረ ሐና ሞተ ብለህ ተናገር ብለው አዲስ አበባ ላኩት። አለቃ ተክሌ ይህንን መርዶ በቤተመንግሥቱ ሲያረዱ ምንም እንኳ ገብረ ሐና ከብዙዎቹ ጋር ቢኳረፉም ታላቅ ሐዘን ሆነ። ከተወሰኑ ቀናት በዃላ አለቃ ራሳቸው አዲስ አበባ ገቡና ጉድ አሰኙ። ምኒልክም አስጠርተው ሞቱ ከተባለው በዃላ ከየት መጡ ቢባሉ «በሰማይ ጣይቱ የለች፤ ምኒልክ የለ፤ ጠጅ የለ፤ ጮማ የለ፤ ባዶ ቤት ቢሆንብኝ ለጠባቂው ጉቦ ሰጥቼ መጣሁ።» ብለው ሁሉንም አሳቋቸው። ጣይቱም መኳንንቱም ይቅር አሏቸው። አለቃ ገብረ ሐና እድሜያቸው እየገፋ አደብም እየገዙ መጡ አዲስ አበባ ተቀምጠውም ትርጓሜ መጽሐፍት ማስተማር ቀጠሉ። ዐጼ ምኒልክ የአብያተ ክርስቲያናቱን የግብዝና መሬት ለመኳንንቱ በመስጠታቸው ካህናቱ ምንም ባለ ማግኘታቸው የተቆጡት አለቃ ገብረ ሐና ተቃውሟቸውን በቀልድ ለዐጼ ምኒልክ አቀረቡ። ይህም ከወይዛዝርቱና ከመኳንንቱ ጋር መልሶ አጋጫቸው። ከዚህ በዃላ አዲስ አበባ መቀመጥ ስላልቻሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ደብረ ታቦር ተመለሱ። ያኔ ልጃቸው አለቃ ተክሌ ደብረ ታቦር ኢየሱስን እልቅና ተሾመው ነበር። ለጥቂት ቀናት ደብረ ታቦር ከልጃቸው ጋር ሰንብተው ወደ ትውልድ ቦታቸው ናባጋ ጊዮርጊስ መጡ። በእድሜያቸው መጨረሻ ዝምተኛ ሆነው ነበር ቀድሞ በሠሩት ሥራ እየተጸጸቱ አንደበታቸውን ከነገር ዘርቅ ከለከሉ። ከጥሩ ምግብና ከጥሩ መጠጥ ተቆጠቡ። ቅዱሳን መጻሕፍትን ሰብስበው «መሳቂያና መሳለቂያ አደረግዃችሁ» እያሉ ይቅርታ ይጠይቁ ነበር ይባላል። በዚህ ሁኔታ ከሰነበቱ በዃላ በ 84 ዓመታቸው የካቲት 1898 ዓ .ም . ዐረፉ። አለቃ ገብረ ሐና ብብዙ ሰዎች ዘንድ በቀልደኝነታቸው ይታወቁ እንጂ በቤተክርስቲያን ታሪክ ወደር ከማይገኝላቸው ሊቃውንት አንዱ ነበሩ። አለቃ ለማ ኃይሉ (የደራሲ መንግስቱ ለማ አባት ) ሰለ አለቃ ገብረ ሃና ሊቅነት ሲናገሩ « የሞያ መጨረሻ እርሳቸው አይደሉም ወይ ? የሐዲስ መምህር ናቸው። የፍትሐ ነገስት መምህር ናቸው። መርሐ እውሩን፤ አቡሻሩን የሚያውቁ ባለሙያ ናቸው። ለዚህ ለዝማሜ እሚባለው ለመቋሚያ እገሌ ይመስለዋል አይባልም። ከገብረ ሐና ፊት የሚዘም የለም።» ብለዋል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴም «አለቃ ገብረ ሐና እጅግ የተማሩ የጎንደር ሊቅ ነበሩ። በዚህም በላይ ኃይለ ቃልና ጨዋታ ያውቁ ነበር» በማለት ይገልጿቸዋል። (ምንጭ (ዚና ሰኔ 1999)) ።በ 1998 ዚና እንዳጻፈው ደግሞ አለቃ ገብረ ሃና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቅ ሲሆኑ አቋቋምና ዜማ ቅኔ ከእነ አግባቡ የሚያውቁ እንደነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል። አለቃ ባልሳሳት የነበሩበት በአጼ ምንይልክ ዘመን ይመስለኛል። በቅርቡ የሳቸውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃውንት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ የታተመ ስለኆነ ስለሳቸውም ኆነ ስለሌሎች ባለ ታሪኮች ጥሩ ግንዛቤ ይኖረናል እላለሁ። አሳታሚው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ሲኆን በቅርቡ በገበያ ላይ እንደ ሚውል ተስፋ አለኝ።

/////////////////////////////////////////////


አለቃ ገብረ ሐና
ከWikipedia
ከህይወት ታሪካቸው ስንጀምር አንዳንዶች የአባታቸው ስም ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ። ምናልባት አንዱ የአለም ሌላው ደግሞ የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናብጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኃላ ወደ ጎጃም ተሻግረው ቅኔን ተቀኙ። ከዚያም ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሰው ከመምሕር ወደ አብ ወልደ ማርያም ጽዋትወ ዜማ፤ ከባሕታዊ ገብረ አምላክ አቋቋም፤ ከዐቃቤ ስብሃት ገብረ መድሕን ትርጓሜ መጽሐፍትን እንዲሁም ድጓን ተምረዋል። በዚህ የሰፋ እውቀታቸው የተነሣ በ26 ዓመታቸው ጎንደር ሊቀካህናትነት ተሾመው ነበር። በዚህም ሹመት ለሰባት ዓመት ማገልገላቸው ይነገራል። በፍትሐ ነገሥት ሊቅነታቸው ደግሞ በዳኝነት እየተሰየሙ አገልግለዋል። አለቃ ገብረ ሐና ጨዋታ አዋቂነታቸው እየታወቀ የመጣው በዚህ ወቅት ነበር። በዚህም እውቀታቸው የትንሹ ዓሊ አጫዋች ሆኑ። አጼ ቴዎድሮስ ሥልጣኑን ሲይዙ አለቃን በቤተ መንግሥት አገኟቸው። አለቃ የቤተ መንግሥቱን ሰዎች በቀልዳቸው ሸንቆጥ ስለሚያደርጉ መስማማት አልቻሉም ነበር። እንዲያውም ዐጼ ቴዎድሮስ «ገብረ ሐና ፍትሐ ነገስቱን ጻፍ፤ ፍርድ ስጥ .. ገንዘብ ያውልህ፤ ቀልድህን ግን ተወኝ።» ሲሉ ተናግረዋቸው ነበር ይባላል። አለቃ ግን አላቆሙም።
በተለይም ደግሞ በንጉሡ ባለሟል በብላታ አድጎ ላይ «አድግ / በግእዝ አህያ ማለት ነው /» እያሉ በሚሰነዝሩት ትችት በተደጋጋሚ ተከሰው ዐጼ ቴዎድሮስ ዘንድ ቀርበዋል። በመጨረሻ ቴዎድሮስ ክስ ሲሰለቻቸው ምላስ ቀርቶ ታገሉና ተሸናነፉ ብለው ፈረዱ። በዚህም ትግል ምሁሩ አለቃ ተሸነፉ። ንጉሡም እንግዲህ ምን ይበጅህ? ሲሉ ጠየቋቸው አለቃም «ድሮስ ትግል የአህያ ሥራ አይደል» ብለው በመመለሣቸው ከአካባቢያቸው ለማራቅ ሲሉ ንጉሡ ገብረ ሐናን ለትግራይ ጨለቆት ሥላሴ አለቃ አድርገው በመሾም ወደ ትግራይ ላኳቸው። ወደካቶሊክነት የተቀየረውና ከአንቷን ዳባዲ ጋር በዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን ስለሆነው ሁሉ ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው የዋድላው ሰው ደብተራ አሰጋኽኝ ጥር 1858 ዓ.ም. ለአንቷን ዳባዲ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ይህን ሁኔታ ገልጦት ነበር «አለቃ ገብረ ሐናን ንጉሥ መቱዋቸው። ወደ ትግሬ ወደ ላስታ ተሰደዱ። እጅግ ተዋረዱ እኔም በዋድላ አገኘኋቸው ወደ ቆራጣም ሄዱ» ሲል ጽፏል።
ደስታ እንዳለ ሁሉ መከራም ያለ ስለሆነ ሁለቱንም በጸጋ መቀበል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ ነው። ካህናት በአጼ ቴዎድሮስ ላይ ባመጹ ጊዜ በአድማው ካሉበት ካህናት መካከል አንዱ ገብረ ሐና መሆናቸው ስለታወቀ ዐጼ ቴዎድሮስ በአለቃ ገብረ ሐና ላይ አምርረው ሊቀጧቸው ዛቱ። አለቃም ሸሽተው ጣና ሐይቅ ሬማ መድኃኔዓለም ገዳም ገቡ። በዚያም ባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ የተባሉ የአቋቋም ሊቅ አገኙ። ሁለቱም ተወያይተው በጎንደር አቋቋም ስልት የመቋሚያውን የአካል እንቅስቃሴ ጨምረው ዝማሜውን አዘጋጁት (በኋላ ተክሌ አቋቋም እየተባለ የሚታወቀው ነው)። ባህታዊ ጸዐዳ «ከእንግዲህ እኔ ወደ ዓለም አልመለስም፤ አንተ ይህንን ስልት አስተምር» ብለው አለቃ ገብረሐናን አደራ አሏቸው። ከዐጼ ቴዎድሮስ ሞት በዃላ በ1864 ዓ.ም. ዐጼ ዮሐንስ ሲነግሡ ከገዳም ወጥተው ወደ ትግራይ አቀኑ። በመቀጠልም በቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ የሚያውቋቸው ምኒልክ በሸዋ መንገሣቸውን ተከትለው ሸዋ መጡ።
ዐጼ ምኒልክ በዐጼ ቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ አለቃ ገብረ ሐናን ስለሚያውቋቸው በደቡብ ጎንደር የሚገኘውን የአቡነ ሐራን ገዳም ሾሟቸው። በዚያም ጊዜ በአካባቢው ከባድ ርሃብ በመከሠቱ አለቃ ከገዳሙ ብር አንድ ሺ አውጥተው ለገበሬዎች አከፋፈሏቸው። በዚህም ተግባራቸው ተከስሰው ወደ አዲስ አበባ መጡ። የፍርድ ሚኒስቴር የነበሩት አፈ ንጉሥ ነሲቡ ስሕተት ነው ብለው ፈርደውባቸው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ በምኒልክ ዘንድ ስለተሰማ ወደ ዙፋኑ ችሎት ተሻገረ። ዐጼ ምኒልክም ይህ ተግባር ያሸልማል እንጂ አያስቀጣም ብለው በመፍረዳቸው አለቃ ነጻ ወጡ። ንጉሥ ምኒልክ አለቃን የእንጦጦ ራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። እርሳቸውም ትርጓሜ መጻሕፍትን ያስተምሩ ነበር። ጥቂት ጊዜ በአዲስ አበባ እንደ ተቀመጡ እንደገና ወደ ጎንደር ተመልሰው፤ ድንግልናቸውን አፍርሰው ወይዘሮ ማዘንጊያን አገቡና ተክሌ የተባለ አንድ ወንድ ልጅና በፍታ የተባለች ሴት ልጅ ወለዱ። አንዳንድ ሊቃውንት አለቃ ገብረ ሐና ሊቅ፤ መልከመልካምና የነገሥታቱ ወዳጅ በመሆናቸው በዚያ ዘመን የነበሩ ሴቶች ወዳጅነት ለማበጀት ይሻሙባቸው ነበር ይላሉ። አለቃ ድንግልናቸውን ያፈረሱት ሆን ብለው ሳይሆን እኔ አስፈርሰዋለሁ በሚል የወይዛዝርት ውድድር የተነሣ ነው ይባላል። የአለቃ መንፈሳዊ ሕይወት የተናጋው ከዚያ በዃላ ነው ይባላል። ተክሌ ለትምህርት ሲደርስ ከሌላው የቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር እርሳቸው ከባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ ጋር ሆነው ያዘጋጁትን ዝማሜ አስተማሩት። አለቃ ገብረ ሐና ደርቡሽ ጎንደርን ሲወርር ልጃቸውን ወደ ወሎ ልከው እርሳቸው ጎጃም ውስጥ ዘጌ ገዳም ገቡ። በዃላም ዐጼ ምኒልክ ደርቡሽን ለመውጋት ወደ ፎገራ መምጣታቸውን ሲሰሙ፤ ከተደበቁበት ወጥተው ንጉሡን ተከትለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ምኒልክም እንደገና የራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። ልጃቸው አለቃ ተክሌ ወሎ ንጉሥ ሚካኤል ዘንድ እያሉ የተንታ ሚካኤል በዓል ሲከበር ከአባታቸው የተማሩትን ዝማሜ በተመስጦ አቀረቡት። ንጉሥ ሚካኤልም በዚህ ተደንቀው በዚያው በተንታ እንዲያገለግሉ አደረጉ። የተክሌ ዝማሜ በይፋ የተጀመረው ያኔ ነው ይባላል። በዃላ ራስ ጉግሣ የአለቃ ተክሌን ዝና ሰምተው ንጉሥ ሚካኤልን በማስፈቀድ ወደ ደብረ ታቦር አምጥተው የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሾሟቸው። አለቃ በአዲስ አበባ እያሉ ከመኳንንቱ ከመሳፍንቱ ጋር ያላስማሟቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። የመጀመርያው ትንባሆ ይጠጣሉ ተብሎ የተነገረው ሐሜት አንድ ቀን በቅኔ ማኅሌት ፒፓቸው ወድቆ በመጋለጣቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአድዋ ጦርነት ታላቅ ጀብዱ ለፈጸሙት ለደጃዝማች ባልቻ ዐጼ ምኒልክ የሚወዷትን ጎራዴያቸውን ሲሸልሟቸው «ወይ ጎራዴ ወይ ጎራዴ ከቤቷ ገባች» በማለት በሽሙጥ በመናገራቸው ባልቻ እገላለሁ ብለው ተነሡ። ይህም አልበቃ ብሏቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በነገር ተኳረፉና መላ የቤተመንግሥቱ ሰው አደመባቸው። ዐጼ ምኒልክ አለቃን ምን ቢወዷቸው በተለይ ከደጃች ባልቻና እቴጌ ጣይቱ ጋር የፈጠሩትን ጠብ አልወደዱላቸውም። በዚህ ምክንያት አለቃ ገብረ ሐና ከአዲስ አበባ ለቅቀው እንዲወጡ ተወሰነባቸው። በጎንደርና በወሎ ጥቂት ጊዜ ከሰነበቱ በዃላ ልጃቸውን ገብረ ሐና ሞተ ብለህ ተናገር ብለው አዲስ አበባ ላኩት። አለቃ ተክሌ ይህንን መርዶ በቤተመንግሥቱ ሲያረዱ ምንም እንኳ ገብረ ሐና ከብዙዎቹ ጋር ቢኳረፉም ታላቅ ሐዘን ሆነ። ከተወሰኑ ቀናት በዃላ አለቃ ራሳቸው አዲስ አበባ ገቡና ጉድ አሰኙ። ምኒልክም አስጠርተው ሞቱ ከተባለው በዃላ ከየት መጡ ቢባሉ «በሰማይ ጣይቱ የለች፤ ምኒልክ የለ፤ ጠጅ የለ፤ ጮማ የለ፤ ባዶ ቤት ቢሆንብኝ ለጠባቂው ጉቦ ሰጥቼ መጣሁ።» ብለው ሁሉንም አሳቋቸው። ጣይቱም መኳንንቱም ይቅር አሏቸው። አለቃ ገብረ ሐና እድሜያቸው እየገፋ አደብም እየገዙ መጡ አዲስ አበባ ተቀምጠውም ትርጓሜ መጽሐፍት ማስተማር ቀጠሉ። ዐጼ ምኒልክ የአብያተ ክርስቲያናቱን የግብዝና መሬት ለመኳንንቱ በመስጠታቸው ካህናቱ ምንም ባለ ማግኘታቸው የተቆጡት አለቃ ገብረ ሐና ተቃውሟቸውን በቀልድ ለዐጼ ምኒልክ አቀረቡ። ይህም ከወይዛዝርቱና ከመኳንንቱ ጋር መልሶ አጋጫቸው። ከዚህ በዃላ አዲስ አበባ መቀመጥ ስላልቻሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ደብረ ታቦር ተመለሱ። ያኔ ልጃቸው አለቃ ተክሌ ደብረ ታቦር ኢየሱስን እልቅና ተሾመው ነበር። ለጥቂት ቀናት ደብረ ታቦር ከልጃቸው ጋር ሰንብተው ወደ ትውልድ ቦታቸው ናባጋ ጊዮርጊስ መጡ። በእድሜያቸው መጨረሻ ዝምተኛ ሆነው ነበር ቀድሞ በሠሩት ሥራ እየተጸጸቱ አንደበታቸውን ከነገር ዘርቅ ከለከሉ። ከጥሩ ምግብና ከጥሩ መጠጥ ተቆጠቡ። ቅዱሳን መጻሕፍትን ሰብስበው «መሳቂያና መሳለቂያ አደረግዃችሁ» እያሉ ይቅርታ ይጠይቁ ነበር ይባላል። በዚህ ሁኔታ ከሰነበቱ በዃላ በ84 ዓመታቸው የካቲት 1898 ዓ.ም. ዐረፉ። አለቃ ገብረ ሐና በብዙ ሰዎች ዘንድ በቀልደኝነታቸው ይታወቁ እንጂ በቤተክርስቲያን ታሪክ ወደር ከማይገኝላቸው ሊቃውንት አንዱ ነበሩ። አለቃ ለማ ኃይሉ (የደራሲ መንግስቱ ለማ አባት) ሰለ አለቃ ገብረ ሃና ሊቅነት ሲናገሩ « የሞያ መጨረሻ እርሳቸው አይደሉም ወይ ? የሐዲስ መምህር ናቸው። የፍትሐ ነገስት መምህር ናቸው። መርሐ እውሩን፤ አቡሻሩን የሚያውቁ ባለሙያ ናቸው። ለዚህ ለዝማሜ እሚባለው ለመቋሚያ እገሌ ይመስለዋል አይባልም። ከገብረ ሐና ፊት የሚዘም የለም።» ብለዋል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴም «አለቃ ገብረ ሐና እጅግ የተማሩ የጎንደር ሊቅ ነበሩ። በዚህም በላይ ኃይለ ቃልና ጨዋታ ያውቁ ነበር» በማለት ይገልጿቸዋል። (ምንጭ (ዚና ሰኔ 1999)) ።በ1998 ዚና እንዳጻፈው ደግሞ አለቃ ገብረ ሃና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቅ ሲሆኑ አቋቋምና ዜማ ቅኔ ከእነ አግባቡ የሚያውቁ እንደነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል። አለቃ ባልሳሳት የነበሩበት በአጼ ምንይልክ ዘመን ይመስለኛል። በቅርቡ የሳቸውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃውንት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ የታተመ ስለኆነ ስለሳቸውም ኆነ ስለሌሎች ባለ ታሪኮች ጥሩ ግንዛቤ ይኖረናል እላለሁ። አሳታሚው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ (ዳንኤል አበራ፣ 2000 ዓ.ም.)

/////////////////////////////////////////////

1 እሳት የማያጠፋው ውሀ፡
2 ቀበጡዋ እመቤት
3 ሁለቱ እብዶች
4 የእብድ አናጺ
5 ስጋ ሻጭ ና አብዱ
6 ጎጃምን ምታ ጎንደርን ምታ
7 'አለቃ ገብረ ሐና እና ቀልዶቻቸው' ተዘጋጀ በዳንኤል አበራ 2000 አ.ም.
8 ሃድጎ -አህያ ሸራህያ
9 ጎመን እያበሰልሁ ነው
10 አይ ጎራዴ አይ አስተጣጠቅ
11 እንደምን አደራችሁ
12 እሱን ይጨርሱና
13 አሸነፈቻቸው
14 ሌላ እደግሞታለሁ
15 እያሳራኝ ነው
16 አለቃ ገብረ ሃና ሞቱ
17 አሬን ስበላ ከረምሁ (1)
18 አሬን ስበላ ከረምሁ (2)
19 አምባው ተሰበረ
20 አለመመጣጠን
21 አለቃ ወረኃና በጣም አጭር - ድንክዬ ሰው ናቸው
22 ገብተሽ አልቀሽ
23 ለሰማይ የምትቀርቢ
24 እዚያም ቤት እሳት አለ
25 በጃቸው
26 ደርቆ ተንጣጣ
27 እሷ ትታቀፋለች
28 ውዳሴ ማርያም ልደገም
29 ቁጭ ብዬ ሳመሽ
30 ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ
31 አስበጂና ላኪልኝ
32 ማን ደፍሮ ይገባል
33 ምልምሎች
34 ጭን እያነሱ መስጠት
35 ዋናውን ይዘው
36 እኔ ለነካሁት
37 መውጫችንን ነዋ
38 ኩኩሉ
39 በጠማማ ጣሳ
40 አስደግፈውት አመለጡ
41 በሰው አገር ቀረሁ
42 ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው
43 የተልባ ማሻው ሚካኤል
44 ወላሂ ኑ እንብላ
45 ግም ግም ሲል
46 ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን
47 ከመሶብዎ አይጡ
48 የመጣሁበት ነው
49 ጠረር አርገሽ ቅጂው
50 ዝግንትሉ ሞልቷል
51 ጥፍር ያስቆረጥማል
52 የጓደኛህን ቀን ይስጥህ
53 በቁሜ ቀምሼ መጣሁ
54 ሺ ነዋ
55 ቡሊ የአለቃ አህያ
56 በጠማማ ቁና ሁለት ሁለት (1)
57 በጠማማ ቁና ሶስት ሶስት (2)
58 አለቃ አለ ዕቃ
59 ሰይጣኑ ይውለድህ
60 በሌባ ጣትሽ አታሳዪኝ
61 አንቺ ባይበላሽ (1)
62 አንቺ ባይበላሽ (2)
63 ቤቴ በየት ዞረህ መጣህ
64 መቋሚያዬን አቀብዪኝ
65 ባዶ ሽሮ
66 ነዪ ብዪ እንጂ
67 ገብርኤልና ሚካኤል ተታኮሱ
68 ለምን ደወልሽው
69 ቃታ መፈልቀቂያሽን
70 ጠረር አድርገሽ ቅጂው
71 አንድማ ግዙ
72 በጠርር ሄጄ በታህሳሥሥ
73 መልግጌ አባስኩት
74 ድንቼ
75 በነካ አፍህ
76 ተኖረና ተሞተ
77 መሞትዎት ነው
78 የአለቃ የልጅ ልጅ



እሳት የማያጠፋው ውሀ፡
ሰውየው ዳብዳቤ በመጻፍ ላይ ሳለ፡ ሠራተኛው በሩን በርግዳ ትገባና "ጌታዬ፡ ማድቤቱ በእሳት ተያይዟል" ትለዋልች። ባለቤትየው ገስግሶ እማድቤቱ ሲደርስም መለስተኛ እሳትና ምድጃው ላይ ተጥዶ የሚንከተከተውን ድስት ሙሉ ውሃ ያያል። በዚህ ጊዜ ተናዶ "አንች ደደብ፡ ወደኔ ከመምጣት ይልቅ የሚፍለቀለቀውን ውሃ አታፈሽበትም ኖሯል?" በማለት ቢገስጻት "ጌታዬ ውሃው'ኮ የፈላ ስለሆነ አያጠፋውም ብዬ ነው" ብላ አሳቀችው።


ቀበጡዋ እመቤት
እመቤቲቱ የባለቤታቸው ጦር ሜዳ መቆየት አላስችል ይላቸውና ከአንዱ ባሪያቸው ጋር የቀበጣሉ። እንዳየደርስ የለም ባል ሳይጠበቁ ከች ይላሉ። ሚስጥራቸው እንዳይወጣ ያሰቡት ሚስትም ስራተኛቸውን ባፋጣኝ ወደባሪያቸው እንዲህ ብለው ይልካሉ 'ባለፈው የተፈጠረውን ነገር ለማነም እንዳትናገር'። ሰራተኛየቱም ብዙ ስዎች ይሰሩበት ወደነበር እርሻ ሄዳ አፋፉ ላይ ትቆምና ስሙን ጠርታ 'እመቤቴ የባለፈውን ነገር ለማንም እንዳትናገር ብለውሃል'ትለዋለች። እሱም መለስ ያደርግና 'ምንም ችግር የለም እኔ ምኔ ሞኝ ነው እመቤቴን በ*ሁ ብዬ የማወራው' ብሎዋት እርፍ። ተፈጸመ


ሁለቱ እብዶች
ሁለት እብዶች ከአማኑኤል ሆስፒታል ዘበኛውን አታልለው ለማምለጥ ይመካከራሉ። በምክራቸው መሰረት ወደመግቢያው ሲያመሩ ዘበኛው በአካባቢው የለም። በመጥፋት ፋንታ እቅዳቸው እንደተበላሸ በማሰብ ወደነበሩበት ተመለሱ።


የእብድ አናጺ
አማኑኤል ሆስፒታል ውስጥ አንዱ እብድ ፎቶ ግድግዳ ላይ ለመስቀል ፈልጎ ሚስማሩን ገልብጦ በመዶሻ ግድግዳው ላይ ለመምታት ይታገላል:: አንድ ሌላ እብድ ባጠገቡ ሲያልፍ ያየውና በሳቅ ይሞታል:: ይሄኛው እብድ ምን ያስቅሃል ይለዋል; እሱም ዝም ብለህ ትለፋለህ የያዝከው ሚስማር እኮ የተሰራው ለዛኛው ግድግዳ ነው ብሎ የሚስማሩ ጫፍ ውደሚያሳይበት ግድግዳ አሳየው::


ስጋ ሻጭ ና አብዱ
አንድ አብድ በስጋ መሽጫ ሱቅ በር ላይ ቆም ሲል ያየ ስጋ ሻጭ በጭራው ሊያስፈራራው አየሞከረ ፤ አትሄድም ከዚህ አንተ አብድ ፡ብሎ ይጮህበታል አብዱም ሳቅ ብሎ <የሞተ ፣አሬሳ ስቅለህ ዝንቡን አሽ ፣አሽ ስትል የምትውል አብድስ አንተ ...> ብሎት አርፍ


ጎጃምን ምታ ጎንደርን ምታ
አንድ በጣም ወፍራም ሴትዮ የእንጦጦን ጋራ በእግራቸው ለመውጣት ይያያዙታል ። ሲደክማቸው ኋላቸውን ዞር በማለት እየተመለከቱ በማረፍ ሲጓዙ አንዴ ፈሳቸውን ብው ሲያደርጉ «ጎጃምን ምታ !» ይላሉ ። አሁንም ወጥተው ወጥተው ሲደክማቸው ዞር ብለው በማየት ፈሳቸውን « ብም ..ብም ..ቡዋ !» ሲያደርጉት «ጎንደርን ምታ !» ይላሉ። በመጨረሻም ዞር ዞር ብለው በመመልከት ፈሳቸውን «ጣጣጣጣጣ ..ጥጥጥጡዋ » ሲያደርጉት «ትግራይ ላይ ወያኔን ምታ !» ብለው ዞር ሲሉ አንድ ዱርዬ ተማሪ ከኋላቸው ቆሞ ያዩታል ። ከዚያም «ውይ ! ልጄ የት ነበርክ ?» ሲሉት «ጎጃምም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ : ጎንደርም ወያኔም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ» ሲላቸው : «ውይ ልጄ ! እናትም የለህ ?» ሲሉት ምን እንዳለ ታውቂያለሽ ? ቂቂቂቂቂ ... «ታዲያ እናት ቢኖረኝ ይታራብኛል እንዴ ?» ብሏቸው አረፈው እልሻለሁ።

ሃድጎ -አህያ ሸራህያ
1. ጋዜጠኛው አረፋይኔ ሀጎስ ስለ አለቃ ገብረ ሃና መጽሀፍ ጽፏል። ታዲያ አለቃ ከአጼ ተዎድሮስ ጊዜ ጀመሮ የነበሩ የቤተክርስቲያን ምሁር እንደሆኑ ነው መጽሀፉ የሚያወራው።ከጊዜው ቀልዳቸው አንዱ እንዲህ ይላል። በአጼ ተዎድሮስ ቤተመንግስት ሀድጎ የሚባል ባለሟል ነበረ ታዲያ ምንም እንኳን ንጉሱ ቀልድ የማያውቁ ኮስታራ ቢሆኑም አለቃ ግን መኮመኪያ ምክንያት አላጡም። እናም ሀድጎን ባገኙት ጊዜ ሁሉ ሀድጊ ብለው ነበር አሉ የሚጠሩት። አህያ ለማለት።ሀድጎም መረረውና ጃንሆይ ዘንድ ከሰሳቸው።. ንጉሱ አለቃን አስጠርተው ለምን ሀድጊ እያሉ እንደሚሳደቡ ቢጠይቋቸው አይ ጃንሆይ እኔ «አህያ ሸራህያ» እያልኩ ስጸልይ ሰምቶኝ እንጂ አልሰደብኩትም ብለው በብልሀት አመለጡ።


ጎመን እያበሰልሁ ነው
2. በእመቤታችን በፍስለታ ጾም አለቃ ቤተክርስቲያን አገልግለው ሲመለሱ ባለቤታቸው ማዘንጊያ የሚበላ ነገር በጎመን ይሰጧቸዋል ጎመኑ አልበስሎም ኑሮ ከምግብ በዃላ አለቃ ኆዳቸውን ወደሳቱ ጠጋ አድርገው ያሻሻሉ። ማዘንጊያ ነገሩ ገርሟቸው አለቃ ምን እያደረጉ ነው ይሏቸዋል አለቃም በአሽሙር ጎመኔን እያበሰልሁ ነው አሉ ይባላል።


አይ ጎራዴ አይ አስተጣጠቅ
3. አንድ የሚኒልክ መኮንን ስልብ ነበሩ ይባላል። መኮንኑ አንድ የጀግንነት ስራ ይሰሩና ሙሉ ትጥቅ ከነልብሱ ይሸለማሉ። አለቃን ያገኟቸውና “አለቃ እንዴት ነው?” “አላማረብኝም” ይላሉ።አለቃም መልሰው “አይ አስተታጠቅ አይ አለባበሥ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ” ይላሉ። ሌሎች መኳንንት መኮንኑን አለቃ ምን አሉህ? ይሉታል አደነቁኝ አይ አስተታጠቅ አይ ጎራዴ አሉኝ ይላል።መኳንንቱም ምን አደነቁህ ሰደቡህ እንጂ ስልብ ስለሆንክ ጎራዳ ነህ - አይ ጎራዴ -የኔ ጎራዳ ነው ያሉህ ብለው አብግነውት አለቃን ካልገደልኩ ብሎ በገላጋይ ነው አለቃ የተረፉት አሉ።


እንደምን አደራችሁ
4. አለቃ ሀሳባቸውን በሰምና ወርቅ በመግለጽ ጥበባቸው ተወዳዳሪ የላቸውም ይባላል። ታዲያ አንድ ቀን አንድ አውቃለሁ ባይ ሰውዬ ስለእርሳቸው ቅኔያዊ አነጋገር ምንም ቦታ እንደማይሰጥና በቅኔ ቢሰድቡት እርሱ ደግሞ ከዚያ በላይ በቅኔ መልሶ ሊሰድባቸው እንደሚችል ጉራውን ይነዛል። ጉራውንም የሰሙት ሰዎች አይ አንተ ሰው! ስለማታውቃቸው ይሆናል እንጂ የሚቻሉ አይደሉም። ይሰድቡሀል። ለማንኛውም ከፈለካቸው ወደገበያው መሄጃ መንገድ አከባቢ ስለማይታጡ ብቅ ማለት ትችላለህ ይሉታል። ሰውዬውም ቢያገኛቸው ለቅኔያቸው የሚሰጠውን መልስ እያሰላሰለ አህያውንም እየነዳ ወደ ገበያ ሲሄድ ያገኛቸዋል። ከዚያም ሰውዬው «አለቃ እንደምን አደሩ?» ይላቸዋል። አለቃም ትኩር አድርገው ያዩትና የተንኮል ሰላምታ መሆኑን በመረዳት «እግዚአብሄር ይመስጌን ደህና ነኝ! እናንተስ ደህና አደራችሁ ወይ?» ብለው በትህትና ለሰላምታው መልስ ሰጥተው ይሸኙታል። ሰውዬውም ስላልተሰደብኩኝ መስደብ የለብኝም ብሎ እየተኩራራ ይመለስና እነዚያን ሰዎች ያገኛቸዋል። ኧሃ ከአለቃ ጋር ተገናኛችሁ? ምንስ ብለው ሰደቡህ? ሲሉት እርሱም አይ ምንም አልሰደቡኝም እንዲያውም በትህትና ሰላምታ ተለዋወጥን። እኔን ሊሰድቡኝ አይችሉም ብያችሁ የለም? አለ። እስቲ እንዴት ነበር የተባባላችሁት ሲሉት አይ እኔ አለቃ እንዴት አደሩ ስላቸው እሳቸውም በትህትና አንገታቸውን ዝቅ አድርገው “እግዚአብሄር ይመስጌን እናንተስ እንዴት ናችሁ ነው” ያሉኝ አላቸው። ሰዎቹም ካንተ ጋር ሌላ ሰው ነበረ ወይ ሲሉት ኧረ የለም አህያዬን እየነዳሁ እሄድ የነበርኩ እኔ ብቻ ነበርኩኝ ሲላቸው አይ ወንድሜ ! አንድ ሰውማ እንዴት አደራችሁ አይባልም አንተን ከአህያህ ጋር አንድ አድርገው በመቁጠር ነው እንዴት አደራችሁ ያሏችሁ ብለው የሰውየውን መሸነፍ እና አህያ መባል አበሰሩለት አሉ።


እሱን ይጨርሱና
(5) አለቃን አንዲት ጉብል ነች አሉ ያሸነፈቻቸው።ዝናዋን ይሰሙና ልጅቱዋ ቤት ሄድው አሳድሩኝ ይላሉ። ቤት ለእንግዳ ይባሉና እራትም በልተው የሚተኙበትን መደብ ጉብሊቱዋ ታሳያቸውና ትንሽ አጎዛ (የበግ /የፍየል ቆዳ) አምጥታ ትሰጣቸዋለች። አለቃም ይቺማ ታንሰኛለች ሌላ ጨምሪልኝ ይላሉ። ጉብሉዋም እሱን ይጨርሱና አክልሎታለሁ አለቻቸው አሉ።


አሸነፈቻቸው
(6) እሩቅ አገር ሄደው መሽቶባቸው ከሚያውቋቸው ቤተሰብ ቤት ደርሰው አርፈዋል። ቤተሰቡም ካስተናገዳቸው በኋላ በይ መደቡ ላይ አንጥፊላቸው ብለው እናቱዋ ለልጂቱ ይነግሩዋታል። ልጅቷም የአንድ ትንሽ ፍየል አጎዛ ወስዳ ታነጥፍና ትመጣለች። አለቃ አንጥፌልዎታለሁና ሄደው ሊተኙ ይችላሉ ትላቸዋለች። ሄደው ሲመለከቱ አጎዛዋ እጅግ ትንሽ ከመሆኗ የተነሳ መደቡ መሐል ሆና አንሳ ትታያቸዋለች። ይሄኔ ይህች ድብዳብ እንድተኛባት መቼ ትበቃኛለች ይሏታል። ልጅቱም ስትመልስላቸው እሱን ከጨረሱ በኋላ እጨምርልዎታለሁ አለቻቸው ይባላል።


ሌላ እደግሞታለሁ
(7) አለቃ ገብረ ሀና እጅግ በጣም ታዋቂና በነገር እንደማይሸነፉ በብዛት ሲወራ ሰምቻለሁ አንድ ወጣት ኮረዳ ግን እንዳሸንፈቻቸው ይነገራል እስቲ .. አለቃ ወደመንገድ ሲሂዱ ይመሽባቸውና ወደሰው ቤት ጎራ ብለው የመሸብኘ መንገደኛ ነኝ ብለው ይጠይቃሉ። ባለቤቶቹም ቤት ለንግዳ ብለው ያስገቧቸዋል። ምግብ በላልተው መኝታ ደረሰ። አለቃ አይናቸው ቁልጭ ቁልጭ ሲል ኮረዳዋ «አለቃ ምን ፈለጉ?» ስትላቸው ልጄ ጎኔን የማሳርፈበት ነገር አምጪልኝ አሏት። እሷም እሺ ብላ አንድ የበግ አጎዛ ሰጠቻቸው። እሳቸውም «ምነው ልጄ ይህቺ ትበቃኝ» ሲሏት፤ «እሷን ሲጨርሱ ሌላ እደግምዎታለሁ» አለች ይባላል።


እያሳራኝ ነው
(8) አንድ ከዚህ በፊት የተረቡት ሰው መንገድ ላይ አግኝቷቸው ሊደብደብ ሲያባርራቸው እሳቸውም ሲሮጡ ቆይተው ሊደርስባቸው ሲሆን ቶሎ ብለው ሱሪያቸውን ፈተው ለመጸዳዳት ቁጭ ይላሉ። አለቃ በነበሩበት ዘመን ይትባሃሉ ሰው ጠላትም ቢሆን የሚገደለው፤ የሚደበደበው ከነሱሪው እንጂ ሱሪ አውልቆ አይደለም። ይሄ ወንድምነትም አያሰኝም። መለኛው አለቃ ይቺን ሰሩዋ። ሰውየውም ሊነርታቸው (ሊያሳራቸው) እስኪነሱ አጠገባቸው ቆሞ ይጠብቃል። እሳቸው ቁጭ እንዳሉ ሰውየው እንደቆመ ሁለቱን የሚያውቅ ሰው በመንገዱ ሲያልፍ ሰላም ብሏቸው የሁለቱ ነገር ገርሞት «ምን እያደረጋችሁ ነው?» ይላቸዋል። አለቃም ፈጠን ብለው «እያሳራኝ ነው።» ብለው መለሱ። ሊደበድባቸው የነበረው ሰውዬ በመልሳቸው ስቆ ትቷቸው ሄደ አሉ።


አለቃ ገብረ ሃና ሞቱ
(9) አለቃ በጣም ቸገራቸውና ልጃቸውን ሂድና ንጉስ ሚኒሊክን አባቴ ሞቶ ግን ተስካሩን የማወጣበት ገንዘብ የለኝም ብለህ ገንዘብ ተቀብለህ ና ብለው ላኩት። ልጅም እንደተባለው ወደ ቤተመንግስት ሂዶ ያባቱን ከዚህ አለም በሞት መለየት ነግሮ እንደተባለው ገንዘቡን ይጠይቃል። ምኒሊክም እጅግ በጣም አዝነውና አልቅሰው ገንዘቡን ሰጥተው ይልኩታል። አለቃም ችግራቸውን ከተወጡ በኋላ ምኒሊክን ሊያዪ ጉዞ ወደ አ.አ. ያቀናሉ። በቤተመንግስቱም ያያቸው በመገረም እን...ዴ? አለቃ ሞተው አልነበር በማለት እየተገረሙ ለምኒሊክ ሊነግሩ ተጣደፉ። ሚኒሊክም ሲያዩአቸው ገብረሀና ሞተህም አልነበር ቢሏቸው አለቃም እንደርሶ የሚስማማኝ ንጉስ ባጣ ተመልሼ መጣሁ ብለው ንጉሱን አሳቋቸው አሉ።


አሬን ስበላ ከረምሁ
(10) አለቃ የሚኖሩበት አካባቢ ድርቅ ጠንቶ ሁሉም ስደት ገባ።አለቃም ሲጓዙ ውለው ጥሩ አካባቢ ይደርሱና የግዜር መንገደኛ ነኝ ብለው አንዷን ባልቴት ለምነው ሊያድሩ ይፈቀድላቸዋል። ሌሊት ላይ ከመደባቸው ይነሱና ባልቴቱዋ ምኝታ ጋ ሄደው አይነ ምድራቸውን ተወጥተው ምኝታቸው ተመልሰው ባልቴቱዋን መጣራት ይጀምራሉ። ሴትየዋም «ምነው? ምን ሆኑ?» ስትላቸው ቤቱ አይነምድር አይነምድር ይሸታል እና መተኛት አቃተኝ ይላሉ። ሴትየዋም ኩራዟን ትለኩስና ፍለጋ ይጀመራል። አለቃም ተነስተው ወደ ባልቴቲቱ ምኝታ አካባቢ ሄደው እዚህ ነው እዚህ ነው ብለው ይጮሃሉ። «ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ እንዴት ቤት ውስጥ ትጸዳጃለሽ ባይሆን እኔ አለሁ አይደል እንውጣ አትይኝም» ብለው ድምፃቸውን የበለጠ ከፍ ያደርጋሉ። ሴትየዋም ጎረቤት እንዳይሰማባት ብላ አለቃን ትለምናቸዋለች። ከዚያም ትንሽ አጉረምርመው አክርሚኝ ይላሉ። በዚህ ተስማምተው፤ አለቃም ከርመው ያ የድርቅ ወቅት ያልፍና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚያውቃቸው ሰው አግኝቷቸው «እንዴት ከረሙ?» ይላቸዋል።አለቃም «አሬን ስበላ ከረምኩ» ብለው መለሱ አሉ።


አሬን ስበላ ከረምሁ
(11) አለቃ ገ /ሀና ከጎንደር አዱ ገነት አፄ ምኒልክ መናገሻ ለደጅ ጥናት ሰንቀው በወረሀው ፆም አካባቢ ይጓዛሉ። ጥኌት ወደ ቤተ መንግስት የወጡ ማታ ወደ ማደሪያቸው እየተመላለሱ የወረሀውን ፆም ጨርሰው ፍስክ ሲገባ ወደ ጠጅ ቤቶች ጎራ እያሉ መልከስከስ ይጀምራሉ። የያዙት ደረቅ ስንቅ አልቆ ወደ ማርትሬዛቸው ምንዘራ ጀምረዋል። ወርሀ ግንቦት ገብቶ ክረምቱ ሊጀምር ሲል ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረባቸው --ደጅ ጥናቱን ትተው ወደ ጎንደር ማቅናት ወይም እየተሟጠጠች ያለችውን ኪሳቸውን የሚያደልቡበት መንገድ መፈለግና ክረምቱን አራዳ ማሳለፍ፤ ደጅ ጥናቱንም መቀጠል። ታዲያ አንዷን የጠጅ ኮማሪት መሳም ከጀመሩ ቀኖች ተቆጥረዋል። አንድ ምሽት ግን ተንኮል አዘጋጅተው ኖሮ እሆን ብለው እዳሪያቸውን ሳይወጡ አብረው ይተኛሉ። ከሥራ በኌላ (ከመሳሳም በኌላ) እንቅልፍ መጥቶ የምኝታ ጓደኛቸውን እየረፈረፈ ሳለ፤ አለቃ ቀ .. ሰ . ስ ብለው ከጠፍር አልጋው እራቅ ብለው ይኮሱና ይዘውት ወደ አልጋው ቀ --ሰ --ስ ብለው ይጋደማሉ። ከዚያ የምኝታ ጓደኛቸውን (የጠጅ ቤቱን) ባለቤት መቀመጫ አካባቢ አብሰው የቀረውን ባካባቢው ያልከሰክሱታል። ሊቆዩ አስበው ሽታው ስላስቸገራቸው ሴትዮዋን መቀስቀስ ይገባሉ። ምነው ብለው ሲነቁ ሽታው እያድቀሰቀሰ የሚያመራው ወደሳቸው ጉያ መሆኑን የተገነዘቡ ኮማሪት። አለቃን። ስለፈጠረዎ በማሪያም ይዠወታለሁ። የሚፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ። ከመሀላችን እንዳይወጣ ማለት። ደጅ ጥናቱንም ቢሆን እስከሚሳካልዎ እዚሁ ከኔ ጋር መቆየት ይችላሉ አሏቸው። አለቃም አይዞሽ ምንም ችግር የለም ያለ ነው። አትሰቀቂ ብለው ያረጋጓታል። በዚህ አስባብ አለቃ ወደ ጎንደር ሳይዘልቁ ክረምቱን ያለምንም ችግር ያሳልፋሉ።በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ደጅ ጠኙ ሁሉ ምኒልክ ግብር ሲገባ እሳቸውም ይገኛሉ። በመገኘታቸው የተገረሙ አፄ ምኒልክም «እንዴ አለቃ እዚህ ምን ስትበላ ከረምህ?» ብለው ሲጠይቋቸው ህ ..ም ብለው «አሬን ስበላ ከረምሁ።» ብለው መመለሳቸውን ሰምቻለሁ።


አምባው ተሰበረ
(12) አለቃ ድንግላዊ መነኩሴ ነበሩ። በእነ አለቃ ዘመን ወይዛዝርት መነኩሴዎችን ካሳቱ ለነሱ ወይ ለቤተሰቦቻቸው የግብር ምህረት ይደረግላቸዋል አሉ። እንደጀግናም ይወደሳሉ። ሰለዚህ መነኩሴን ለማሳት እና ለመገናኘት የማይደረግ ጥረት የማይፈነቀል ድንጋይ የማይቧጠጥ ዳገት የለም። እንደሚታወቀው የታቦት ንግስ ቀን ድግስ በየቦታው ይኖራል።ካህናትም ይጠራሉ ይባርካሉ ይበላሉ ይጠጣሉ።አንድ ቅዳሜ ቀን በዋለ ንግስ እለት የእነአለቃም የካህናት ቡድን ከቀትር በኋላ ወደእነማዘንጊያ ቤት ተጉዞ ሲበሉ ሲጠጡ ሲጫወቱ ውለው አመሻሹ ላይ ድንግላዊው መነኩሴ ገብረ ሃና መጠጥ አዳክሟቸው ኖሮ ካህናት ጓደኞቻቸው እና የማዘንጊያሽ ቤተሰብ ይስማሙና አለቃ እዚያው እንዲያድሩ ትተዋቸው ይሄዳሉ። አለቃም አደሩ። አዳራቸው ግን የወትሮው አልነበረም። ከማዘንጊያ ጋር ነበር። ማዘንጊያም እንደጎጃሞች አምባው ተሰበረ እንደነጅበላ ይፈር የነበረ አሉዋ። መነኩሴው ድንግልናቸውን አፈረሱ። በማግስቱ አለቃ አዝነው ወደ ሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ሄደው የደረሰባቸውን ተናገሩ። ካህናቱም ምን ሲደረግ አሉ። አለቃም የእናንተስ ስራ ተገቢ ነው ጓደኛ ጥሎ መሄድ አሉ። አለቃና ማዘንጊያም ተጋቡ።


አለመመጣጠን
(13)ማዘንጊያን ካገቡ በሁዋላ የቁመታቸው ያለመመጣጠን ችግር ፈጥሮባቸው ነበር ይባላል። አለቃ በጣም አጭር ማዘንጊያ በጣም ረጅም! ታዲያ ሲራ ሲጀምሩ ቢያንስ ከማዘንጊያ ግማሽ አካል በታች መውረድ ግዴታቸው ነበር። በስራ ወቅት መሳሳምም ሆነ ማውራት አይመቻቸውም። ስለዚህ ስራ ሊጀምሩ ሲሉ በይ ማዘንጊያ ደህና ሰንብቺ እኔ ወደ ቆላ መውረዴ ነው ብለው ይሰናበታሉ ይባላል።


አለቃ ወረኃና በጣም አጭር - ድንክዬ ሰው ናቸው
(14)ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ደግሞ ሲበዛ 1ሜትር ከ80 ናቸው። መንገድ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ሠማዩን አይተው አለቃ ዝናብ ሊዘንብ ነው መሰለኝ ይሏቸዋል። ከዚያ አለቃ ከኋላቸው ኩስ ኩስ እያሉ ሲመልሱላቸው! «እኔ ምን አውቃለሁ ለሰማዩ ቅርቡ አንቺ ነሽ» አሏቸው ይባላል።


ገብተሽ አልቀሽ
(15)አንድ ቀን ከወዳጃቸው ዘንድ ድግስ ተጠርተው ሄደው እዚያ ውለው ወደ ቤታቸው ሲመጡ አሽከራቸው በር ሲከፍት አስቀደመው አለቃ ገብተው የባለቤታቸውን መግባት ሲጠባበቁ ትንሽ ዘግየት ስላሉ «እባክሽ ገብተሽ ገብተሽ አልቀሽ እንደሆን በሬን ልዝጋበት» አሉ። የቁመታቸውን መርዘም መናገራቸው ነው።


ለሰማይ የምትቀርቢ
(16)ወ /ሮ ማዘንጊያ የአለቃ የህግ ሚስት ረጅም ነበሩ። መንገድ አብረው ሲሄዱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ወደ ሰማይ ያዩና «አለቃ ዝናብ የሚዘንብ ይመስሎታል ብለው ይጠይቃሉ»። አለቃም ሲመልሱ “ለሰማይ የምትቀርቢ አንቺ አይደልሽም እንዴ?” “እኔ ምኑን አውቀዋለሁ” ብለው ባለቤታቸውን በቁመታቸው ምክንያት ተረቧቸው።


እዚያም ቤት እሳት አለ
(17)አለቃ የጎረቤት ፍቅር ይጀምሩና ባለቤታቸው ወ /ሮ ማዘንጊያ ዉኃ ሊቀዱ ሲወርዱ ጎረቢት ፍቅርን ልትቃመስ ትመጣለች። መጥታም ከአለቃ ጋር ሲንጎዳጎዱ ሳያስቡት ወ /ሮ ማዘንጊያ ቢደርሱባቸው ውሽምዬም ከመደንገጧ የተነሳ ልጅዋን ያነሳች መስሏት ያለቃን ልጅ አንጠልጥላ ትሮጣለች። ነገሩ የገባቸው ማዘንጊያም ልጁን አንስተው «አሁን እዚህ እሳት ውስጥ ልክተተው?» ቢሏቸው አለቃም ማዘንጊያ እዚያም ቤት እሳት አለ ብለው ልጁን አተረፉ አሉ። ከርታታ (Jun 11, 2005)


በጃቸው
(18)አለቃ በጣም ሴሰኛ መሆናቸው ይነገራል። በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት አይተዋት በመውደዳቸው ወላጆችዋን እንደምንም ብለው በማስፈቀድ ያገቧታል። አንሶላ የመጋፈፊያው ጊዜ ሲደርስ አለቃ ወረድ ብለው ስራ ሊጀምሩ ሲሉ እንትናቸው ተኝቶ አልነሳ እምቢ ይላቸዋል። ቢታገሉ ቢታገሉ አልተሳካላቸውም። ስለዚህ ሌላ አማራጭ በመውሰድ ለእጃቸው ተጨማሪ ስራ ሰጥተው ሲያሰሩ ያድራሉ። መከራዋን ስታይ ያደረች ልጅም ጠዋት ለሽንት እንደወጣች በዚያው ጠፍታ ወደ ወላጆችዋ ትሄዳለች። ችግሯን ግን ደፍራ አልነገረቻቸውም። ይሁንና አለቃ ሳያፍሩ ሽማግሌ ሰብስበው ወደ ልጂቱ ቤት ይመጣሉ። ሽምግልናም ይጀመራል። ለምን ትተሻቸው እንደመጣሽ፤ ምን እንደበደሉሽ ንገሪን ትባላለች። እንዴት ደፍራ ትናገር! ተቸገረች። በመጨረሻም ሲያዋክቧት ግራ ገባትና በእጃቸው .....ብላ የሚቀጥለውን መጨረስ ሳትችል ትቀራለች። አለቃም ምን ለማለት እንደፈለገች ይረዱና ወዲያውኑ ለሽማግሌዎች እስቲ እግዜር ያሳያችሁ! ድሮውንስ ላይበጀኝ ነው ያገባኋት በጃቸው የምትለኝ? ብለው ለጊዜው ጉዳቸው ሳይወጣ አሸንፈው ወሰዷት ይባላል።


ደርቆ ተንጣጣ
(19)አንድ ሰሞን አለቃ በጣም ቆንጆ ልጅ ያገባሉ። ከዚያም ያው እንደ ባህል ወጉ ልጂቱ እሳቸው ጋ ልታድር ቤታቸው ትሄዳለች። እናም ቀኑ ተገባዶ ማታ ላይ አለቃ ቆጥ ላይ ወጥተው ሲጠብቋት እሷ ማታ ወደ ቤተሰቦቿ ከድታ ልትሮጥ ከቤት ስትወጣ ውጪው እንደአጋጣሚ ዝናባማ ስለነበር አድልጧት ትወድቅና ተመልሳ ቤት ትገባለች። ቤት ገብታም ምድጃ ዙሪያ ተቀምጣ ልብሷን ስታደርቅ ሳት ይላትና ጡጥ ታደርጋለች። ይህን የሰሙት አለቃ «አንቺ አትተኝም?» ይሏታል። እሷም «እስኪ ይቆዩ ልብሴ ምጥጥ ምጥጥ ይበልልኝ» ትላለች። እሳቸውም እሺ ብለም ዝም ሲሉ ልጂቱ አሁንም ደግማ ዛጥ ታደርጋለች።በሁኔታው የተቆጡት አለቃ በስጨት ብለው «አንቺ አትተኝም?» ሲሏት። እሷ «እስኪ ይቆዩ...ልብሴ ይድረቅ ትላለች።» ከዚያም አለቃ ቀጥለው «ኧረ ...ኤዲያ ...ልብስሽ ደርቆማ እየተንጣጣ» ብለው ባሽሙር ጠቅ አረጓት ይባላል።


እሷ ትታቀፋለች
(20)የመሸባቸው መንገደኞች አለቃ ገብረሀና ቤት ምሽቱን ለማሳለፍ ይጠይቁና እንደ ባህሉ አለቃ “ቤት ለእንግዳ” ብለው ማደሪያ ይሰጧቸዋል። እንግዶቹም ፈረሶቻቸውን እደጅ አስረው ይገባሉ። አለቃንም «እባክዎ ፈረሶቹ እርቧቸዋልና ሳር ይስጡልን» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «ምን ችግር አለ ታዲያ ከውጭ አጭጄ አመጣላቸዋለሁ» ይላሉ። ነገር ግን የአንዱ እንግዳ አይን ማዘንጊያ ላይ ሲቁለጨለጭ ያጤኑት አለቃ፤ ነገሩ ስላላማራቸው ማዘንጊያን ነይ እስቲ ተከተይኝ ይላሉ። እንግዶቹም«ለምን እሳቸውን (ማዘንጊያን) ያደክማሉ?» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «አይደለም እኮ እንዲያው እኔ ሳጭድ እርሷ ትታቀፋለች ብዬ ነው» በማለት ስጋታቸውን በዘዴ ገለጹ።


ውዳሴ ማርያም ልደገም
(21)አለቃ ገብረሀና የማይለመድ ለምደው ማታ ማታ ሰራተኛቸው ጋ ብቅ ሳይሉ አያድሩም ነበር። አንድ ቀን ሰራተኛቸው ጋ አምሽተው ቆይተው ቀስ ብለው ተደብቀው ገብተው ይተኛሉ። ትንሽ እንደቆዩ እንደገና ያምራቸውና ቀስ ብለው ምንም ሳያሰሙ እራቁታቸውን ሊሄዱ ሲነሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ነቄ አሉና «አንቱ ወዴት ኖት በዚህ በጭለማ» ብለው ወይዘሮ ማዘንጊያ ሲጠይቋቸው። «ቆዪ እስኪ አንዴ ውዳሴ ማርያም ደግሜ ልምጣ»አሉ። «ታዲያ ውዳሴ ማርያም እራቆት ተኩኖ ነው የሚደገም?» «ምን ላድርግ? እራቁቴን ሆኜ እንኳን ብትሰማኝ» ብለው እርፍ።


ቁጭ ብዬ ሳመሽ
(22)ውሽምዬ አለቃ ሲወጡ ቤት ይመጣል እና ተማዘንጊያ ጋር ተላምደው ኖሯል።አለቃ ከውጭ ድክም ብሏቸው መጥተው ደጃፍ ያለች መደብ ላይ ቁጭ ብለዋል። ማዘንጊያም ከውሽምዬ ጋር የስንብት ሲሳሳሙ አለቃ አይተው ዝም ብለዋል። ውሽ...ም በጓሮ ተሸኝቶ ማዘንጊያ ወደ ደጃፍ ብቅ ሲሉ አለቃን ያዩዋቸዋል። «አለቃ መጥተዋል እንዴ?» ይላሉ። «እንዴ እዚህ ቁጭ ብዬ ሳመሽ አላየሽኝም እንዴ» ብለው ማዘንጊያ ሲሳሙ ማየታቸውን ተናገሩዋ። ታዲያ ይሙቱ እንዴ ታፍነው?


ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ
(23)አለቃ ከስራ በጣም ደክሟቸው ያለሰአት ወደ ቤት ይመጣሉ። ልክ እቤት እንደደረሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ሲያቃትቱ ሰምተው መቋሚያቸውን ጠበቅ አድርገው ወደ ቤት ሳያንኳኩ ..ሰተት ይላሉ ልክ እንደገቡ የሳቸው [የአለቃ] ቅርብ ጓደኛቸው አልጋቸው ላይ ከማዘንጊያ ጋር ጉዳዩን ተያይዞት ያያሉ። አለቃም ተገርመው «እና...ንተ» ቢልዋቸው። ማዘንጊያሽ እና ጓደኛቸው ደንግጠው «አለቃ ምነው ያለሰአቶ» ቢሏቸው እሳቸውም መልሰው «የስራ ባልደረቦቼን ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ» አሉአቸው።


አስበጂና ላኪልኝ
(24)የአለቃ ገብረሀና ጎረቤት የሆኑት አንዲት ወ /ሮ የአለቃን ባለቤት ወ /ሮ ማዘንጊያን ከአንድ ጎበዝ ጋር አስተዋውቃ ሁለቱ በየጊዜው ከቤቷ እየተገናኙ የልባቸውን ይወያያሉ። ከእለታት አንድ ቀን አለቃ ቤተ ክርስቲያን ተሳልመው ሲመለሱ ቤታቸው የፊጥኝ ታስሮና ተዘግቶ ስላገኙት ባለቤታቸው ወ /ሮ ማዘንጊያ ወዴት አንደሄዱ ጎረቤታቸውን ይጠይቋታል። እርሷም «መደብ እየሰራሁ ስለሆነ ማእዘኑን እያበጀችልኝ ነው» በማለት መልስ ትሰጣለች። እርሳቸውም “ቡና ስለጠማኝ ቶሎ አስበጅና ላኪልኝ” በማለት ትክክለኛውን መልእክት በዘዴ አስተላለፉ አሉ።


ማን ደፍሮ ይገባል
(25)አለቃ ሚስታቸው የቂጥኝ በሽታ ይዟቸው ወሸባ ገብተው (የቤት ውስጥ ህክምና ) ከቤት ተኝተዋል። በሽታውን ማን እንዳስያዛቸው ሲመረመሩ ማንደፍሮ የሚባል የመንደር አውደልዳይ መሆኑን ሰምተዋል። ታዲያ አንድ ወዳጃቸው የሆነ ሰው «ኧረ ለመሆኑ ከርስዋ ቤት ማን ገብቶ ነው ሚስትዎን ቂጥኝ ያስያዛቸው?» ብሎ ቢጠይቃቸው «አዬ ወንድሜ ያስያዛትንማ ማን ብዬ ልንገርህ ከኔ ቤት ማን ደፍሮ ይገባል?» ብለው መለሱለት ያስያዛት ማንደፍሮ ነው ማለታቸው ነው።


ምልምሎች
(26)ለእንጦጦ ማርያም ይመስለኛል ጣይቱ ለመዘምራንነት ድምጸ መረዋ የሆኑ ስልቦችን ለአገልጋይነት ይሰጣሉ። እነዚህ መዘምራን ከአለቃ ጋር በምን እንደተጣሉ አይታወቅም። አለቃ እነሱን እናንተ ምልምሎች ይሏቸዋል። መዘምራኑም ምኒልክ ዘንድ ይከሳሉ ተሰደብን ብለው። አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ አልተሳደብኩም ይላሉ። ከዚያ ምን ብሎ ነው አለቃ የሰደባችሁ ይላሉ ምኒልክ። መዘምራኑ አፍረው ዝም ሲሉ አለቃ ምን ትላለህ ይሏቸዋል። አለቃም አልተሳደብኩም እቴጌ ጣይቱ ከአገልጋዮቻቸው መካከል መርጠው መልምለው ለእንጦጦ ማርያም ስለሰጡ ነው ምልምሎች ያልኩት አሉ። ምኒልክም ስቀው ዝም አሉ አሉ።


ጭን እያነሱ መስጠት
(27)የምኒልክ ወዳጅ የሆኑትን አለቃ በተረባቸው እትጌ ጣይቱ በጣም ይጠሏቸው ነበር አሉ። እናም አንድ ቀን በአል ነበር በአሉን ረሳሁት ለአለቃ እቴጌ አንድ የበሬ ንቃይ ይልኩላቸዋል። አንድ ጊደር ወይም ወይፈን የጠበቁት አለቃ በተላከላቸው የበሬ ንቃይ እግር (ጭን) ተናደው። «አይ እተጌ እንዲያው ለሰው ሁሉ አንዳንድ ጭን እያነሱ እየሰጡ ለምኒልክ ምን ሊተርፋቸው ነው? አይይ ኧረ ይሄን ለማንም እግር እያነሱ መስጠቱን ቢተውት ይሻላል።» ብለው በመናገራቸው ከምኒሊክ ቤተመንግስት ለመጨረሻ ጊዜ ተባረዋል።


ዋናውን ይዘው
(28)አለቃ በቀልዳቸው በመወደድም ይሁን በመፈራት የሚፈልጉትን የማግኘት እድላቸው ሰፊ ነው ይባላል። በመሆኑም አንድ ለቤተመንግስት ሰዎች ቅርብ የሆኑ ታዋቂ እመቤት ቤት በእንግድነት ይገቡና በዚህም በዚያም ብለው በድብቅ ከእመቤቲቱ ጋር ወሲብ ይፈጽማሉ። ከዚያም ለካ ባልጠረጠሩበት መንገድ ሚስጥሩ ሾልኮ ቤተክርስቲያን ከባልደረቦቻቸው ጆሮ ገብቶ ባልደረቦቻቸውን አስቆጥቷቸዋል። አጅሬ ይህን ጉድ ሳይሰሙ እንደልማዳቸው ስራቸውን ሰርተው አድረው ጠዋት አገልግሎት ሊሰጡ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ቀሳውስቱ ተመካክረው ከሴት ጋር አድረው መጥተው ቤተክርስቲያናችንን ሊያረክሱብን አይገባቸውም ብለው ሰድበው ያብርሯቸዋል። አለቃም ባጋጠማቸው ነገር አዝነው ከቤተክርስቲያኑ ይወጡና ካጥር ውጪ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ዳዊታቸውን እየደገሙ ሳሉ እመቤቲቱ ፈረስ ላይ ቁጭ ብለው ከነአጃቢያቸው ይመጡና ከፈረሱ ወርደው ወደ ግቢ ያመራሉ። በዚህን ጊዜ አለቃ ብድግ ይሉና «በንጉስ አምላክ ይመለሱ! ወደ ውስጥ ሊያልፉ አይገባዎትም» ብለው ይጮሀሉ። ሰው ግራ ገብቶት «ምነው አለቃ ! ምን እያሉ ነው?» ሲል እሳቸውም ምንም የሌለው ምስኪን ካልተፈቀደለት እሳቸው ዋናውን ይዘው እንዴት ሊገቡ ይችላሉ?» በማለት ለሴትየዋ በሚገባ ዘዴ ተናግረው በማሳፈር መለሷቸው ይባላል።


እኔ ለነካሁት
(29)አለቃ እንዲሁ ሴት ጋር ያድሩና ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ይከለከላሉ እንዳይገቡ ያያቸው ሰው ስለነበር። እናማ በሴቶች በር በኩል ሄደው ዛሬ ሴቶች አይገቡም እዚህ ከገርገራው ውጪ ሆናችሁ ጸልዩ ብለው ሴቱን ሁሉ ከልክለው ካህናቱ ገርሟቸዋል አንድም ሴት ሳያዩ በመቅረታቸው። «ምን ሆነው ነው?» ሲሉ አንድ ያለቃን ስራ ያየ ካህን «አለቃ ከልክለው ነው ሴቶች እንዳይገቡ» ብሎ ያስረዳል።አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ «እኔ ለነካሁት ከተከለከልኩ እነሱ ይዘው እንዴት ይግቡ» ብዬ ነው አሉ።


መውጫችንን ነዋ
(30)ቦታው የት እንደሆነ አላውቅም ብቻ ጣይቱ በእንጨት ደረጃ ወደ ፎቅ ይወጣሉ። ድሮ ያው ግልገል ሱሪ አልነበረም ፎቅ ሲወጡ አለቃ ደረጃው ስር ሆነው አንጋጥጠው የጣይቱን ምስጢር ያያሉ። ጣይቱም መለስ ብለው ወደታች ወደ አለቃ አዩና አለቃ «ምን እያዩ ነው?» ቢሏቸው። «መውጫችንን ነዋ» አሏቸው።


ኩኩሉ
(31)መኳንንቱ በአለቃ ፍጥነት የሰላ አቃቂር ምን እናድርግ ብለው መከሩ። ነገ ሁላችንም እንቁላል ይዘን እንምጣና አለቃን እናፋጣቸው ብለው ተስማምተው በማግስቱ ጉባኤ ሁሉም ከኪሱ እንቁላሉን ብቅ ሲያደርግ አለቃም በቅጽበት እጃቸውን አርገፈገፉና ኩኩሉ አሉ። ከዚያም ለጥቀው ይህንን ሁሉ እንቁላል ያስወለድኩት እኔ ነኝ አሉ ይባላል። መኳንንቱ ሁሉ ሴት ዶሮ ሆነ።


በጠማማ ጣሳ
(32)በአለቃ ተረብ በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶበት በቁጭት ላይ የነበረ ሰው እርሳቸውን የሚተርብበት ጥሩ አጋጣሚ በማግኘቱ እጅግ በጣም ደስ ይለዋል። ይሄውም አለቃ እሰው ቤት እንጀራ በምስር ወጥ ተጋብዘው እስኪጠግቡ ይበሉና በወጡ የተለቃለቀውን አፋቸውንም ሆነ ከንፈራቸውን ሳይታጠቡ ሰው ወደተሰበሰበበት አደባባይ ይመጣሉ። ሰውዬውም ያገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም በሰው ፊት አዋርዷቸው ዝና ሊያገኝ በመጣደፍ፤ «አለቃ! በዛሬው ገበያ የምስር ዋጋ ምን ያህል ነበር?» ይላቸዋል። አለቃም የሰውየውን ተረብ በቅጽበት ይረዱና ቀና ብለው ሰውየውን ሲያዩት ጉንጩ በጣም የከሳና የተጣመመ መምሰሉን ይረዳሉ። ታዲያ ለሰውየው የሚሰጡት መልስ ምን መሰላችሁ። «አይ ልጄ! ምስርማ ዛሬ ተወዶ በጠማማ ጣሳ በብር አንድ ሲሸጥ ውሏል።» በማለት የጉንጩን መጣመም ጠቆም አድርገው ቆሽጡን አሳረሩት ይባላል።


አስደግፈውት አመለጡ
(33)አለቃ መቼም ሲናገሩ ለነገ የለም እና አንዱን ዲያቆን አበሳጭተውት ሊደበድባቸው ይፈልጋቸዋል።እናም አንድ እለት በሩቅ ያዩትና ሮጠው እንደማያመልጡት ሲገባቸው ቶሎ ሮጥ ብለው አንድ ዘመም ወዳለ ጎጆ ይሄዱና ሊወድቅ ያለውን የጎጆውን ግድግዳ በጃቸው ደግፈው እንደቆሙ፤ ዲያቆኑ ይደርስባቸውና ምን እያደረጉ እንደሆነ ይጠይቃቸዋል። እሳቸውም ግድግዳው ሊወድቅ ስለሆነ ደግፈው መቆማቸውን እና እሱ ቢተካላቸው አጣና አምጥተው ግድግዳውን እንደሚያስደግፉ ነግረውት እሱ ሲተካላቸው አለቃ አስደግፈውት አመለጡዋ። አይ የያዛቸው ቀን እኔ የለሁበትም ቆርጦ ቆርጦ ነው የሚጥላቸው።


በሰው አገር ቀረሁ
(34)አለቃ መንገድ ወጥተው ይመሽባቸውና የመሸበት እንግዳ ብለው ሰው ቤት ይጠጋሉ። በኋላም ያረፉባት ሴትዮ ያለቃን ተረብ ታውቅ ኖሮ ተጨንቃ ተጠባ አሳ ወጥ ሰርታ እራት ታቀርባለች። ያው ሴትየዋም አሳው ወጥ ላይ የማይገባበትን ውሀ ጨምራበት ነበርና ትንሽ ቀጠን ብሎ ነበር። ታዲያ አለቃም የቀርበላቸውን እራት ጥርግ አድርገው ከበሉ በኋላ ለቅሶ ይጀምራሉ። እንደው ያዙኝ ልቀቁኝ ሰዎቹም ተጨንቀው አረ አለቃ ምነካዎ? ብለው ቢጠይቁ «አዬ አሳ አገሩ ሲገባ እኔ በሰው አገር ቀረሁ» ብለው የሴትየዋን የአሳ ወጥ በደንብ አለመስራት ተናገሩ።


ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው
(35)አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል።


የተልባ ማሻው ሚካኤል
(36)አለቃ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲመለሱ ያው የግድ የአባይን በረሀ ማቋረጥ ነበረባቸው። አብረዋቸው የነበሩ መንገደኞች በቃ የአባይ ሽፍታ ሊዘርፈን ነው ብለው ሲያለቃቅሱ። አለቃ ብራችሁን ሰብስቡና አምጡ ብለው - መንገድ ሲሄዱ ተልባ እየወቀጡ የሚበሉበት ሙቀጫ ውስጥ ብሩን በሙሉ ይጨምሩና አፉን ወትፈው፤ ሙቀጫውን የቤተ ክርስቲያን ጨርቅ አልብሰው ለአንዱ መንገደኛ እንደታቦት አሽክመው ሲጓዙ ሽፍቶቹ ዘንድ ይደርሳሉ። ሽፍቶቹም ብቅ ብቅ ይሉና «ምንድናችሁ?» ይላሉ። አለቃም ፈጠን ብለው «ታቦት ልናስገባ ይዘን የምንመጣ መንገደኞች ነን» ይላሉ። አንዱ ሽፍታም «የታቦቱ ስም ማን ነው?» ይላል። አለቃም «የተልባ ማሻው ሚካኤል ነው» ብለው መለሱ። ሽፍቶቹም ተሳልመው መንገደኞቹም በሰላም በረሀውን አለፉ።


ወላሂ ኑ እንብላ
(37)አለቃ ከሩቅ ቦታ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ሽፍቶች ሊደርሱባቸው ሲል ያላቸውን ገንዘብ አገልግል ውስጥ ከተው ጠበቁዋቸው። ለሽፍቶቹም ኑ እንብላ ወላሂ ጥሩ የዶሮ ወጥ ነው ቢሏቸው እኛ የእስላም ስጋ አንበላም ብለው ትተዋቸው ሔዱ ይባላል።


ግም ግም ሲል
(38)ሊቁ ገብረሀና በሀያ ስድስት ዓመታቸው ጎንደር ውስጥ ሊቀ ካህናት ሆነው ተሾሙ። በዚህ ጊዜ አንዲት ጎንደሬ ዘንድ ጠበል ተጠርተው ቢሄዱ የሚወጡት ሰዎች ሁሉ «ጠላው ጥሩ አይደለም» ሲሉ ይሰሙና ተመልሰው ወደቤታቸው ይሄዳሉ። ሴትዮዋም በመቅረታቸው አዝና ቤታቸው ሄዳ «ምነው አባ ጠበል ጠርቼዎት ሳይመጡ ቀሩ?» ብትላቸው “ኧረ መጥቼ ሰው ግም ግም ሲል ጊዜ ነው የተመለስኩት።” አሏት።


ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን
(39)በሀገራችን እንደተለመደው ድግስ ካለ ቄሱም ሼሁም ሁሉም እንደየሀይማኖቱ ይጠራሉ። አዝማሪዎችም አይቀሩም። ስለዚህ የአለቃ ግዳጅ አንዱ ድግስ መሄድ ነው። ሴትየዋ ያው እንደነገሩ አሸር ባሸር የሆነ ድግስ ብጤ አድርጋ ኖሮ አለቃ ወጡም ቅጥንጥን ጠላውም ውሀ ውሀ ብሎባቸው ኖሯል። ደጋሽ መጥታ አለቃ ይብሉ እንጂ ትላለች። አለቃም «የመጣንበትን ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን» ብለው የልባቸውን ተናገሩዋ ድግሱን የፈቀዱ መስለው።


ከመሶብዎ አይጡ
(40)ሰው መቼም ወዶም ይሁን ፈርቶ አለቃን ይጋብዛቸዋል። አንድ ቀን ሊጋበዙ ወደ አንዱ ቤት ጎራ ብለው እንደተቀመጡ ጋባዥዋ ሴት እንጀራ ለማቅረብ መሶቡን ከፈት ስታደርገው ትንሽ አይጥ ዘላ ትወጣና ትሰወራለች። አለቃም ይህችን ጠንቀኛ አይጥ አይተዋት እንዳላዩ ጸጥ ብለዋል። ርቧቸው ስለነበረ ከራሳቸው ጋር እየታገሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይበላሉ። ከዚያም በመጨረሻ ማእድ ሲነሳ መመረቅ የተለመደ በመሆኑ እንዲህ ብለው ይመርቃሉ ;- በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ እ /ር ይስጥልኝ ከመሶብዎ አይጡ።


የመጣሁበት ነው
(41)አለቃ ገብረሀና አንድ ጣና ሀይቅ ላይ ካለ ደሴት ላይ የምትኖር ሴት ጸበል ቅመሱ ብላ ትጠራቸዋለች። አለቃም በጥሪው ቀን በጀልባ ተሳፍረው ከጥሪው ቦታ ይደርሳሉ። ነገር ግን ትንሽ አርፍደው ነበርና ብዙው ምግብ ቀድሞ በመጣው ተጋባዥ ተበልቶ ወደማለቁ በመቃረቡ ያለውን ወጥ እንደ ነገሩ ቀጠንጠን አድርጋ ነበር ሴትዮዋ ያቀረበችላቸው። ቢሆንም ግን አሁንም አሁንም ብቅ እያለች «አለቃ ይብሉ እንጂ» ትላለች። «እሺ....እሺ» ማለት የሰለቻቸው አለቃም በመጨረሻ እንዲህ ብለው ይመልሳሉ። «እንዴ እበላለሁ እንጂ ....ምናለ ይሄ እኮ የመጣሁበት ነው» ......... ውሀ ነው ለማለት ያክል።


ጠረር አርገሽ ቅጂው
(42)አለቃ አንድ ቤት በእንግድነት ሄደው ሳለ ጠላ ይጋበዛሉ። ጋባዥ የነበረችው ሴትዮም ጠላውን ልትደግማቸው ጎንበስ ብላ ስትቅዳ ንፋስ ፈሷ ያመልጣታል። አለቃም ሰምተው እንዳልሰማ ይሆናሉ። የቀረበላቸውን ሲጨርሱ ሴትዮዋ እንደገና መጥታ «አለቃ ልድገሞት» ትላለች። አለቃም «ልድገም ብለሽ ነው? በይ እስቲ እንደቅድሙ ጠረር አርገሽ ቅጂው» ብለው መፍሳቷን እንዳወቁ በዘዴ ተናገሩ።


ዝግንትሉ ሞልቷል
(43)አንድ ቀን አለቃ ግብዣ ተጠርተዉ ይሄዱና ምግብ ቀርቦ እየበሉ ሳለ ትል ያጋጥማቸዉና አኩርፈዉ እየበሉ ሳለ ጋባዡ በድንገት ይመጡና «ምነው አለቃ በደንብ ብሉ» ይሉዋቸዋል።አለቃም ተናደዉ ኖራልና «እሺ ጌቶች እየበላሁ ነው። ምን ጠፍቶ ዝግን ትሉ እንደሆን ሞልቷል።» አሉ ይባላል።


ጥፍር ያስቆረጥማል
(44)አንድ ቀን አለቃ በእንግድነት ሰው ቤት ይሄዱና ምግብ ይቀርብላቸዋል። እየበሉ ሳለ በድንገት ከምግብ ጋር የገባ የጥፍር ቁራጭ ያገኙበታል። ከዚያም ባልቴቷም ትመጣና «አለቃ ብሉ እንጂ አይጣፍጥም እንዴ?» ትላቸዋለች።አለቃም የተቋጠረ ፊታቸውን ፈታ በማድረግ «ኧረ ይጣፍጣል ከመጣፈጥም አልፎ ጥፍር ያስቆረጥማል!!» አሉ አሉ።


የጓደኛህን ቀን ይስጥህ
(45)አለቃ ገብረ ሀና ከሸዋ ወደ ጎንደር ግብዣ ተጠርተው ግብዣው ላይ ለመገኘት ይጓዙና ጎጃም ላይ ሲመሽባቸው ወደ አንድ ኮማሪት ቤት ይገቡና መጠጥ አዘው ቁጭ ይላሉ። አለቃ ደርባባዋ ኮማሪትዋ ቃ ትላቸውና እዛ ለማደር ያስባሉ። በጣም ሲመሽም ኮማሪትዋ ሌሎቹን ሰዎች ታስወጣና አለቃን አይታ እኚሕ ሽማግሌስ ምንም አያደርጉኝም ብላ ለሳቸው መደብ ላይ አንጥፋ ከጎናቸው ፈንጠር ብላ ትተኛለች። በነገራችን ላይ ሴትየዋ አንድ እግሯ የተቆረጠ እና በአርተፊሻል እግር ነበር የምትራመደው። አለቃም ለሊት ላይ ወደ ሴትየዋ ተጠግተው አሰስ ዳሰስ ማድረግ ሲጀምሩ ሴትየዋም ነቅታ በደህና እግሯ በርግጫ ብላ ትመታቸዋለች። አለቃም ቀበል ያደርጉና «የጓደኛህን ቀን ይስጥህ ሌላ ምን እላለሁ» ብለው እርፍ።


በቁሜ ቀምሼ መጣሁ
(46)አለቃ ድግስ ተጠርተው አረፋፍደው ድግስ ቤቱ ቢደርሱ ሰዉ ሁሉ ተሳክሮ በብርሌ ሲፈነካከት ይደርሳሉ። ገና በሩን ገባ ከማለታቸው አንድ የተወረወረች ብርሌ ግንባራቸውን ትላቸዋለች። አይ ከዚህስ ቢቀርብኝ ይሻላል ብለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ አንድ የሚያውቁትን ሰው መንገድ ላይ ያገኛሉ። ሰውየው «አለቃ ድግሱ እንዴት ነበር?» አለቃም «በጣም ቆንጆ ነበር። ቶሎ ሂድ እንዳያመልጥህ እኔ እንኳን አንድ በቁሜ ቀምሼ መጣሁ» ብለውት እርፍ።


ሺ ነዋ
(47)አለቃ ገብረሃና አጤ ምኒልክ ግብር ሊበሉ ሄዱ። ተበልቶ ተጠጥቶ ለሽንት መውጣት አይፈቀድም ነበር። አለቃ ግን እወጣለሁ ብለው ተወራረዱ። ዘበኞች አናስወጣም ቢሏቸው «እምዬ ምኒልክ ለሽንት እንድወጣ ፈቅደውልኛል አሉ።» ዘበኞቹ «አይደረግም አሉ።» አለቃ «በሉ ንጉሱ ምን እንደሚሉ ስሙ አሉዋቸው።» ወደእምዬ ምኒልክ ጠጋ ብለው በጆሮዋቸው አንሾካሸኩ። «"500+500" ስንት ይሆናል?” እምዬ ምኒሊክም ሂሳብ አይችሉም እንዳይባሉ ጮክ ብለው «ሺነዋ» አሉ። አለቃም «ሺነዋ (ሽናው ) ተብዬአለሁ» ብለው ወደሽንት ቤት ሄዱ።


ቡሊ የአለቃ አህያ
(48)አንዴ አለቃ ቤት ጅብ ይገባና አህያቸው ቡሊ በፍርሀት ጩኸቱን ያቀልጠዋል። ሚስታቸው ማዘንጊያ አለቃን ቀስቅሰው ጅቡን እንዲያባርሩ ቢንግሯቸው «ባክሽ እኔ እፈራለሁ» በማለት አለቃ ሲመልሱ ማዘንጊያም ፈጠን ብለው «ኡኡቴ ለስሙ ነዋ ያንጠለጠሉት?» በማለት ይጠይቃሉ። አለቃም «ለማንጠልጠሉማ ቡሊ ይበልጠኝ አልነበር» በማለት መለሱ።


በጠማማ ቁና ሁለት ሁለት (1)
(49)አለቃ ምግብ በተልባ በልተው አፋቸውን ሳያብሱ አደባባይ ወጥተዋል። አንዲት የተልባ ቅንጣት ወደ አገጫቸው ተለጥፋ ኖሯለች።አንድ ተጫዋች ወዳጃቸው አለቃ «ዛሬ ተልባ ስንት ስንት ዋለ?» ብሏቸዋል። አለቃም ገብቷቸው ስለነበረ ሰውየው የኔ ብጤ ውልግድግድ ያለ ስለነበረ «በቅፅበት በጠማማ ቁና ሁለት ሁለት ዋለ» አሉት አሉ።


በጠማማ ቁና ሶስት ሶስት (2)
(50)አለቃ ገብረሀና የኢትዮጵያ ዘመናዊ ጥበበ ቀልድ /ኮሚዲ መስራች ሊባሉ ይገባል። አንዳንድ ተቺ ሰው አለ አይደል ዝም ብሎ መተቸት የሚወድ አይነት። አለቃ የበሉት ተልባ አፋቸው ላይ ሳይጠረግ አይቶ «ተልባ ገበያ ላይ እንዴት ዋለ?» ቢላቸው ሰውየው አፉም እግሩም የተጣመመ ስለነበር «በጠማማ ቁና ሶስት ብር ነበር።» አሉት።


አለቃ አለ ዕቃ
(51)አንዴ አለቃ ገብረ ሀና መንደራቸው ካለ ግድግዳ ተጠግተው ሽንታቸውን እየሸኑ ሳለ ,አንድ ጎረቤታቸው አይቷቸው ሰላምታ ሊሰጥ «አለቃ» ቢላቸው እሳቸው «ቆሜ ስሸና እያየህ እንዴት አለቃ (= አለ እቃ ) ትለኛለህ» አሉት ይባላል።


ሰይጣኑ ይውለድህ
(52)አለቃን አንዱ «ምነው ትንቦ ይጠጣሉ?» ቢላቸው። «ብጠጣው ምን አለበት?» አሉት። እሱም «ኧረ የሰይጣን ነው ይባላል። ስለዚህ ነውር ነው!» አላቸው። እሳቸውም ቀበል አድርገው «ሰይጣኑ ይውለድህና ያን ጊዜ ትከሰኛለህ! ለመሆኑ አንተ ለሰይጣኑ ምኑ ነህ?» አሉት ይባላል። (ምንጭ :- ቢልጮ 1948 ከአበበ አይቸህ )


በሌባ ጣትሽ አታሳዪኝ
(53) አለቃ እጓሯቸው ዱባ ተክለዋል። ዱባውም አድጎ ፍሬ ይዟል። ፍሬውም ጎምርቶ (አሽቷል ) እሱንም ጧት ማታ እየተንከባከቡ ይጠብቃሉ። ከጎረቤታቸው አንዲት በሌብነት የሰለጠች ጋለሞታ ነበረች። አንድ ቀን ጧት ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ አይታ ቀጥፋ ወሰደችባቸው። ሲመለሱ ዱባቸውን ያጡታል አዝነውና ተናደው ወይ ዱባዬ እያሉ ሲቃትቱ ያቺ አልማጭ ሌባ ከቤት ወጥታ «ምን ሆኑ አለቃ?» አለቻቸው። እሳቸውም «ዱባዬን ጉድ ሆንኩ ተሰረቅሁ» ይላሉ። እሷም ያዘነች በመምሰል ከንፈሯን እየመጠጠች የዱባው ፍሬ የነበረበትን ስፍራ በሌባ ጣታ እያመለከተች «አዎ አለቃ ትላንትና እዚህ ነበር እኔም አይቼዋለሁ» ስትል እሷ እንደሞጨለፈችው አውቀው «ተይው ልጄ በሌባ ጣትሽ አታሳዪኝ» ብለው ስርቆቷን ነገሯት።


አንቺ ባይበላሽ (1)
(54)አለቃ ጠዋት ተነስተው ወጥተው፤ ስራ ውለው ለምሳ ሲመለሱ በጣም እርቧቸው ነበርና ምሳ እስከሚቀርብላቸው ይጠብቃሉ። ማዘንጊያ ሆዬ ለካስ ስራቸውን እየሰሩ ከአይቡም ጎረስ ሲያደርጉ ውለው ነበርና ምሳ ላይ ቸለል ብለዋል። አለቃም «ማዘንጊያ አትበይም» ብለው ቀና ሲሉ አፋቸው ላይ አይብ አይተዋል። «አይ ማዘንጊያ በይ ተይው አንች ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ» አሉ ይባላል።


አንቺ ባይበላሽ (2)
(55)አለቃ አመሽተው እቤት ይመጣሉ ባለቤታቸው ቁጭ ብላ ፈትል ትፈትል ነበር። «እንደምን አመሹ አለቃ?» ትላለች «እኔስ ደህና ይላሉ»። ትንሽ ቆይታ እራት ታቀርባለች እንጀራ በሚጥሚጣ። አለቃም «ነይ ቅረቢ ይሏታል»። «አይ እኔ አልበላም ትላለች»። አለቃም «አይ አንች ባይብ በላሽ እኔ እበላዋለሁ» አሉ።


ቤቴ በየት ዞረህ መጣህ
(56)እንግዲህ እሳቸው አያልቅባቸውም አይደል አንዴ ምን ሆኑ መሰላችሁ። ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ነጋ ጠባ እንጀራ በተልባ እያቀረቡ ቢያስቸግሯቸው ጊዜ የተለየ ምግብ አላጣም ይሉና ቅምጣቸው ቤት ብቅ ይላሉ። ውሽማቸውም «ደህና መጡ» ትልና እንጀራ በተልባ ታቀርብላቸዋለች። ከዛ አለቃም በተራቸው ውሽሚት ሳትሰማ ዞር ብለው «ቤቴ በየት ዞረህ ቀደምከኝ ብለው እርፍ»።


መቋሚያዬን አቀብዪኝ
(57)አንድ ቀን አለቃ ቀን ዘመድ ጥየቃ ውለው ሙቀቱ ድብን አድርጓቸው ድክም ብሏቸው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ወጥ እየሰሩ ይደርሳሉ። አሁን ገብተው አረፍ እንዳሉ ባለቤታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ የሚበላ ነገር እንዲያቀርቡላቸው ግና ወ /ሮ ማዘንጊያ እየደጋገሙ ወጡን በማማሰያ ሲቀምሱ የታዘቡ አለቃ «ማዘንጊያ እንግዲህ እራታችን እሱ ከሆነ ለእኔም መቋሚያዬን አቀብዪኝ» ብለው እርፍ።


ባዶ ሽሮ
(58)ወራቱ ሁዳዴ ነው ታዲያ አለቃ ሲያስቀድሱ ውለው እቤት ይመለሳሉ። የአለቃን መምጣት ያዩት ማዘንጊያም ምሳ ለማቅረብ ተፍ ተፍ ይላሉ ታዲያ በዚህን ጊዜ አለቃ ከማዘንጊያ ደረት ላይ ተጣብቃ የቀረች አይብ ያያሉ። ትንሽ ቆይቶም ማዘንጊያ ባዶ ሽሮ ወጥ ይዘው ይቀርባሉ። አለቃም «በይ ነያ እንብላ?» ማዘንጊያም መልሰው «አይ እቴ ይቅርብኝ አላሰኘኝም።» አለቃም ማዘንጊያን ምሳቸውን አይብ እንደበሉ ገብቷቸው እንዲህ አሉ አሉ «በሁዳዴ ሽሮ እንዳይጥም አውቃለሁ አንቺ ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ»


ነዪ ብዪ እንጂ
(59)ጾም ነው ሮቡዕ ቀን። አለቃ ጸሎት ከአጥር ግንብ ጎን ሆነው ይደግማሉ እንደገናም ወዴቤት እያሾለቁ ይመለከታሉ። ወይዘሮ ማዘንጊያ ወተት ንጠው ወተቱን አፍልተው አይብ ሠርተው እሱን ጎረስ ጎረስ ጎረስ በጤፍ እንጀራ ያደርጋሉ። አለቃ ይኼንን አይተዋል። ፀሎት አሣርገውወደ ቤት ይገባሉ ከሠዓት ላይ ነው። ለአለቃ ማዘንጊያ ቁርስም ምሣቸውን በማሰብ ምግብ በሽሮ ወጥ ያቀርቡላቸዋል። ይሔኔ አለቃ ማዘንጊያሽ «ነይ ብዪ እንጂ» ይሏቸዋል። ማዘንጊያም «አለቃ ምግብ አልበላ ብሎኛል ይሏቸዋል» ይሄኔ አለቃ «አንቺ ባይበላሽ እኔ እበላዋለሁ» ብለው ብቻቸውን ምሣቸውን በሉ ይባላል።


ገብርኤልና ሚካኤል ተታኮሱ
(60)ወይዘሮ ማዘንጊያ ይፈሱና «ውይ ገብርኤልየ» ይላሉ። ይቆዩና እንደገና ይፈሳሉ «ውይ ሚካኤልየ» ይላሉ ከዛ ድንገት ዞር ሲሉ አለቃ ገብረሀናን በመስኮት ቆመው ያዩዋቸዋል። ድንግጥ ይሉና «እርሶ ደግሞ እዛ ቆመው ምን ያረጋሉ?» ብለው ይጠይቋቸዋል።አለቃ ገብረሀና ደግሞ «እን..ዴ.. ገብርኤልና ሚካኤል ሲታኮሱ እያየሁ ነዋ!» አሏቸው ይባላል።


ለምን ደወልሽው
(61)አንድ ሴት ዉሀ ልትቀዳ ጎንበስ ስትል አንድ ጊዜ ያመልጣትና ድዉ ታደርገዋለች። ዘወር ብላ ስታይ አለቃ ገብረሀና ከኋላዋ ቆመዋል። ከዛም ደንገጥ ብላ «አለቃ ለመሆኑ ሰአት ስንት ሆነ ስትላቸው?» «አይ አንች ካላወቅሽዉ ለምን ደወልሽዉ?» አሏት ይባላል።


ቃታ መፈልቀቂያሽን
(62)ሴትዮዋ ድምጽ ሳይሰማ ማስተንፈስ ፈለጉና በጣታቸው አንድ መቀመጫቸውን ከፈት አድርገው ቢለቁት ሳይሳካላቸው ቀርቶ ዱጥ ቢልባቸው ደንግጠው «ደራን ወጋው» ይሉና ዞር ሲሉ አለቃን ያዩዋቸዋል። ከዛም “አለቃ መቼ መጡ?” ብለው ቢጠይቋቸው «ደራ የተወጋ ጊዜ» ብለው ይመልሱላቸዋል። ሴትዮዋም በመደንገጥ «ምነው ጣቴን በቆረጠው?» ቢሉ አለቃም ቀበል አድርገው «ተይ እንጂ ምነው ቃታ መፈልቀቂያሽን» አሏት አሉ፡፡


ጠረር አድርገሽ ቅጂው
(63)አለቃ አንድ ጊዜ መንደር ጠላ ቤት ይገቡና ሲጠጡ አሳላፊዋ አንዴ እሳቸው ጋር ስትደርስ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ ፈስዋ ያመልጣትና ጠርር ታድርገዋለች እየቀዳች። ይህን የሰሙ አለቃ አንድ ጊዜ እሳቸው ጋር መጥታ «አለቃ ጠላ ልጨምርልዎት እንዴ?» ስትላቸው። «አዎዋ እስቲ እንደ ቅድሙ ጠረረ አድርገሽ ቅጂው» አሉ ይባላል።


አንድማ ግዙ
(64)አለቃ ገብረሀና መሸት ሲል ጠላ ቤት ተቀምጠው ሲጠጡ ቆዩና ሽንት ለመክፈል በጓሮው በኩል ወጣ ብለው በሚሸኑበት ጊዜ ፈሳቸው ያመልጣቸውና ጡጥ ያደርጋሉ። ሰው ሰምቶ ይሆን ብለው ትንሽ ዞር ብለው ሲመለከቱ ኮማሪትዋም ትንሽ ራቅ ብላ እቃ እየፈለገች ኖራ ሰምታ ይሆናል ብለው በመስጋት አህያ እንደሚያባርሩ በመምሰል «ዙር !! ዙር !!» ብለው ሲጣሩ ሴትዮዋ ሰምታ «ኧረ! እኛ አህያ የለንም» ስትል አለቃ መልስ አይጠፋቸውም አይደል «አንድማ ግዙ» አሉ ይባላል።



በጠርር ሄጄ በታህሳሥሥ
(65)አንድ ጊዜ አለቃ በመንገድ ላይ ከወዳጃቸው ጋር ሲሔዱ ወዳጃቸው ፈሱን መፍሳቱን ሰምተው ኖሮ ሰለነበር እንዴት እንደሚናገሩ እያስቡ ሳለ ድንገት ሰውየው «መቼ ነው ከከተማ የመጡት» ቢላቸው «በጠርርርር ....... ሄጄ በታህሳስስ .... ተመለስኩ» አሉ ይባላል። ሰውየን ማሰቀየም አልፈልጉም ማለት ይሆን?


መልግጌ አባስኩት
(66)አለቃ ለቅሶ ሂደው ራት ከተበላ በኋላ ተጎዝጉዞ ከለቀስተኛ ጋር በመደዳ ይተኛሉ። ትንሽ ቆይቶ ፈሳቸው ይመጣባቸውና ቀስ ብለው ያለ ድምጽ ሊፈሱ አስበው ቂጣቸውን በጃቸው ከፍተው ቢለቁት ጠርር ብሎ ያሳፍራቸዋል። አለቃም አዝነው «አዬ መልግጌ አባስኩት» አሉ ይባላል።


ድንቼ
(67)አንዲት አጠር ደልደል ያለች ደባካ መሳይ የኣለቃ ገብረሃና ጎረቤት ደግሞ «አባ ሰው ሁሉ ድንቼ የኔ ድንች እያለ ያቆላምጠኛል» ብትላቸው «አዮ ሞኝት እውነት መስሎሽ ነው?ድንቼ ድንቼ የሚሉሽ ሊልጡሽ እንጂ ነው» አሏት።


በነካ አፍህ
(68)አለቃ ገብረሀና ከአንዱ ባለሱቅ ስውየ ጋር ማእድ ተቀምጠው ከተመገቡ በኋላ ስውየው የበላበትን እጁን ሲልስ አይተው ኖሮ «ወንድም በነካ አፍህ» ብለው እጃቸውን መቀሰራቸው ይነገራል።


ተኖረና ተሞተ
(69)አንዲት እድሜ ልኩዋን በድህነት የኖረች አሮጊት በነ አለቃ ገብረሀና ሰፈር ውስጥ ታርፍና ሰው ለቀብር ጉድ ጉድ ሲልና ሲሯሯጥ ሲጣደፍ አለቃ በዚያው መንገድ ሲያልፉ “ምንድን ነው እጅብ እጅቡ” ብለው ይጠይቃሉ። “እንዴ አለቃ አልሰሙም እንዴ ?”፥ “ምኑን?”፥ “ያቺ ደሀ አሮጊት መሞቷን?”። አለቃም ቀጠል ያደርጉና “አሄሄ ተኖረና ተሞተ?” ብለው ተናገሩ። በህይወትም እያለች የቁም ሙት ሞታለች ያም ኑሮ ሆኖ ሞት ለሷም መጣባት ወይ እንደማለት ነው።


መሞትዎት ነው
(70)አባ ገብርሀና የተዎለዱትና አርጅተው የሞቱት በጎንደር ክ /ሀ , ፎገራ ወረዳ ናበጋ ጊዮርጊስ የሚባል ገጠር ነበር። ክርስቶስ ሰምራ እየተባለ የሚታወቀው አካባቢ ማለት ነው። እናም ሰው መቼም ኑሮ ኑሮ መሞት አይቀርምና እሳቸውም ነፍሳቸው ልትወጣ እየተንፈራገጡ ሳለ (ሊሞቱ ማለት ነው) አንድ ከጎናቸው ተቀመጦ ጣረ ሞታቸውን ሲከታተል የነበረ ሽማግሌ አለቃን ጠርቶ «በቃ መሞትዎት ነው?» ብሎ ሲጠይቃቼው፣ «የግሚት ልጅ ታድያ ቆዳ እያለፋሁ መሰለህ» ብለውት እርፍ አሉ ይባላል።


የአለቃ የልጅ ልጅ
(71)ነገሩ የሆነው ፎገራ ውስጥ ሲሆን በደርግ ዘመን ነው። ካድሬው ህዝቡን ሰብስቦ ስለ መንደር ምስረታ አስፈላጊነት ሲያብራራ «በመንደር ከሰፈራችሁ ውሃና መብራት በየቤታችሁ ይገባላችኋል» እያለ ከቀሰቀሰ በኋላ የህዝቡም ተቃውሞ አዳማጭ ሳያገኝ ሰፈሩ ሜዳ ላይ ተሰርቶ ሕዝብ ሰፈረ። ክረምት ሲመጣም ጣና ሐይቅ እንደተለመደው የፎገራን ሜዳ ቤቴ ብሎ ሲያጥለቀልቀው ህዝቡ ወደ በአካባቢው ከተሞች ተሰደደ። በዛን ወቅት የአለቃን የልጅ ልጅ ጋዜጠኛ አግኝቶ ስለ ሁኔታው ሲያነጋግረው «ያው በካድሬው እንደተነገረን ውሃው በየቤታችን ገብቷል መብራቱ ብቻ ነው የቀረው» ብሎ አስተያየቱን ሰጠ።

Nessun commento: